አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ኤግዚቢት ምንድን ነው?
በተለያዩ አጋጣሚዎች ኤግዚሂቢት ተያዘ፣ ኤግዚቢት ተመለሰ፣ ቀረበ ወዘተ ሲባል ሰምተዋል ብለን እናስባለን። ለመሆኑ ኤግዚቢት ምንድን ነው?

በክርክር ሂደት የአንድን አከራካሪ ፍሬ-ነገር መኖር ወይም አለመኖር ማረጋገጥ የሚቻለዉ ማስረጃ በማቅረብ ነዉ፡፡ ማስረጃ በምስክሮች፣ በሰነድ ወይም በተለይ በወንጀል ክርክር በኤግዚቢት መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ በዚህ ፅሁፍ የኤግዚቢትን ምንነት እና ኤግዚቢትን በሚመለከት የሚሰጡ ውሳኔዎችን በአጭሩ እንደመለከታለን፡፡

የኤግዚቢት ምንነት

ኤግዚቢት በወንጀል ምርመራ ወይም ክስ ሂደት አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ ማስረጃ ተደርጎ የሚቀርብ ተጨባጭነት ያለው ንብረት ወይም ቁስ (real item) ነው፡፡ አንድ ቁስ ኤግዚቢት ሊሆን የሚችለው ተፈፀመ ከተባለው የወንጀል ድርጊት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አሣማኝ ግንኙነት ያለው ሲሆን ነው፡፡ ኤግዚቢት ወንጀሉ የተፈፀመበት፣ ለመፈፀሚያነት የዋለ እና ሌላ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ያለውን ቁስ ሁሉ ያካትታል፡፡

ኤግዚቢትን በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎች
ዐቃቤ ህግ ኤግዚቢቱ የማስረጃነት ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ካገኘው ክስ ሲመሰርት የኤግዚቢቱን ምንነት እና ያለበትን ሁኔታ በማስረጃ ዝርዝር በመጠቀስ ሊጠቀምበት ወይም ፍርድ ቤት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ኤግዚቢት በዚህ መልኩ በማስረጃነት የሚቀርበው ፍርድ ቤት ተመልክቶት በክሱ የተካተተው የወንጀል ፍሬ ነገር መፈፀሙን ግንዛቤ እንዲወስድ ለማስቻል ሲሆን ፍርድ ቤቱ በዋናው ጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ አብሮ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡ በአንፃሩ ዐቃቤ ህግ የቀረበውን ኤግዚቢት የማስረጃነት ጠቀሜታ ካላገኘበት ወይም ሌላ በቂ ማስረጃ ካለው እንደ ኢግዚቢቱ አይነት ንብረቱ ለባለቤቱ እንዲመለስ፣ በህግ መሰረት ለመንግስት ገቢ መሆን ያለበት ከሆነ ገቢ እንዲሆን ወይም አደገኛ በመሆኑ መወገድ ያለበት ከሆነ እንዲወገድ ሊወስን ይችላል፡፡

ፍርድ ቤት ኤግዚቢት በማስረጃነት ተጠቅሶ ከቀረበለት ኤግዚቢቱ ለወንጀል ተግባር ሊያገለግል የሚችል ወይም ያገለገለ ወይም የወንጀል ተግባር ፍሬ ከሆነ እና የህዝብ ሰላም፣ ጤና እና መልካም ጠባይን የሚጎዳ ሲሆን እንዲወረስ የመወሰን ስልጣን አለው፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀፅ 100(1) መሰረት ወንጀል ለመፈፀም ማነሳሻ፣ ለተፈፀመ ወንጀል ዋጋ የተሰጠ ወይም ሊሰጥ የታቀደ ጥቅም ሁሉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በወንጀል ህግ አንቀፅ 98(2) ላይ እንደተመለከተው ተከሳሹ ጥፋተኛ ከተባለ ወንጀለኛው በወንጀል ተግባሩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ያገኘውን ንብረት ሁሉ እንዲወረስ ሊወሰን ይችላል፡፡ በአንፃሩ ንብረቱ የግለሰብ ንብረት ከሆነ እና ንብረቱ አደገኛነት የሌለው ወይም በህግ ያልተከለከለ የንፁ ሶስተኛ ወገኖች ንብረት ከሆነ ለባለቤቱ እንደሚመለስ ከወንጀል ህጉ አንቀፅ 140(2) መረዳት ይቻላል፡፡ ሆኖም ባለንብረቱ እስከ 5 አመት ካልተገኘ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ንብረቱ በባህሪው ጎጂ ከሆነ ማለትም እንደ አደገኛ እፅ፣ የተበላሹ መድሀኒቶች እና የመሳሰሉት ከሆነ እንዲወገድ ውሳኔ ይሰጣል፡፡

በሌላ መልኩ የሚነሳው እግዚቢት እና የወንጀል ፍሬ መካከል ያለው ግንኘነት ነው፡፡ እላይ በተገለፀው አግባብ አንድ ማስረጃ ኤግዚቢትም የወንጀል ፍሬም ሊሆን ይችላል፡፡ አግዚቢት የወንጀል ፍሬ በሚሆንበት ጊዜም በህግ የሚወረስ ሲሆን ይህንኑ እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው ህጋዊ ለማስመሰል መሞከር በተጨማሪ ወንጀል ያስጠይቃል፡፡ በዚህም በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኘነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 አንቀፅ 35 መሰረት ንብረቱ ወይም ገንዘቡ ከወንጀል የተገኘ ሲሆን ህጋዊ ለማስመሰል ከተሞከረ ለወንጀሉ መፈፀሚያ የዋለ ንብረት፣ በንብረቱ ተለውጦ የተገኘው ፍሬ፣ ንብረቱ ተቀላቅሎት የተገኘው ወንጀለኛው ንብረት እንደሚወረስ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የሙስና ወንጀልን በተመለከተ በተሻሻለው ልዩ የፀረ ሙስና ሥነ ሥርአትና የማስረጃ ህግ አዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀፅ 29 መሰረት በሙስና ወንጀሉ ወንጀለኛው ያገኘው ንብረት እና በዚሁ ንብረት ያፈራው ንብረት እንዲሁም በመንግስት፣ በህዝባዊ ድርጅት እና የመንግስት የልማት ድርጀት ጥቅም ላይ ላደረሰው ጉዳት ማካካሻ የሚሆን የወንጀለኛው ንብረት ሊወረስ ይችላል፡፡

በጥቅሉ ኤግዚቢት ከአንድ ከተፈፀመ ወንጀል ጋር ግንኙነት ያለው እና ወንጀሉ ስለመፈፀሙ የሚያሳይ ተጨባጭነት ያለው ንብረት ወይም ቁስ ሲሆን ይህንኑ ንብረት በተመለከተ የሚሰጡ ውሳኔዎችም እንደየ ጉዳዩ አይነት ንብረቱ በመንግስት እንዲወረስ፣ ለባለቤቱ እንዲመለስ ወይም እንዲወገድ ሊወሰን ይችላል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
አለመቻሉ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
በፍትሀብሄር ክርክር የሚቀርብ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ

ሰዎች በእለት ተእለት በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በራሳቸው መፍታት ሳይችሉ ሲቀሩ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረባቸው በየእለቱ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ሲቀርብም ከክስ አቀራረብ ጀምሮ የክርክር ሂደቱ የሚመራበት ሥነ ሥርአት አለው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ በሚያቀርብበት ወቅት ሊቀርብ የሚችልን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምንነት እንዲሁም የሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ እንመለከታለን።

የመጀመሪያ ደርጃ መቃወሚያ ምንነት

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናው ክርክር መግባት ሳያስፈልግ የቀረበው ክስ ውድቅ የሚሆንበትን ምክንያት በመግለፅ ክሱ ውድቅ እንዲሆን በማንኛውም ተከራካሪ ወገን የሚቀርብ መቃወሚያ እንደሆነ ከፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(1) መረዳት ይቻላል።

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ምክንያቶች

አንድ ሰው የፍትሐብሔር ክስ ቀርቦበት መልስ እንዲያቀርብ በታዘዘ ጊዜ በቀረበበትን ክስ ላይ ከሚያቀርባቸው ክርክሮች መካከል አንዱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነው። የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244(2) የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊቀርብ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በዝርዝር አመልክቷል፡፡ ይኸውም፡-

• ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ነገሩን ወይም የቀረበውን ክስ ለመስማት ስልጣን የሌላው ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ ከሆነ
• ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ ከሆነ
• አንደኛው ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ገብቶ መከራከር አይገባውም የሚባል ከሆነ
• ክሱ በይርጋ የታገደ ከሆነ
• ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ ከሆነ
ይህን በመግለፅ መቃወሚያ ሊቀርብ ይችላል።

ለቀረበበት ክስ መልስ የሚሰጥ ማንኛውም ወገን ከላይ ከተጠቀሱት መቃወሚያዎች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ እንደመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሊያቀርብ የሚችል ሲሆን በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው መቅረብ አለባቸው። አንድ ተከራካሪ መቅረብ ከሚገባው መቃወሚያ ውስጥ አንዱን የተወ እንደሆነ ፍርድ ለመስጠት የሚያሰናክል ካልሆነ በስተቀር መቃወሚያውን ለማቅረብ እንዳልፈለገ እንደሚቆጠር በድንጋጌው ንኡስ ቁጥር 3 ላይ በግልፅ ተመልክቶ ይገኛል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔና ውጤቱ

የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ሲቀርብ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ሌላኛው ወገን በጉዳዩ ላይ ያቀረበውን ክርክር ከሰማ በኋላ በቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማስረጃ እንዲቀርብለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(1) መሰረት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ተገቢና በቂ በሆነ ማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ የቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ጉዳይ በመሆኑ ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ በመሆኑ ወይም ለእርቅ የተቀጠረ በመሆኑ እንደሆነ የቀረበውን ክስ በመዝጋት ባለጉዳዮችን ያሰናብታል። የቀረበው መቃወሚያ ከእነዚህ ውጭ ሆኖ መቃወሚያው ተገቢ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ባረጋገጠ ጊዜ መዝገቡን በመዝጋት ተገቢ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።

ሌላው የቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት አግኝቶ መዝገቡ የተዘጋ እንደሆነ ከሳሽ ክሱን አሻሽሎ በዚያው ጉዳይ መጀመሪያ ክስ ላቀረበበት ፍርድ ቤትም ይሁን ለሌላ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ክሱን እንደገና የማቅረብ መብቱ የተረጋገጠ ሲሆን ፍርድ ቤቱም መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት ከሳሽ እንደገና ክስ የማቅረብ መብት እንዳለው በትእዛዙ ላይ መግለፅ እንደሚችል በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(3) ላይ በግልፅ ተደንግጎ ይገኛል።

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቱ መዝገቡን የዘጋው ‘ፍርድ ቤቱ ነገሩን የማየት ስልጣን የለውም’ በሚል መቃወሚያ መሰረት ሲሆን ከሳሽ ከከፈለው የዳኝነት ገንዘብ ላይ የሚቀነሰው ተቀንሶ የተረፈው ገንዘብ እንደሚመለስለት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 245(4) ላይ በግልፅ ተደንግጓል።

በአጠቃላይ የፍትሐብሔር ክስ የቀረበበት ማንኛውም ሰው ወደ ዋናው ክርክር ከመግባቱ በፊት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ህግ ቁጥር 244 ሥረ የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባሉ ጊዜ ይህንኑ በመጥቀስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ይህም ወዲያውኑ መቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
በድሬዳዋ ሊሰርቅ የሰው ቤት ገብቶ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ውስኪ ሲጠጣ የተገኘው ሌባ በ3 አመት እስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታወቀ!

ተከሳሽ እንዳሻው ታደሰ ነዋሪነቱ በድሬዳዋ ከተማ ሲሆን ሀምሌ 9 ቀን 2015ዓ.ም ከቀኑ 8ሰአት ገደማ በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ጎሮ 32 መንገድ ከሚገኘው የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በር ሰብሮ በመግባት ነበር አስገራሚ የሆነውን ተግባር የፈፀመው።

ተከሳሹ የግል ተበዳዮችን በር ሰብሮ ከገባ በኋላ ጤረጵዛ ላይ ታብሌት ስልክ ተቀምጦ ይመለከታል እሱን ይዞ ለመውጣት ያስብና ቀና ሲል ውስኪ ብፌ ውስጥ ያያል ልቡ ሸፈተ ቆይ በዚህ ውስኪ ለምን ትንሽ ዘና አልልም ይልና ብርጭቆ አቅርቦ ሶፋ ላይ ፈልሰስ ብሎ ተቀምጦ ልክ እንደራሱ ቤት እየተዝናና እያለ ነበር ከተወሰነ ሰአት በኋላ የግል ተበዳዮች መምጣታቸውን ይሰማና ጠረጴዛ ላይ የነበረውንና የዋጋ ግምቱ 12ሺ ብር የሚያወጣ ታብሌት ስልክ ብድግ አድርጎ በድንጋጤ ሽንት ቤት ይደበቃል፣ የግል ተበዳዮችም ወደ ቤታቸው ሲገቡ ውስኪውን እና ብርጭቆ ጤረጴዛ ላይ ይመለከታሉ ታዲያ በዚህ ሰአት ማነው እዚህ ቤት የገባው ብለው በድንጋጤ ቤታቸውን ሲፈትሹ ተከሳሹን ግለሰብ ከነሰረቀው ንብረት ሽንትቤት ውስጥ እጅከፍንጅ በመያዝ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይደውላሉ።

በዚህም መሰረት ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ ወደ ጣቢያ ይወሰዳል ለፈፀመው ከባድ የስርቆት ወንጀልም በአቃቤ ህግ ክስ ይመሰረትበታል።

በፖሊስ ተጣርቶ በአቃቤ ህግ የተመሰረተበትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሀምሌ 21 ቀን 2015ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ እንዳሻው ጥፋተኛ ሆኖ ስላገኘው በሶስት አመት ከሶስት ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ዘገባው የድሬዳዋ ፖሊስ ነው።
#ethio_mereja
#State_of_Emergency

ነገ በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕዝብ ተወካዮች በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል።

ምክር ቤቱ፤ ከቀናት በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ሰኞ 8 ሰዓት ለምክር ቤት አባላት አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ መሰረት አባላት ተሰብስበው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሕጉ ምን ይላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሀ) ይደነግጋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የታወጀ እንደሆነ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት፣ የምክር ቤቱን ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘም ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ ቀጣይ አንቀጽ ይደነግጋል።

6ኛው ዙር ምርጫ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭትና አለመረጋጋት ሳቢያ በተሟላ ሁኔታ ባለመከናወኑ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ካሉት 547 ወንበሮች መካከል የተወሰኑት የተጓደሉ ናቸው።

በአጠቃላይ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው ምክር ቤት መቀመጫ የያዙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት 427 መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ም/ ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ ይኖርበታል በሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊፀና የሚችለው ከአጠቃላይ የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በስድስተኛው ዙር ተመርጠው በምክር ቤቱ መቀመጫ ከያዙት 427 ተወካዮች መካከል 285 የሚሆኑት የድጋፍ ድምፅ ከሰጡ ነው።

ከተጠቀሱት 427 ተመራጮች ውስጥ 142 የምክር ቤት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ከሰጡ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ ሊሆን ይችላል። 

በም/ቤቱ ወንበር ካገኙ አጠቃላይ 427 አባላት ወስጥ 410 የሚሆኑት በገዢው ፓርቲ ብልፅግና አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 125 ያህሉ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት የተወዳደሩና የክልሉን ሕዝብ የሚወክሉ ናቸው።

ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ አምስት የሕዝብ ተወካዮች ሲኖሩ፣ በኢዜማ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ ሌሎች አራት የሕዝብ ተወካዮች እንደሚገኙም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ በቀረቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ላይ ለተሰጠው ድምፅ ሥሌት የተደረገው በዕለቱ የነበረውን የምክር ቤቱ ምልዓተ ጉባዔ መሠረት አድርጎ በመሆኑ፣ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምክር ቤት በሚቀርብበት ወቅት የሚኖረው የድምፅ አሰጣጥ ሥሌት በዕለቱ የሚኖረውን ምልዓተ ጉባዔ ታሳቢ የሚያደርግ ይሆናል።

በመሆኑም የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሥሌቱ ከላይ የምክር ቤቱን ጠቅላላ አባላት መሠረት በማድረግ ከተገለጸው ውጤት ያነሰ የድጋፍ እና ተቃውሞ ድምፅ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

(የሕግ ጉዳይ ማብራሪያ ከሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
ስለ ይዞታ እና የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት
በ፡ ሙሉቀን ሰዒድ

በዚህ አጭር ጽሑፍ የይዞታ ትርጉም ምን እንደሆነ፣ ይዞታን መሠረት ያደረገ የሁከት ይወገድልኝ ክስ በምን አግባብ ሊቀርብ እንደሚችልና ይህ ክስ ከባለቤትነት ክርክር ጋር ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ፣ ሁከት ይወገድልኝ የሚል ክስ ሲቀርብ ፍርድ ቤቶች የሚይዙት ጭብጥ በተመለከተ ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቀዳሚነት ግዥ ይገባኛል የማለት መብት ትርጓሜው ምን እንደሆነና ቀዳሚ የመግዛት መብት ካለው መሀከል ባልና ሚስትን፣ ወራሾችን በተመለከተ በህጉ ሊስተናገዱ የሚችሉበት አግባብ ለማየት ተሞክሯል፡፡

በመጨረሻም የቅድሚያ ግዥ መብት ያለው ሰው በሚገዛበት ጊዜ ስላለው የሽያጭ ስነ- ስርዓት፣ ግድግዳና ጣራቸው በአንድ በኩል የተያያዙ ቤቶችን በተመለከተ በቅድሚያ ግዥ መብት ሊስተናገዱ የሚችሉበት የህግ አግባብና የዘመዶች በቅድሚያ የመግዛት መብትን እስመልክቶ በጽሁፍ በወፍ በረር ቅኝት ተደርጎበታል፡፡

መልካም ንባብ!

https://www.abyssinialaw.com/blog/possessory-action-and-priority-acquisition
ክስ ይዛወርልኝ

• በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ የግዛት ስልጣን በሌለው ሌላ ፍርድ ቤት ወይም በዛው ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት ተዛውሮ እንዲታይ በመጠየቅ በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ

በአንድ ወረዳ ፍ/ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ወደ ሌላ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ አንደኛው ወገን ሲያመለክት ተገቢ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጦ በክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው እንደየሁኔታው አግባብነት ያለው ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም ቀድሞ የተዘጋ መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ የሚቀርብ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 93171 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 31

የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ /Change of Venue/ የሚስተናገድበትን አግባብ ህጉ የዘረጋው ስርዓት ያለ ሲሆን በ1958ቱ የፍትሐብሔር ስነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 31 ስር የተመለከተው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ህግ በኋላ በፌደራልም ሆነ በክልሎች የወጡት የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጆች ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ድንጋጌ ስራ ላይ አውለው ይገኛል፡፡ አንድ ክስ ወደ ሌላ ስፍራ ሊዛወር የሚችልበትን አግባብ ከሚደነግጉት የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ጥያቄው ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ መሆኑና ህጋዊ ምክንያቶች ተብለው በህጉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ መሟላት ያለበት መሆኑን ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 66945 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
31
ኢትዮ-ሕግ🇪🇹⚖️🇪🇹Ethio-Law
   ለቴሌግራም መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
#EthioLawtips

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሳካት የግል ዘርፉ ሚና ወሳኝ ነው።
========================
አዲስ አበባ 10/12/2015ዓ.ም (ንቀትሚ) ኢትዮጵያ የፈረመችበትና ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰችበት የምትገኝበት የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ዓላማዎች መሳካት የግል ዘርፉ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፡፡

የንግድ ቀጣናው ስለሚፈጥራቸው እድሎችና ፈተናዎች ግንዛቤውን ማሳደግ፤ ለብሄራዊ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናው ትግበራ ስትራቴጂ ግብአት መስጠት፤ በብሄራዊ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ኮሚቴ አባል በመሆን ማገዝ፤ በቀሪዎቹ የድርድር ጉዳዮች ላይ የመንግስትን አቋም መደገፍ ወይም ተፅእኖ መፍጠር እንዲሁም  በንግድ ቀጣናው ውስጥ በንግድና ኢንቨስትመንት መሳተፍ የግል ዘርፉ ተሳትፎውን ሊያረጋግጥባቸው የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ጥናቶችን በማድረግና ምክረ ሀሳቦችን ለመንግስት በማቅረብ የፖሊሲ፣ የህግና ተቋሟዊ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ጫና ማድረግ ብሎም  ከመንግስት ጋር ግልፅና መደበኛ ውይይቶችን በማድረግ በአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣናው ዙሪያ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ተጠቃሚነቱን እና ተወዳዳሪነቱን ማረጋገጥ እና ጉዳቱን መቀነስ እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣውን አስመልክቶ በተሰጠው ስልጣና ላይ ተብራርቷል፡፡

http://www.motri.gov.et
Ethiopian ministry of trade and regional itegration
የፍቅረኛውን ምስል ያለፈቃዷ ያጋራው ሰው 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር እንዲከፍል ተወሰነበት


ግለሰቡ ፍቅረኛውን ለመበቀል ሲል የእርቃን ፎቶዎችን ከፈቃዷ ውጪ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ አጋርቷል ተብሏል።
ሙሉውን ያንብቡ፦
https://am.al-ain.com/article/man-fined-us-posting-lover-photo
የልጅን ስም የማውጣት ቀዳሚ መብት የአባት ነው 😁
ሴቶች እንዳትናደዱ እኔ አላልኩም ህጉ ነው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 34 (1)የአንድን ልጅ የግል ስም የሚመርጠው አባቱ ወይም አባቱ በሌለ ግዜ የእናቱ ቤተ ዘመድ ነው::
(2) ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርስዋ እንደሌለች የእናቱ ቤተ ዘመዶች መርጠው ቢያወጡለት ይችላሉ ምን ለማለት ነው ከባሎቻችሁ ጋር ብዙ ስም ለማውጣት አትከራከሩ በህጉ አግባብ ቀዳሚ መብት የነርሱ ነው ::
via Tigist Kibret
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
አለሕግAleHig ️
የልጅን ስም የማውጣት ቀዳሚ መብት የአባት ነው 😁 ሴቶች እንዳትናደዱ እኔ አላልኩም ህጉ ነው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 34 (1)የአንድን ልጅ የግል ስም የሚመርጠው አባቱ ወይም አባቱ በሌለ ግዜ የእናቱ ቤተ ዘመድ ነው:: (2) ለልጁ ሁለተኛ የግል ስም እናቱ ወይም እርስዋ እንደሌለች የእናቱ ቤተ ዘመዶች መርጠው ቢያወጡለት ይችላሉ ምን ለማለት ነው ከባሎቻችሁ ጋር ብዙ ስም ለማውጣት አትከራከሩ በህጉ አግባብ…
የፍታብሔር ህጉ አንቀጽ 34(1) ስንመለከት የእናት ስም የማውጣት ደረጃ 3ኛ ላይ ሆኖ እናገኘዋለን🤔🤔...

መጀመሪያ #አባት እሱ ከሌለ #የእናት_ቤተዘመዶች(እዚህ ጋር የአባት ቤተሰብ ለማለት ተፈልጎ የጽሑፍ ስህተት ይመስለኛል ምክንያቱም አንቀጽ 34(2) ላይ እናት ከሌለች የእናት ቤተዘም ይላል) ሶስተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ #እናት ተቀምጣለች የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 34(2) ላይ ተቀምጧል።

እዚህ ጋር ማየት ያለብን ነገር የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 34(1) እና 34(2) ላይ የተቀመጠው ከFDRE ህገመንግስት አንቀጽ 35 ጋር በግልጽ ይቃረናል ህገመንግስቱ ሴት በሁሉም ነገር(በቤተሰብ፣ ንብረት በማስተዳደር፣ንብረት በማፍራት....) ከወንድ እኩል መብት አላት ይላል። የህገመንግስቱን እና የፍትሐብሔር ህጉን Hierarchy ስንመለከት ህገመንግስቱ ከላይ ሆኖ እናገኘዋለን ይህ ማለት የፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 34 በህገመንግስቱ አንቀጽ 35 የተሻረ ነው።
እና ምን ለማለት ነው ባሎቻችሁ እኛ በህጉ መሰረት የልጃችንን የመጀመሪያ ስም የማውጣት ተቀዳሚ መብት አለን ካሉ እንዳተሰሙ ለማለት ነው።😂
Via Ephrem H/mariam

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Forwarded from Higawinet
ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመድ በማጋራት ስለ ህግ አጠቃላይ እውቀት እና መረጃ ጅንዲኖራቸው በማድረግ ተመስጋኝ ይሁኑ።
👆👆👆👆👆👆👆

#አለ_ህግ የቴሌግራም ቻናል
ጠቃሚ በመሆኑ ጓደኞቼ እና ወዳጅ ዘመዶቼን በማጋራት ሼር በማድረግ እንዲጠቀሙ አደርጋለሁ።

ማን ያውቃል የትኛው መረጃ ለማን እንደሚጠቅም...
ብቻ ሼር አደርጋለሁ።
አለ ህጎች በርቱ። #Ale_Hig #Lawsocieties #Share #ሼር @Lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Worth Reading the Key learnings from "How to Live on 24 Hours a Day" by Arnold Bennett, along with illustrative examples:

1. Value Time Wisely:
Recognise the true worth of time and avoid wasting it on trivial activities. Instead of endlessly scrolling through social media, use that time constructively, such as reading a book or acquiring a new skill.

2. Prioritise Meaningful Pursuits:
Give precedence to activities aligned with personal aspirations and contentment. If physical fitness is a priority, allocate time for regular exercise over less significant commitments.

3. Establish a Structured Routine:
Create a well-organized daily routine to optimize time utilization. Designate specific time blocks for work, family, hobbies, and self-improvement.

4. Eliminate Time Drains:
Identify and remove activities that consume time without adding value. Minimize excessive TV viewing and social media engagement to free up hours for more purposeful endeavors.
Continued.... 👆👆👆👆👆👆

5. Make Commuting Time Count:
Maximise commuting time by engaging in productive pursuits. Utilize public transport time for reading or listening to educational podcasts.

6. Harness Brief Time Intervals:
Capitalise on short gaps in your day for productive tasks. Use waiting periods or breaks for tasks like responding to emails or brainstorming ideas.

7. Intentional Leisure Time:
Approach leisure time with purpose. Plan and allocate time for enjoyable recreational activities rather than aimless weekends.

8. Prioritise Quality over Quantity:
Focus on effectiveness rather than filling every hour with tasks. Dedicate focused and efficient hours to work instead of dragging tasks over extended periods.

9. Regular Self-Reflection:
Reflect on daily time usage and make necessary adjustments. Allocate a few minutes each day to review time allocation and identify areas for enhancement.

10. Strive for Balance: Embrace a balanced lifestyle to prevent burnout. Allocate time for rest, relationships, recreation, and personal goals alongside work commitments.

These insights and examples highlight practical strategies from "How to Live on 24 Hours a Day" that empower individuals to manage their time effectively and lead more fulfilling lives.
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ለፌደራል ጠበቆች የህግ አማካሪዎች እና የጥብቅና ድርጅቶች አዲስ መረጃ ‼️
******

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህ
በር ለፌደራል ጠበቆች የህግ አማካሪዎች እና የጥብቅና ድርጅቶች የግብር አከፋፈል ላይ ለአመታት የቀጠሉ እና ባለፉት ሁለት አመታት ደግሞ እጅግ ተባብሰው የቀጠሉ የህግ እና የአሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውንና ማህበሩም የሚደርስበትን ውጤት በየግዜው እንደሚያሳውቅ መግለፁ ይታወሳል::

- በዚህም ደረጃ "ሐ" ግብር ከፋይ ጠበቆችን በተመለከተ በተደረገው ከፍተኛ ጥረት ሁሉም ጠበቆች እና የህግ አማሪዎች በየቅርንጫፎቻቸው መስተንግድዎ እንዲያገኙ ተደርጎ ተጠናቋል::

የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር በተመለከተ በጠበቆች ማህበር አስተባባሪነት ከፍትህ ሚ/ር እና ከገንዘብ ሚኒስቴር በተውጣጡ ባለሙያዎች የተደረገው ጥናት ከተቀመጡ መደምደሚያና መጠቁሞች Conclusions & Recommendations አብዛኞቹ በፖሊሲ አውጪው አካል ተቀባይነት ማግኘታቸውን ለማብሰር እንወዳለን::

ይህንኑም የገንዘብ ሚ/ር በቀን 05/12/2015ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ ለማህበሩ አሳውቋል:: በዚሁ መሰረት ፤

- ማናቸውም - ገቢውን ለማመንጨት ፤ -ስራውን ዋስትና ለመስጠት እና - ስራውን ለማስቀጠል የሚወጡ የጠበቆች ወጪዎች በሙሉ በተቀናሽነት እንዲያዙ ተወስኗል::

- ይህም ሲሆን ለምሳሌ ለመኪና ታርጋ ቁጥር (ኮድ 2 መሆን አለመሆኑ) ፤ የንግድ ፍቃድ አለመኖር እና ተያያዥ በግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ይቀርቡ የነበሩ ምክንያቶች ቀሪ እንዲሆኑ ተወስኗል::

በሌላ በኩል ይህ መመሪያ ለተጠናቀቀው የግብር ዘመን ሊፈፀም ስለሚችልበት ሁኔታ የማህበሩ አመራር ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ጋር በደብዳቤና በአካል ንግግሮችን እያደረገ ያለ ሲሆን የዚህኑ ውጤት በቅርብ ቀናት በተመሳሳይ የምናሳውቅ ይሆናል:: በተያያዘ የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮች በአንዳንድ ቅርንጫፎች የገጠመው ችግር በዚሁ መፍትሄ እንዲሰጠው እየተሰራ መሆኑን አውቃችሁ እንድትጠበቁ ማህበሩ ይገልፃል::

ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ የገንዘብ ሚኒስቴርና በማህበሩ የተፃፉ ሁለት ደብዳቤዎችን አያይዘናል::

የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር

ነሀሴ 12 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤