አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም። ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።

ሰ/መ/ቁጥር 215444 | ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም


👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍10🥰3
Forwarded from ሕግ ቤት
ሰ/መ/ቁጥር 220553 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም
ከተሽከርካሪ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ተከሳሽ ጉድለት ያለበትን ተሽከርካሪ ስላስረከበኝ በተሽከርካሪው ሰርቼ ማግኘት ያለብኝን ገቢ እንዲከፍለኝና ውሉ እንዲሰረዝ በሚል በከሳሽ የተጠየቀ ዳኝነት እንደውሉ ባለመፈጸሙ ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ካሳ እንዲከፈልና እና ውሉ እንዲሰረዝ (actions for cancellation of a contract and damage) የቀረበ ክስ በመሆኑ በክሱ ላይ ተፈጻሚነት ያለዉ የይርጋ ጊዜ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1845 ስር የተደነገገዉ የ 10 ዓመት የይርጋ ጊዜ እንጂ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2298 ስር የተደነገገዉ አይደለም።
👍19
ወላጆች ለህፃናት ልጆቻቸው ሞግዚትና አስተዳዳሪ የመሆን መብታቸው ሊከበር የሚችለው ለህፃናቱ ጥቅምና ደህንነት እስከሰሩ ወይም ሊሰሩ የሚችሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ ሲቻል ብቻ ነው ።

አባት ከመወለዱ በቀር አይቶት የማያውቅ ልጅ እናቱ በምትሞትበት ጊዜ ለልጅ ጥቅም ሳይሆን በንብረቱ ለመገልገል በማሰብ ሞግዚት እና አስተዳደሪ እንዲሆን ቢጠይቅ ከህገመንግስቱ አንቀፅ 36 አንፃር የህፃናትን ጥቅም ለማስጠበቅ ተብሎ ተከልክሎ ሌላ ሰው ሊሾም ይገባል።
የሰ/መ/ቁ23632 ቅፅ 5
ይህ ጽሁፍ ለጠቅላላ እውቀት ብቻ ነው።
ለበለጠ መረጃ የሕግ ባለሙያ/ጠበቃ ያማክሩ!
0920666595
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig
👍3
የትምህርት_ማስረጃ_ማረጋገጫ_እና_የአቻ_ግመታ_መመሪያ_990.pdf
5.5 MB
Educational Credentials Authentication and Equivalency Directive No 990/2024
ትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ
👍14🤬1
 ክርክሩ የስራ ክርክር ሲሆን የምድብ ችሎትን ስልጣን በተመለከተ ያቀረበው መቃወሚያ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 222 መሰረት አንድ ከሳሽ በክስ አቤቱታው ላይ የተከራካሪ ወገኖች ሙሉ አድራሻ መገለፅ አለበት፡፡
ይህ የሚሆንበት ዋናው ጉዳይ የሚታይበትን ምድብ ችሎት ለመለየት እና ባለጉዳዮች በፍርድ ቤት አሰራር በሚደረግ ምደባ እንጂ በግል ዳኛና ምድብ ችሎቶችን እንዳይመረጡ ለማስቻል ነው፡፡ በዚህም መሰረት የአመልካች አድራሻ የካ ክፍለ ከተማ ሲሆን የተጠሪ አድራሻ ደግሞ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ነው ሆኖ እያለ ጉዳዩ በአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት ጉዳዩን የማየት ሥልጣን እንደሌለዉና ፍርድ ቤቱ ባስቀመጠዉ አሰራር መሰረት መዝገቡ ለየካ ምድብ ችሎት እንዲተላለፍ በማለት ነው።
ችሎቱ ይህን አስመልክቶ የሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጉም የሚከተለው ነው።
አሁን ባለዉ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በፌዴራል ደረጃ ያለዉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንድ ፍርድ ቤት ብቻ እንደሆነና የሚያስችለዉም በአዲስ አበባ እና በድሬ ዳዋ ከተሞች እንደሆነ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/3 ፣ ከአንቀጽ 14-16 እና 30/2 ስር ከተደነገጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በየክፍለ ከተማዉ ያሉት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች በሕግ የአካባቢ(የግዛት ክልል)ሥልጣናቸዉ ተወስኖ የተደረጁ ሳይሆኑ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ተደራሽ ለመሆን በአስተዳደራዊ ዉሳኔ የተዋቀሩ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም በሬጅስትራር በኩል መዛግብቶች ሲከፈቱ ምድብ ችሎቶቹ የተዋቀሩበትን ዓላማ በሚያሳካ መልኩ እየታየ መዝገቦች እንዲከፈቱ መደረግ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የአንድ ክስ መዝገብ የተከሳሹ አድራሻ ከሚገኝበት ክፍለ ከተማ ዉጭ በሆነ ምድብ ችሎት ዘንድ ከተከፈተ ምድብ ችሎቱ በአንድ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ማዕቀፍ ዉስጥ ሆኖ ጉዳዩን የሚዳኝ በመሆኑና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአካባቢ(የግዛት ሥልጣን)በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በመላዉ የከተማ አስተዳደሩ ግዛት ክልል ዉስጥ በመሆኑ ክሱ የቀረበለት ምድብ ችሎት ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን የለዉም ተብሎ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም፡፡

አመልካች ምድብ ችሎትን መምረጥ ዳኛን እንደመምረጥ የሚቆጠር ነዉ በማለት ያነሳዉን ክርክር በተመለከተም አንድ ዳኛ ከባለጉዳዩ ወይም ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ስላለዉ ጉዳዩን የገለልተኛነት እና የዳኝነት ነጻነት መርህ ጠብቆ ለመዳኘት አይችልም የሚባል ከሆነ ዳኛ ከችሎት እንዲነሳ የሚጠየቅበት ሥነ ሥርዓት በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 33 እና 34 ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡በመሆኑም አመልካች ጉዳዩን ከዳኘዉ ምድብ ችሎት ተገቢነት ጋር በተያያዘ ያቀረበዉን ክርክር የሥር ፍርድ ቤት ባለመቀበሉ የተፈጸመ ስህተት አላገኘንም፡፡
የሠ/መ/ቁጥር 205068 ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም የምድብ ችሎት ስልጣን
በአብርሃም ዮሀንስ ሎው ኮርነር ቴሌግራም ገጽ ተገኘ
ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ።

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


👉የቴሌግራም ቻናል 👈

👉Facebook Page 👈

👉YouTube 👈

0920666595
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
👍132
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የጆሮ ማዳመጫ አድርገው ዜብራ ሲያቋርጡ የሚገኙ እግረኞችን 80 ብር መቅጣት መጀመሩ ታውቋል።ከሳምንት በፊት ለሚኩራ ክ/ከተማ ጎሮ አደባባይ የተጀመረው ቅጣት በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎችም እየተጀመረ ነው ተብሏል።
https://t.me/lawsocieties
#አለሕግ #Alehig @Lawsocieties
ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ።

0920666595

👉የቴሌግራም ቻናል 👈

👉Facebook Page 👈

👉YouTube 👈
http://alehig.wordpress.com/
👍134
205068_የምድብ_ችሎት_ስልጣንና_የስራ_መሪ.pdf
509 KB
 ክርክሩ የስራ ክርክር ሲሆን የምድብ ችሎትን ስልጣን በተመለከተ ያቀረበው መቃወሚያ

ይህ የሚሆንበት ዋናው ጉዳይ የሚታይበትን ምድብ ችሎት ለመለየት እና ባለጉዳዮች በፍርድ ቤት አሰራር በሚደረግ ምደባ እንጂ በግል ዳኛና ምድብ ችሎቶችን እንዳይመረጡ ለማስቻል ነው፡፡
አሁን ባለዉ የፍርድ ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በፌዴራል ደረጃ ያለዉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አንድ ፍርድ ቤት ብቻ እንደሆነና የሚያስችለዉም በአዲስ አበባ እና በድሬ ዳዋ ከተሞች እንደሆነ ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 2/3 ፣ ከአንቀጽ 14-16 እና 30/2 ስር ከተደነገጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ በየክፍለ ከተማዉ ያሉት
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምድብ ችሎቶች በሕግ የአካባቢ(የግዛት ክልል)ሥልጣናቸዉ ተወስኖ የተደረጁ ሳይሆኑ ለተገልጋዩ ሕብረተሰብ ተደራሽ ለመሆን

በአስተዳደራዊ ዉሳኔ የተዋቀሩ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም በሬጅስትራር በኩል መዛግብቶች ሲከፈቱ ምድብ ችሎቶቹ የተዋቀሩበትን ዓላማ በሚያሳካ መልኩ እየታየ መዝገቦች እንዲከፈቱ መደረግ ያለበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ
የአንድ ክስ መዝገብ የተከሳሹ አድራሻ ከሚገኝበት ክፍለ ከተማ ዉጭ በሆነ ምድብ ችሎት ዘንድ ከተከፈተ ምድብ ችሎቱ በአንድ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሥልጣን ማዕቀፍ ዉስጥ ሆኖ ጉዳዩን የሚዳኝ በመሆኑና የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአካባቢ(የግዛት ሥልጣን)በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በመላዉ የከተማ አስተዳደሩ ግዛት ክልል ዉስጥ በመሆኑ ክሱ የቀረበለት ምድብ ችሎት ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን የለዉም ተብሎ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም፡፡
👍174
የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ ክልከላ በተደረገባቸው እቃዎችና ተሽከርካሪዎች ላይ የተደረገ ማስተካከያ
https://t.me/lawsocieties
#አለሕግ #Alehig @Lawsocieties
ምንም ውሳኔ ከመወሰንዎ በፊት አማራጭ የሕግ እውቀት ያግኙ።

0920666595

👉የቴሌግራም ቻናል 👈

👉Facebook Page 👈

👉YouTube 👈
👍10🤯1