የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት እንድታጠናክር ትልቅ እድል ይፈጥራል
=========================
አዲስ አበባ 27/10/2015 የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 መርሃ ግብሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ነው፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 ሀገራት ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 47ቱ አጽድቀዋል፡፡ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቱ ለሸቀጦች እና አገልግሎቶች አንድ ገበያ በመፍጠር በአፍሪካ ሀገራት መካከል የሚካሄድን ንግድ ማሳደግ እና ማስተዋወቅ እንዲሁም የአህጉሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት እና ልማት ለማሳደግ ያለመ ነው።
ኢትዮጵያ ስምምነቱን የፈረመችው በ2010 ዓ.ም ሲሆን በ2011 ዓ.ም አጽድቃ ቀሪ የድርድር ሂደቶችን እያካሄደች ትገኛለች፡፡
ስምምነቱ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ለሚሆን ህዝብ ገበያ በመፍጠር የኢትዮጵያን ምርቶችና አገልግሎቶች የገበያ ተደራሽነት፣ የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገትና ልማትን እንደሚያሳድግ ይጠበቃል።
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
facebook:- Ethiopianministryof tradeandregionalitegration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et

አለግባብ_የተከፈለ_ደመወዝ_ስለሚመለስበት_ሁኔታ_229247.pdf
880.8 KB
አንድ ሰራተኛ X ከተባለ አሠሪ ጋር የስራ ውል መስርቶ የስራ ውሉ ሳይቋረጥ እንደገና ከሌላ Y በተባለ ድርጅት ተቀጥሮ በተመሳሳይ ጊዜ ሁለት ቦታ ተቀጥሮ ደመወዝ ሲከፈለው ነበር።
ከስምንት ወራት በኋላ Y ሰራተኛው ሁለት ቦታ መቀጠሩን ሲያውቅ የስራ ውሉን አቋረጠው።
ጥያቄው Y ለስምንት ወራት ለሰራተኛው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል? በየትኛው የህግ አግባብ?
አሰሪው የከፈለውን ደመወዝ ማስመለስ ይችላል የሚባል ከሆነ መብቱ የመጀመሪያው አሠሪ (X) ነው ወይስ የኋለኛው አሠሪ (Y)?
ወይስ ሁለቱም ማስመለሴ ይችላሉ?

239841 - Stamped.pdf
932.4 KB
የስራ ላይ ጉዳት ካለ በግልጽ ዳኝነት ካልተጠየቀበት ካሳ ሊወሰን አይገባም የሰ/መ/ቁጥር 239841
#Daniel Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)/

ከህክምና_ሙያ_ጋር_የሚፈፀሙ_ወንጀሎች.pdf
775.7 KB
የሕክምና የሞያ ስህተት እና የሚያስከትለው ተጠያቂነት
............
በኢትዮጵያ ምንም አንኳን ዜጎች የጤና መብታቸውን በተሟላ ሁኔታ የሚያስጠብቅ በህይወት የመኖርና የአካል ደህንነት መብታቸውን የሚያረጋግጥ ህግ ማንግስታዊ ዋስትና ቢኖራቸውም ሀገሪቱ በጤና አገልግሎት በተወሰኑ አመታት ውስጥ ካሳየችው አዎንታዊ መሻሻል ባልተናነሰ መልኩ በህክምና ቸልተኝነት ምክንያት ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ዜጎች ለሞት፣ ለዘላቂ አካል ጉዳትና ለዘላቂ ተጨማሪ የጤና ጉዳቶች እየተዳረጉ ይገኛሉ። የማዋለድ አገልግሎት፣
* የኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 41 እና 90
የህፃናት ህክምና እና የቀዶ ህክምና የህክምና ቸልተኝነት ችግር በስፋት የሚከሰትባቸው ዘርፎች መሆናቸውን አንዳንድ ፅሁፎች ያመለክታሉ።......
.....
....
https://t.me/lawsocieties

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌደራል ፍ/ቤቶችን የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ አፀደቀ
****************
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል ፍ/ቤቶችን የአስተዳደር ሠራተኞች ረቂቅ ደንብ ”ደንብ ቁጥር 1/2015” አድርጎ አፀደቀ፡፡
ረቂቅ ደንቡን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ያቀረቡት የም/ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የተከበሩ ወ/ሮ ዕፀገነት መንግሥቱ ምክር ቤቱ በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሔደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ ረቂቅ ደንቡ ለዝርዝር ዕይታ በዋናነት ለም/ቤቱ የሕግና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴ፣ በተባባሪነት ደግሞ ለሰው ሐብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መመራቱን አስታውሰው በዚህ መሠረት ረቂቅ ደንቡን በመመርመር ሒደት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለም/ቤቱ አባላት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በማብራሪያቸውም በቋሚ ኮሚቴዎቹ ማሻሻያና ማስተካከያ የተደረገባቸውን የረቂቅ ደንቡን ድንጋጌዎች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ማብራሪያውን ተከትሎ ከተከበሩ የም/ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ረቂቅ ደንቡ በም/ቤቱ አባላት በአብላጫ ድምጽና በአንድ ተቃውሞ ”ደንብ ቁጥር 1/2015” ሆኖ መጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ረቂቅ ደንቡ የፀደቀው በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 55/1 ላይ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አዋጁን ለማስፈጸም ደንብ ሊያወጣ እንደሚችል በተደነገገው መሠረት ነው፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

#news
የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ተ/ፕሬዚደንት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው የአፍሪካ ጠበቆች ማህበር (PALU) ም/ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ!!!
***********************
እ.ኤ.አ ከጁላይ 5 ቀን 2023 ጀምሮ በዛምቢያ ሀገር ሊቪንግስተን ከተማ እየተካሄደ ባለው 13ኛው የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረት ጉባኤ ከመላው አፍሪካ ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ፤ ከአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ ክፍለ አህጉሮች የተውጣጡ ከ 250 በላይ የጠበቆች ማህበር ፕሬዝደንቶችና የአመራር አባላት ፤ አካባቢያዊ የባር አሶሲዬሽን መዋቅሮች ፤ አለም አቀፍ የጥብቅና ድርጅቶች ፤ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች ተወካዮች እና የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ::
በዚሁ ጉባኤ ላይ ለህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች ለተደረገው ምርጫ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበርን እየመሩ ያሉት አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው ከተወዳዳሪዎቹ ይልቅ ከአባል ሀገራቱ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት የአፍሪካ ጠበቆች ማህበር (PALU) ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው ተመርጠዋል::
አቶ ቴዎድሮስን በእጩነት እንዲወዳደሩ የጠቆመው 7 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈውና ከ28,000 በላይ አባላት ያሉት የ East African Law Society ነው:: ቴዎድሮስ ከምስራቅ አፍሪካ ፤ ከደቡብ አፍሪካ እና ከማእከላዊ አፍሪካ ዞናት ሙሉ ድጋፍ ያገኙ ሲሆን ከምእራብና ሰሜን አፍሪካ ተወካዮች ደግሞ አብላጫውን ድጋፍ በማግኘት ሊመረጡ ችለዋል::
የአፍሪካ ጠበቆች ማህበራት ህብረትን በም/ፕሬዝደንትነት ለመምራት ኢትዮጵያዊ ሲመረጥ የመጀመሪያው ሲሆን ህብረቱ በአዲስ አበባ በተመሰረተበት ግዜ ከ21 አመታት በፊት አንጋፋው የህግ ባለሙያ አቶ ጌታቸው ቅጣው የህብረቱ ዋና ፀሀፊ ሆነው አገልግለዋል:: ላለፉት 18 አመታት በህብረቱ ከፍተኛ አመራር ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ምንም አይነት ቦታ ማግኘት ሳይችሉ ቆይተዋል:: በአሁኑ ወቅት የህብረቱ ፕሬዚደንት ፈረንሳይኛ ተናጋሪው ካሜሮናዊው የህግ ባለሙያና ጠበቃ ሚ/ር ካሪ አብዶል ባጉይ ሲሆኑ የሴክሬታሪያቱ መቀመጫ በታንዛኒያ አሩሻ እንደሚገኝ ይታወቃል::
የኢትዮዽያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሀምሌ 02 ቀን 2015ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤
#መረጃዎች በቶሎ እንዲደርሷችሁ ይፋዊ የፌስቡክ ገፃችንን በሚከተለው ሊንክ ይቀላቀሉ::
https://www.facebook.com/ethiopianbarassociation?mibextid=LQQJ4d

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪዎች የንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፌዴራል ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መዞሩ ተገለጸ::
====================================
አዲስ አበባ 03/11/ ከ2015 ዓ.ም (ንቀትሚ) በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪዎችና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኩል ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪ የንግድ አገልግሎት አስተዳዳራዊ ክፍተቶች የታዩበት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ የተበራከተበት በመሆኑና በወቅቱ አገልግሎቱ ያልወረደላቸው ክልሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው ሚኒስትር መስራ ቤቱ ይህን ችግር ለመፍታት የአስመጪና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሃምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን ሚኒስትር መስራ ቤቱ አስታውቋል፡፡
የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ከሃምሌ 1/2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ማንኛውም አስመጪና ላኪ ነጋዴ የትም ማሄድ ሳይጠበቅበት ሲስተሙን በመጠቀም ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚችል ሲሆን በአገልግሎቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎች ካሉ በ 965 የጥሪ መዕከል ደውሎ መረጃ ማግኘት የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
facebook:- Ethiopianministryof tradeandregionalitegration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
====================================
አዲስ አበባ 03/11/ ከ2015 ዓ.ም (ንቀትሚ) በክልሎች ይሰጥ የነበረው የአስመጪዎችና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሐምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኩል አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በኩል ይሰጥ የነበረው የአስመጪና ላኪ የንግድ አገልግሎት አስተዳዳራዊ ክፍተቶች የታዩበት፣ የኮንትሮባንድ ንግድ የተበራከተበት በመሆኑና በወቅቱ አገልግሎቱ ያልወረደላቸው ክልሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በማንሳታቸው ሚኒስትር መስራ ቤቱ ይህን ችግር ለመፍታት የአስመጪና ላኪዎች ንግድ አገልግሎት ከሃምሌ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራል ተግባራዊ እንዲሆን መወሰኑን ሚኒስትር መስራ ቤቱ አስታውቋል፡፡
የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፍቃድ አገልግሎት ከሃምሌ 1/2013 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ማንኛውም አስመጪና ላኪ ነጋዴ የትም ማሄድ ሳይጠበቅበት ሲስተሙን በመጠቀም ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎት ማግኘት የሚችል ሲሆን በአገልግሎቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጥያቄዎች ካሉ በ 965 የጥሪ መዕከል ደውሎ መረጃ ማግኘት የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን:-
Email: fdremotri@gmail.com
fdremotri@motri.gov.et
facebook:- Ethiopianministryof tradeandregionalitegration
For trade license : www.etrade.gov.et
website: www.motri.gov.et
ስትወሰልት የተያዘች ሚስት በባሏ እርዳታ የምትወደውን ሰው አገባች
በሚስትየዋ ድርጊት የተበሳጩ የሰፈሩ ሰዎችም ሚስትየውን እና የሰው ሚስት የሚያባልገውን ሰው እጅ ከፍንጅ ይዘው ለባልየው አስረክበዋል።👇
https://am.al-ain.com/article/india-cheating-women-marrying-lover

አል ዐይን ኒውስ
ስትወሰልት የተያዘች ሚስት በባሏ እርዳታ የምትወደውን ሰው አገባች
ሴትዮዋ ከምታፈቅረው ሰው ጋር በትዳሯ ላይ ስትወሰልት የመንደሩ ሰው እጅ ከፍንጅ ይዘዋታል
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎች በቅርቡ ባሳተመው ቅፅ 25 ላይ የገጠር መሬትን በተመለከተ ምን አዲስ እይታ ይዞ መጣ?
****
1. የገጠር መሬትን በተመለከተ ሁለት ዳኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣን በተመለከተ በመሬት አዋጁ፣ በስነ-ስርዓት ህጉ እና የክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መካከል ግጭት ካለ የመሬት አዋጁ ልዩ ህግ በመሆኑ በቀዳሚነት ሊተገበር ይገባል (Special prevails over the geberal)። የሰበር መ/ቁ. 191968
2. ወራሽነትን ቀድሞ በማረጋገጥ የገጠር መሬትን ቀድሞ መያዝ ልዩ የወራሽነት መብትን የማያጎናፅፍ በመሆኑ ሌሎች ወራሾችን ድርሻቸውን ከመጠየቅ አይገድብም። የሰበር መ/ቁ. 181643
3. የገጠር መሬት አዋጁ ላይ የገጠር መሬትን በሽያጭ ዉል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም ዉሉ ህግን ያለተከተለ ሰለሆነ አይፀናም። የሰበር መ/ቁ. 186431
4. የገጠር መሬት ስጦታ ተደርጎል ተብሎ የሚመዘነው በጊዜው በነበረው የገጠር መሬት ህግ እንጅ ከስጦታው በኋላ ተሻሽሎ በወጣው ህግ አይደለም። (Principle of non-retroactivity) የሰበር መ/ቁ. 185848
5. የገጠር መሬት ስጦታን በተመለከተ የመሬት አዋጆቹ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ ወይም ደግሞ በህጎቹ ባልተሸፈኑ ጉዳዪች ላይ የፍ/ህጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ የተዘረዘሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባል። (Common approach of the Cassation using the 1960 Civil Code provisions as a gap feeling to rural land matters) የሰበር መ/ቁ. 188853
6. ከሚመለከተው የመንግስት አካል በስተቀር አንድ ግለሰብ የያዘውን መሬት አያያዙ በህገ-ወጥ መንገድ በሚል አስለቅቆ መያዝ አይችልም። (No one can take justice by his own hand) የሰበር መ/ቁ. 187618
7. የገጠር መሬት ኪራይ ይርጋ ጋር በተያያዘ የመሬት አዋጁ በግልፅ ካላስቀመጠ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ የፍ/ህ/ቁ. 1845 ነው። የሰበር መ/ቁ. 187484
8. ትዳር በሞት ምክንያት ከፈረሰ በሌላኛው ተገቢ የተያዘ የገጠር መሬት እንዲመለስ በወራሾች የሚቀርብ ጥያቄ በጋብቸ የተፈራ የንብረት ክፍፍል ጥየቄ ስለሆነ ሰበር ቀደም ብሎ በቅፅ 4 የመ/ቁ. 17937 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሰበር መ/ቁ. 186461. Credit to #Ayalew Asfaw

የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሕግ በኢትዮጵያ
በሀገራችን ኢትዮጵያ የተሽከርካሪ አደጋ በእጅጉ እየበዛ እና ከፍተኛ የሆነ ሞት፣ አካል ገዳት እና የንብረት ጉዳት እያስከተለ ይገኛል፡፡ ከአደጋው አስከፊነትና ከሰብአዊነት አንፃር የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሕክምና እርዳታ ማግኘት ይገባቸዋል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ጉዳት አድራሹ በመሰወሩ ምክንያት ላይታወቅ የሚችልበት እድል ከመኖሩም በላይ ቢታወቅም እንኳን በወቅቱ ወጪውን ለመሸፈን የሚያስችል አቅም የሌለው የሚሆንባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡ ይህም ተጎጂዎችን ለተጨማሪ ጉዳትና እንግልት ሊዳርግ ይችላል፡፡
ይህንን ችግር ለማቃለል የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን አስገዳጅ በሆነ መልኩ በሕግ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ የሚገኝ ሕግ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሑፍ የሕጉን ይዘት እንዳስሳለን፡፡
የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ምንነት
መድን ወይም ኢንሹራንስ ስለሚለው ቃል ከተለያየ አቅጣጫ በማየት ትርጉም ሊሰጠው እንደሚችል የዘርፉ ምሁራን ይገልፃሉ፡፡ ከግለሰቦች መነሻ ነጥብ ተነስቶ የሚሰጠው ትርጉም የመጀመሪያው ሲሆን እሱም “አንድ ሰው በንብረቱ፣ በህይወቱ ወይም በአካሉ ላይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ሊያጋጥም በሚችል አደጋ ምክንያት የሚደርስ በገንዘብ የሚለካ ጉዳትን ለኢንሹራንስ ድርጅት ማስተላለፊያ መንገድ ነው፡፡” ሁለተኛው መነሻ ነጥብ ከኢንሹራንስ ሰጪው ድርጅት በመነሳት ሲሆን “ኢንሹራንስ ሰጪው በአደጋ ምክንያት የሚያጋጥምን ኪሳራ ለተመሳሳይ አይነት አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የሚያከፋፍልበት መንገድ ወይም ዘዴ ነው፡፡”
በሀገራችንም በነባሩ የንግድ ሕግ አንቀጽ 654(1) ላይ “የኢንሹራስ ውል ፖሊሲ ማለት ኢንሹራንስ ሰጪ የሚባለው በአንድ ወይም በብዙ የተመደበውን የኢንሹራንስ መግቢያ ዋጋ (ፕርምየም) ተቀብሎ በውሉ የተመለከተው አደጋ በደረሰ ጊዜ ኢንሹራንስ ለገባው ሰው የተወሰነ ገንዘብ ለመክፈል ግዴታ የሚገባበት ነው፡፡” በማለት ትርጉሙን አስቀምጧል፡፡ ይህ የጠቅላላው የመድን ውል ትርጓሜ ሲሆን የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድንን በተመለከተ ደግሞ በአዋጅ ቁጥር 799/2005 አንቀፅ 2(8) እና (10) ስር ከተሰጡት ትርጉሞች ተነስተን መረዳት እንችላለን፡፡ በዚህም መሰረት “የመድን [ውል] ማለት የመድን ገቢው ተሸከርካሪ በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው የሞት አደጋ፣ የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ኪሳራ ካሳ ለመክፈል እና የአስቸኳይ የሕክምና አገልግሎት ክፍያን ለመፈፀም መድን ሰጪው ውለታ የሚገባበት ሰነድ ነው” ይላል፡፡ ሦስተኛ ወገን ማለት ደግሞ “በመድን [ውሉ] መሰረት ኃላፊነት ያስከተለ የተሽከርካሪ አደጋ በደረሰ ጊዜ ከመድን ገቢው፣ ከመድን ገቢው ቤተሰብ፣ ከአሽከርካሪው ወይም ከመድን ገቢው ተቀጣሪ ሰራተኛ በስተቀር የመድን [ውሉ] ተፈፃሚነት የሚመለከተው ማንኛውም ሌላ ሰው ነው” ይላል፡፡ በመሆኑም የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ማለት የተሽከርካሪ አደጋ የደረሰበት ሰው ሊያገኘው የሚገባ ካሳ ወይም የሕክምና ወጪ ሽፋን መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
የተሸከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን አስፈላጊነት
የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን አዋጅ ቁጥር 799/2005 እንሊወጣ ያስፈለገበት አራት ምክንያቶች በመግቢያው ላይ የተጠቀሱ ሲሆን እነዚህም በተሽከርካሪ ምክንያት እየደረሰ ያለው አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እየጨመረ መምጣቱ፣ በተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት የሚደርሰው የሰው ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ኪሣራ ማህበራዊ ችግር እያስከተለ ያለ መሆኑ፣ የተሽከርካሪ አደጋ ተጎጂዎች አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ሥርዓት ማመቻቸት እና የተሽከርካሪ ባለንብረቶች የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን እዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ መድን ወይም ኢንሹራንስ እጅግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ ከነዚህ ጠቀሜታዎቹ ውስጥ አንደኛው በአንድ ሰው ላይ የሚደርስን ፍትሐብሔራዊ ተጠያቂነትን፣ የንብረት ጉዳትን፣ በሞት ወይም የአካል ጉዳት ምክንያት የሚደርስን የኢኮኖሚያዊ ኪሳራን በካሳ መልክ የኢንሹራንስ ድርጅቱ ስለሚከፍለው በተቻለ መጠን ጉዳት አድራሽ ወይም ጉዳት የደረሰበት ሰው የከፋ ኪሳራና ምስቅልቅል ውስጥ እንዳይገቡ ያደርጋል፡፡
የሕጉ ተፈፃሚነት ወሰን
ህጉ ከብስክሌትና ከአካል ጉዳተኞች ተሽከርካሪ (ዊልቼር) በስተቀር በመንገድ ላይ በሚሄድ በኤሌክትሪክ ወይም በመካኒካ ኃይል በሚሰራ ባለሞተር ተሽከርካሪ፣ ግማሽ ተሳቢ ወይም ተሳቢ ላይ ሁሉ ተፈፃሚ እንደሚሆን ከአዋጁ አንቀጽ 2(5) እና ከአንቀፅ 3 ጣምራ ንባብ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህም ማለት ከባጃጅ እንስቶ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ሁሉ ይህን የመድን የምስክር ወረቀት ሳይዙ መንቀሳቀስ አይችሉም። በአዋጁ አንቀጽ 3(1) ላይ እንደተገለፀው ማንኛውም ሰው ተሽከርካሪው በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው አደጋ የፀና የመድን ሽፋን ሳይኖረው ተሽከርካሪውን በመንገድ ላይ መንዳት፣ መጠቀም ወይም ሌላ ሰው እንዲነዳ ወይም እንዲጠቀም ማድረግ ወይም መፍቀድ እንደማይችል ተደንግጎ እናገኛለን፡፡ የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፋን ምስክር ወረቀት ካልያዙ ሽፋኑ እንደሌላቸው ተቆጥሮ ተሽከርካሪዎቹ በፖሊስ ተይዘው ይቆያሉ። ተሽከርካሪው የመድን ተለጣፊ ምልክት ከሌለው ወይም በወቅቱ የታደሰ ካልሆነ መድህን ለተሽከርካሪው የመግባት ግዴታ ያለበት ሰው አዋጁን እንደጣሰ ተቆጥሮ በሕግ እንደሚጠየቅ በአዋጁ አንቀጽ 13 ላይ ተደንግጓል። ለተሽከራካሪው የሦስተኛ ወገን መድን የመግባት ግዴታ ያለበት የተሽከርካሪው ባለቤት፣ ተሽከርካሪው ላይ በኪራይ ወይም በውክልና መብት አግኝቶ የሚጠቀም ሰው ወይም ሌሎች እንዲጠቀሙበት መፍቀድ የሚችል ማንኛውም ሰው ነው፡፡
የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፋን የሚሸፍነው ጉዳት
በአዋጁ አንቀጽ 4(2) ላይ በተገለፀው መሠረት የሦስተኛ ወገን የመድን ሽፋን ፖሊሲ መድን የተገባለት ተሽከርካሪ ለሚያደርሰው የሰው ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ኪሳራ መከፈል የሚገባውን ካሳና አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት ወጪ የሚሸፍን ነው፡፡
ነገር ግን በመድን ገቢው ወይም ቤተሰብ (የትዳር ጓደኛ፣ ልጅ፣ አባት፣ እናት ወይም የሚያስተዳድረው ማንኛውም ሰው) ላይ የሚደርስ ሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ጉዳት፣ በመድን ገቢው ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው በሥራው ላይ እያለ በሚደርስ የግጭት አደጋ ወይም የሞት ወይም የአካል ጉዳት ወይም የንብረት ጉዳት፣ መድን በተገባለት ተሽከርካሪ ላይ የሚደርስ አደጋ፣ መድን በተገባለት ተሽከርካሪ ላይ በኪራይ ወይም በክፍያ በሚጓጓዝ ንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊነት እና ከኢትዮጵያ ግዛት ክልል ውጪ የደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ ተከትሎ የመጣ ኃላፊነትን የማይሸፍን መሆኑን እና ካሳ እንደማይከፈለው ከአዋጁ አንቀጽ 7 እንረዳለን፡፡ በሌሎች ሕጎች ግን ጉዳት አድራሹን ወይም ተሽከርካሪው የመድህን ሽፋን ካለው መድህን የሰጠውን ኩባንያ ካሳ የመጠየቅ መብታቸው እንደተጠበቀ ነው።
የካሳው መጠን

በአዋጁ አንቀጽ 16 መሰረት በሦስተኛ ወገን የተሽከርካሪ መድን ፖሊሲ ለደረሰ ጉዳት የሚሸፍነው የካሳ መጠን የሞት አደጋ ከብር 5 ሺ ያላነሰና ብር 40 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ፣ በአንድ ሰው ላይ ለሚደርስ ለአካል ጉዳት ከብር 40 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ እንዲሁም በንብረት ላይ ለሚደርስ ጉዳት ወይም ኪሳራ ከብር 100 ሺ ያልበለጠ የገንዘብ ካሳ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሕግ ከተቀመጠው የገንዘብ መጠን በላይ ጉዳት የደረሰበት ሰው ጉዳት አድራሹን ወይም በሕግ ኃላፊነት ያለበትን ሰው በፍ/ቤት ተገቢነት ባለው ሌላ ሕግ መሠረት ከሶ ካሳ መጠየቅ ይችላል፡፡
በሦስተኛ ወገን የተሽከርካሪ የመድን ዋስትና የአሽከርካሪውን እድሜ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ሁኔታ፣ የተሽከርካሪውን ሁኔታ፣ የፈረስ ጉልበት ወይም የሲሊንደር ችሎታ ወይም ዋጋ፣ የሚይዘው ሰው ብዛት፣ የሚጭነውን እቃ ክብደት፣ አካላዊ ባህሪ ወይም ልዩ መሳሪያ፣ ተሽከርካሪው አገልግሎት ላይ የሚውልበትን ጊዜ ወይም አካባቢ ካሳ እንዳይከፈል ገደብ ሊያስደርጉ አይችሉም።
እንዲሁም እንደ ሌሎች የመድን ዋስትናዎች በመድን ውሉ በተስማማነው መሠረት አይደለም በሚል የመድን ኩባንያው ወይም ሌላ አካል ካሳው እንዳይከፈል መቃወም ወይም መከልከል አይችልም። የመድን ፈንድ ኤጀንሲው ጉዳት አድራሹ ተሽከርካሪ ካልታወቀ ወይም የመድህን ሽፋን ከሌለው በተሽከርካሪው ለደረሰ የሞት ወይም የአካል ጉዳት ከላይ የጠቀስነውን የካሳ መጠን ይከፍላል። የአስቸኳይ ህክምና ወጪንም ይሸፍናል፡፡
አስቸኳይ የህክምና እርዳታ
ማንኛውም ሰው በተሽከርካሪ አደጋ ጉዳት ከደረሰበት ከአደጋው ቦታ፣ ወደ ህክምና በሚጓጓዝበት ወቅትና በድንገተኛ ክፍል እስከ ብር 2 ሺህ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ የማግኘት መብት አለው፡፡ ማንኛውም የጤና ተቋም ይህን አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ክፍያ ሳይጠይቅ የመስጠት ግዴታ አለበት። ክፍያውን አገልግሎቱን ከሰጠ በኋላ ከመድን ኩባንያው ወይም ከመድህን ፈንድ ኤጀንሲው የሚጠይቅ መሆኑን በአዋጁ አንቀጽ 27(3) እና (4) ላይ ተገልጿል።
የመድን ምስክር ወረቀት እና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ
የመድን ምስክር ወረቀት ማለት የተሽከርካሪው ባለንብረት ወይም ህጋዊ ግዴታ ያለበት ሰው ተሸከርካሪው በሦስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሰው አደጋ በአዋጁ መሠረት መድን የገባለት መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰነድ ነው፡፡ መድን ሰጪ ድርጅት ከመድን ገቢው ጋር የመድን ሽፋን ለመስጠት ከተስማሙ የመድን ፖሊሲውን (የመድን ስምምነት ውላቸውን) ለመድን ገቢው ይሰጠዋል፡፡ ከመድን ፖሊሲው በተጨማሪ በአዋጁ አንቀጽ 9(1) እና 12(1) ላይ እንደተገለፀው የመድን ምስክር ወረቀት እና የመድን ተለጣፊ ምልክት ለመድን ገቢው አብሮ መስጠት እንዳለበት ሕጉ በመድን ድርጅቱ ላይ ግዴታ ጥሎበታል፡፡
ይህ በአዋጁ አንቀጽ 9 መሠረት የተሰጠ የመድን ምስክር ወረቀት ከተሰጠበት ቀን አንስቶ ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ የሚፀና ነው፡፡ የመድን ሽፋን ውሉ ሲቋረጥ ወይም የውል ዘመኑ ሲያልቅ መድን ገቢው የመድን ምስክር ወረቀቱንና የመድን ተለጣፊውን ወዲያውኑ ለመድን ሰጪው ድርጅት መመለስ አለበት፡፡
የመድን ፈንድ
የመድን ፈንድ ማለት ቋሚ የፋይናንስ ምንጭ ሆኖ በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ በሚከፈት ልዩ የባንክ ሂሳብ ውስጥ ተቀማጭ እንዲሆን በአዋጁ የተቋቋመ ቋሚ የገንዘብ ምንጭ ነው፡፡ የፈንዱ የገንዘብ ምንጭ ከፈንዱ ተመን የሚሰበሰብ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወሰን ሌላ ተጨማሪ ገቢ ነው፡፡ ይህን ፈንድ የሚስተዳደረው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ በተቋቋመው የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ ሲሆን የፌደራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 ስያሜው የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት በሚል ተቀይሯል፡፡
የፈንዱ ዓላማ መድን ባልተገባለት ወይም ባልታወቀ ተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰበት ሰው አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰበት ሰው ካሳ እንዲከፈለው ማድረግ እና ለሞተ ሰው ቤተሰብ አባላት ካሳ እንዲከፈል ማድረግ ነው፡፡ በአዋጁ አንቀጽ 20(2) ላይ እንደተገለፀው ከፈንዱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚከፍለው የካሳ ክፍያ መጠን መድን የተገባለት ተሽከርካሪ አደጋ ባደረሰ ጊዜ በሚከፈለው የካሳ መጠን ልክ እንደሆነ ተደንግጓል፡፡
የመድን ፈንድ አገልግሎቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት በሕጉ የተቀመጠውን የጉዳት ካሳ መጠን ከከፈለ በኋላ ይህን የከፈለውን ክፍያ ለጉዳቱ በኃላፊነት ተጠያቂ ከሆነው ሰው ላይ የማስመለስ መብት እንዳለው በአዋጁ አንቀጽ 20(3) ተደንግጎል፡፡
ተጠያቂነት
የተሽከርካሪ የሶስተኛ ወገን ህግን አለማክበር የማስተካከያ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ከማስከተሉም በተጨማሪ ክልከላዎችን ተላልፎ መገኘት ከብር 3 ሺ እስ ብር 5 ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ወይም ከ1 አመት እስከ 2 አመት በሚደርስ እስራት እንደሚያስቀጣ በአዋጁ አንቀፅ 30 ተደንግጓል፡፡
የተሽከርካሪ አደጋ የሦስተኛ ወገን መድን ህግ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች ከደረሰባቸው ችግር በተወሰነ መልኩ እንዲቋቋሙ እና አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ለማስቻል ተግባራዊ የተደረገ ህግ ነው፡፡ ስለሆነም ሕብረተሰቡም የተሽከርካሪ አደጋ እንዳይደርስ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ አደጋ ከደረሰ ግን በጠቀስናቸው መብቶች መጠቀም የሚችል መሆኑን መገንዘብ እንዳለበት መጠቆም እንወዳለን፡፡
በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties

በቅርቡ ለምንጀምረው አለ ህግ የህግ ጉዳዮች ዩቱብ ቻናል ፕሮግራም ሰብስክራብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ፣
ሼር በማድረግ አድርሱልን።
subscribe our channel
Share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@Lawsocieties

በቅርቡ አለ ህግ የተሰኘው ፕሮግራም ይጀምራል ሼር እና ሰብስክራብ አድርጉልን።
ሼር በማድረግ አድርሱልን።
#subscribe our YouTube channel
and #Share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@Lawsocieties
ሼር በማድረግ አድርሱልን።
#subscribe our YouTube channel
and #Share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://youtube.com/@Lawsocieties
Forwarded from ሕግ ቤት
Law LLB EE 2015 Result 43.xlsx
11.9 KB
Wolkite university Law LLB Exit Exam Result
ብንዘገይም አልቀረንም #አለ_ህግ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ እና ሼር አድርጉልን በቅርቡ ለሚጀመረው አለ_ህግ ለተሰኘው ፕሮግራም አባል ይሁኑ።
https://youtube.com/@Lawsocieties
subscribe and share Ale_Hig YouTube channel.
Coming soon 🔜🔜🔜🔜🔜

አንድ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ የወራሽነት መብቱን ለአካለ መጠን ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 15 አመት ባለው ጊዜ ውስጥ ቢጠይቅ በይርጋ ሊታገድ አይገባም፡፡
የፌ.ጠ.ፍ.ሰ.ሰ.ችሎት ቅፅ 20 በመ/ቁ 120841
የፌ.ጠ.ፍ.ሰ.ሰ.ችሎት ቅፅ 20 በመ/ቁ 120841
የፍትሐብሔር ክርክር ሂደት.pdf
694 KB
የፍትሐብሔር ክርክር ሂደት፡- ከክስ አቀራረብ እስከ ፍርድ አሰጣጥ
በዚህ ጽሑፍ የተብራሩ የፍትሐብሔር ክርክር ሂደት ደረጃዎች፡-
👉 የክስ ማመልከቻን መመርመር
👉 ለተከሳሽ መጥሪያ መላክ
👉 የመከላከያ መልስን መመርመር
👉 የጽሑፍ ማስረጃ ስለሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ
👉 የጽሑፍ ክርክር የማቀባበል ሥራን ማጠናቀቅ
👉 ክስን መስማት
👉 የሦስተኛ ወገኖች ጣልቃ ገብነት ወይም ክስ ውስጥ መግባት
👉 ተከራካሪዎችን መመርመር
👉 በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች
👉 የክርክሩን ጭብጥ መያዝ
👉 ለምስክሮች መጥሪያ መላክ
👉 ምስክሮችን መመርመር
👉 ፍርድ
#EsubalewAmareLawOffice
በዚህ ጽሑፍ የተብራሩ የፍትሐብሔር ክርክር ሂደት ደረጃዎች፡-
👉 የክስ ማመልከቻን መመርመር
👉 ለተከሳሽ መጥሪያ መላክ
👉 የመከላከያ መልስን መመርመር
👉 የጽሑፍ ማስረጃ ስለሚቀርብበት ጊዜና ሁኔታ
👉 የጽሑፍ ክርክር የማቀባበል ሥራን ማጠናቀቅ
👉 ክስን መስማት
👉 የሦስተኛ ወገኖች ጣልቃ ገብነት ወይም ክስ ውስጥ መግባት
👉 ተከራካሪዎችን መመርመር
👉 በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች
👉 የክርክሩን ጭብጥ መያዝ
👉 ለምስክሮች መጥሪያ መላክ
👉 ምስክሮችን መመርመር
👉 ፍርድ
#EsubalewAmareLawOffice
#ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) እና የአክሲዮን ማህበር ተመሳሳይነትና ልዩነት
በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ዉስጥ ካሉት የንግድ ማህበራት መካከል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC ) እና የአክሲዮን ማህበር ይገኙበታል ።
ሁለቱም ማህበራት አክሲዮን ያላቸዉ ወይም ካምፓኒዎች ሲሆኑ ተመሳሳይነትና ልዩነት አላቸዉ።
#ተመሳሳይነታቸዉ
• ህጋዊ ሰዉነት ያላቸዉ መሆኑ ፣
• የራሳቸዉ ንብረት ያላቸዉ መሆኑ፣
• የራሳቸዉን ትርፍና ኪሳራ ተጠያቂነት ያለባቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም ትንሹ የአባላት ብዛትና የመነሻ ካፒታል ያላቸዉ መሆኑ፣
• ሁለቱም በቦርድና በማናጀር መመራት የሚችሉ መሆኑ ነገር ግን ለ PLC አሰገዳጅ አለመሆኑ፣
• የሁለቱም ተጠያቂ በተዋጣዉ የገንዘብ መጠን (አክሲዮን ) መሆኑ ፣
• ሁለቱም የሙያ መዋጮን የማይቀበሉ መሆኑን (የንግድ ህግ 256 እና 501 )
• በሁለቱም ካፒታል ማሳደግና መቀነስ የሚቻል መሆኑ ፣
• በሁለቱም አክሲዮኖች በመያዣ /በዋስትና / መያዝ ሚችሉ መሆኑ ፣
#ልዩነታቸዉ
አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር / PLC/ private Limited Company/ ለማቋቋም የአባላት ብዛት ከሁለት ማነስ የማይችሉ መሆኑ እንዲሁም ከሀምሳ መብለጥ እንደማይችሉ በንግድ ህጉ አንቀጽ 495(4) ላይ ተገልጿል። የአክሲዮን ማህበርን ( share company ) በተመለከተ ለማቋቋም ከ5 አባላት ማነስ የማይችል ሲሆን ብዛት ግን ገደብ የሌለዉ መሆኑን በንግድ ህጉ አንቀጽ 248(3) ላይ ይገኛል።
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መነሻ ካፒታል 15000 ሺህ ብርና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋም በኢትዮጵያ ብር አንድ በመቶ ማነስ አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር (496)
• አክሲዮን ማህበር መነሻ ካፒታል 50000 ሺህ እና ከዚያ በላይ ሲሆን የአንድ አክሲዮን ዋጋ ከአንድ መቶ ብር በታች መሆን አይችልም (የንግድ ህግ ቁጥር 247)
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታሉ ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የተከፈለ ሲሆን የአክሲዮን ማህበር ግን ሙሉ በሙሉ አስቀድሞ የሚከፈል አይደለም ነገር ግን ከተፈረሙ አክሲዮኖች ቢያንስ 1/4 (25%) መከፈል አለበት የቀረዉ በሂደት የሚከፈል ይሆናል (የንግድ ህግ ቁጥር (495(1)
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የአክሲዮኖች ሽያጭ ለህዝብ ክፍት የሚደርግ አይደለም አንቀጽ 495(2) ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ለህዝብ ክፍት የሚደረግ ነዉ (የንግድ ህግ ቁጥር248)
• ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( PLC) ላይ አክሲዮን ማህበር ዉስጥ ያለ ሰዉ አክሲዮኑን ለሶስተኛ ሰዉ ማስተላለፍ አይችልም ምክንያቱም መተዳደሪያ ደንቡ ላይ አባላት ይህን እስካልፈቀዱ ድረስ በህጉ መሰረት sale freely transfrable አይደለም። ነገር ግን አክሲዮን ማህበር ላይ አክሲዮን ማስተላለፍን በተመለከተ አክሲዮን የገዛ ሰዉ አክሲየኑን ለሌላ አባል ላልሆነ ሰዉ በቀላሉ ማስተላለፍ ይችላል ። ስለዚህ አክሲዮን ማስተላለፍ ከተፈለገ በቀላሉ የአክሲዮን ማህበርን መምረጥ ያስፈልጋል ማለት ነዉ።
• አስተዳደራዊ አካል (ቦርድ) ን በተመለከተ አክሲዮን ማህበራት ሁሉ ከ3-12 ሰዉ የሚይዝ ቦርድ ኦፍ ዳይሬክተር ሲቋቋም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ( plc) ዉስጥ ቦርድ የለም።
#የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ
#ethiolawtips