አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ጊዜያዊ የመጠባበቂያ እርምጃ (Provisional Interim measure) እና የፍርድ ቤት ስልጣን
ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን

ከመደበኛ የፍርድ ቤት ክርክር ጋር በተገናኘ ፍርድ ቤቶች የተለያዩ ጊዜያዊ ትዕዛዞችን ሊሰጡ የሚችሉ ሲሆን እነዚህ ትዕዛዞች ጊዜያዊ መፍትሔዎች (provisional remedies) ተብለዉ የሚታወቁት ናቸዉ፡፡ ጊዜያዊ የሚል ስያሜ የተሰጣቸዉ ብቻቸዉን ፀንተዉ ሊኖሩ የማይችሉ ከዋናዉ ክርክር ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ በመሆናቸዉ ነዉ፡፡ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕጉ እንደ ጊዜያዊ መፍትሔዎች ከተቀመጡት ዉስጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 151 ንብረት ማስከበር (attachment before judgment)፣ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 154 ለጊዜዉ የሚሰጥ የማገድ ትዕዛዝ (temporary injunction) እንዲሁም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 160 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት ከፍርድ በፊት የሚሰጡ ሌሎች ጊዜያዊ ትዕዛዝ (interlocutory orders) ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

ይህ ጽሑፍ በግልግል ወይም በእርቅ የሚታዩ ጉዳዮችን ተከትሎ የሚሰጡ ጊዜያዊ የመጠባበቂያ እርምጃዎች ወይም ትዕዛዝ (Provisional Interim measure) ያላቸዉን የሕግ ማዕቀፍ እና ተግባራዊ አፈጻጸም የሚዳስስ ነዉ፡፡

https://www.abyssinialaw.com/blog/provisional-interim-measure
የዓመት ፈቃድ መተላለፍ ሰ/መ/ቁ 203965

አሠሪ ሠራተኛዉ በሥራ ላይ አልነበረም ወይም ደግሞ የዓመት እረፍቱን ተጠቅሟል የሚል ክርክር ካላቀረበ የሥራ ሁኔታዉ በማስገደዱ በአሠሪዉ ውሳኔ የዓመት እረፍት እንደተላለፈ ሊቆጠር ይገባል።
ስለሆነም ሰራተኛው በሕጋዊ መንገድ ቅጽ ሞልቶ ስላላስተላለፈ ያልተጠቀመበት የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ ሊከፈለው አይገባም በማለት አሰሪው የሚያቀርበው መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም።
አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 79(2) እና (3)
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
የይግባኝ ሰሚ ችሎቶች ከዚህ በኋላ በደፈናው ይግባኝ ያስቀርባል አያስቀርብ በማለት ብቻ መዝገብ መመለስ እንደማይችሉና ይግባኙን ያልተቀበሉበትን ምክንያት አትተው መጻፍ እንዳለባቸው የተጻፈ ደብዳቤ።
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
Forwarded from PIN NGO
Public Information Noble (PIN)ፒን is an CSO working on the right to access information.
ፐብሊክ ኢንፎርሜሽን ኖብል

"Information is a key – let's provide access to all"

Title:
The Impact of Access to Information on Economic Development

Introduction:👉👉👉👉
In today's interconnected world, access to information plays a pivotal role in shaping economic development. The ability to obtain and share information efficiently empowers individuals, businesses, and governments to make informed decisions, innovate, and foster growth. This article explores how access to information can significantly influence economic development, with specific examples highlighting its transformative power.

Enhancing Education and Skill Development:
Access to information promotes education, which is vital for economic growth. Through digital platforms and online resources, individuals can access educational materials, courses, and lectures that were previously inaccessible. This democratization of knowledge equips individuals with the skills and expertise required for various industries, leading to an overall increase in productivity and innovation. For example, online learning platforms like Coursera and Khan Academy have enabled countless people from developing nations to gain new skills and improve their employability.

Facilitating Market Efficiency and Transparency:
Timely access to market information provides businesses with valuable insights into consumer preferences, competitor strategies, and evolving trends. In turn, this facilitates better decision-making, increased competition, and improved efficiency. For instance, e-commerce platforms such as Amazon have revolutionized retail by providing sellers with real-time data on product demand, enabling them to optimize pricing and inventories accordingly.

Empowering Entrepreneurs and Start-ups:
Access to information lowers barriers to entry for budding entrepreneurs and start-ups. Online platforms and communities provide vital resources, mentorship, and networking opportunities, enabling aspiring founders to gather knowledge, seek funding, and connect with potential partners or customers. Communities like Y Combinator and Techstars have played a significant role in nurturing successful start-ups by granting access to invaluable guidance and networks.

Strengthening Good Governance:
Access to information promotes transparency and accountability, fostering good governance practices within societies. Governments that embrace open data initiatives enable citizens to monitor public spending, scrutinize policies, and engage in participatory decision-making processes. This transparency reduces corruption, ensures efficient resource allocation, and encourages foreign investments. The Open Government Partnership and Freedom of Information Acts in various countries exemplify the positive impact of access to information on governance.

Promoting Agricultural Development:
Access to information can revolutionize agriculture, a crucial sector for many developing nations. Real-time weather data, market prices, and farming techniques empower farmers by enabling informed decision-making related to crop selection, planting schedules, and pest management. Services like IBM's Weather Underground and mobile applications like iCow have improved crop yields, reduced risks, and increased profitability for farmers in Africa.

Conclusion:🟢🔜🕚
Access to information serves as a catalyst for economic development across various sectors. By enhancing education, fostering market efficiency, empowering entrepreneurs, strengthening good governance, and promoting agricultural advancements, societies can unlock their full potential and achieve sustainable growth. Governments, organizations, and individuals must continue to prioritize initiatives that expandaccess to information, ensuring equitable opportunities for progress on a global scale.
https://t.me/PublicInformationNoble
@PublicInformationNoble
#ETA

" ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም "

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ፤ ባዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ ረቂቅ መመሪያ ላይ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወይም የስልጠና ተቋማት በሁሉም መርሃ ግብሮች #የሕግ እና #የመምህርነት ትምህርት ዘርፎችን #አሁንም ማስተማር እንደማይችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በፊትም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሁሉም መርሃግብሮች የሕግ እንዲሁም የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ የተደረገ ሲሆን አሁንም በአዲሱ መመሪያ የሕግ እና የመምህርነት ትምህርት መስጠት አይችሉም ተብሏል።

ሌሎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ አሰጣጥ #ረቂቅ መመሪያ ላይ ምን ተካቷል ?

- ማንኛውም ተቋም አዲስ ፕሮግራም ለመከፈት ወይም ነባሩን ፕሮግራም ለማስቀጠል የፍላጎት ዳሰሳ፣ የገበያ ጥናት እና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ እውደ ጥናት ማካሄድ ይኖርበታል፡፡

- ለማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት የፕሮግራም ፈቃድ የሚሰጠው ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ ብቻ ይሆናል፡፡

- የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከፍቷቸው ፕሮግራሞች ባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) የሚያወጣቸውን የመመዘኛ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

- ለማንኛውም ተቋም የሚሰጥ ፈቃድ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ተገምግሞ ለተፈቀደለት ካምፓስና የትምህርት መስክ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም ተቋም የጤና የትምህርት መስኮችን መስጠት የሚችለው በመደበኛ መርሃ ግብር ብቻ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በርቀት ትምህርት መርሃ ግብር ማስተማር የሚችለው ከድንበር ተሻጋሪ ወጪ በመጀመሪያ ዲግሪ ብቻ ይሆናል።

- ማንኛውም የግል ትምህርት ወይም ስልጠና ተቋም #የመምህርነት እና #የህግ ትምህርት ዘርፎችን ማስተማር አይችልም፡፡

- ማንኛውም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋም የትኛውንም ስልጠና በርቀት መርሃ ግብር ለማሰልጠን የሚቀርብ የፈቃድ ጥያቄ የማይስተናግድ ይሆናል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም #በህክምና_ዶክትሬት እና #በስፔሻሊቲ ትምህርት ፈቃድ ለማግኘት ተቋሙ #የህክምና_ሆስፒታል ሊኖረው ይገባል።

- በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ ጊዜው ሳያበቃ የስርዓተ ትምህርት ወይም የዲግሪ ስያሜ ለውጥ ካለባለስልጣኑ ፈቃድ ወጪ ማድረግ አይችልም።

- በሀገር ደረጃ በትምህርት ፖሊሲ ስርዓተ ትምህርቱ እስካልተቀየረ ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ በተቋም ወይም በካምፓስ ደረጃ የጸደቀ ስርዓተ ትምህርት የፈቃድ/ፈቃድ እድሳት ጊዜው እስካላበቃ ድረስ በሌሎች ካምፓሶች መተግበር ወይም መጠቀም ይችላል።

- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በበየነ መረብ ወይም በርቀት ትምህርት መርሃ-ግብር ፈቃድ ሲጠይቁ በባለስልጣኑ (የኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን) ስርዓተ-ትምህርቱ ቀድሞ መገምገም እና ተገቢ ማስተካከያ ተደርጎ መፅደቅ ይኖርበታል።

- ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በብሎክ ኮርስ ትምህርት ለመስጠት ያለው አመቺነትና ተገቢነት እንዲሁም የትምህርት ጥራት ላይ የሚኖረውን ተፅህኖ ከግምት በማስገባት ስርዓተ ትምህርቱ ከጸደቀ በኃላ ሊተገብር ይችላል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ያገኘው ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መሪ አስፈፃሚ ሕይወት አሰፋ ነው።

@tikvahethiopia
ወራሽ የሆነ ወገን አውራሹ ተካፋይ በነበረበት ክርክር ላይ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.358 መሰረት መቃወም አይችልም ::
ቅፅ 25 መ/ቁ 180551
ስለ ቼክ ማወቅ ያለባችሁ ወሳኝ የህግ ነጥቦች
በቼክ ገንዘብ ሊሰጣችሁ ወይም ቼክ ልትፈርሙ ስለምትችሉ ቀጣዮቹን ቼክን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች እናንሳ።
ቼክ ማለት ገንዘብን ተክቶ የሚያገለግል ተላላፊ የገንዘብ ሰነድ ነው፡፡ ቼክ ሊፈርም የሚችለው በአንድ ባንክ ውስጥ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ያለው ሰው ነው፡፡ድርጅት ከሆነ ደግሞ ፈራሚው በድርጅቱ ቼክ ላይ የመፈረም ስልጣን የተሰጠው መሆን አለበት፡፡ -ቼክ ከመቀበላችሁ በፊት በቼኩ ላይ -የሚከፈለው የገንዘብ መጠን በአሀዝና በፊደል መፃፉን - የሚከፈለው ሰው ስም እና የባንኩ ቅርንጫፍ መፃፉን -ቼኩን የሰጠው ሰው ፊርማ መኖሩን -ቼኩ የተፃፈበት ቀን እና ቦታ መኖሩ ማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ መሆኑን የንግድ ህግ አንቀፅ 827 ይደነግጋል። -ቼኩ ለማን እንደሚከፈል ስም ካልተጠቀሰበት ማንኛውም ቼኩን ይዞ የቀረበ ሰው ይከፈለዋል። ቼኩ በስሙ የተፃፈለት ሰው ወይም በትዕዛዝ የሚል ካለበት ደግሞ በቀላሉ ከጀርባው በመፈረም ለሌላ ሰው ሊያስተላልፈው ይችላል ።ያም ሰው በጀርባው ፈርሞ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላል፡፡ -የገንዘብ መጠኑ ያልተጠቀሰበትን ቼክ ፈርሞ መስጠት አደገኛ ነው ፡፡ ቼኩ የተፃፈለት ወይም የተላለፈለት ሰው የፈለገውን ገንዘብ ሊሞላበት ይችላል፡፡ -ቼኩ የሚከፈለው ለባንኩ ለክፍያ በቀረበ ቀን ነው። - ሆኖም ቼኩ በን/ሕ/ቁ 857 መሠረት የወጣበት ቀን ከግምት ሳይስገባ ቼኩ ላይ ከተፃፈው ቀን ጀምሮ በ6 ወር ውስጥ ለባንኩ ለክፍያ መቅረብ አለበት፡፡ -ቼኩን የሚፈርመው ሰው የክፍያውን ቀን ቼኩን ከፃፈበት ወይም ቼኩን ካወጣበት ቀን ወደፊት ወይም ወደ ኋላ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ዛሬ ቼኩን ሲፅፍ የተፃፈበት ቀን ወደኃላ 7 ወር አድርጎ ቀኑን ቢፅፈው ለክፍያ መቅረብ ያለበት 6 ወር ጊዜ ስላለፈ ባንኩ መክፈልም ሆነ ያልከፈለበትን ምክንያት ለመግለፅ ሳይገደድ ቼኩ ለክፍያ መቅረብ ባለበት ጊዜ ባለመቅረቡ ብቻይመልሰዋል፡፡ ዛሬ የሚሰጥህን ቼክ ወደፊት የዛሬ 4 ወር አድርጎ ቀኑ ከተፃፈበት ለክፍያ መቅረብ የሚችለው ከአራት ወራት በኃላ ካለው ቀን ጀምሮ ባለው 6 ወራት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ ቼክ ተቀባዬች የሚሰጣቸውን ቼክ ገንዘቡን መቀበል ከሚችሉበት ቀን አንፃር በጥንቃቄ የተፃፈበት ቀን ማየት አለባቸው -ቼክ የሰጠው ሰው ቼኩ ለባንኩ ለክፍያ ከመቅረቡ በፊት ባንኩን እንዳትከፍል ብሎ መከልከል ይችላል። ባንኩም የክፍያ መከልከያ ትእዛዝ ከደረሰው መክፈል የለበትም። -የተረጋገጠ ቼክ (cpo) የተጠቀሰው ገንዘብ መኖሩ በባንኩ ተረጋግጦ የተቀመጠ በመሆኑ ከተራ ቼክ የበለጠ አስተማማኝ ነው። -ቼኩን ለባንክ አቅርበህ በቼኩ ላይ የተጠቀሰውን ያህል በቂ ገንዘብ ከሌለ በሂሳቡ ውስጥ ያለውን ያህል መቀበል ይቻላል። -ለቀረው ገንዘብ ደግሞ ባንኩ ‘‘በቂ ስንቅ ለውም’’ የሚል የፅሁፍ ማስረጃ ቼኩን ይዞ ለቀረበው ሰው ይሰጠዋል። -በተለምዶ ‘‘ደረቅ ቼክ’’ የሚባለው ለክፍያ ሲቀርብ በሂሳቡ ውስጥ በቂ ገንዘብ ከሌለው ሲሆን ባንኩ በሚሰጠው ማስረጃ መሰረት ቼክ ሰጪውን ወይም አውጭውን በወንጀል ያስጠይቃል። ሆን ተብሎ ከተፈፀመ ቼክ አውጪው በወንጀል ህግ አቀፅ 693 መሰረት በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ከሆነ ደግሞ ከአስር አመት በማይበልጥ ፅኑ እስርና በመቀጮ ይቀጣል። -ደረቅ ቼኩ የተሰጠው በቸልተኝነት ከሆነ ደግሞ ሰጭው በመቀጮ ወይም ከንድ አመት በማይበልጥ ቀላል እስር ይቀጣል ፡፡ -ሳይከፈል የቀረውን የቼኩን ገንዘብ ና ወጭውን ቼኩ የተፃፈለት ወይም ተፈርሞ የተላለፈለት ሰው በፍትሀ ብሔር ከሶ ገንዘቡን ማስመለስ ይችላል፡፡ -በብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሰረት ደረቅ ቼክ የሚሰጡ ሰዎች በጥፋታቸው በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሚገቡ ሲሆን ከገንዘብ መቀጮ አንስቶ በቼክ ሂሳብ የማንቀሳቀስ መብታቸውን እስከማሳጣት ቅጣት ይጣልባቸዋል፡፡ እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው ህጎች ቼክን የገንዘብ ያህል አስተማማኝ ለማድረግ የተደነገጉ ናቸው። ለግብይት ቅልጥፍና እንዲሁም ለገንዘብ እንቅስቃሴ አመቺነት በቼክ መጠቀሙ ከጥሬ ገንዘብ የተሻለ ዘመናዊ አሰራር በመሆኑ ቼክ አስፈላጊና ልንጠቀምበት የሚገባ የገንዘብ ሰነድ ነው። ለማንኛውም ቼክ ስንሰጥም ሆነ ስንቀበል ከላይ የተነሱትን ነጥቦች ልብ እንበል፡፡
By Yesuf Akeberegn
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
There is no definitive ranking of the top 10 international conventions related to human rights, as different conventions may have different scopes, impacts, and challenges.
However, based on the results of web search
,

10 core human rights treaties that are widely recognized and ratified by many states.

These are:👇👇👇👇👇👇

1 - The International Convention on the Elimination of All Forms of Racial Discrimination (ICERD), which aims to combat racial discrimination and promote racial harmony¹.

2 - The International Covenant on Civil and Political Rights (ICCPR), which protects the rights to life, liberty, security, freedom of expression, assembly, association, religion, and fair trial².

3 - The International Covenant on Economic, Social and Cultural Rights (ICESCR), which protects the rights to work, education, health, social security, and cultural participation³.

4 - The Convention on the Elimination of All Forms of Discrimination against Women (CEDAW), which promotes and protects the human rights of women.

5 - The Convention against Torture and Other Cruel, Inhuman or Degrading Treatment or Punishment (CAT), which prohibits torture and other forms of ill-treatment¹.

6 - The Convention on the Rights of the Child (CRC), which recognizes the special needs and rights of children.

7 - The International Convention on the Protection of the Rights of All Migrant Workers and Members of Their Families (ICRMW), which safeguards the rights of migrant workers and their families¹.

8 - The International Convention for the Protection of All Persons from Enforced Disappearance (ICPPED), which prevents and punishes enforced disappearances¹.

9 - The Convention on the Rights of Persons with Disabilities (CRPD), which affirms the dignity and rights of persons with disabilities.

10 - The International Convention on the Elimination of All Forms of Discrimination against Women (CEDAW), which promotes and protects the human rights of women.


Source: Bing, 6/30/2023
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig
639-2009 የፍትሃብሄር ህግ ማሻሻያ አዋጅ.pdf
98.9 KB
የፍትሃብሄር ህግ ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 639/2009
" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " - የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለዓመታት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ዝቅተኛ የደመወዝ የሚወስነውን " የደመወዝ ቦርድ " ማቋቋም እንደሚገባ መደንገጉን፣ ይሁን እንጂ ለዝቅተኛ ተከፋዮች የኑሮ ሁኔታን የዋጀ የአከፋፈል ሥርዓት ያስተካክላል ተብሎ ሲጠበቅ ዓመታት ያስቆጠረው " የደመወዝ ቦርድ " የማቋቋም ድንጋጌ፣ አሁንም ጆሮ ዳባ መባሉን የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ገልጸዋል፡፡

ኢሠማኮ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ደጅ ቢጠናም፣ አሁንም የዝቅተኛ ሠራተኞች ጉዳይ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡

ተገቢውን ቅደም ተከተል በመከተል በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ትኩረት እንዲያገኝ ኢሠማኮ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ባለማግኘቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕልባት እንዲገኝ አቤቱታ ማቅረቡን አክለዋል፡፡  

ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄው መቅረቡን ገልጸው፣ " የሚሰጡትን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው " ብለዋል፡፡

ኢሠማኮ በየዓመቱ በሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በኑሮ ውድነት ምክንያት በሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መፍትሔ እንዲያገኝና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ምጣኔ እንዲሻሻል፣ በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ሊያቀርብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካለት መቅረቱ ይታወሳል፡፡

በሰላማዊ ሠልፉ ሊነሱ የታሰቡ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት ቢቀርቡም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከመፍቀድ በዘለለ ወሳኙ የሠራተኞች የህልውና ጥያቄ መፍትሔ እንዳልተሰጠው ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " ያሉት ፕሬዚዳንቱ " ሌሎች ሕጋዊ አማራጮችን በመጠቀም መፍትሔ ለማግኘት እንሠራለን " ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ተካልኝ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም የራሱ የሆነ አሉታዊም አዎንታዊ ጎን አለው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም ከሥራ አጥነትና ከኑሮ ውድነት አኳያ፣ ለሚተላለፈው ኢኮኖሚው መቋቋም ይችላል የሚለውን ጉዳይ ለማየት ጥናት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎ ሚኒስቴር አገር አቀፍ የኢኮኖሚው ሁኔታ ተፅዕኖ መፍጠር አለመፍጠሩን በጥናት ከመለየት በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ግለሰብ ለመኖር የሚያስፈልገው ወርኃዊ ገቢ ጭምር እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

" የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም አሁን ካለው አገራዊ ሁኔታ አንፃር መታየት ስላለበት፣ በድጋሚ ጥናት እየተደረገበት ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪና ውስብስብ በመሆኑ፣ ቦርዱን ለማቋቋም እንደገና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወሰንባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ዳሰሳ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ለማቋቋም አሁን ባሉ አገር አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የፖለቲካዊ ሁነቶች አስቻይና ከልካይ ሁኔታዎችን ያማከለ እንዲሆን ያለመ ብሔራዊ የዳሰሳ ጥናት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት መረጃ ለማግኝት የሚያስችል 965 የተባለ የጥሪ ማዕከል ይፋ ተደረገ
አዲስ አበባ 26/10/2015ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ አገልግሎት መረጃ ለማግኝት የሚያስችል 965 የተባለ የጥሪ ማእከል ይፋ ተደርጓል፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት መሠረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን የጥሪ ማዕከሉ መከፈት የንግድ ስራን ለመጀመር የሚፈልግ ግለሠብም ሆኑ ተቋማት በሁሉም የአገልግሎት አይነቶች ላይ ሙሉ መረጃ ለማግኘት እንደችሉ የሚያግዛቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የንግድ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹ ሚኒስትር ዴኤታው ከሀምሌ 1 2016ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት በኦን ላይን መሰጠት እደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡
የንግድ ስራን የመጀመር ሂደትን አመቺ ለማድረግ፣ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት እና የንግድ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በርካታ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሀላፊዎች በድርጅት ስም፣ በንግድ ስም፣ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እና በአጠቃላይ በ19 አገልግሎቶች ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Lawsocieties
#ሼር #Share
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/AleHig