አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ማስታወቂያ
አዲስ የጥብቅና ፈቃድ ለምታወጡ የፌደራል ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች በሙሉ፤
****
የኢ
ትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር በአዋጅ ከመጋቢት ወር 2014ዓ.ም ጀምሮ የዳግም   ምዝገባ እያካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም አዲስ የጥብቅና ፈቃድ የምታወጡ ጠበቆች እና የጥብቅና ድርጅቶች እንዲሁም የጥብቅና ፈቃዳችሁን በአደራ አስቀምጣችሁ ቆይታችሁ አሁን ላይ ፈቃዳችሁን በድጋሚ እየወሰዳችሁ ላላችሁ ጠበቆች በሙሉ ፍቃዳችሁን በወሰዳችሁ በአንድ ወር ውስጥ የመመዝገቢያ ክፍያ 1,000.00 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል የክፍያውን ደረሰኝ እና የጥብቅና ፈቃዳችሁን ኮፒ  በመያዝ በማህበሩ ቢሮ በመገኘት የተዘጋጀላችሁን ፎርም ሞልታችሁ የአባልነት ምዝገባ ማድረግ እንደሚጠበቅባችሁ እየገለጽን በማናቸውም ምክኒያት 1 ወሩን አሳልፈው ቢገኙ ለሚደርሰው አስተዳደራዊ ቅጣት እንዳትዳረጉ ማህበሩ በድጋሚ ያሳስባል፡፡

*የማህበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር- 1000469494218 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ.

*ማስታወሻ፡- የምዝገባው ቦታ ፒያሳ አራዳ ምድብ ችሎት (የፍትህ አካላት ህንፃ) 9ኛ ፎቅ በማህበሩ ቢሮ ቁጥር 922 መሆኑን እናሳውቃለን::

የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
    አዲስ አበባ፤
  ጥር 26 ቀን 2015ዓ.ም
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
እሁድ እሁድ ስናካሂድ የነበረውን ከምሽቱ 2:30 የእሁድ ችሎት ነፃ ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ ሲሆን ውይይቱን ስንጀምር የምናሳውቅ ይሆናል‼️

#የእለቱ_ችሎት

#የችሎቱ_ጭብጥ

ፕሮግራም ለአልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠ መሆኑን ስለማሳወቅ‼️

#ውሳኔ
ችሎቱ ቢያመልጥዎት በሌሉበት የሚሰማ ይሆናል።

ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ @lawsocieties የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ሆኖ ተራዝሟል።

ወደ ቴሌግራም ቻናላችን ይመለሱ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ#አለ_ህግ ስም አለበት
https://t.me/lawsocieties
የቤት ኪራይ መጨመርና ማስለቀቅ የታገደበትን የጊዜ ገደብ እስመልክቶ በውስጥ መስመር ብዙ ጥያቄ ስለመጣ በድጋሚ የተለጠፈ

ቀነ ገደቡ እስካልተራዘመ ድረስ የካቲት 18/2015 ዓ.ም. ያበቃል ይላል ።
በአስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ወጣት አለምነህ ተካ ተክሌ በ 9 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፦
  👉 ተከሳሽ ለጊዜው ካልተያዘው ግበብረ አበሩ ጋር በመሆን ህዳር 25 ቀን 2015ዓ/ም በግምት ከምሽቱ  4:00 ሲሆን አዲ አርቃይ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ከ አቶ አስረሳሀኝ አሰፋ ቤት የግል ተበዳይ የሆነችውን ተኝታ ከነበረበት ከሌላ ዶርም ቤት አንኳክተው ካስከፈቱ በኀላ "የ ህግ አካል ነን መታወቂያሽን ካለበት ከመኖሪያ ቤትሽ ወስደሽ አሳይን" በማለት ይዘዋት ከወጡ በኀላ አፏን እና ፊቷን በሽርጥ አፍነው ሀዋዛ በር ከተባለ ቦታ በመውሰድ አስገድዶ ወንጀል ፈፅመውባታል በማለት የአዲ አርቃይ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት በ ወንጀል ህጉን 620(2)  በመጥቅ ክሱን ለ ወረዳው ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡ የ አዲ አርቃይ ወረዳ ፍ/ቤትም የሰው ምስክር እና የህክምና ማስረጃዎችን በማየት መዝገቡን ከመረመረ በኀላ በቀን 29/05/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተካሳሽን በ 9 አመት ፅኑ እስራት የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል በማለት የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ መረጃውን አድርሰውናል፡፡
# ማስታወቂያ

በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን  በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-

በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ  መሆኑን እንገልጻለን።

በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ)  ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን  በቀጣዩ ሊንክ 

https://student.ethernet.edu.et

በኩል ብቻ እንድትልኩ እየገለጽን ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

                        
ትምህርት ሚኒስቴር!
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ባደረገው የድንገተኛ ጉብኝት ፍተሻ የስነ-ስርዓት ጥሰት ፈጽመው በተገኙ #ሐራምቤ ዩንቨርስቲ (ሲኤምሲ ካምፓስ)፤ #ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ (አራት ኪሎ ካምፓስ) እና #ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ (አዲስ አበባ ካምፓስ) ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን ይፋ አደረጓል፡፡

ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት

፨ሐራምቤ ዩንቨርሲቲ በሲኤምሲ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በዲግሪ መርሀ ግብር በቢዝነስ ማኔጅመንት የትምህርት መስክ ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ፤ ፈቃድ ባላገኘባቸው ማስተርስ ኢን ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ማስተርስ ኢን አካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ የትምህርት መስኮች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር አድርጎ ማስታወቁ እና የመጀመሪያ ዲግሪ መግቢያ መስፈርት ያላሟሉ ተማሪዎችን መዝግቦ ማስተማሩ በመረጋገጡ...

፨ያርድስቲክ ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአራት ኪሎ ካምፓሱ ከባለስልጣኑ ፈቃድ ሳያገኝ በሁለተኛ ዲግሪ መርሀ ግብር በማስተርስ ኦፍ ፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሜንስትሬሽን የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን መዝግቦ በማስተማር ላይ መሆኑ በመረጋገጡ...

፨ኒውጀነሬሽን ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ካምፓሱ ከተፈቀደለት የተማሪዎች ቁጥር በላይ ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ በማስተርስ ኦፍ በቢዝነስ አድሜንስትሬሽን እና ግሎባል ስተዲስና ኢንተርናሽናል ሪሌሽን እያስተማረ መሆኑ በባለሥልጣኑ በመረጋገጡ...

⭕️በሶስቱ ተቋማት ላይ የተላለፈውን የማስተካከያ እርምጃ ከምስሉ ያንብቡ።
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የግብር/ የታክስ ህግ ዓላማ
የታክስ ሥርዓትና የታክስ ህግ ዓላማ በዋናነት ለልማትና ለአገራዊ በጀት የሚያስፈልገውን ወጪ በታክስ ገቢ መሸፈን ቢሆንም ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎችም አሉት፡፡ ከጠቀሜታዎቹ ውስጥ፡-
 የፊሲካል ፖሊሲው መሣሪያ በመሆን የመንግስትን ሁለንተናዊ አቅም መገንባት፣
 ኢንቨስትመንትን በመሳብ
- ኢኮኖሚውን ማረጋጋት፣
- የሥራ ዕድል መፍጠር፣
- የሥራ ተነሳሽነትን ማሳደግ፣
- ልማትንና ዕድገትን ማፋጠን፡፡
 የሃብት ክፍፍልን ፍትሃዊ ማድረግ፣
 ቁጠባን ማበረታታት ከጠቀሜታዎቹ ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።
Urgent
🔷Vacancy🔷
                                              
1. Driver
2. Junior Cashier and secretary 
3. Guday Asfetsami (ጉዳይ አስፈፃሚ)

          👉 How to Apply 👈
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
consultantentrust@gmail.com
Deadline
February, 10/2023

Share for your friends
     👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
ያለአግባብ የታሰሩ ሰዎች ካሳ የማግኘት መብት አላቸው???         
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ስው የሚታሰረው በምክንያታዊ ጥርጣሬ ላይ ተመስርቶ ለእስሩ አሳማኝ የሆነ ማስረጃ ሲኖር ነው። ይህ ግን ሁልጊዜ እውነት ላይሆን ይችላል ። ምክንያቱ ደግሞ ምክንያታዊ ጥርጣሬ ያጭራል ተብሎ ምርመራ ተደርጎ የሚገኘው ውጤት  ግለሰቡን ለእስር የዳረገው ተግባር ወይም/እና ማስረጃ በፓሊስ፣በአቃቤ ህግ ወይም በፍርድ ቤት ሚዛን ሲታይ ቀሎ ሊገኝ ይችላል። አንዳንዴም በነዚህ የህግ አካላት አይን ሞልቶ ጥፉተኛ አስብሎ በእስራት ያስቀጣ ተግባር እስሩ እየተተገበረ እያለ ወይም እስሩ ከተገባደደና ካለቀም  በኋላ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ሌላ አካልና ሌላ ግለሰብ ሆኖ ይገኝና ሰውየው የተወሰነበት ፣ የታሰረው ሲልም መቀጮ የከፈለው ያለጥፉቱ ፣ያለስህተቱ ፣ ያለአግባብ ይሆናል። በሃገራችንም ብዙ መሰል ጉዳዮችን መዘርዘር ይቻላል።

ለመሆኑ እንዲህ አይነት ያለአግባብ የሆነ እስር ሲያጋጥም አለ አግባብ ነውና የታሰርኩት ከህግ ውጪ  ስለሆነ  ለባከነብኝ ጊዜ ፣ ገንዘብ፣ ለደረሰብኝ የሞራል ጉዳት ወዘተ መንግሥት ካሳ ሊከፍለኝ ይገባል ቢል ይህን ሊያስፈፅምበት የሚችል ህግ ይኖር ይሆን? መልሱ አዎም አይም ነው።

ህግ የለንም የሚለው መከራከሪያ ሃሳብ ግልፅ በሆነ መልኩ የወጣ ሃገራዊ ህግ የለም። ይሄም በዝርዝር ሊቀመጡ የሚችሉ የሃገራችንን ሁኔታ ያገናዘበ ነው፣ አለም አቀፍ ህግ ቢኖርም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፣ ተተርጉሞ፣ በአዋጅነት እስካልፀደቀና እስካልታተመ ድረስ ሊተገበር(ሩ) አይገባም የሚል መከራከሪያን ያነሳሉ። [2]

በተቃራኒው ወገን የቆሙ ደግሞ ኢትዮጵያ በህገ መንግስቷ አንቀፅ 9(4) እና 13(2) መሰረት አለም አቀፍ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነት ህጎችን ተቀብላ እስካፀደቀች ድረስ የሃገሪቱ ህግ አንድ አካል ሆኖ ተግባር ላይ ሊውል ይገባል የሚል መከራከሪያን አስቀድመው ይህ ደግሞ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና በየደረጃው ያሉ ፍርድ ቤቶች ሳይቀር በተግባር ያደረጉት እያደረጉትም ያለ ተግባር ነው በሚል የሚከተሉትን የሠበር ውሳኔዎች በምሳሌነት ይጠቅሳሉ [3] ለጥቀውም ከላይ ያለው  መከራከሪያ በተግባር በፍርድ ቤቶችበተዘዋዋሪ ትርጉም ስለተሰጠበት አለም አቀፍ ህግን ጠቅሶ / በተለይ የሰብዓዊ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳኖችን/ ጠቅሶ መወሰን ሊነቀፍ እሚገባ አይደለም ይላሉ።
በካሳ ጉዳዩ ላይ ብዙ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ህጎች በአለማችን ላይ ተቀባይነት አግኝተው እየተተገበሩ ይገኛል። እንደ አሜሪካ ያሉ ሃገራት ያለአግባብ የታሰረ ሰው በትንሹ ለታሰረበት እያንዳንዱ  አመት 50,000 ዶላር እስሩ ያለአግባብ መሆኑን ላስረዳ ሰው እንደሚከፍሉ በተለያዩ ክልሎቻቸው ባሉ ህጎች ደንግገዋል።
በመሰረታዊነት ለአላግባብ እስር ካስ መከፈል እንደሚገባ የደነገገው አለም አቀፉ የሲቪልና የፓለቲካ መብቶች አለም አቀፍቃል ኪዳን [ 1 ]  ሲሆን ከላይ የተጠቀሱና ሌሎችም የሰበር ሰሚው ውሳኔዎች ህጉን በቀጥታ እየጠቀሱ ውሳኔ በመስጠት ተግባር ላይ ዕንዳዋሉት የታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በማስረጃነት ማንሳ ት  ይቻላል።
ሲጠቃለል በሃገራችን ብዙ ህገ ወጥ የሆኑ እስሮች እና አፈናዎች  በስህተት፣ በቸልተኝነትም ይሁን ሆነ ተብሎ ይፈፀማሉ። እነዚህ እስሮች ኢ-ሰብአዊ፣ ኢ-ህገመንግስታዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ድርጊት ናቸው። እነዚህን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፉት ያላግባብ የታሰሩና የታፈኑ ሰዎች ካሳ የሚጠይቁበትን ህግ በህጎቻችን ላይ በግልፅ ቢካተት ወይም በሁለተኝነት በተነሳው መከራከሪያ መሰረት ጠበቆች እና የህግ ባለሙያዎች አለም አቀፉ ድንጋጌው ተግባር ላይ ሊውል የሚችልበት የህግ መከራከሪያ  ሰፊ ስለሆነ በክርክር ጭብጥ አርጎ መነሳትና መሄድ ያለባቸውን ያክል ሄደው አስገዳጅ ውሳኔ እንዲሰጥ ቢያደርጉ መልካም  ነው።

ማጣቀሻ

[1]የሲቪልና የፓለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳን
አንቀፅ 14(6) "በአንድ  ሰው   ላይ  ተላልፎ   የነበረው  የመጨረሻ  ፍርድ በማያሻማ  አኳኋን  ኢፍትሃዊ  የነበረ  ስለመሆኑ  አዲስ በተገኘ  ማስረጃ አማካኝነት  የተረጋገጠ  የሆነ  እንደሆነ እና  በዚህም   ምክንያት  ይህ  ሰው   ምህረት  ካገኘ  አልያም  ደግሞ  ተላልፎበት  የነበረው  ውሳኔ  የተሻረ  እንደሆነ   በ እንዲህ  ዓይነቱ   ፍርድ  ምክንያትነት ደርሶበት  ለነበረው  ቅጣት  በህጉ   መሰረት  ሊካስ ይገባል፡፡  "
[2]የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ መቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 3/1987
አንቀፅ 3(2)" ማናቸውም የፌዴራል መንግሥት ሕግ የሚወጣው በፌዴራሉ ነጋሪት ጋዜጣ ይሆናል።"
አንቀፅ 3(3) "ማናቸውም የፌዴራል ወይም የክልል ህግ አውጪ፣ አስፈጻሚ እና ተርጓሚ እንዲሁም ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው  አካል  በፌዴራል  ነጋሪት  ጋዜጣ  የሚወጣ  ሕግን  የመቀበል  ግዴታ ይኖርበታል።"
[3]   ሠ/መ/ቁ . 95921፣ ሠ/መ/ቁ.100860  / ሁለቱም ቅፅ 18 ላይ ታትመው የወጡ/ አለም አቀፉየሲቪልና የፓለቲካ መብቶች አለም አቀፍቃል ኪዳን  ጠቅሰው ውሳኔ ሰጥተዋል።
//// አለም አቀፍ ህጉን ከሌሎችም መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ቃል ኪዳኖች ጋር  ከስር  ያገኛሉ///👇👇👇
ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ  #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ለዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
..................................................
የካቲት 1/2015 ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በሁሉም የትምህርት መስኮች እና መርሀግብሮች በግልና በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የመውጫ ፈተና በመጪው ሀምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሰሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል፡፡

ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርስቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ዶክተር ሳሙኤል በአሁኑ ወቅትም የፈተና ንድፈ ማሳያና / Blueprint / የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡

በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርስቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱም ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንቶች ተገኝተዋል፡
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ #አለ_Share #lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አጠቃቀም

ታክስ ከፋዮችን ለመለየት እንዲቻል እንዲሁም ለታክስ ሕጐች ዓላማ ሲባል ለታክስ ከፋይነት ለተመዘገበ ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር በሚል የሚታወቅ ቁጥር ይሰጣል:: ታክስ ከፋዩም የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን የታክስ ሕጎች በሚያዙት መሠረት መጠቀም አለበት፡፡
.
ከዚህ አንጻር የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አጠቃቀምን አስመልክቶ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የህግ ድንጋጌዎች ተቀምጠዋል፡፡

 የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጠው ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን በማንኛውም የታክስ ማስታወቂያ፣ ማስታወቂያ ወይም ለታክስ ሕግ ዓላማ ሲባል በሚቀርብ ወይም ጥቅም ላይ በሚውል ሰነድ ወይም በታክስ ሕግ መሠረት በሚዘጋጅ ሰነድ ላይ መግለጽ ይኖርበታል፣ እንዲሁም ታክስ ከፋዩ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት ግዴታ ባለበት ሰው ክፍያዎች በሚፈጽምለት ጊዜ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን መስጠት አለበት፡፡
.
 የንግድ ሥራ ለመሥራት ፈቃድ ይሰጠው ዘንድ ማመልከቻ የሚያቀርብ ታክስ ከፋይ ፈቃድ ለሚሰጠው ባለሥልጣን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን መስጠት አለበት፡፡

 ታክስ ከፋዩ ፈቃዱን በሚያድስበት ጊዜ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚጠበቅበት የመጀመሪያው የፈቃድ ማመልከቻ ከቀረበ ወዲህ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩ የተቀየረ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

 የንግድ ወይም የሥራ ፈቃድ የሚሰጥ የመንግሥት አካል ወይም ተቋም ታክስ ከፋዩ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን ሳያቀርብ ፈቃድ መስጠት አይችልም፡፡

 የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ለተሰጠው ሰው ብቻ የሚያገለግል ስለሆነ በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም፡፡
.
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et

https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ  #lawsocieties
አርደህ እንደምትበላት እያወክ በጀርባህ አዝለሀት ትሄዳለህ። የሆድን በጀርባ። ዋው......!
#አለ_ህግ #ale_hig #lawsocieties
የፌደራል_ፍርድ_ቤቶች_የሠራተኞች_ደንብ_አጭር_ማብራሪያ.pdf
122 KB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሠራተኞች ረቂቅ ደንብና ማብራሪያ።
የፌደራል_ፍርድ_ቤቶች_የሠራተኞች_ደንብ.pdf
436.8 KB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች የሠራተኞች ረቂቅ ደንብና ማብራሪያ።