አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በሲም ካርዳችን ወንጀል ከሚሰሩና ከሚዘርፉ አጭበርባሪዎች ራሳችን እንዴት እንጠብቅ?

የሰዎችን የስልክ ቁጥር የራስ በማስመሰል የሚሰሩ የማጭበርበር ወንጀሎች መበራከታቸው ተነግሯል።

ይህን ስራ የሚሰሩት አጭበርባሪዎች ወደ ቴሌኮም ኩባንያ በመደወል ስልካቸው እንደተሰረቀ ወይም እንደተበላሸ በመንገር የሰዎችን ስልክ ቁጥርን ወደራሳቸው በማዞር ነው ገንዘብ እና ግላዊ ሚስጥሮችን የሚመነትፉት።

የስልክ ቁጥሩ ባለቤት ስልኩ እጁ ላይ እያለ የሚደወሉ ስልኮች እና መልዕክቶች በአጭበርባሪዎቹ እጅ የሚገባ ሲሆን ቀጥሎም የባንክ እና ዲጂታል መገበያያ መተግበርያ የይለፍ ቃሎችን በመቀየር አጭበርባሪዎቹ ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ለዚህ ጥቃት የሚያጋልጡ ምክንያቶችን እና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በዝርዝር ያንብቡ፦ https://bit.ly/4bDdidL
👍7
Authority Delists over 250 CSOs for Failing to Report
Ethiopian Lawyers Association, Ethiopian Society for Consumer Protection and 253 other civil society organisations were dissolved last week for failing to submit their annual reports and re-register by the Authority for Civil Society Organisations (ACSO). The Authority is adopting stricter regulations following revisions to its legal framework in recent years. Last year, it began implementing reforms to address registration and administration issues that have often been unclear and contentious. Fasikaw Molla, deputy director of the Authority, issued a final notice two weeks ago warning the organisations to submit their reports as proof of their activity. The grace period ended on July 6th, and the 11-member board of directors approved the motion to remove the non-reporting organisations from its registry.
Via Addis fortune
Authority Delists over 250 CSOs for Failing to Report https://addisfortune.news/authority-delists-over-250-csos-for-failing-to-report/

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍31
ስራ ለመቅጠር የእርግዝና ምርመራ የሚጠይቁት የቻይና ኩባንያዎች

ረጂም የወሊድ ፈቃድ አሰላችቶናል ያሉት ኩባንያዎች አዳዲስ እና ነባር ሰራተኞቻቸው የእርግዝና ምርመራ እንዲያደርጉ እያስገደዱ ነው።

ዝርዝሩን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3WtozZu

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👏2
ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት

ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦

ሀ) ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
ለ) ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
👉 የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
👉 መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
👉 ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
ministry_of_revenues
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍31
አዲስ ፓስፖርት ለማዉጣት መሟላት ያለባቸው ሰነዶች

1. ከ 40 አመት በታች ከሆኑ የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት(Aunthenticated birth certificate )

2. የታደሰ ቀበሌ መታወቂያ (ጊዜያዊ ከሆነ መታወቂያዉን ካወጡበት ቀበሌ የድጋፍ ደብደቤ ያስፈልጋል)

ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች አሟልተው በኦንላይን www.ethiopianpassportservices.gov.et በመመዝገብ 3 ሰዓት ሳያልፍ በመረጡት የክፍያ አማራጭ ክፍያ በመፈፀም ፕሪንት አውት በማድረግ በቀጠሮ ቀን (Appointment date) ብቻ ያመለከቱበት ኢሚግሬሽን ቢሮ በአካል በመቅረብ አሻራና ፎቶ መስጠት አለብዎት።

በቀጠሮ ቀን(Appointment date) አሻራና ፎቶ ለመስጠት ወደ መስሪያ ቤታችን ሲመጡ ኦርጅናል የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ኦርጅናል የልደት ምስክር ወረቀት እንዲሁም ያመለከቱበትን ፕሪንት አውት ይዘው መምጣት ይኖርብዎታል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍111
የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን
👆👆👆👆👆👆👆👇


ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ) የተሸከርካሪውን የመጫን አቅም (የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣ ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘው ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

ተገጣጥመው ወደ ሀገር የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 1300 ከሆነ 75.67%ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ1800 በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሽከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሽከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው ያገለገሉ(USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

በቀጣይ የተሽከርካሪ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን አስመልክቶ መረጃ እናቀርብልዎታለን፡-

በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
   የገቢዎች ባለ ሥልጣን
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍93😁1🎉1
▪️For Fresh Graduates#ACE Investment & Impact Advisors PLC#

▪️Job Position - Paid Internship Program
▪️Education: Degree in Economics Law, Statics, Management, Engineering, or related fields
.
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧
https://elelanajobs.com/job/ace-investment-impact-advisors-plc-july-17-24/

▪️Deadline: July 21/24
👍1
አስቸኳይ የስራ ቅጥር ማስታወቂያ
ለሴቶች ብቻ👇👇👇👇


በማንኛውም የትምህርት አይነት፣
ዲፕሎማ /ዲግር

ጾታ ሴት

0 ዓመት የስራ ልምድ

የስራ መደቡ፥ የሴክሬታሪያት፣ ደንበኞች አገልግሎት እና መረጃ ኦፊሰር

ከሚከተሉት ቢያንስ ሁለቱ መሟላት ያለበት መስፈርት ነው።

እንግሊዘኛ ቋቋን የምትችል፣
የኮምፒውተር እውቀት ያላት ወይም ምሩቅ፣ ማርኬቲንግ፣ ነርስ፣ ወይም የጤና ትምህርት የወሰደች፣

ሶሻል ሚዲያዎች አጠቃቀም ጠቅቃ የምታውቅ እና በሶሻል ሚዲያ ላይ የቪዲዮ ማስታወቂያ ለመስራት ፈቃደኛ የሆነች፣


ደንበኛ አያያዝ፣ ከደበኞች ግኙነት እንዲሁም መረጃ አሰጣጥ ጥሩ ተነሳሽነት ያላት።

በአጭር የቀናት ስራ ለመጀመር ዝግጁ የሆነች።

ሼር ... ሼር ... ሼር በማድረግ በስራ እጦት ምክንያት ለሚንገላቱ ወገኖች እንዲደርስ እናድርግ።


ይደውሉ፡
+251978265892
ኢሜል፣ consultantentrust@gmail.com
ዌብሳይት፡ https://www.entrustmedicalconsultant.com/
ቴሌግራም፡ https://t.me/Entrustmedical
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61561888596174&mibextid=ZbWKwL
የቢሮአችን አድራሻ፡ https://maps.app.goo.gl/z1cDNjFRRnuhEP5B9
👍9
Directive SBB_92_2024.pdf
1.5 MB
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ባንኮች ከባንክ ሥራ ውጪ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት የሚገድብ አዲስ መመሪያ  ዛሬ ይፋ አደረገ።
የመመሪያው ሙሉ ይዘት ከላይ አያይዘነዋል።

Source: Financialethiopia
#Ethiopianbusinessdaily
👍4
የ11 ዓመት ታዳጊ ልጁን የደፈረው አባት በ16 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ11 ዓመት ታዳጊ ልጁን የደፈረው አባት በ16 ዓመት ከ 6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል።

ተከሳሽ ሙሂዲን ወራቄ በመጋቢት ወር  2016 ዓ.ም  ቀንና ሰዓቱ በውል ባልታወቀባቸዉ የተለያዩ ጊዜያት የግል ተበዳይ የሆነችውን የ11 ዓመት ህፃን ልጁን ተደጋጋሚ የሆነ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል እንደፈፀመባት የክስ መዝገቡ ያስረዳል።

ጉዳዩ እንዲህ ነው፥ የግል ተበዳይ፥ በሰራተኝነት ከተቀጠረችበት አዲስ አበባ ወደ ከዊሶ የተመለሰችዉ በቤተሰቡ መበተን ምክንያት በብቸኝነት የሚኖረዉን አባቷ ለመደገፍ እሳቤ ስለነበራት ነበር።

ተከሳሽ ጋብቻ እየመሰረተ ሲፈታ ከሶስት ጊዜ በላይ ትዳር መስርቶ ፍቺ የፈፀመ  ሲሆን የደረሱ ልጆቹንም ድሮ የልጅ ልጅ ለማየት በቅቷልም ነዉ የተባለዉ።

አባቴን ትቼ  የትም አልሄድም ስትል ከወላጅ አባቷ መኖር የጀመረችዉ ታዳጊ ታዲያ አንድ ቀን በወላጅ አባቷ ጭካኔና የነዉረኝነት ባህሪ የደረሰባትን በደል ለወላጅ እናቷ ትናገራለች።

እናትም ወደ ወረዳዉ ሴቶች ጉዳይ ጽህፈት ቤት አቅንታ ሰዉየዉ ለፍርድ ይቀርብ ዘንድ እገዛ እንዲደረግልኝ ስትል አቤቱታ በማሰማቷ ክስ ሊመሰረት ችሏል።

በሰውና በሰነድ የተደገፈውን የፖሊስ ማስረጃ የተቀበለው አቃቤ ህግ በተከሳሽ ላይ በወንጀል ህግ አንቀጽ 627(1) በህፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ክስ እና በወንጀል ህግ 654  በዘመዳሞች መሀከል የሚፈጸም የግብረ ስጋ ግንኙት ክስ መስርቶበታል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የተመለከተዉ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ በማለት በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

መረጃው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@tikvahethmagazine
😭21👍20🤬71
የ358 መቃወሚያ.pdf
848.8 KB
የ358 መቃወሚያ.pdf
ክርክሩ የውርስ ከሆነ ወራሽ የሆነ ሰው ከዚህ ፊት ክርክር በፍርድ ቤት መኖሩን ቢያውቅም ክርሩን ታውቃለህ ተብሎ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ሊደረግ አይገባም።
#ethiolawtips
👍15
👍10
በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስቀጡ
እና በወንጀል ክስ አቅራቢነት
የሚያስቀጡ ወንጀሎች ልዩነት


ወንጀሎች ክብደታቸውን እና የሚያስከትሉትን ጉዳት መነሻ በማድረግ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ እና በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስከስሱ (የግል አቤቱታ የማያስፈልጋቸው) ተብለው በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህ የወንጀል ዓይነቶች በክብደታቸው፣ በሚያስከትሉ ጉዳት መጠን እንዲሁም ከወንጀል ጥቆማ ጀምሮ እስከ ክርክር ሂደት ልዩነቶች አሏቸው፡፡ ይኸውም

• በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች በባህሪያቸው ቀላልና
ጉዳታቸው በግለሰቦች ላይ ተወስኖ የሚቀር ሲሆን በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስጠይቁት ግን ከባድ፣ ውስብስብና ከግለሰብ አልፈው በሕዝብና በሀገር ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ስድብ፣ ዛቻ፣ ስም ማጥፋትና የመሳሰሉት በተበዳይ የግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ወንጀሎች ሲሆኑ ውንብድና፣ ሽብርተኝነት፣ ሙስና፣ ግድያና የመሳሰሉት ወንጀሎች ደግሞ በወንጀል ክስ አቅራቢነት (በማንኛውም ሰው ጠቋሚነት) የሚያስከስሱ ወንጀሎች ናቸው፡፡

• በግል አቤቱታ አቅራቢነት ብቻ የሚያስቀጣ መሆኑ በወንጀል ሕጉ ልዩ ክፍል ወይም በሌላ ማሟያ የወንጀል ሕግ ተደንግጎ በተገኘ ጊዜ በግል ተበዳይ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ አቤቱታ ካልቀረበ በቀር የወንጀል ክስ ማቅረብ እንደማይቻል በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 212 ስር ተደንግጓል፡፡

በሌላ በኩል በባህሪያቸው ከግላዊ ይልቅ ህብረተሰባዊ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ፣ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ወንጀሎችን በሚመለከት ጥቆማዎችንና መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል መስጠት የሁሉም ዜጎች መብትም ኃላፊነትም ነው፡፡ ሆኖም ከባድ ወንጀሎችን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ግዴታ ሆኖ የሚደነገግባቸው ሁኔታዎችም አለ፡፡ ለአብነትም የሽብር ወንጀልን በተመለከተ ያወቀውን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ ግዴታ ሲሆን ይህን ግዴታ አለመወጣት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 15 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት የሚስከትል ነው፡፡

• ሌላው ልዩነት በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች በዕርቅ
ሊቋረጡ የሚችሉ ሲሆን በማንኛውም ሰው በሚቀርቡ ጥቆማዎች መሰረት በተመሰረተ ክስ ግን የበዳይና ተበዳይ መታረቅ ቅጣት ሲጣል በማቅለያነት ከሚያዝ በስተቀር ክስ ሊያቋርጥ አይችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በግል አቤቱታ የሚያስቀጡ ወንጀሎች ክስ ቀጣይነት በተበዳይ ፍላጎት ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን በወንጀል ክስ አቅራቢነት የሚያስጠይቁት ግን የተበዳይ ፍላጎት ተፅኖ አያሳድርባቸውም፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
የፍትህ ሚኒስቴርን
በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍102
8,649 በፍቺ ምክንያት ትዳር የተበተነ ሲሆን

በ2016 ዓመት ስንት ትዳር ተበተነ (ፍቺ ) ያልነው መረጃ ወጥቷል :

በአዲስ አበባ :-

* ባለፈው ዓመት በ2015
4 ሺህ 696 በፍቺ ምክንያት ትዳር የተበተነ ሲሆን

* በዚህ ዓመት በ2016 ደሞ
8 ሺህ 949 በፍቺ ምክንያት ትዳር ተብትኗል::

Note: ይህ ቁጥር

* ዝም ብሎ
* እልል ብሎ
* እልምም ብሎ

ትዳሩን ጥሎ

* የጠፋ
* የጠፋችን ሳይቆጠር ነው:
በጉርሻ ፔጅ

በጠበቃና የሕግ አማካሪ 0920666595
#ጠበቃ #ሚኪያስመላክ #MikiasMelak
አለሕግ #Alehig
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

👉Telegram👈
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.wordpress.com
👍75😱3😢3