አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
በቸልተኝነት መንገድ የሚሻገር ሰውን በመኪና ገጭቶ መግደል የሚያስከትለው ውጤት በሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠ የህግ ትርጉም:- 👇👇🛑 Via #ethiolawtips
ኑዛዜን መቃወም የሚቻልበት የግዜ ገደብ በፍታብሔር የውርስ ሕግ ሙሉ አይታ/ጠበቃ/
👇👇👇👇👇👇👇👇
ውድ አንባቢዎች እንዴት ሰንበታችኋል!አንድ ሰው በህይወት ዘመኑ ያፈራውን ንብረት በኑዛዜ ለወራሾቹ ማስተላለፍ የሚችል ስለመሆኑ በፍታብሔር ሕጉ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

ኑዛዜ በሚደረግበት አግባብ /ፎርማሊቲ/ መሰረት በግልጽ የሚደረግ ፤በተናዛዡ ጽሁፍ የሚደረግ እና በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ተብሎ በሶስት ይከፈላል፡፡በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እየተናገረ ማናቸውም ሌላ ሰው የሚጽፈው ሲሆን በ 4 ምስክሮች ፊት ወይንም ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው ተቋም ቀርቦ ከተደረገ በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተደረገ ፈራሽ ነው፡፡
በተናዛዡ ጽሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ ራሱ በሙሉ ካልጻፈው ፈራሽ ይሆናል፤ተናዛዡ በኮምፒዩተር የሚጽፈው እንደሆንም እያንዳንዱ ገጽ ላይ በእጅ ጽሁፍ ራሱ የጻፈው መሆኑን ካላረጋገጠ በቀር ፈራሽ ይሆናል፡፡በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ የሞቱ መቅረብ ተሰምቶት በሁለት ምስከሮች ፊት የሚያደርገው የኑዛዜ አይነት ሲሆን ግምቱ ከብር 500 ከሆነ ንብረት በላይ በቃል ኑዛዜ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
አንድ ሰው ከላይ ከተቀመጡት በአንዱ ፎርም ንብረቱን እና የንብረቱን አስተዳደር፤የቀብር ስነስርዓት አፈጻጸሙን፤አካለመጠን ያላደረሱ ልጆቹን አስተዳደግን እና የመሳሰሉትን አስመልክቶ በኑዛዜ ማስተላለፍ እና ግዴታዎችን ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ሟች ያደረጋቸው ኑዛዜዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ በሕጉ ላይ የተቀመጡ ፎርማሊቲዎች እና ሕጉ ግዴታ አድርጎ ያስቀመጣቸውን ድንጋጌዎች የተላለፈ እንደሆነ ኑዛዜው ፈራሽ እንዲሆን ኑዛዜው ጥቅሜን ጎድቶኛል የሚል ማንኛውም ሰው ሊጠይቅ ይችላል፡፡በውርስ ሕጉ ከተቀመጡ አስገዳጅ ሁኔታዎች መካከል ሟች ወደታች የሚቆጠር ተወላጅን ተቀባይነት ካለው ምክንያት ውጪ ከውርስ ሐብቱ ምንም እንዳያገኝ በማድረግ ከውርስ በመንቀል ወይንም በሕጉ ከሚያገኘው 1/4ኛ በታች እንዲያገኝ በማድረግ በኑዛዜ ሐብቱን ማከፋፈል አይፈቀድለትም፡፡ይህ በሆነ ግዜም ክፍፍሉ ጎድቶኛል ወይንም ከውርስ ተነቅዬያለሁ የሚለው ተወላጅ ኑዛዜው እንዲፈርስ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
ታዲያ ሟች ያደረገው ኑዛዜ አይጸናም በሚል የሚቀርብ ክስ በማንኛውም ግዜ የሚቀርብ ሳይሆን በሕጉ በተቀመጠ የግዜ ገደብ ውስጥ ያልቀረበ እንደሆነ ጥያቄው በይርጋ ይታገዳል፡፡ይርጋ በሕግ ተለይቶ ከተቀመጠው የግዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዳይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የሕግ ጽንሰ ሀሰብ ሲሆን ይርጋ ያስፈለገበት ምክንያትም ከሳሽ በተገቢ ትጋት  መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል /ለማንቃት እና ተከሳሽም ዘግይተው የሚመጡ ክሶችን ለመከላከል ማስረጃ እንዳያጣ ብሎም ዘግይተው የሚቀርቡ ክሶች ፍትህን ከማስገኘት ይልቅ ለማጥቂያ በመሳሪያነት እንዳይውሉ ለመከላከል መሆኑን የህግ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡
በፍታብሔር ሕጉ አንቀጽ 973 አንድ ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይም የተወከሉ ወራሾች በኑዛዜ የተነገረው ቃል አይጸናም ሲሉ ክስ የሚያቀርቡበትን የግዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት ኑዛዜ ሲነበብ የነበሩ ወይንም የተወከሉ ሰወች ኑዛዜው አይጸናም የሚሉ እንደሆነ ይህንኑ ክስ የማቅረብ ሐሳባቸውን ለውርስ አጣሪው፤ለዚሁ ለተወከሉ ሽማግሌዎች ወይንም ለዳኞች ኑዛዜው በፈሰሰ / በተነበበ / በ15 ቀን ግዜ ውስጥ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ይህ የግዜ ገደብ ለፍርድ ቤት ክስ የማቅረቢያ ግዜ ሳይሆን ክስ የማቅረብ ሀሳብን መግለጫ የሚሰጥበት ግዜ መሆኑን እና መግለጫው ከተሰጠ ወይንም በኑዛዜው ውስጥ የሰፈረው  ከታወቀበት ግዜ አንስቶ በ 3 ወር ግዜ ውስጥ ክስ ያልቀረበ እንደሆነ ኑዛዜውን አስመልክቶ የሚቀርብ ክስ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን ድንጋጌውን አስመልክቶ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 82585 አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቶበታል፡፡
ኑዛዜው ሲነበብ ያልነበሩ እንዲሁም ስለኑዛዜው መኖር ያላወቁ ሰወች ኑዛዜው ከተነበበ ከ 5 ዓመት በኋላ ስለ ኑዛዜው መጽናትም ሆነ ስለ ክፍያ አመዳደብ መቃወሚያ ማቅረብ አይችሉም፡፡በሌላ በኩል ሟች ያደረገው ኑዛዜ ተወላጅን ከውርስ የመንቀል ውጤት ያለው በመሆኑ እና ማግኘት ከሚገባው ከ1/4ኛ በታች እንዲያገኝ ያደረገ በመሆኑ እንዲፈርስ በሚል የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄ የሚታየው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1123 መሰረት መሆኑን እና በ2 ዓመት ግዜ ውስጥ ጥያቄው ያልቀረበ እንደሆነ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 152134 አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቶበታል፡፡
በስተመጨረሻም ሟች ያደረገው ኑዛዜ በተናዛዡ ንብረት ላይ ሳይሆን  በሌላ ሰው ንብረት ላይ መሆኑን ወይንም የሌላ ሰው ንብረት በኑዛዜው ላይ የተካተተ መሆኑን በመጥቀስ በባለንብረቱ የሚቀርብ የኑዛዜ ይፍረስልኝ ክስ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረት በይርጋ የማይታገድ ስለመሆኑ የሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 53223 አስገዳጅ የሕግ ትርጓሜ ሰጥቶበታል፡፡
ውድ አንባቢዎች ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ኑዛዜ አይጸናም በሚል ክስ የሚቀርብበት የግዜ ገደብን አስመልክቶ በፍታብሔር ሕጉ ውስጥ የተጠቀሱ የይርጋ ድንጋጌዎች የሰበር ሰሚ ችሎት ድንጋጌዎቹን አስመልክቶ ከሰጠው አስገዳጅ የህግ ትርጓሜ ጋር በማገናዘብ የቀረበ ሲሆን በሸሪአ ሕጉ የውርስ መብትን መጠየቅ የሚያበቃበት የግዜ ገደብ /የይርጋ ጽንሰ ሐሳብ መኖሩን፤ስለ ይርጋ መርህ ፍትሀዊነት እና ሌሎችም  ተመሳሳይ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሸረአ ሕግ ምሁር በሆኑት ኡስታዝ ሙስጠፋ ሐሚድ ሳምንት የሚቀርብ ይሆናል፡፡መልካም ሳምንት!


#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
ውልና ማስረጃ ምን አለ
በየትኛውም ቦታ ሁነው ሰነዶች ማረጋገጫ(ውልና ማስረጃ) ጉዳይ አላችሁ
👉ውክልና
👉 ብድር ውል
👉 የሺያጭ ውል
👉ቃለ ጉባዔ
👉ሼር መግዛት /መሸጥ..........

ሌሎችንም አገልግሎት በአካል መገኘት ሳይጠበቅብዎች በአሉበት ቦታ ሁነው መረጃውን ይሰጡና በባለሙያ ተፅፎ በቴሌግራም፣ ዋትስአፕ ወይም በኢሜል ይላክላችኋል።
ከእናንተ የሚጠበቀው ፕሪንት አድርጎ ወደ ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ ምን ጊዜ ሳያባክኑ አገልግሎት ማግኘት ብቻ።
ስለ አስፈላጊ ሰነድ መረጃ በነፃ ይገኛሉ።
ይደውሉ:- 0909039999
የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት (ውልና ማስረጃ) ሲፈልጉ
Emails:-
admin@entrustconsult.com
info@entrustconsult.com
consultantentrust@gmail.com
1. Power of attorney/ውክልና
2. Any contracts/ውል
3. Sales agreement/የሺያጭ ውል
4. Loan agreement/የብድር ውል
5. Share transfer or sales/ሼር ማስተላለፍና መሸጥ
6. Car and house sales agreement/ቤትና መኪና የመሸጥ እና የመግዛት ውል

- Do you need a power of attorney to act on your behalf in legal matters?
Don't worry, we have you covered. Just provide us with the information and we will write a professional power of attorney for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email.
You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it validated. Call us at 0909039999 for more details.

- Whether you are starting a new business, hiring an employee, renting a property, or buying a car, you need a contract to protect your rights and obligations. But writing a contract can be time-consuming and complicated. That's why we offer you a convenient and affordable service to write any contract for you online.

Just provide us with the information and we will write a customized contract for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it signed. Call us at 0909039999 for more information.

- Are you looking for a sales agreement to sell or buy goods or services? We can help you with that. Just provide us with the information and we will write a clear and concise sales agreement for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it finalized. Call us at 0909039999 for more assistance.

- Do you need a loan agreement to borrow or lend money? We can help you with that too. Just provide us with the information and we will write a secure and fair loan agreement for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it approved. Call us at 0909039999 for more support.

- Do you want to transfer or sell your shares in a company?
We can help you with that as well. Just provide us with the information and we will write a valid and legal share transfer or sales agreement for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it executed.
Call us at 0909039999 for more guidance.

- Do you want to sell or buy a car or a house?
We can help you with that also. Just provide us with the information and we will write a comprehensive and accurate car or house sales agreement for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it completed.
Call us at 0909039999 for more advice.

- Do you want to make a testament to distribute your assets after your death?
We can help you with that too. Just provide us with the information and we will write a lawful and effective testament for you and send it to you via Telegram, WhatsApp or email. You can print it and go to document authentication and registration service (DARS) within 15 days to get it witnessed.
Call us at 0909039999 for more consultation.

We also offer free information about important documents on our website https://t.me/EntrustConsultant
. Don't hesitate to contact us if you need document verification and registration service.
We are here to serve you online anytime, anywhere! 😊
Forwarded from PIN NGO
Public Information Noble(PIN) ፐብሊክ ኢንፎርሜሽን ኖብል #ፒን is an NGO/CSO, Public Information Noble (PIN) is an NGO/CSO https://www.pinngo.org
working on the right to access information.
"Information is a key_let's promote access to all"
The NGO is looking for 22 volunteers from all professional background to work on Access to Information in Ethiopia.
The NGO aims to promote the right of all persons to seek, obtain and communicate any information held by public bodies.
The government has the responsibility to share information on request, except for a few information, namely third-party information, information that endangers the country's defense, security and international relations, and some information that is required by law to be kept secret. The volunteers will be engaged in the access to information in all government service providers and other sectors.
Although there is no salary, all volunteers will be certified.......

Follow us vis the following social medias:
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

Website:👇👇👇👇👇
https://www.pinngo.org

Telegram: 👇👇👇👇
https://t.me/PublicInformationNoble

Twitter :👇👇👇👇👇
https://twitter.com/PINNGO_et?t=xKZd2ejDdUIKvS4bkrdZ5A&s=09

Facebook: 👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/PublicInformationNoble?mibextid=ZbWKwL

Emails:
support@pinngo.org


publicinformationnoble@gmail.com
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የመኪና ሽያጭ፡ የመኪና ሽያጭን በተመለከተ ሻጭ ከመኪናው ጋር በተገናኘ ከመኪናው ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ሰነዶችን ለገዥ አሟልቶ ያስረከበ መሆኑ ከተረጋገጠ ገዥ ስመ ኃብቱ በስሜ አልተዘዋወረም በሚል ምክንያት ብቻ ውሉ እንዲፈርስ የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ስመ ሀብቱን ለማዞር አስፈለጊ ሁኔታዎችን አሟልቶ ስም እንዲዘዋወርለት ለሚመለከተው የአስተዳደር አካል ጥያቄ አቅርቦ መብቱ ሊረጋገጥለት ያልቻለ ሰው መብቱን የሚያስጠብቀው በሚመለከተው አከል ላይ በፍርድ ቤት ክስ በመመስረት እንጂ ውሉ እንዲፍርስለት በመጠየቅ አይደለም::
ቅጽ 12; ሰ/መ/ቁ 56569
በሠራተኛ ቅጥር ሂደት ስለሚፈፀም የኋላ ታሪክ ፍተሻ፣ አስፈላጊነት እና ሕጋዊነት
By: ኃይለማርያም ይርጋ

ይህ ጽሑፍ በቅጠር ወቅት የኋላ ታሪክ ፍተሻ አስፈላጊነት፣ በሃገራችን ተግባሩን የሚፈቅድ ወይም የሚከለክል ሕግ ስለመኖሩ፣ የሕግ ወሰን ወይም ቅድመ ሁኔታ ከኖረ ይህንኑ አክብሮ የኋላ ታሪክ ፍተሻ ስለሚደረግበት ሁኔታ አግባብነት ካላቸው የሃገራችን ሕጎችን አንፃር ይመለከታል።

https://www.abyssinialaw.com/blog/the-need-to-background-check-on-recruiting-employees
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
===============================
አዲስ አበባ 25/11/2015ዓ.ም(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን አስመልክቶ ለንግዱ ማህበረሰብ፣ ለምሁራን፣ ለሚዲያ ባለሙያዎችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጠበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ኢትዮጵያ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለመግባት የተቃረበችበት ወቅት በመሆኑ ሁሉም የንግድ ማህበረሰብና ምሁራን እንዲመክሩበትና አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ታልሞ መሆኑን የሚኒስቴር መስራ ቤቱ የንግድ ትስስርና ወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ምንነት፣ ለተግባራዊነቱ ከማን ምን ይጠበቃል የሚሉትና ቀጣናዊ የንግድ ትስስር ምንነት የስልጠናው ይዘቶች ናቸው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et

For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
ሰ.መ.ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም

የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም። ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም። ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም።
Join 🛑👇
#ethiolawtips
contract farming directive .pdf
1.2 MB
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ ምርት የግብይት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 929 /2015

በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት የግብይት አፈጻጸም

መመሪያ ቁጥር ቁጥር 929 /2015

ሙስና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት የግብይት አሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአምራቹን እና የአስመራቹን መብቶች እና ጥቅሞችን ማስከበር በማስፈለጉ በል እና ኢንቨስትመንት እርሻ የተመረቱ ምሮቶች ግብይት ስርዓት ወስጥ የታዩ ህግ ወጥ ድርጊቶችን እና የቀርብ የተዛባ የምርት መረጃዎችን / በመከላከል ፍትሃዊና በዉድድር ላይ የተመሰረት ግብይት ስርዓትን በማሳለጥ የጠጪ ምርቶች ለ በ በማቅረብ የገቢ ግኝትን ጎቤ ማሳደግ በማስፈለጉ

የጥራጥሬ ምርቶች ግብይት ደንብ ቁጥር 377/20e እንቀጽ 21 እና የሰሊጥ እና ነጭ ቦሎቄ ግብይት ደንብ ቁጥር 17520 አንቀጽ 27 መሰረት የንግድ እና ጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ይህንን በመሪያ አውጥቷል፡፡

1. አጭር ርዕስ

ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌዎች

ይህ መመሪያ በውልና በኢንቨስትመንት እርሻ የለማ የሰብል ምርት ግብይት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር ቁጥር 929 /2015 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
..ዜና መግለጫ.............................................................

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ ይሆናሉ፡፡
*****
የፌዴራል
ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግስቱ እና በሕግ በተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተናገድ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ ሰላም እና ስርዓት እንዲከበር የማድረግ ተግባራትን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በዚህ መሰረት በ2015 በጀት ዓመት በነበረዉ የመዛግብት አፈጻጻም አንጻር ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች በአጠቃላይ 213,116 መዛግብት ቀርበዋል። ከእነዚህም ዉስጥ ለ184,467 (86.56%) መዛግብት እልባት መስጠት የተቻለ ሲሆን 28,675 (13.44%) መዛግብት ደግሞ ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ የበጀት ዓመቱ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2014 በጀት ዓመት ለፌ/ፍ/ቤቶች የቀረቡት 209,317 መዛግብት ሲሆኑ ዕልባት ያገኙት ደግሞ 176,767 ነበሩ፡፡ በዚህም መሠረት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት መዛግብት በ2014 በጀት ዓመት ከቀረቡት በ3,799 (1.8%) ከፍ ያሉ ሲሆን በተመሳሳይ ዕልባት ያገኙትም በ7,670 (4.3%) መዛግብት ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

የፍርድ ቤቶቹ አፈጻጸም በተናጠል ሲታይ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት 26,185 መዛግብት ቀርበው ለ19,201 ዕልባት የተሰጠ ሲሆን 6,984 መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት ተሻግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በ2015 በጀት ዓመት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡት የመዛግብት ብዛት 33,721 ሲሆን 26,301 መዛግብት ዕልባት አግኝተዋል፡፡ ወደ 2016 የተሻገሩት መዛግብት ብዛትም 7,420 ሆኗል፡፡ እንዲሁም ለፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት የቀረቡት 153,210 መዛግብት ሲሆኑ 138,965 ዕልባት በማግኘታቸው 14,245 ወደ 2016 በጀት ዓመት ተላልፈዋል፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጁ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 38 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የስራ ጊዜ የተደነገገ ሲሆን በዚህም ፍርድ ቤቶቹ ከነሐሴ1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ፍርድ ቤቶች አስቸካይ ጉዳዮች ሊያስተናገዱ እንደሚችሉ ይደነግጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በከፊል ዝግ የሚሆኑ ሲሆን ፍርድ ቤቶቹ በዚህ በከፊል ዝግ በሚሆኑበት ጊዜ አሰቸኳይ የሆኑ ጉዳዮችን በተረኛ ችሎት ላይ በሚመደቡ ዳኞች የሚያስተናግዱ ይሆናል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ቀናት ውስጥ ዳኞች በፈቃደኝነት የበሰሉ የምርመራ መዝገቦችን በመመርመር የተለያዩ የዳኝነት ተግባራትን በተለይም ፍርድ እና ውሳኔዎችን በመሥራት የሚያሳልፉ ይሆናል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በሚከፈቱበት ወቅት በክረምት የዳኞች እረፍት ጊዜያት እልባት የተሰጠባቸዉ መዛግብቶች ከጥቅምት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለባለጉዳዮች በግልጽ ችሎት የሚገለጹ ይሆናል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በ2015 በነበረው አፈጻጻም ላይ ለተገኘው ውጤት ዳኞች፣ የጉባኤ ተሻሚዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ለነበራቸው ትጋት ምስጋና እያቀረቡ በቀጣይ በ2016 ለሚሰጠው የዳኝነት አግልግሎት በቂ ዝግጅት በማድረግ ፍርድ ቤቶቹ የተጣለባቸውን ሕገ መንግስታዊ እና ሕጋዊ ኃላፊነቶች በላቀ ውጤታማነት ለማከናወን በጋራ እንስራ ለማለት ይወዳሉ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Ale_Hig is a law society's channel who provides alternative legal Education (ALE), such as free legal consulting, different laws, proclamations, directives, regulations, lawsuits, contract forms, articles, cassation decisions and other legal documents. We have a YouTube channel 👇👇👇 https://www.youtube.com/@Lawsocieties where you can find all kinds of laws and experts. We also offers a telegram 👇👇👇 https://t.me/lawsocieties and an email address lawsocieties@gmail.com for contacting us. we believes that basic legal information knowledge is key and important for everyone. Subscribe and follow us to learn more about the law. All in one, for all.
It's great to see a platform like Ale_Hig providing free legal services and information. Having access to legal resources is crucial for individuals. Make sure to check out their YouTube https://www.youtube.com/@Lawsocieties channel and follow them https://t.me/lawsocieties for updates in the law!
የዓይነት ጥቅሞች

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብርን በተመለከተ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 410/2009 መሰረት በዓይነት ለተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማጥቅም ዋጋ የሚሰላበትና የሚወሰነው እንደሚከተለው ነው፡-

የዓይነት ጥቅሞችን በተመለከተ ቀጣሪ ለተቀጣሪ የሚሰጣቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጥቅሞች የዓይነት ጥቅሞች ናቸው፡-

 ከዕዳ ነጻ የመደረግ፤
 የቤተሰብ አገልግሎት ሠራተኞች፤
 የመኖሪያ ቤት፤
 የቅናሽ ወለድ ብድር፤
 የምግብ ወይም የመጠጥ አገልግሎት፤
 የግል ወጪዎች፤
 የንብረት ወይም አገልግሎቶች፤
 የሰራተኞች የአክሲዮን ዕቅድ፤
 የተሽከርካሪ እና
 ሌላ ዓይነት ጥቅም፡፡

 አንድ ተቀጣሪ ጥቅም ያገኘ እንደሆነ፣ ይህን ጥቅም ለማግኘት ያወጣው ወጪ የቅጥር ገቢን ለማግኘት ያደርገው የነበረ ወጪ እስከሆነ ድረስ እንደ ዓይነት ጥቅም አይቆጠርም፡፡

 ማንኛውም ጥቅም የዓይነት ጥቅም መሆኑን እና የዓይነት ጥቅምን ዋጋ ለመወሰን ጥቅሙን በማስተላለፍ ረገድ የተጣለ ገደብ መኖሩ እና ጥቅሙ በሌላ ሁኔታ ወደገንዘብ መለወጥ አለመቻሉ ከግምት ውስጥ አይገባም፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Ethiopia-Digital-ID-proc.1284-2023.pdf
1.6 MB
Ethiopian Digital Identification Proclamation 1284/2015

አዋጅ ቁጥር 1284/2015 የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ
ኤግዚቢት ምንድን ነው?