አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የቤት ሽያጭ ዋጋ ታክስ ይፉ ሆነ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከዚህ ቀደም የቤት ግብይትን ዋጋ በተመለከተ ይቀርብ የነበረው የሽያጭ ውል ወቅቱን እና እውነታውን ያላገናዘበ እንዲሁም የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጣ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ይህንን መነሻ በማድረግ የከተማ አስተዳደሩ የጥናት ቡድን በማቋቋም ወቅታዊ የቤት ሽያጭ ዋጋ አስጠንቶ ያጠናቀቀ ስለሆነ ይህንኑ ጥናት ከዚህ ቀደም ባለው መመሪያና አሰራር መሰረት ማለትም የካፒታል ክፍያን፣ የቴንብር ቀረጥ እና አሹራ ክፍያ ከጠቅላላ የቤቱ ዋጋ በፐርሰንት ተሰልቶ በጥናቱ መሰረት ይህ ደብዳቤ ወጪ ከሆነበት ቀን ሰኔ 8/2ዐ15 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንድታርጉ እያሳሰብን የተጠናውን ጥናት 3 ገፅ አባሪ ከዚህ መሽኛ ደብዳቤ ጋር ተልኳል።
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ብንዘገይም አልቀረንም #አለ_ህግ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ እና ሼር አድርጉልን በቅርቡ ለሚጀመረው አለ_ህግ ለተሰኘው ፕሮግራም አባል ይሁኑ።

https://youtube.com/@Lawsocieties

subscribe and share Ale_Hig YouTube channel.
Coming soon 🔜🔜🔜🔜🔜
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
ችሎታ (capacity) በህግ እይታ
ሰዎች በማህበራዊ መስተጋብር እርስ በርሳቸው በሚኖራቸው ግንኙነት ህጋዊ ተግባራትን ለመፈፀም፣ መብታቸውን ለማስከበር፣ ግዴታቸውን ለመወጣት እንዲሁም ህጋዊ ሀላፊነት ወይም ተጠያቂነትን ለመውሰድ ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል።

በ1960 እ.ኢ.አ በወጣው የኢትዮጵያ ፍሐሀብሔር ህግ እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው ችሎታ የሌለው መሆኑ በሕግ ተወስኖ ካልተገለፀ በቀር ማንኛውንም ዓይነት የማህበራዊ ኑሮውን ተግባር ለመፈፀም ችሎታ አለው። ይህም የሚያሳየው ህግ የሚወስደው ግምት ማንኛውም ሰው በመርህ ደረጃ ችሎታ እንዳለው ነው። በዚህ አጭር የንቃተ-ህግ ፅሁፍ የሰዎች ችሎታ ምንነት፣ የችሎታ ጠቀሜታ ወይም አስፈላጊነት እንዲሁም የሰዎች ችሎታ የማይኖርባቸውን ሁኔታዎች ከፍሐሀብሔር ህጉ አንፃር እንዳስሳለን።

የሰዎች ችሎታ ምንነት

የህግ መዝገበ ቃላት በሆነው መሪያም ዌብስተር እንደተሰጠው ትርጉም ህጋዊ ችሎታ ማለት አንድ ሰው በሕግ መሠረት አንድን የተወሰነ ሁኔታ ወይም ግንኙነት ከሌላው ጋር የማድረግ ወይም በአንድ የተወሰነ ሥራ ወይም ግብይት ላይ የመሳተፍ ችሎታ እና ኃይል ነው። በተጨማሪም ችሎታ ውሳኔ ለማድረግ መረጃን የመጠቀም እና የመረዳት ችሎታ እና ማንኛውንም ውሳኔ ማስተላለፍ አቅም ማለት ነው። አንድ ሰው አእምሮው ከተዳከመ ወይም በሆነ መንገድ ጤናው ከተጓደለ አቅም ይጎድለዋል። ይህም ማለት በዚያን ጊዜ ውሳኔ ማድረግ አይችልም ማለት ነው። የሕግ ችሎታ በሕጉ መሠረት በእኩልነት የመስተናገድ መሠረታዊ የሰብአዊ መብት አካል ነው። በመሆኑም ችሎታ ያለው ሰው በፍትሐብሔር ሥነ ስርዓት ህግ ቁጥር 33(1) መሰረት ፍትሐብሔር ክስ ማቅረብ የሚችል ሲሆን የፈፀመው የወንጀል ድርጊትም ካለ የወንጀል ህጉ መሰረት ሀላፊነት ይሆናል ማለት ነው።

• የችሎታ ጠቀሜታ ወይም አስፈላጊነት

ችሎታ ህጋዊ ግንኙነቶችን በራስ ለማከናወን ጠቀሜታ አለው። ለአብነት ያክል አንድ ሰው ውል በራሱ ለመዋዋል ለምሳሌ ሽያጭ ለመፈፀም ችሎታ ሊኖረው ይገባል። ይኸውም እድሜው በህግ በተወሰነው ልክ መሆን ያለበት እንዲሁም የአይምሮው የጤንነት ሁኔታ ጤነኛ መሆን ይኖርበታል። ያለበለዚያ ግን ህጉ በሚያስቀምጠው ሥርዓት ወይም በወኪል በኩል ህጋዊ ግንኙነቶችን ለመፈፀም ይገደዳል። እንዲሁም በወንጀል ጉዳይ የወንጀል ህግን መሰረት በማድረግ ተጠያቂነትን ወይም ተከሳሽነትን ለመወሰን ወይም ሀላፊ እና ኢ-ሀላፊን ለመለየት የአንድ ሰው ችሎታ መኖር ወይም አለመኖር ማወቅ አስፈላጊ ነው።

• ሰዎች ችሎታ የሚያጡበት ሁኔታ

በፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 193 ስር እንደተደነገገው ጠቅላላ የችሎታ ማጣት ሁኔታ የሚያስከትሉ ምክንያቶች ዕድሜ ወይም የሰው አእምሮ ሁኔታ ወይም በተሰጠ የፍርድ ቅጣት ናቸው። በተጨማሪም የፍትሐብሔር ህጉ የተለየ የችሎታ ማጣት ሁኔታን የያዘ ሲሆን ይኸውም የተለየ ችሎታ ማጣትን ለመወሰን በግምት ውስጥ ለማስገባት የሚቻለው የሰውዬውን ዜግነት በመመልከት ወይም የሚያከናውነውን ሥራ መሰረት አድርጎ በመያዝ ነው። የችሎታ ማጣት አስረጂን በተመለከተ ሰው ሁሉ ችሎታ እንዳለው የሚገመት ሲሆን ይህ ሰው ችሎታ የሌለው ነው ብሎ ማስረዳት የሚገባው ሰውዬው ችሎታ የለውም ብሎ የሚከራከር ወገን ነው (የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 196)። ከተፈጥሮ ሰዎች በተጨማሪ የሰውነት መብት የተሰጣቸው ድርጅቶችና ለልዩ አገልግሎት የተመደቡ ንብረቶች ችሎታ ያላቸው መሆኑ የሚረጋገጠው እንደ አይነታቸው ለነዚሁ የሰውነት መብት በሚሰጧቸው ድንጋጌዎች መሰረት ነው። ችሎታ የሚያሳጡ ሁኔታዎችን እንደሚከተለው በዝርዝር እንመለከታለን።

• በእድሜ ምክንያት ችሎታ ማጣት (Minors)

በእድሜያቸው ምክንያት ችሎታ የሌላቸው ሰዎች ወይም አካለመጠን ስላልደረሱ ሰዎች ሁኔታ በፍትሐብሔር ህጉ የተደነገጉት ድንጋጌዎች የተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ ተፈፃሚ በሚሆንባቸው መስተዳድሮች ተፈፃሚ እንደማይሆን በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 319 ስር ተደንግጎ ይገኛል። በመሆኑም በቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 215 ስር እንደተደነገገው በእድሜያቸው ምክንያት ችሎታ ያጡ ሰዎች ወይም አካለመጠን ያልደረሰ ሰውን በተመለከተ ትርጉም የሰጠ ሲሆን በትርጉሙ መሰረት አካለመጠን ያልደረሰ ሰው ማለት ፆታ ሳይለይ እድሜው አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ልጅ ነው። በእድሜው ምክንያት ችሎታ ያጣ አካለመጠን ያልደረሰ ሰው ህጋዊ ግንኙነቶቸን በራሱ ማከናወን ህጉ ስለማይፈቅድለት ስለመልካም አስተዳደጉና ደህንነቱ ጉዳይ በአሳዳሪው የሚጠበቅ ሲሆን ንብረት ነክ ጥቅሞቹንና በአጠቃላይ የንብረቱን አስተዳደር በሚመለከት በሞግዚት ይወከላል (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 216)። ስለአሳዳሪ እና ሞግዚት አስተዳደር በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ከአንቀፅ 215 እስከ 318 በዝርዝር ተደንግጎ ይገኛል።

• በአእምሮ ሁኔታ ችሎታ ማጣት
አዕምሮዋቸው ስለ ጎደለ ሰዎች፡- የፍትሐብሔር ህጉ ትርጉም የሰጠ ሲሆን አዕምሮው ጎደሎ ነው የሚባለው በተፈጥሮ ዕውቀቱ ያልተስተካከለ በመሆኑ ወይም በአእምሮ መናወጥ ወይም በእርጅና ምክንያት የሚሰራውን ሥራ የሚያደረሰውን ለማወቅ የማይችል ነው። የአእይምሮ ደካሞች ሰካራም ወይም በመጠጥ አፍዛዥ በሆኑ ነገሮች ልማድ የተመረዙና ገንዘብ ያለ አግባብ የሚያባክኑ ሰዎች አእምሮዋቸው እንደጎደለ ሰዎች ይቆጠራሉ (የፍ/ሕ/ቁ. 339)።

በግልፅ ስለታወቀ የአእምሮ ጉድለት ያለበት ሰው፡- የአእምሮ ጉድለት ያለበት ዕብደቱ በግልፅ እንደ ታወቀ ሰው ሆኖ በህግ የሚቆጠረው ይህ የተባለው ሰው በሆስፒታል ውስጥ ወይም በአንድ የአእምሮ ጉድለት ያለባቸው ሰዎች መኖሪያ ቦታ ውስጥ በአእምሮው ሁኔታ ምክንያት በአንድ የጤና ጥበቃ ቤት ውስጥ ተዘግቶበት በዚህ በተዘጋበት ቦታ እስከሚቆይበት ጊዜ ነው (የፍ/ሕ/ቁ. 341)። በግልፅ የታወቀ እብድ የሚሰራቸውን ሥራዎች በተመለከት እብደቱ ግልፅ በሆነበት ጊዜና ቦታ ላይ የሠራቸውን ሥራዎች እርሱ ወይም ወኪሎቹ ወይም ወራሾቹ ሊቃወሟቸው ይችላሉ (የፍ/ሕ/ቁ. 343)። ተቃራኒ የሚሆን አስረጂ ከሌለ በቀር የነዚህ ሰዎች ሥራና ፈቃድ የውለታን ፈራሽነት የሚያስከትል ጉድለት ያለበት ነው ተብሎ ይገመታል። እንዲሁም በስህተት መገኘት ምክንያት የሥራዎችና የውሎች መፍረስ የሚመለከቱት የፍትሐብሔር ህግ ደንቦች በተመሳሳይ ተፈፃሚዎች ይሆናሉ (የፍ/ሕ/ቁ. 344)። ይሁንና የአእምሮ ጉድለት ያለበት ሰው ከእርሱ ጋር የተደረጉት ውሎች በመፍረሳቸው ምክንያት በቅን ልቡና በተዋዋዮች ሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ሀላፊ ይሆናሉ። በሌላ በኩል ከውል ውጪ ሀላፊነትን በተመለከተ ለጤናማ ሰው እንዳለው ሀላፊነት የሚኖርበት ከመሆኑ በተጨማሪ ይህ የአእምሮ ጉድለት ያለበት ያለ አግባብ ካገኘው ብልፅግና የተነሳ ላሉት ግዴታዎች ጤናማ ለሆነ ሰው ያሉበት ግዴታዎች ይኖሩበታል (የፍ/ሕ/ቁ. 350)።

የአእምሮ ጉድለት ያለበቱ በግልፅ ስላልታወቀ ሰው፡- የአእምሮ ጉድለቱ በግልፅ ያልታወቀ ሰው የፈፀማቸው የህግ ሥራዎች ውሎች በዚሁ ሰው የአእምሮ ጉድለት ምክንያት ሊሻሩ አይችሉም። ሆኖም የአእምሮ ጉድለት ያለበት ሰው እነዚህን ውሎች በፈፀመበት ጊዜ ጉድለት የሌለበት ፈቃድ ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ እንደ ነበረ ለማስረዳት ከቻለ ውሎቹን ለማፍረስ ይችላል (የፍ/ሕ/ቁ.
347)። የአእምሮ ጉድለቱ በግልፅ ያልታወቀ ሰው ወራሾች ወይም ባለገንዘቦች ይህ ሰው ለፈፀመው ውል ጉድለት የሌለበት ፈቃድ ቃል አልሰጠበትምና ውሉ ሊፈርስ ይገባዋል ሲሉ የአእምሮ ጉድለት ያለበቱን ምክንያት በማድረግ የውሉን መፍረስ ለመጠየቅ አይችሉም። ይሁንና የውል አድራጊው የአእምሮ ጉድለት ከተደረገው የውል ቃል የሚታወቅ እንደሆነ ይህ ደንብ ተፈፃሚ አይሆንም (የፍ/ሕ/ቁ. 348 እና 349)።

• በፍርድ የሚደረግ ክልከላ (Judicial interdiction)

መከልከሉ ለጤናውና ለጥቅሙ የሚያስፈልግ ሆኖ ሲገኝ አእይምሮው የታወከ ሰው/የፍትሐብሔር ህጉ እንደሚያስቀምጠው እብድ ሰው/ እንዲከለከል(እንዲጠበቅ) ዳኞች ፍርድ ለመስጠት ይችላሉ (የፍ/ሕ/ቁ.351)። እንዲሁም ስለ ዕብዱ ሰው ወራሾች ጥቅም ዳኞች የእብዱን መከልከል ሊፈርዱ ይችላሉ። በፍርድ ስለሚደረግ ክልከላ የክልከላ ውሳኔ እንዲሰጥ ዕብድ የሆነው ሰው ወይም ከባልና ሚስት አንዱ ወይም ከስጋ ወይም ከጋብቻ ዘመዶች አንዱ ወይም ዐቃቤ ህግ ሊጠይቅ ይችላል። ዳኞች የክልከላ ፍርድ ሲሰጡ በሚሰጠው ውሳኔ ውስጥ ጊዜውን በመወሰን የተባለው ሰው ዕብደት የጀመረው ከእንደዚህ ያለው ጊዜ ጀምሮ ነው ሲሉ ለማስታወቅ ይችላሉ። በተሰጠው ውሳኔ ውስጥ የተቆጠረው ቀን ስለ ክልከላው ከቀረበው ጥያቄ በፊት ከሁለት ዓመት የበለጠ ጊዜ ሊኖረው አይችልም (የፍ/ሕ/ቁ.352)።

በሌላ በኩል ዳኞች የክልከላ ፍርድ ሲሰጡ ወይም ውሳኔ ከሰጡ በኋላ የክልከላውን ውጤቶች ማጥበብ የሚችሉ ሲሆን ለተከለከለው ሰው እርሱ ራሱ እንዳንዶቹን ውሎች እንዲያደርግ ሊፈቅዱለት ይችላሉ። የተከለከለ ሰው የፈፀማቸውና ከስልጣኑ በላይ የሆኑት ሥራዎች መቃወም ይቻላል። እንዲሁም የተከለከለ ሰው ችሎታ የሌለው መሆኑን ከማያውቅ ቅን ልቦና ካለው ሰው ጋር ያደረገ እንደሆነ ውሉ በመፍረሱ ምክንያት በዚህ በቅን ልቡና በተዋዋለው ሰው ላይ ስለሚደርስ ጉዳት የተከለከለው ሰው አሳዳሪ በሀላፈነት ይጠየቃል (የፍ/ሕ/ቁ.374)።

በፍርድ የተከለከለ ሰው ጥበቃን በተመለከተ ለአካለመጠን ስላልደረሰ ሰው የሚደረግ ጥበቃ ማለትም በአሳዳሪና በሞግዚት የሚተዳደርበት ህግ ተፈፃሚ ይሆናል። በፍርድ ስለተከለከለ ሰው ክልከላ የማሳወቅ ግዴታ የአሳዳሪው ሲሆን ይህም የተከለከለው ሰው በሚኖርበት ቦታ ወይም ተቀማጭ ሆኖ እንዲኖር በተጠራበት ስፍራ ይሆናል። የተከለከለው ሰው አሳዳሪ ይህ የተከለከለ ሰው ችሎታ የሌለው ለመሆኑ በህግ መሰረት ማስታወቂያ በወጣበት ቦታ ተቀማጭ ሆኖ እንዲኖር መጠበቅ አለበት (የፍ/ሕ/ቁ.362)። የመኖሪያ ቦታውንም የለወጠ እንደሆን በአዲሱ መኖሪያ ማስታወቂያ እንዲወጣ ማድረግ አለበት። ይህን በፍርድ ከተከለከለ ሰው ጋር ህጋዊ ግንኙነት መፈፀም የሚፈልጉ ሰዎች ስለ ሁኔታው እውቀት እንዲኖራቸው እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል።

በፍርድ የተከለከለ ሰው ህጋዊ ግንኙነቶች

ስጦታ፡-

የተከለከለ ሰው ሞግዚት በተከለከለ ሰው ስም ለተከለከለው ሰው ተወላጆች ልጆች ስጦታ ለማድረግ የሚችሉ ሲሆን እነዚህ ስጦታዎች በተከለከለው ሰው ቤተ ዘመድ ምክር ጉባኤ የተፈቀዱ ካልሆኑ በቀር ፈራሾች ናቸው (የፍ/ሕ/ቁ.367)።

ኑዛዜ፡-

የተከለከለ ሰው ክልከላው በፍርድ ከተነገረ በኋላ ኑዛዜ ለማደረግ የማይችል ሲሆን ከተከለከለበት ቀን በፊት የተናዘዘው ኑዛዜ ይፀናል። ነገር ግን የኑዛዜው ቃላት ለርትዕ ተቃራኒ መስለው ለዳኞች የታዩ እንደሆነና የተናዘዘውም የጤናው ሁኔታ ያስደረገው መስሎ የታያቸው እንደሆነ ዳኞቹ ኑዛዜውን በሙሉ ወይም በከፊል ፈራሽ ሊያደርጉት ይችላሉ(የፍ/ሕ/ቁ.368)።

ጋብቻ፡-

በፍርድ የተከለከሉ ሰዎች ፍርድ ቤት ካልፈቀደ በቀር የጋብቻ ውል መዋዋል አይችሉም። ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የተደረገ የጋብቻ ውል በማንኛውም ጥቅሜ ይነካል በሚል ወገን ተቃውሞ ሊቀርብበት ይችላል (የፍ/ሕ/ቁ.369)። ፍቺና ልጅ መካድን በተመለከተ
ያሳዳሪው ፍቃድ አስፈላጊ እንደሆነ የፍትሐብሔር ህጉ ይደነግጋል።

የክልከላ መቅረት

ስለክልከላ የተሰጠው ፍርድ ሲሻር የችሎታ ማጣት ፍፃሜ ሲሆን የክልከላው ውሳኔ መቅረት አካለመጠን ያልደረሰ ልጅ ከሞግዚት አስተዳደር መውጣት ያለው ውጤት ይኖረዋል። ይህም የሚሆነው ክልከላው እንዲወሰን ያደረጉት ምክንያቶች በቀሩ እና የተከለከለው ሰው ንብረቱን ለመምራት እና ለማስተዳደር ሲችል ነው። አእምሮው ከጎደለው ሰው በቀር ስለ ክልከላው ፍርድ እንዲሰጥ ለመጠየቅ የሚችሉ ሰዎች በማናቸውም ጊዜ የክልከላው ውሳኔ እንዲቀር ጥያቄ ለማቅረብ የሚችሉ ሲሆን አሳዳሪው ወይም ሞግዚቱም የክልከላው ውሳኔ እንዲቀር ለመጠየቅ ይችላሉ (የፍ/ሕ/ቁ.377)።

• በህግ የተከለከሉ ሰዎች

በህግ የተከለከለ ሰው ማለት አንድ በወንጀል የተቀጣ ሰው በመቀጣቱ ምክንያት ንብረቶቹን እንዳያስተዳድር ህግ የከለከለው ሰው እንደሆነ የፍትሐብሔር ህጉ ቁጥር 380 የሚደነግግ ሲሆን አንድ ሰው በህግ እንደ ተከለከለ ሆኖ የሚቆጠርባቸው ሁኔታዎች በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ተወስነዋል።

በህግ የተከለከለ ሰው አሳዳሪ የማይኖረው ሲሆን የንብረቶቹ አስተዳደር ዳኞች ለመረጡት ሞግዚት ይሰጣል(የፍ/ሕ/ቁ.382 እና 383)፡፡ በህግ የተከለከለ ሰው በፍርድ ከተከለከለ ሰው በተቃራኒ ጋብቻን ማድረግ፣ ፍቺ መጠየቅ፣ ልጅነት መቀበልና መካድ የሚችል ሲሆን ሞግዚቱ በህግ በተከለከለው ሰው ስም እነዚህን ሥራዎች መፈፀም አይችልም(የፍ/ሕ/ቁ.386)። በህግ የተከለከለው ሰው ያደረጋቸው ሥራዎች ወይም ውሎች ከስልጣኑ በላይ የሆኑ እንደሆነ ፈረሽ ናቸው። በህግ የተከለከለ ሰው ችሎታ ማጣትን ያስከተለው ቅጣት በተፈፀመ ጊዜ በህግ የተወሰነበት ክልከላ ቀሪ ይሆናል(የፍ/ሕ/ቁ.388)።

በአጠቃላይ ችሎታ ህጋዊ ግንኙነትን ለማከናወን መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን ማንኛውም ሰው ህጋዊ ግንኙነቶችን ከሰዎች ጋር ከመፈፀሙ በፊት የሚዋዋለው ሰው ችሎታ ያለው መሆኑን ማረጋገጥ በኃላ ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ እንደ ውል መፍረስ ካሉ ችግሮች የሚታደገው ስለሆነም ተገቢው ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።


በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑን ያውቃሉ ?

የህግ ምንነት

ህግ የሚለው ቃል በማህበረሰቡ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ቃል ነው፡፡ በተለይ ህግ አስገዳጅ መሆኑን የሚረዳው ለመሆኑ ቀደም ባለው ጊዜ በየዕለት ኑሮ ፀብ ሲገጥመው እንኳን “በህግ አምላክ” ብሎ ፀብ የማብረድ ልምድ የነበረው መሆኑ ማሳያ ነው፡፡ ሆኖም ማህበረሰቡ ህግን የሚረዳው በተለምዶአዊው አረዳድ እንጂ የዘርፉ ባለሞያዎች በሚረዱበት መልኩ አይደለም፡፡

በመሰረቱ ህግ ለሚለው ቃል ትርጓሜ መስጠት ቀላል አይደለም፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ ምሁራን ቃሉን በተለያየ መንገድ የሚገልፁት በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም የቃሉ ፍቺ ሊደረስባቸው በሚፈለጉት የተለያዩ ዓላማዎች ምክንያት ሊለያይ ይችላል።

ለህግ ቃላት ትርጉም በመስጠት የሚታወቀው ብላክስ ሎው የህግ መዝገበ ቃላት በተሻሻለው ስድስተኛ እትሙ (Black’s Law Dictionary, 6th ed.,) ለህግ ትርጉም ሲሰጥ law is “a body of rules of action or conduct prescribed by controlling authority, and having binding legal force, which must be obeyed and followed by citizens subject to sanctions or legal consequence is a law.” ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ ስልጣን ባለው አካል የተደነገገ የተግባር ወይም የምግባር ደንብ እና አስገዳጅ የህግ ኃይል ያለው አካል ነው። ይህንንም ዜጎች ሊታዘዙት እና ሊከተሉት የሚገባ ሆኖ ማዕቀብ ወይም ህጋዊ ውጤት የሚጥል ህግ መሆኑን መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም የአንድ ሀገር ሕግ፡- ሰላምን ለማስጠበቅ፣ ነባራዊ ሁኔታውን ለማስጠበቅ (maintain the status quo)፣ የግለሰብ መብቶችን ለማስጠበቅ፣ አናሳዎችን ከብዙኃን ለመከላከል ( protect minorities against majorities)፣ ማኅበራዊ ፍትህን ለማስፈን( promote social justice) እና ሥርዓት ያለው ማህበራዊ ለውጥ እንዲኖር ለማድረግ
( provide for orderly social change) ያገለግላል።

• የህግ መሰረታዊ ባህሪያት

የህጎችን የተለመዱ ባህሪያት እና ተፈጥሮ መፈተሽ የህግ ጽንሰ-ሀሳብን ለመገንዘብ የሚረዳ ሲሆን ከእነዚህ ባህሪያት እና ተፈጥሮዎች መካከል እንደ ወሰኝ ወይም አስፈላጊ የሚታሰቡት አጠቃላይነት(ህግ በሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይነት (uniformity) እና እኩልነትን (Equality) የሚፈፀም መሆኑ)፣ መደበኛነት (ህግ ማህበራዊ ባህሪን በመፍቀድ፣ በማዘዝ ወይም በመከልከል ልማዶችን የሚፈጥር መሆኑ) እና ማዕቀብ ወይም ቅጣትን (ህግን ያላከበረ ቅጣት የሚጠብቀው መሆኑን) ያካትታሉ፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ

በወንጀልም ሆነ በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ህጎቹ ስልጣን ባለው የህግ አውጪ አካል ወጥተው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንደሚውሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ዜጎች የህጎቹን መኖር ወይም መውጣት የማወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይኸውም ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው የህግ መርህ በላቲን Ignorantia juris non excusat ወይም በእንግሊዘኛ "ignorance of the law excuses not" ከሮማውያን ህግ የተወሰደ ሲሆን ህግን የማያውቅ ሰው ይዘቱን ባለማወቅ ብቻ ህጉን በመተላለፍ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል የሚገልጽ የህግ መርህ ነው። እንዲሁም የህግ ስህተት (mistake of law) ሰዎች በአንድ ጉዳይ ላይ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ እንዴት እንደሚተገበር የሚይዙትን የአረዳድ ስህተቶችን የሚያመለክት የሕግ መርህ ነው። ‘ህግን አለማወቅ’ እና ‘የህግ ስህተት’ የሚሉት ቃላቶች በህጋዊ እይታ ውስጥ ተመሳሳይ ትርጉም የማይሰጡ ሲሆን አለማወቅ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አጠቃላይ የእውቀት ያለመኖርን ያመለክታል። ማሳሳት ግን እውቀትን ተቀብሎ ወይም እውቀት እንዳለ አምኖ ነገር ግን የተሳሳተ መደምደሚያን ላይ መድረስን ያሳያል። ይሁንና ህግን አለማወቅም ሆነ የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን እንደ አንድ የህግ መርህ ይወሰዳል፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ ምክንያት (rationale for "ignorance of the law excuses not" principle)

በመሠረቱ አንድ ሰው ህግን ከጣሰ ህጉን ስለመጣሱ ምንም እውቀት ባይኖረውም ተጠያቂ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ሰዎች ህጉን አላውቀውም በማለት ድርጊታቸውን ሊከላከሉ እንደማይችሉ ያመለክታል፡፡ የዚህ ህግ መርህ ምክንያት( rationale) አለማወቅ ሰበብ ቢሆን ኖሮ ምንም እንኳን ያ ሰው ህጉ መኖሩን ቢያውቅም በወንጀል ህግ ወይም በፍትሐ ብሄር ጉዳይ ቢከሰስ ህጉን አላወኩም በማለት ከተጠያቂነት ማምለጫ እንዳይሆን በሚል ነው፡፡ በመሆኑም ከመርህ በስተጀርባ ያለው ምክንያት አለማወቅ ሰበብ ከሆነ ማንኛውም በወንጀል ወይም በፍትሐ ብሄር የተከሰሰ ሰው ተጠያቂነትን ለማስወገድ አላዋቂ ነኝ ሊል ይችላል የሚል ነው። ስለዚህ ህጉ የቱንም ያህል አጭር ጊዜ ቢቆይ ሁሉም ህጎች በስልጣኑ ውስጥ ላለ ለእያንዳንዱ ሰው ተፈፃሚ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

በኢትዮጵያም ህግን አለማወቅ ወይም የህግ ስህተት ከተጠያቂነት እንደማያድን በወንጀል ህጉ አንቀፅ 81 ስር ተደንግጓል፡፡ በዚሁ መሰረት ሕግን አለማወቅ ወይም በህግ ላይ መሳሳት መከላከያ ሊሆን እንደማይችል ያስቀምጣል፡፡ በሌላ በኩል በፍትሐ ብሄር ህግ አንቀፅ 2035/1 እና 2 ስር አንድ ሰው በህግ ላይ በትክክል የተገለፀውን ድንጋጌ፣ ልዩ ደንብና ሥርዓት የጣሰ እንደሆነ ጥፋተኛ እንደሆነ እና ህግን አለማወቅ ይቅርታ ሊያስገኝ የማይችል መሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

• የህግ መኖር ማወቅ የሚቻልበት መንገድ

ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም የሚል የህግ መርህ ተቀባይነት አለው ማለት ሁሉም ሰው ህግ የማወቅ ግዴታ እንዳለበት እና የህግን መኖር ያውቃል የሚል ግምት እንደሚወሰድ ያመለክታል፡፡ ታዲያ ሁሉም ሰው ህግን የተማረ ሊሆን የማይችል በመሆኑ እንዲሁም ህግን ቢማር እንኳ ሁሉን ህግ በተገቢው ሁኔታ ያውቃል ማለት ተጨባጭ (realistic) የማይመስል በመሆኑ የህግን መኖር እንዴት ማወቅ ይቻላል የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡

የህግን መኖር በተለያዩ መንገዶች ማወቅ ይቻላል፡፡ ይኸም በዋናነት ህጎች የሚፀኑበትን ጊዜ ከሚገነግጉ ድንጋጌዎች ሲሆን ህግ የሚፀናበት ጊዜ በተለያዩ ህጎች ላይ በተለያየ ሁኔታ ተገልፆ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት ህጉ ወይም አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ የሚፀና ይሆናል፣ ህጉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል እና የተወሰነ ቀን በማስቀመጥ ከዛ ቀን ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ሊደነገግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ መንግስት በህዳር 29/1987 የፀደቀ ሲሆን ከነሐሴ 15/1987 ጀምሮ በሥራ ላይ እንደሚውል እና የፀና እንደሚሆን በመደንገግ ህጉ የሚፀናበትን ጊዜ በዚህ መልኩ አውጇል ፡፡ በመሆኑም ህጎቹ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታውጀው ከፀደቁበት ቀን ጀምሮ ወይም በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ጊዜ ጀምሮ በህብረተሰቡ ይታወቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

• ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ የማይፈፀምበት ልዩ ሁኔታ
ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት የማያድን መሆኑ መርህ የማይፈፀምበት ልዩ ሁኔታ የተፈጠረው በዓለም አቀፍ ደረጃ በፍርድ ቤቶች በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ነው። ፍርድ ቤቶች የህግ አለማወቅ እንደ ሰበብ የተቀበሉት የህግ ጥሰት ሆን ተብሎ ያልተፈፀመ ወይም ያለጥፋት ሲጣስ ሆኖ በዚህ ጊዜ ቅጣት ለመጣል ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ስለሆነም የሕግ ስህተት እንደ መከላከያ የሚሠራው የሕግ ስህተቱ ሐቀኛ ሆኖ በቅን ልቦና ሲሠራ ነው። እንዲሁም የተከሳሽ ህግን አለማወቅና ስህተት ምክንያታዊ በሆነ ጊዜ አጠቃላይ ህግን አለማወቅ እና የህግ ስህተት ከተጠያቂነት አያድንም የሚለው መርህ ተፈፃሚ አይሆንም ማለት ነው፡፡

በተመሳሳይ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ወንጀል ህግ አንቀፅ 81/2 ስር እንደተደነገገው ድርጊቱን ለመፈፀም መብት ያለው መሆኑን በቅን ልቦና ለማመንና እንደዚህ ባለ የተሳሳተ እምነት ላይ ለመገኘት በቂና እርግጠኛ ምክንያት ያለው ሆኖ ለተገኘ ወንጀለኛ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን ሊያቀልለት እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የሚወስነው ከስህተት የደረሰበትን ምክንያት በተለይም የስህተትና የነገሩን ሁኔታ በመገመት ነው፡፡ በተጨማሪ ምክንያት ሊገኝበት በሚችልና ፍፁም በሆነ አለማወቅና ቅን ልቦና እንዲሁም ወንጀሉን የማድረግ አሳብ መኖሩን በግልፅ በማይታይባቸው የተለዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ከቅጣት ነፃ ለማድረግ እንደሚችል የወንጀል ህጉ ይደነግጋል፡፡

በአጠቃላይ ህግ የሰዎችን የእለት ተዕለት ተግባር በመግዛት ሰላማዊ ኖሮ እንዲኖሩ የሚያስችል አንዱ መሳሪያ በመሆኑ ሰዎች ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት እንደማያድን እና መከላከያ ሊሆን እንደማይችል በማወቅ በተቻለ መጠን ህገ ወጥ ከሆኑ ተግባራት እራሳቸውን ማራቅ ይኖርባቸዋል፡፡
በንቃተ ህግ፣ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties
Law of Traders and Business Organizations ABOUT-LAW.pdf
2.7 MB
LAW OF TRADERS AND BUSINESS
ORGANIZATIONS:
A New TEXTBOOK By
Mesganaw Kifelew (PH. D)
Dagnachew Worku
Fekadu Petros
Gizachew Silesh
https://t.me/lawsocieties
አለግባብ_የተከፈለ_ደመወዝ_ስለሚመለስበት_ሁኔታ_229247.pdf
880.8 KB
አንድ ሰራተኛ X ከተባለ አሠሪ ጋር የስራ ውል መስርቶ የስራ ውሉ ሳይቋረጥ እንደገና ከሌላ Y በተባለ ድርጅት ተቀጥሮ በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ቦታ ተቀጥሮ ደመወዝ ሲከፈለው ነበር።
ከስምንት ወራት በኋላ Y ሰራተኛው ሁለት ቦታ መቀጠሩን ሲያውቅ የስራ ውሉን አቋረጠው።
ጥያቄው Y ለስምንት ወራት ለሰራተኛው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል? በየትኛው የህግ አግባብ?

አሰሪው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል የሚባል ከሆነ መብቱ የመጀመሪያው አሠሪ (X) ነው ወይስ የኋለኛው አሠሪ (Y)?
ወይስ ሁለቱም ማስመለሴ ይችላሉ?
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
ብንዘገይም አልቀረንም #አለ_ህግ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ እና ሼር አድርጉልን በቅርቡ ለሚጀመረው አለ_ህግ ለተሰኘው ፕሮግራም አባል ይሁኑ።

https://youtube.com/@Lawsocieties

subscribe and share Ale_Hig YouTube channel.
Coming soon 🔜🔜🔜🔜🔜
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
#እርቅ በወንጀል ጉዳዮች ያለው ፋይዳ!

#አገራችን ኢትዬጲያ የበርካታ ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ፤ ቋንቋዎች ፣ ባህሎች እና ወጎች ፣ ያላት ሀገር ነች፤የሀገራችን ህዝቦች የየራሳቸውን የሆነ ባህል /ወግ፣ አለባበስ እንዲሁም አገር በቀል የሆነ የዕርቅ፣ የሰላም መጠበቂያ እና የሰላም ግንባታ ስነ-ዘዴዎችም ያሏቸው ህዝቦች ናቸው፤ሀገር በቀል የሰላም መስሪያ ፣ የሰላም መጠበቂያና የሰላም ግንባታ ዘዴ የምንለው ኢ-መደበኛ የሆነው እና ማህበረሰቡ ከአያት ቅድመ አያቶቹ የወረሰው ሰነ-ዘዴ ነው፡፡

#በመሆኑም በእንግሊዘኛው አጠራር non-state based customary institutions የሚያመላክት ሆኖ በዚህ የሰላም እና የፍትህ ስርዓት በዳኝነት የሚቀመጡት መንግስት የሾማቸው ዳኞች ሳይሆኖ ማህበረሰቡ አምኖና ተቀብሎ ለዳኝነት የሾማቸው ባለ ልዪ ተስጦኦ የሆኑ የዕድሜ ባለፀጋ ሽማግሌዎች፤ባህላዊ መሪዎች እና ሀይማኖት አባቶች ሲሆኑ በዚህ ሂደት ውስጥም ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ይህ መልካም የሆነ ታሪክ እና ባህል በቂ ነው ባይባልም በህጉም እውቅና ተሰጥቶት የነበረ ሲሆን በፍርድ ቤቶችም ጭምር በወንጀል አድራጊው እና ተበዳይ መካከል እርቅ ሲበረታታ ይታያል፡፡ በሁሉም የወንጀል አይነቶች እርቅ መታረቅ ያልተከለከለ ሲሆን ነገር ግን እንደወንጀሉ አይነት እና በጠቅለላዉ እርቁ ፍትህን የማያረጋግጥ በሆነ ጊዜ ከሆነ እርቁ ተፈጻሚ የማይደረግ ሲሆን ነገር ግን ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንጻር ፍ/ቤቶች ፍርድ ከሰጡ በኀላ ለቅጣት ማቅለያነት ይጠቀሙታል፡፡

#በወንጀል ህጉ በእርቅ ሊያልቁ የሚችሉ ወንጀሎችን በአፈፃፀሙ እና ቅጣቱ ቀላል በመሆኑ የህብረተሰቡን ሰላም እና መልካም ግንኙነት ተጠብቆ ለማቆየት እንደሚጠቅም ተመልክተዋል፡፡
ሌላው በወንጀል ጉዳይ የመታረቅ ጥቅሙ፡ -የመዝገብ ክምችትን ይቀንሳል፣ ከእስራት ይልቅ በእርቅ ማለቁ ለሁለቱም ወገን ዘላቂ ሰላም ያመጣል፣ በወንጀል አድራጊው ላይ የባህሪ ለውጥ ሊመጣ ስለሚችል፣ እንዲሁም የፍርድ ቤቶችን የስራ ጫና እና የተከራካሪዎችን ግዜ ፣ ወጭ እና ጉልበት ያቀላል፡፡

#ከዘህም ባሻገር እርቅ ቀጣይነት ያለውን ሰላም በማስፈን፣የተጎዳን በመካስ ብሎም ሁለንተናዊ የሆነ ማህበራዊ ተግባቦትን በመመለስ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ነገር ግን እርቅና የተለያዩ አማራጭ የግጭት መፍቻ ሀገር በቀል እውቀቶችና ስርዐቶች እየተረሱና እየተሸረሸሩ በመሄዳቸው በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ለመፈናቀል ለሞት እና ለንብረት ውድመት ሰለባ የሆኑባቸው አጋጣሚዎች ተከስተዋል፡፡

#በመሆኑም በአገር በቀል የግጭት አፈታት እና የዕርቅ ሥርዓቶች ላይ ትኩረት በማደረግ ወደ ቦታቸው መመለስ እንዲሁም በህግ ማዕቀፎቻችንም በሰፊው እንዲካተቱና እውቅና እንዲያገኙ ማድረግ ህብረተሰቡን በሰፊው የሚጠቅም ከመሆኑም በላይ በፍትህ ዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመሠረታዊነት የሚፈታ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

#ድሬዳዋ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዬች ቢሮ
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
#Share #ሼር
#አለ_ህግ #Alehig
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ 
ይህንን ሊንክ ተከትለው #አለ_ህግ  የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ እና ሼር አድርጉልን
አለ_ህግ 

https://youtube.com/@Lawsocieties

subscribe and share Ale_Hig YouTube channel.
Coming soon 🔜🔜🔜🔜🔜
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
#አለ_ህግ  የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ እና ሼር አድርጉልን አለ_ህግ  የተሰኘ ፕሮግራም በቅርቡ ይዘንላቸወሁ እየመጣን ነው🔜🔜🔜

https://youtube.com/@Lawsocieties

subscribe and share Ale_Hig YouTube channel.
Coming soon 🔜🔜🔜🔜🔜
https://youtube.com/@Lawsocieties
https://youtube.com/@Lawsocieties
ሰ.መ.ቁ 193295 ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም

የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419(1)(ሀ)(ለ) ጋር በተያያዘ በዓቃቤሕግ እና በተከሳሹ ላይ የተጣለው የማስረዳት ሸክም ተፈጻሚነቱ በተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ ተከሳሹ ራሱ የሚኖርበትን የኑሮ ደረጃ፤ በተከሳሹ በራሱ ስም የተገኘውን ንብረት ወይም ገንዘብ ብቻ የሚመለከት በሆነ ጊዜ ነው፡፡

የወንጀል ሕግ አንቀጽ 419(1)(ሀ)(ለ) ድንጋጌ የመንግስት ሠራተኛ የሆነ ወይም የነበረ ማንም ሰው የኑሮ ደረጃው አሁን ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ሥራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ሕጋዊ ገቢ የበለጠ እንደሆነ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ አሁን ባለበት ወይም አስቀድሞ በነበረበት የመንግስት ሥራ ወይም በሌላ መንገድ ከሚያገኘው ወይም ሲያገኝ ከነበረው ሕጋዊ ገቢ ጋር የማይጣጣም እንደሆነ የዚህ ዓይነቱ የኑሮ ደረጃ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ወይም የገንዘብ ምንጩ በእጁ እንዴት ሊገባ እንደቻለ ለፍርድ ቤቱ ካላስረዳ በቀር በድንጋጌው የተመለከተውን ቅጣት ይቀጣል በማለት ይደነግጋል፡፡
ከድንጋጌው ይዘት መገንዘብ የሚቻለው ከሳሽ የሆነው ዓቃቤሕግ ማስረዳት የሚጠበቅበት ተከሳሹ የመንግስት ሠራተኛ ሆኖ ሲያገኝ የነበረውን የገቢ መጠን ማሳወቅ ሌሎች የገቢ ምንጮች ካሉ ማሳየት እና ኑሮው ወይም ሀብቱ ከገቢው ጋር ሲነጻጸር ያልተመጣጠን መሆኑን ማስረዳት ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ተከሳሹ አሁን ያለው የኑሮ ደረጃ እንዴት ሊኖረው እንደቻለ ወይም ያለው ንብረት ወይም የገንዘብ ምንጭ በእጁ እንዴት ሊገባ እንደቻለ የማስረዳት ሸክሙ ወደ ተከሳሹ የሚዞር መሆኑን ነው፡፡ ሆኖም ይህ በዓቃቤሕግ እና በተከሳሹ ላይ የተጣለው የማስረዳት ሸክም ተፈጻሚነቱ በተከሳሹ ላይ የቀረበው ክስ ተከሳሹ ራሱ የሚኖርበትን የኑሮ ደረጃ፤ በተከሳሹ በራሱ ስም የተገኘውን ንብረት ወይም ገንዘብ ብቻ የሚመለከት በሆነ ጊዜ ነው፡፡
BDU-JL Vol 13 No 1.pdf
3.6 MB
በሕግ አውጭው በኩል ለብዙ ዘመናት ያገለገለውን የኢትዮጵያ ከውል ውጭ ኃላፊነት ሕግ እንዲሁም የታክስ ሕግጋትን የማሻሻል ዕቅድ አለ፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ በUSAID ፍትሕ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ጥናት ተካሄዷል፡፡ በጥናቱ ከሕግ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል ፡፡ የጥናቱ ዉጤት ከውል ውጭ ኃላፊነት ሕግን እና የታክስ ሕግጋትን ለማሻሻል ለሕግ አውጭዎች እና ለፖሊሲ አርቃቂዎች ዐብይ ግብዓት ይሆናል፡፡ የእነዚህ ጥናቶች አጭርና ጥቅል የውጤት መግለጫ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መጽሔት ቅጽ 13 ቁጥር 1 ታትሟል፡፡

የእነዚህን ጥናቶች ጥቅል የውጤት መግለጫ ከተያያዘው ፋይል ማግኘት ይችላሉ፡፡
https://t.me/lawsocieties
221476 የአደራ ውል.pdf
802.3 KB
ገንዘብ በባንክ የተላከበት የባንክ ሐዋላ ወረቀት የብድር ውል ሆነ የአደራ ውል መኖሩን ለማስረዳት በቂ አይደለም።
ሰ/መ/ቁጥር 221476 ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም
የባንክ ሐዋላ ወረቀት የብድር ውል መኖሩን የሚያስረዳ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 31737 ላይ የህግ ትርጉም መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በመዝገብ ቁጥር 150290 በሐምሌ 23 ቀን 2010 ዓ.ም እና በሌሎች በርካታ መዝገቦች በተሰጠ ውሳኔ የባንክ የገንዘብ መላኪያ ሰነድ ገንዘብ መላኩን ከማስረዳት ውጪ በምን ምክንያት ገንዘቡ መላኩን ወይም ገንዘቡ በብድር የተሰጠ መሆኑን ሊያስረዳ እንደማይችል የህግ ትርጉም ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም በሰበር መዝገብ ቁጥር 31737 የተሰጠው የህግ ትርጉም በመዝገብ ቁጥር 150290 እና ሌሎች በርካታ መዝገቦች ላይ በተሰጠ ውሳኔ ተቀይሯል።
https://t.me/lawsocieties
220830.pdf
825.3 KB
ከባንክ ሂሳቤ ላይ ገንዘብ አላአግባብ ወጪ በመደረጉ ባንኩ ገንዘቡን እንዲመልስ የሚል ክስ ሲቀርብ የፎረንሲክ ምረመራውን ውጤት ብቻ መሠረት በማድረግ ባንኩን ለክሱ ኃላፊ ማድረግ መሰረታዊ ስህተት ነው።
ሰ/መ/ቁ. 220830 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
በወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ በሲስተሙ ላይ ከተመለከተዉ የፊርማ ናሙና ጋር ተመሳሳይ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ የወጪ ማዘዣው ላይ የተመለከተዉ ፊርማ ከናሙና ፊርማ ጋር የሚመሳሰል መሆን አለመሆኑ ገለልተኛ በሆነ አካል ታይቶ መረጋገጥ ይኖርበታል።
በመሆኑም ክስ ከቀረበበት ባንክ ዉጪ በሌሎች ባንኮች ከወጪ ማዛዣ ክፍያ ጋር በተያያዘ ልምድ ባላቸዉ የባንክ ባለሙያዎች እንዲታይ በማድረግ ባንኩ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ግዴታዉን የተወጣ መሆን አለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ የባለሂሳቡ ባንክ ደብተር ቀርቦ ሂሳቡ ተቀንሶ የተጻፈ መሆን አለመሆኑ ሆነ የባለሂሳቡ መታወቂያ በማየት ባንኩ ያረጋገጠ መሆን አለመሆኑ ደግሞ በሰው ማስረጃ ሆኖ የባንክ ሂሳብ ደብተሩ ካለ በማስቀረብ መረጋገጥ ይኖርበታል።
https://t.me/lawsocieties
የግብር አከፋፈል መረጃ ‼️

***

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህ
በር የተያዘውን አመት የጠበቆችና የህግ አማካሪዎች የግብር አከፋፈል ሁኔታ ላይ እየገጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶች ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወስ ነው::

- በዚሁ መሰረት የደረጃ -ሐ ግብር ከፋይ የሆናችሁ ጠበቆችና የህግ አማካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በየቅርንጫፎቻችሁ በመገኘት ግብራችሁን በማሳወቅ እንድትከፍሉ ከመግባባት ላይ የተደረሰ መሆኑን እናሳውቃለን::

በየቅርንጫፉ በምትስተናገዱበት ወቅት ከሂሳብ መዝገብና መሰል ተጨማሪ ምክንያቶችን የሚያቀርቡ ባለሙያዎችና ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ካሉ ማህበሩ ለመደባቸው ከዚህ ለሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በስራ ሰአት ብቻ ወዲያውኑ ሪፖርት እንድታደጉ እናሳስባለን:: የስልክ ቁጥሮች:
              1ኛ) 0913- 66 1578 
             2ኛ) 0915- 58 1888

በሌላ በኩል የደረጃ - ለ  እና
                    የደረጃ -ሀ ግብር ከፋዮች በተመለከተ ማህበሩ እያደረገ ያለውን ያላሰለሰ ጥረት ቀጥሎ በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ቀጣይ ውይይቶች መደምደሚያ ላይ የምንደርስ ሆኖ ፤  የሚደረስበትን ውጤት በተመሳሳይ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን::

የደረጃ - ለ  እስከ ጳግሜ 05 ቀን 2015ዓ.ም እንዲሁም የደረጃ -ሀ ግብር ከፋዮች እስከ ጥቅምት 30 2016 ዓ.ም ድረስ ግብር የሚከፈል መሆኑን እያስታወስን ቀሪ የደረጃ - ሐ ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታችሁን በአግባቡ እንድትወጡ ማህበሩ ከአደራ ጭምር ያሳስባል::

መረጃውን #share በማድረግ ላልደረሳቸው እንድታሳውቁ እንጠይቃለን::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሀምሌ 20 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤

https://t.me/lawsocieties
#Concept_Note _አሰራር

አንድ ጥናት ወይም ፈንድ ለማፈላለግ ከሚሰራ ፕሮጀክት (ከፕሮፖዛል በፊት) በፊት የሚዘጋጅ ሃሳባዊ መግለጫ ሲሆን ከተቻለ በአንድ ገጽ ካልተቻለ በሁለት ገጽ እንዲሆን ይመከራል (ነገር ግን እንደ ተቀባይ ድርጅት ወይም የትምህርት ተቋም የገጽ መጠኑ በጥቂቱ ከፍ ሊል ይችላል)፡፡

ርዕስ

1.የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ (የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግ ለመጠየቅ የሚሰራ) አልያም ለመስራት የምታስቡትን ማንኛውም የጥናት ርዕስ በተገቢው መጥቀስ::

መግቢያ (Introduction)

1.ለመስራት ያሰባችሁት ጥናት አልያም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ጭብጥ በአጭሩ ማስረዳት፤

2.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ አስፈላጊነት በአግባቡ ማስረዳት፤

3.የጥናቱን ወይም የፕሮጀክት ፈንድ ፍቃድ ጥያቄ ስለሚፈታቸው ችግሮች ወይም ስለሚያረጋግጠው ጉዳይ ማስረዳት፤

4.እንደ አስፈላጊነቱ ከማህበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ፋይዳዎች አንጻር ምን እንደሚመስል ማስረዳት፤

ዓላማ (Objectives)

1.ዋና የጥናቱ ውጤት መግለጫ ዓላማ (General Objective) እና ትክክለኛ ገላጭ የሆኑ ዝርዝር ዓላማዎች (Specific Objectives) መግለጽ፤

የጥናት ስልት (Research Methodology)

1.የታሰበውን ጥናት ከክፍተት መነሳቱን ማረጋገጥ (Research Gaps)፤

2. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛ ስልት (Research Design) ማቅረብ፤

3. የታሰበውን ጥናት ትክክለኛውን የናሙና አመራረጥ/ስብጥር ስልት ማቅረብ፤

4.የታሰበውን ጥናት የውጤት ትንተና ስልቶቹ (Data Analysis Methods) ትክክለኛነት ማረጋገጥ፤

5.የታሰበውን ጥናት የጥናቱን ጥራት (Validity እና Reliability) ስለሚረጋግጥበት መንገድ ማስረዳት፤


የሚጠበቅ ውጤት (Impact)

1.ከታሰበው ጥናት ይመጣሉ የሚባሉ ውጤቶች እንዴት እንደሚለኩ ማስረዳት፤

2. የሚመጣውን ጥናት ግኝት እንዴት ወደ ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚቻል ማስረዳት፤


የጊዜ እና የወጪ ሰሌዳ (Work Plan and Budget Schedule)

1.ትክክለኛ የጥናቱን እና የፕሮጀክቱን የጊዜ ሰሌዳ መግለጽ፤

2.ለጥናቱ ወይም ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ የበጀት ዝርዝር ማቅረብ፤

ዋቢ ጽሁፍ (Reference)

1. በአጭር ሰነድ ውስጥ የተጠቀማችሁት ዋቢ ካለ ትክክለኛ መንገዱን ተከትሎ መጥቀስ፤
Via #WaseAlpha

#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig