አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
4. የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽንን በተመለከተ

የኤለክትሮኒክ መልዕክቶች በማንኛውም የሕግ ሂደቶች ተቀባይነት እንዳላቸው እናበማንኛውም የህግ ሂደት ተቀባይነት ኖሯቸው እንደ ማስረጃ እንደሚያገለግሉ የኤሌክተሮኒክ ትራንዛክሽንን ለመደንገግ በወጣ አዋጅ ቁጥር 1205/2012 አንቀጽ 13 ሥር የተደነገገ ሲሆን
ሀ. የኤለክተሮኒክ መልክቱ የመነጨበት፣ የተከማቸበት ወይም የተሰራጨበት አግባብ አስተማማኝነት፣
ለ. የኤለክተሮኒክ መልክቱ ይዘት ሳይቀየር የቆየበት መንገድ አስተማማኝነት፣
ሐ. የመልዕክቱ አመንጪ ተለይቶ የታወቀበት መንገድ፣ እና
መ. ፍርድ ቤት አግባብነት አላቸው ብሎ የሚያስቀምጣቸው ሌሎች እውነታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የአሌክትሮኒክ መልክቱ የማስረጃ ክብደት እንደሚመዘን ይደነግጋል፡፡

5. የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁጥር 958/2008 ስለ ማስረጃና የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች

የኮምፒዩተር ወንጀል የራሱ የሆነ ባህሪ ያለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የወንጀል ሕግ ጠቅላላ ክፍል እንዲሁምየማስረጃ አሰባሰብና የፍርድ ሂደትንበተመለከተ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑበት ነው፡፡የማስረዳት ሸክምን በተመለከተ አዋጁ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ የተቀመጠውን ፍሬ ነገር ማስረዳት እና በህግ በተቀመጠው መመዘኛ መሰረት የማረጋገጥ ሀላፊነት የተጣለበት ሲሆን አቃቤ ህግ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮችን ካስረዳ እና ፍርድ ቤት የማስረዳት ሀላፊነቱን ወደ ተከሳሽ ማዞር አስፈላጊ መሆኑን ካመነ የማስረዳት ሸክሙ ወደ ተከሳሽ ሊዞር እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል፡፡

የማስረጃ ተቀባይትን በተመለከተም አዋጁ
 በበአዋጁ መሰረት የተያዘን የኮምፒዩተር ዳታ የሚመለከት ሰነድ፣ የሰነዱ የተረጋገጠ ግልባጭ ወይም የተረጋገጠ የኤሌክትሮኒክስ መዝገብ ወይም ህትመት በፍርድ ቤት ለቀረበ የክስ ጉዳይ በማስረጃነት መቅረብ የሚችሉ እና ተቀባይነት ያላቸው እንደሆኑ
 በወንጀል ሥነ ሥርአት ህጉ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት የሚቀርቡ ማስረጃዎች እንደተጠበቁ ሆነው በአዋጁ መሰረት የሚሰበሰቡ ማስረጃዎች እንዲሁም አግባብነት ባለው የውጪ ሀገር ህግ አስከባሪ አካል የኢትዮጵያ ህግ በሚፈቅደው መሰረት የተገኙ የዲጂታል ወይም ኤልክትሮኒክ ማስረጃዎች የኮምፒውተር ወንጀሎችን ጉዳይ ለማስረዳት ተቀባነት ያላቸው ማስረጃዎች እንደሆኑ ደንግጓል፡፡

ሆኖም በሌሎፍ ህጎች የሰነድ ማስረጃ ስለሚረጋገጥበት ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖእነዚህን ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤት በማስረጃነት የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው የማስረጃዎቹን ተአማኒነት እና ትክክለኛነት የማስረዳት ኃላፊነት በአዋጁ ተጥሎበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ዋና የኤሌክትሮኒክስ ሰነድ (Original Electronic Document) ስለሚገኝበት ሁኔታ እና ይህን ለማግኘት የሚያስችለው የኤሌክትሮኒክስ መዝገብ ሥርአትን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ባልተቻለበት ጊዜ ሊቀርቡ ስለሚችሉ ማስረጃዎች በአንቀፅ 35 በዝርዝር አስቀምጧል፡፡

6. ቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል
የቴለኮም ማጭበርበር ወንጀልን በተመለከተ የወጣው አዋጅ ቁጥር 761/2004 አንቀጽ 15 ላይ ተቀባይነት ስለሚኖራቸው ማስረጃዎች ደንግጓል፡፡ ይኸውም በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሠረት የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ
 ዲጅታል ወይም የኤሌክትሮኒስ ማስረጃዎች፣
 በጠለፋወይም በክትትል የተገኙ ማስረጃዎች፣ እና
 በዉጭ ሀገር የሕግ አስከባሪ አካላት በተደረገ ጠለፋ የተገኙ ማስረጃዎችበቴሌኮም ማጭበርበር ጉዳዮች በፍርድ ቤት በማስረጃነት ተቀባይነት አላቸው፡፡

በአጠቃላይ በሀገራችን የማስረጃ ድንጋጌዎች በተለያዩ ህጎች ውስጥ ተሰባጥረው የሚገኙ ሲሆንለማሳያነትም በተመረጡ ህጎች የተካተቱ የማስረጃ ድንጋጌዎችን በሁለት ክፍል ተመልክተናል፡፡ ከላይ እንደተገለፀው የማስረጃ ድንጋጌዎችበፍርድ ቤት በሚደረጉ ክርክሮች የሚቀርቡ እና ተቀባይነት የሚኖራቸውን ማስረጃዎች የሚደነግጉ እንደመሆኑ በክርክር ሂደት ወሳኝ ሚና ያላቸው በመሆኑ ህብረሰተቡ ህጎችን የማንበብ ልማዱን ቢያሳድግ መልካም ነው፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት ተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
Forwarded from አለሕግ🔵AleHig
አለሕግAleHig ️
Photo
*ሴቾች ክብር ይገባቸዋል*🙏‼️ ጥቃታቸውን አንወድም‼️🙏
https://t.me/lawsocieties
ሼር ይደረጋል‼️🙏
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉የስም ማጥፋት ተጠያቂነት

የስም ማጥፋት ተግባር በመገናኛ ብዙሀን ሲፈጸም ከፍትሐብሔር ሀላፉነት በስተቀር በወንጀል አያስጠይቅም፡፡

ነገርግን ምንም ዓይነት የሕዝብ ጥቅም በሌለበት በግለሰቦች ላይ ከሚፈጸመው በስተቀር፣የመጉዳት ሀሳብ ከሌለና የንግግሩ ይዘት እውነተኛ የሆነ እንደሆነ ፣

የንግግሩን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ተቀባይነት ያላቸውን አካሄዶችና መንገዶች ሁሉ ተጠቅሞ ያገኘው መረጃ ትክክለኛ እንደሆነ በቅንነት በማመን ያደረገው ንግግር ከሆነ ወይም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የተደረገ ንግግር ከሆነ በስም ማጥፋት ተጠያቂነት አያስከትልም።

👉 የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ፣
አዋጅ ቁጥር 1238/2021 ፤ አንቀጽ 84
ጥሩ ሥነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ ማን ነው?
• የትራፊክ ሕግና ደንብ ሙሉ በሙሉ የሚያከብር፣

እግረኛ በሚበዛባቸው ሆስፒታሎችና ት/ቤቶች አካባቢ በዝግታ የሚያሽከርከር፣

• እይታን በሚጋርዱና መታጠፊያ ቦታዎች ከመጠን ያለፈ

ፍጥነት በቂ ጥንቃቄ የሚያደርግ፣ • ሁል ጊዜ ለእግረኛ ቅድሚያ የሚሰጥ፣

ትኩረቱን ሁል ጊዜ በመንገዱ ላይ ብቻ የሚያደርግ፣

አልኮል ጠጥቶና ጫት እየተጠቀመ የማያሽከረክር፣

በቁጣ ስሜትና በብስጭት ወቅት የማያሽከረክር፣

ትዕግስተኛ የሆነ፣ ራሱን ከእልክ ያራቀ፣ በቂ እረፍት ወስዶ የሚያሽከረክር፣

የቀኝ መስመር ረድፍን ጠብቆ የሚያሽከረክር ወዘተ፣

“አስተውለው በማሽከርከር የነገ ህልምዎን እውን ያድርጉ!!”
https://t.me/lawsocieties
የወንጀል እና የፍትሐብሔር ህግ ልዩነት
ህጎች የሚያካትቱትን ጉዳይ፣ የሚያስከትሉትን የኃላፊነት ዓይነት፣ የተሳታፊ አካላትን (parties) እና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ጉዳዮች ከግንዛቤ በማስገባት የወንጀል እና የፍትሐብሔር ተብለው ይከፈላሉ፡፡


የወንጀል ሕግ የህብረተሰብ ሕግ (public law) አካል ሲሆን የፍትሐብሔር ሕግ ደግሞ የግል ሕግ (private law) አካል ነው፡፡ ከሕግ ግንዛቤ እጥረት የተነሳ ማህበረሰቡ በሁለቱ የሕግ ዓይነቶች መካከል ያለውን ልዩነት ባለመገንዘብ ግር ሲሰኝ ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ ሰዎች ክርክርና ሙግት ሲገጥማቸው ጉዳዩ ወንጀል ይሁን ፍትሐብሔር ባለመለየት የወንጀል ጉዳይን በፍትሐብሔር ክርክር ለመፍታት የፍትሐብሔር ጉዳይን በወንጀል እንዲጣራ ጥያቄ ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በወንጀል እና በፍትሐብሔር ህግ መካከል ያሉትን ዋና ዋና የልዩነት ነጥቦች እንመለከታለን፡፡

የወንጀል ሕግ አና የፍትሐብሔር ሕግ ምንነት

ስለ ወንጀል ሕግ እና ፍትሐብሔር ሕግ ከማየታችን በፊት ህግ ምንድነው የሚለውን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ሕግ ማለት በአጭሩ ዜጎች ማድረግ ያለባቸው ወይም ማድረግ የሌለባቸውን ድርጊቶች የሚዘረዝር፣ በማድረግ ወይም ባለማድረግ ህጎችን መተላለፍ የሚያስከትለውን ቅጣት ወይም ውጤት የሚይዝ ገዢ ደንብ ነው፡፡

የወንጀል ሕግ በአጠቃላይ የሀገርን እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የሚወጣ ሆኖ እንደ ወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶች የሚዘረዝር እና ተፈጽመው ሲገኙ የሚያስከትሉትን ቅጣቶች የሚደነግግ ሕግ ነው፡፡
👇👇👇👇👇👇የቀጠለ
የወንጀል ሕግ በአጠቃላይ የሀገርን እና የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የሚወጣ ሆኖ እንደ ወንጀል የሚቆጠሩ ድርጊቶች የሚዘረዝር እና ተፈጽመው ሲገኙ የሚያስከትሉትን ቅጣቶች የሚደነግግ ሕግ ነው፡፡ በድርጊቶቹ መፈጸም ቀጥተኛ ተጎጂዉ አንድ ግለሰብ ቢሆንም እንኳን ጉዳቱ በማህበረሰብ ላይ እንደደረሰ ተደርጎ የሚቆጠር በመሆኑ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች እንዲቀጡ፣ ሌሎች ደግሞ ወንጀል እንዳይፈጽሙ ለማድረግ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች እንዲኖረው ተደረጎ የሚወጣ ሕግ ነው፡፡

የፍትሐብሔር ሕግ ግለሰባዊ ግንኙነቶችን እና መብቶችን እንዲሁም ግዴታዎችን (private relationships, rights and obligations) የሚደነግግና የሚገዛ ሲሆን በዋናነት የንብረት፣ የውል፣ የቤተሰብ፣ የውርስ ህግን እና ከውል ዉጭ ኃላፊነትን የሚመለከቱ ህጎችን አካቶ የያዘ የሕግ ዘርፍ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች ወይም ግንኙነቶች በአግባቡ እንዲከበሩ እንዲሁም ባለመከበራቸው ምክንያት ጉዳት የደረሰበት አካል ሲኖር መብቱን የሚጠይቅበትን ሥነ-ሥርዓት የሚደነግገው ሕግም በዚሁ የሕግ ዘርፍ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ በፍትሐብሔር ሕግ መሰረት የሚፈጠሩ መብቶች ሲጣሱ ወይም ግዴታዎች ሳይከበሩ ሲቀሩ የሚከሰቱ ችግሮች እንደአጠቃላይ የማህበረሰብ ጉዳት የሚታዩ ሳይሆኑ በቀጥታ ጉዳቱ የደረሰበት አካል ጉዳት ናቸው፡፡

የወንጀል እና የፍትሐብሔር ህግ መሰረታዊ የልዩነት ነጥቦች

በፍትሐብሔር ሕግ የተደነገገ መብት በመጣሱ ምክንያት በሚመለከተው አካል ፊት ቀርቦ መብቱን መጠየቅ የሚችለው መብቴ ተጥሷል የሚለው ሰው ሲሆን የወንጀል ድርጊት በተፈጸመ ጊዜ ግን ኃላፊነት ወስዶ አጥፊዎች እንዲቀጡ የሚያደርገው ዐቃቤ ህግ ነው፡፡ በወንጀል የሚኖር ተጠያቂነት በመርህ ደረጃ በማድረግ ወይም ባለማድረግ በቀጥታ ተሳታፊ በሚሆን ሰው ላይ ሲሆን በፍትሐብሔር ሕግ ግን ከጥፋት ውጪ (strict liability) በሆነ መንገድ ወይም በሌሎች ጥፋት (vicarious liability) ተጠያቂነት ጥፋት በሌለበት ሰው ላይ ሊኖር ይችላል፡፡

ወንጀልን መሰረት አድርጎ የሚፈጠር የግለሰቦች ተቃርኖ በግለሰቦቹ በግል አቤቱታ አቅራቢነት የሚያስከስሱ ቀላል ወንጀሎች ካልሆኑ በስተቀር እርቅ ወይም ስምምነት ክሱን ቀሪ ሊያደርግ አይችልም፡፡ እርቅ ቢደረግም እንኳን ለአጥፊው እንደ ቅጣት ማቅለያ ከሚያዝ በስተቀር ከተጠያቂነት የሚያድን አይሆንም፡፡ ፍትሐብሔራዊ ጉዳይን መሰረት አድርጎ በግለሰቦች መካከል የሚፈጠር አለመግባባት ግን በማናቸውም ጊዜ በተበዳዩ ፍላጎት አልያም በሁለቱ ወገኖች እርቅ (ስምምነት) ክሱ ቀሪ ሊሆን ይችላል፡፡

ጥፋትን ለማስረዳት ወይም ለማረጋገጥ ተግባራዊ ከሚደረገው የማስረጃ ምዘና መለኪያ አንጻርም ዘርፎቹ ይለያያሉ፡፡ የወንጀል ሕግ ሲጣስ ወንጀል ፈጻሚውን ጥፋተኛ ለማድረግ ወንጀል የተባለውን ድርጊት የፈጸመ ስለመሆኑ ዐቃቤ ህግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ (beyond reasonable doubt) በሆነ አግባብ የማስረዳት ግዴታ ሲኖርበት በፍትሐብሔር ረገድ ኃላፊነትን ለማቋቋም ከሳሽ ተከሳሽ ከሚያቀርበው ማስረጃ በተሻለ መልኩ አሳማኝ የሆነ ማስረጃ (preponderance of evidence) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የፍትሐ ብሔር ህግ ዋና ዓላማ ተጎጂን በተቻለ አቅም እንዲካስ ማድረግ ሲሆን የወንጀል ሕግ ደግሞ የማህበረሰቡን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው፡፡ የፍትሐብሔር ሕግ በአብዛኛው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ወይም የጉዳት አድራሽን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚነካ ውሳኔን የሚያስከትል ሲሆን ይህም ያደረሰውን ጉዳት ወደነበረበት መመለስ ወይም መካስ ሊሆን ይችላል፡፡ የወንጀል ሕግ በአንጻሩ ጥፋተኞችን የሚያስተምርና ሌሎችን ወንጀል እንዳይፈጽሙ የሚያስጠነቅቅ ቅጣቶችን መጣል ላይ ያተኮረ እና እንደ መቀጮ፣ እስራት አለፍ ሲልም የሞት ቅጣት የሚያስከትል ነው፡፡
የውሳኔውም አፈጻጸም ሲታይ በወንጀል ክርክር በፍርድ ቤት የሚሰጥ ውሳኔን ተከታትሎ የሚያስፈጽመው መንግስት ሲሆን በፍትሐብሔር ክርክር የሚሰጥ ውሳኔን ተከታትሎ የማስፈጸሙ ኃላፊነት ውሳኔ የተወሰነለት ሰው ወይም የፍርድ ባለመብት ነው፡፡

ማጠቃለያ

የወንጀል እና የፍትሐብሔር ህግ ያላቸው መሰረታዊ ልዩነት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እነዚህን ልዩነቶች ማወቅ ለሚገጥሙ ችግሮች የምንፈልገውን መፍትሄ የሚወስኑ በመሆኑ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ጠንቅቆ መረዳት ያስፈልጋል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
የወንጀል ክስ የተመሰረተበት ተከሳሽ ባመነው ክስ ላይ ፍርድ ቤት ምስክሮችን የሚሰማበት
የህግ አግባብ

የወንጀል ክስ የተመሰረተበት ተከሳሽ ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ ሲሰማ የእምነት ክህደት ቃሉን የሚጠየቅ ሲሆን ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ ሊያምን ወይም ሊክድ ይችላል፡፡ ተከሳሽ ፍርድ ቤት ቀርቦ ድርጊቱን ስለመፈፀም አለመፈፀሙ በግልፅ ችሎት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ በክሱ የተዘረዘረውን ስለመስራቱ ሙሉ በሙሉ ያመነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የተከሣሹን ቃል በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 134(1) መሰረት ቃሉን በመዝገብ አስፍሮ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደሚሰጥ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በመሰረታዊነት በወንጀል የተከሰሰ ሰው የክሱን ድርጊት ሙሉ በሙሉ አምኖ የእምነት ቃሉን ከሰጠ ማስረጃ መሰማት ሳያስፈልግ ጥፋተኛ ይሆናል፡፡ ተከሣሽ ክሱ በችሎት ተነቦለት አምኗል የሚባለው ሙሉ በሙሉ የወንጀሉን የሀሳብ ክፍል፣ የድርጊቱን አፈፃፀም እና የተከሰሰበትን የወንጀል ድንጋጌ እንደ ክሱ አቀራረብ ወይም የክሱን ዝርዝር ፍሬ ቃል ያለምንም ተቃውሞ (ተአቅቦ ሳይኖር) አምኖ የእምነት ቃሉን የሰጠ እንደሆነ ነው፡፡ ሆኖም ተከሳሽ ቢያምንም ፍርድ ቤት ማስረጃ እንዲሰማ የሚያዝበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል በሥነ ሥርአት ህጉ ተደንግጓል፡፡

ይኸውም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ህግ አንቀፅ 134(2) መሰረት ፍርድ ቤቱ ማስረጃ መሰማቱን *አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው* በዐቃቤ ህግ በኩል ለክሱ የሚደግፍ ማስረጃ እንዲያቀርብ ለማዘዝ እና ተከሳሹም መከላከያ ማስረጃ ካለው እንዲያቀርብ ሊያዥ የሚችል ሲሆን፣
👇👇👇👇

ተከሳሽ አምኖ የእምነት ቃል ከሰጠ በኋላ ፍርድ ቤቱ ክሱን መስማት በሚቀጥልበት ጊዜ ጥፋተኛ አይደለሁም የማለት ቃል መመዝገብ የሚገባው ሆኖ ካገኘው በክህደት ተመዝግቦ ማስረጃ እንደሚሰማ በሥነ ሥርአት ህጉ አንቀፅ 135 ተደንግጓል፡፡

በንቃተ ህግ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/lawsocieties
ጥያቄ አንድ
አለ ህግ እየሰራ ባለው ስራ ደስተኛ ከሆኑ ለምን ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራብ (Subscribe) አታደርጉልንም።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@Lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አሁኑኑ ሰብስክራብ (Subscribe) አድርጉ እና ሼር ለወዳጅ ለዘመድ🙏
"ከሥርዓተ-ፆታዊ ጥቃት አንፃር ባሉት ህጎች ላይ ያሉ ክፍተቶች"

" Gaps on existing laws from Gender Based Violence (GBV) perspective"

Key Note Speaker; LAWYER Hanna Hailemelekot
HEAD of LEGAL AID: 👈
ETHIOPIAN WOMEN’S LAWYER ASSOCIATION.
HANNA HAILEMELEKOT LAW OFFICE
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

እሁድ ምሽት 2:30 ቀጥታ ስርጭት

🔘 Live on Telegram 👈👈
https://t.me/lawsocieties
#በአለ_ህግ ቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን።

ሼር በማድረግ ላልሰማ ያሰሙ ወደ ወይይቱ ይጋብዙ👆👆👆
https://t.me/lawsocieties
የእሁድ #ችሎት ከምሽቱ 2:30 የፍትህ ክርክር የሴቶች በምስክርነት ተሳትፎ ተበይኗል🙏👁‍🗨
#የእለቱ_ችሎት
#በጠበቃ እና ህግ አማካሪ ወ/ሮ ሀና ሀይለመለኮት
ከኢትዮጵያ ሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር የህግ ድጋፍ ኃላፊ፡ 👈 እንዲሁም ጠበቃ እና ህግ አማካሪ ይመራል።
#የክርክሩ_ጭብጥ
"ከሥርዓተ-ፆታዊ ጥቃት አንፃር ባሉት ህጎች ላይ ያሉ ክፍተቶች" "Gaps on existing laws from Gender Based Violence (GBV) perspective"
#ውሳኔ
ውይይቱ ቢያመልጥዎት ከመፀፀት አይድኑም
ቀጠሮው እሁድ ማታ በስልክዎት በ #አለ_ህግ የቴሌግራም ቻናል በመዝገብ ስዓት ቁጥር 2:30 የመገኘት መብትዎ የተከበረ ነው።
#ትዕዛዝ
የውይይት መዝገቡ ክፍት ነው። ወደ ቴሌግራም ይመለስ።
https://t.me/lawsocieties
#የሚነበብ #አለ_ህግ ማስታወቂያ አለበት
https://t.me/lawsocieties
ሴትን አከብራለሁ፣ ጥቃቷንም እከላከላለሁ፣ አስፈላጊውን የጤና ምላሽ እሰጣለሁ!
#stopviolenceagainstwomen
ዛሬ እሁድ ምሽት 2:30  በሚኖረን ውይይት የሴቶችን ተሳትፎ በእጅጉ እንጠብቃለን🙏👁‍🗨

እንግዳችን
ጠበቃ እና ህግ አማካሪ ወ/ሮ ሀና ሀይለመለኮት

ከኢትዮጵያ ሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር የህግ ድጋፍ ኃላፊ፡ 👈

https://t.me/lawsocieties
Live stream started