አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎች በቅርቡ ባሳተመው ቅፅ 25 ላይ የገጠር መሬትን በተመለከተ ምን አዲስ እይታ ይዞ መጣ?
****

1. የገጠር መሬትን በተመለከተ ሁለት ዳኝነቶች በአንድ ላይ ተጣምረው ሲቀርቡ የፍርድ ቤት ስልጣን በተመለከተ በመሬት አዋጁ፣ በስነ-ስርዓት ህጉ እና የክልል ፍ/ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ መካከል ግጭት ካለ የመሬት አዋጁ ልዩ ህግ በመሆኑ በቀዳሚነት ሊተገበር ይገባል (Special prevails over the geberal)። የሰበር መ/ቁ. 191968

2. ወራሽነትን ቀድሞ በማረጋገጥ የገጠር መሬትን ቀድሞ መያዝ ልዩ የወራሽነት መብትን የማያጎናፅፍ በመሆኑ ሌሎች ወራሾችን ድርሻቸውን ከመጠየቅ አይገድብም። የሰበር መ/ቁ. 181643

3. የገጠር መሬት አዋጁ ላይ የገጠር መሬትን በሽያጭ ዉል ማስተላለፍ ክልከላ የተደረገበት ከሆነ መሬቱ ላይ ቤት ቢኖርበትም ባይኖርበትም ዉሉ ህግን ያለተከተለ ሰለሆነ አይፀናም። የሰበር መ/ቁ. 186431

4. የገጠር መሬት ስጦታ ተደርጎል ተብሎ የሚመዘነው በጊዜው በነበረው የገጠር መሬት ህግ እንጅ ከስጦታው በኋላ ተሻሽሎ በወጣው ህግ አይደለም። (Principle of non-retroactivity) የሰበር መ/ቁ. 185848

5. የገጠር መሬት ስጦታን በተመለከተ የመሬት አዋጆቹ ስራ ላይ ባልነበሩበት ጊዜ ወይም ደግሞ በህጎቹ ባልተሸፈኑ ጉዳዪች ላይ የፍ/ህጉ የማይንቀሳቀስ ንብረት በስጦታ ስለሚተላለፍበት ሁኔታ የተዘረዘሩት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ ይገባል። (Common approach of the Cassation using the 1960 Civil Code provisions as a gap feeling to rural land matters) የሰበር መ/ቁ. 188853

6. ከሚመለከተው የመንግስት አካል በስተቀር አንድ ግለሰብ የያዘውን መሬት አያያዙ በህገ-ወጥ መንገድ በሚል አስለቅቆ መያዝ አይችልም። (No one can take justice by his own hand) የሰበር መ/ቁ. 187618

7. የገጠር መሬት ኪራይ ይርጋ ጋር በተያያዘ የመሬት አዋጁ በግልፅ ካላስቀመጠ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ የፍ/ህ/ቁ. 1845 ነው። የሰበር መ/ቁ. 187484

8. ትዳር በሞት ምክንያት ከፈረሰ በሌላኛው ተገቢ የተያዘ የገጠር መሬት እንዲመለስ በወራሾች የሚቀርብ ጥያቄ በጋብቸ የተፈራ የንብረት ክፍፍል ጥየቄ ስለሆነ ሰበር ቀደም ብሎ በቅፅ 4 የመ/ቁ. 17937 በሰጠው የህግ ትርጉም መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል። የሰበር መ/ቁ. 186461. Credit to #Ayalew Asfaw