አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Live stream finished (1 hour)
አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf
3.4 MB
'አዲሱ-የንግድ-ሕግ #አለ_ህግ #Ale_Hig @Lawsocieties
Audio
https://t.me/lawsocieties
ለምን ተከሰሱ ለሚለው አላውቅም
የሰው ነፍስ አጥፍተዋል‼️
#Ethiopia Road Authority(ERA)#🚩For Fresh & Exp

▪️25 Open Positions
▪️Qualification: Automotive Technology, Electro Mechanical Engineering, LLB law, Construction Law, Machine Operator, 8th, 10th, 12th & relateds.
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧
    https://bit.ly/3OG5huH

▪️Deadline: December 09/2022
ሀ.👉የራስ ታክስ ስሌት የማሻሻያ ጥያቄ አቀራረብና አፈጻጸም መመሪያ ረቂቅ
ለ.👉የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ መመሪያ ረቂቅ
ሐ.👉የታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት አሰጣጥ መመሪያ ረቂቅ
ረቂቁ የቀደሙትን መመሪያዎች ( መመሪያ 144/2011,142/2011 እና 139/2010 ( መመሪያ 128/2009 እና 55/2003 ጨምሮ ) እንደሚተኩ የሚጠበቅ ሲሆን, በገቢ ሚንስትር ከተፈረሙበት ጀምሮ ተፈፃሚ ናቸው::
_//_................
Hima _ Tax Solutions
Source: HIMA_Xpress_Tax
ተገዶ_የመያዝ_Habeas_corpus_ስረ_ነገር_ስልጣን.pdf
320.7 KB
የሰበር መዝ/ቁ. 230167፣ 230168፣ 230169 /ያልታተሙ/
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1)(ኘ) መሰረት ተገድዶ የመያዝን ህጋዊነት ለማረጋገጥ የሚቀርብን አቤቱታ / Habeas corpus/ ተቀብሎ የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው እንጂ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አይደለም ።
#Click Ethiopian Laws
የማስረጃ ህግ ጽንሰ ሀሳቦች
= ማስረጃ ምንድነዉ ?
ማስረጃ በመመርመር ላይ ያለ ወይም አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገር  ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ፍሬ ነገር ሲብራራ ደግሞ ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ማስረጃ ማለት ሰዎች በስሜት ህዋሳቶቻቸው የሚረዱአቸው/የሚለዩአቸው ኩነቶች ወይም ክስተቶች ስለመኖር/ያለመኖሩ፣ እውነት /ሀሰት ስለመሆኑ ከሚረጋገጥባቸው ነገሮች አንዱ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ሰዎችም ብዙ ግዜ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡት የዚህን ፍሬ  ነገር መኖር አለመኖር ወይም እዉነት/ሀሰት መሆን እንዲረጋገጥላቸዉ ስለሚፈልጉ ነዉ፡፡ የዳኞችም ስራ ይህ ፍሬ ነገር በማስረጃ መረጋገጡን ማጣራት ነዉ፡፡
= የማስረጃ አይነቶች
1. የቃል ማስረጃ፡- በምስክር አንደበት የሚነገር ወይም የሚሰማ
2. የሰነድ ማስረጃ፡-ወረቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኝና የሚነበብ ወይም ሀሳብ የያዘ ነገር
 3. የቁሳዊ/ገላጭ ማስረጃ፡-መጠኑን ፣ዓይነቱን…ወዘተ  የሚያሳይ ነዉ፡፡ዳኞች በራሳቸው የስሜት ህዋሳት ተረድተው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሚቀርብ ዳኞች በአካል የሚመለከቱትን፣ የሚሰሙትን…የሚያመለከት ነው፡፡
4. የሳይንሳዊ ማስረጃ፡-የህክምና ሳይንስን ጨምሮ በሌሎች ሳይንሳዊ ዘዴዎች የተሰበሰበን፣ የተገኘን፣ የታወቀን፣ የተረጋገጠን… ፍሬ ነገር የሚመለከት
5. የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃ፡-በኮምፒውተር፣ በኢንተርኔት ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ውስጥ የሚገኝ የማይጨበጥ/የማይዳሰስ መረጃ ናቸዉ።
= በማስረጃ የሚረጋገጥ እና የማይረጋገጥ ፍሬ ነገር ምን ማለት ነዉ?
የሚረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
1. ከመሰረታዊ  ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ
2. ከማስረጃ ህግ በመነጨ በጭብጥ የሚያዙ ተቀጽላ ወይም ተጓዳኝ  ፍሬ ነገሮች፤
3. በጭብጥ ለተያዙ ፍሬ ነገሮች አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች  ናቸዉ፡፡
እነዚህንም ፍሬ ነገሮች
በፍሬ ነገር ማረጋገጫ ዓይነቶች-
• በፍርድ ቤት ፊት የሚሰጥ የእምነት ቃል (Formal Admission)፣
• የዳኞች ግንዛቤ መዉሰድ/መያዝ (Judicial Notice)፣
• የህግ ግምት (Presumption)፣
• የመኃላ ቃል (Oath)፣
• ማስረጃ (Evidence) ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
= የማይረጋገጡ ፍሬ ነገሮች
- በፍ/ቤት ፊት በተከራካሪ ወገን የታመኑ (Formally Admitted Facts) 
- በዳኞች ግንዛቤ የሚያዝባቸው (Facts which judges take Judicial Notice)
- በህግ ግምት የሚወሰድባቸው (Presumed Facts) ሆነው ከተገኙ ነው፡፡
ስለዚህ እነዚህን ፍሬ ነገሮች ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ሳያስፈልግ በነዚህ በቀረቡት ሁኔታዎች ብቻ ማስረዳት ይቻላል፡፡
= አግባብነት ወይም አስፈላጊነት እና ተቀባይነት ያለዉ ማስረጃ ምንነት
አግባብነት፡- አግባብነት ሲባል አንድ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ከሌላ ፍሬ ነገር ወይም ማስረጃ ጋር ያለውን ተዛመዶ ወይም ትስስር የሚገልጽ ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት በተከራካሪ ወገን የሚቀርብ ማንኛዉም ማስረጃ ሳይሆን በግራቀኝ ለቀረበዉ ክርክር ተገቢነት ኖሮት ሊያስረዳ የሚችል ማለት ነዉ፡፡
ተቀባይነት፡- ሲባል አንድ ማስረጃ ለፍርድ ቤት ሲቀርብ ችሎቱ ይቀበለዋል ወይስ አይቀበለዉም የሚለዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ችሎትም ማስረጃዉን ሊቀበለዉ ወይም ማስረጃዉን ሊተወዉ የሚችለዉ ደስ ስላለዉ ወይም ስላላለዉ ሳይሆን ማስረጃዉ በህጋዊ ሁኔታ መምጣት አለመምጣት ማጣራት እንዳለበት የሚያሳይ ሃሳብ ነዉ፡፡
 = ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ወይም የማን ሸክም ይሆናል?
ማስረጃ ለማቅረብ ማን ይገደዳል ሲባል መጀመሪያ ማስረጃ ማን ማቅረብ አለበት የሚለዉን ሃሳብ የሚያንጸባርቅ ነዉ፡፡ይህም ከሁለቱ  ወገኖች አቤቱታ ይዘትና በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው አንጻር ታይቶ የሚለይ ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ነገር እንዳለ የሚከራከር ወገን ይህ ፍሬ ነገር ስለመኖሩ ቀድሞ የማስረዳት ወይም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ፍሬነገሩም እንዳለ  ተከራካሪዉ ካስረዳ ይህን ማስረጃ በማቅረብ መቀልበስ ወይም መቃወም ያለበት የሌላኛዉ ወገን ድርሻ ይሆናል ማለት ነዉ፡፡ይህም የማስረዳት ሸክም ዞረ ይባላል፡፡
= የማስረጃ አቀራረብ መንገዶች
በመሰረቱ ማስረጃ ለፍርድ ቤት መቅረብ ያለበት ከአቤቱታ ወይም ከመልስ ጋር ነዉ፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ማስረጃዎች በምንፈልገዉ ሰሀት እና በምንጠይቀዉ ሰአት ላናገኛቸዉ እንችላለን፡፡ እነዚህንም ማስረጃዎች በወንጀልም ይሁን በፍትሐብሔር ክርክሮች እንድናቀርብ የምንጠይቅባቸዉ አግባቦች አሉ፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ በማስረጃ ዝርዝራችን ላይ በፍርድ ቤቱ ትእዛዝ እንዲቀርቡ በመጠየቅ፣ክስ ከመሰማቱ በፊት በችሎት በማቅረብ፣ እንዲሁም ክርክሩ እየተካሄደ ባለበት ግዜ በበቂ ምክንያት ሳይቀርቡ የቀሩ ማስረጃዎች ለችሎቱ በማቅረብ ነዉ፡፡
ዉበአለም መስፍን የቦ/ክ/ከ/ፍ/ጽ/ቤት/የህ/ስ/ም/መ ዳይሬክቶሬት ዐ/ህግ 
ምንጭ የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
Characterization
ካልታተሙት የሰበር ውሳኔዎች መካከል በምርጥነት ከሚፈረጁት አንዱ ሰ/መ/ቁ 197753 ነው።

በዚህ መዝገብ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሲሰጡ መርሳት የሌለባቸውን መሰረታዊ ቁምነገር ያስጨብጣል። በችሎቱ የተነሳው ነጥብ ተፈጻሚውን ህግ አስቀድሞ መለየት ይመለከታል።
ተፈጻሚውን ህግ ለመለየት በመጀመሪያ ጉዳዩ በምን የህግ ክፍል ስር እንደሚወድቅ መመደብ characterization ያስፈልጋል። characterization በተለይ በ conflict of laws ክርክሩ በየትኛው አገር ህግ እንደሚገዛ ለመለት ወሳኝ ሂደት / stage of the procedure to resolve a lawsuit that involves foreign law/ ነው። አንድ ፍርድ ቤቱ ለክርክሩ ተፈጻሚነት ያለው ህግ የቻይና አሊያም የፈረንሳይ ወይም የኢትዮጵያ መሆኑን ለመወሰን በቅድሚያ የጉዳዩ ዓይነት የቤተሰብ፡ የውርስ፡ የውል፡ ከውል ውጭ ሀላፊነት ስር እንደሚወድቅ መወሰን አለበት። አንዳንድ ጊዜ በአንዱ የህግ ክፍል ስር እንዲሁ ንዑስ የህግ መደቡን መለየት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ጉዳዩ የቤተሰብ ህግ ስር የሚመደብ ቢሆንም ጋብቻ፡ እንደ ባልና ሚስት፡ ጉዲፈቻ ወዘተ ስር የሚወድቅ መሆኑ ካልተፈረጀ በስተቀር ተፈጻሚውን አገር ህግ ለመለየት የሚያስችሉትን conflict of laws ደንቦች ማወቅ ያስቸግራል።
ሁለተኛው characterization አስፈላጊ የሚሆንበት ሁኔታ በአንድ ክስ ላይ የተነሳ/ሱ/ መቃወሚያ/ዎች/ ለመወሰን ነው። አንድ ፍርድ ቤት የይርጋ ደንቦችን ተፈጻሚ ለማድረግ ጉዳዩ በየትኛው የህግ ክፍል ስር እንደሚወድቅ መወሰን ይኖርበታል። በተለይ በፍ/ህ/ቁ የተመለከተውን የይርጋ ደንብ ተፈጻሚ ለማድረግ ፍርድ ቤቱ በልዩ ህግ ላይ የተመለከተ ይርጋ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርበታል። “በልዩ ህግ ላይ ይርጋ የለም” ለማለት ጉዳዩ በየትኛው ልዩ ህግ ስር እንደሚመደብ መወሰን ይኖርበታል። ይህን ሳያደርግ የፍ/ህ/ቁ 1845 ተፈጻሚ ሊያደርግ አይችልም።
የሰበር ችሎት ከላይ በተጠቀሰው ሰ/መ/ቁ 197753 ላይ ተፈጻሚውን ህግ መለየትን አስመልክቶ የሰጠው ትርጉም የስር ፍርድ ቤቶች አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መመሪያ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል።
ተፈጻሚውን ህግ አስቀድሞ መለየት የአንድ ፍርድ ቤት ዓይነተኛ ተግባርና ግዴታ ስለመሆኑ ችሎቱ በግልጽ አብራርቶ የሰጠው የህግ ትርጉም እንደሚከተለው ይነበባል።
የፍትሐብሔር ጉዳይ የቀረበለት ፍርድ ቤት በቀዳሚነት እንዲያከናውን ከሚጠበቁበት ተግባራት ውስጥ አንዱ እና መሠረታዊዉ ለቀረበለት ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለዉ የህግ ክፍል የመለየት ተግባር (identification of applicable law) ነው፡፡ አስቀድሞ ይህን ማድረግ የቀረበው ክስ የክስ ምክንያት ያለው መሆን አለመሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው መሆን አለመሆኑን እና ሌሎች የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ካሉ አስቀድሞ በመለየት መርምሮ ተገቢዉን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉ ሲሆን፣ ጉዳዩ ወደ ሙሉ የክርክር ሂደትት (full scale trial) የሚገባ ከሆነም በጉዳዩ ላይ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችለዉን ጭብጥ ይዞ ክርክሩን በመምራት ለጉዳዩ ተፈፃሚነት ያለዉን ድንጋጌ በአግባቡ ለይቶ ፍትሐዊ ውሳኔ ለመስጠት ያስችላል።
By Abrham Yohannes
https://t.me/lawsocieties
አለአግባብ መበልጸግ በኢትዮጵያ ህግ
=============================⤵️
ያለአግባብ መበልፀግ ህግ የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጭ ያለ ሃላፊነት ህግ ክፍል በተጨማሪ የፍታብሔር ግንኙነትን የሚገዛ የህግ ክፍል ነው፡፡ ይህ የህግ ክፍል የውል፣ የንብረት እና ከውል ውጪ ያለ ሃላፊነት ህጎች የማይገዙትን የሰው ግንኝኑነት ክፍተት ለመሙላት በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል ህግ ሲሆን ከዚህ ባሻገር ይህ የህግ ክፍል የሰዎችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከመግዛት አኳያ ሰፊ ድርሻ ያለው ነው፡፡
ያለአግባብ መልፀግ ህግ በመሰረታዊነት የሚመነጨው ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መበልፀግ የለበትም ከሚለው መርህ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛው ሰው በሌላ ሰው ጉዳት ወይም ኪሳራ ምክንያት ያለአግባብ የበለፀገ እንደሆነ ጉዳት ወይም ኪሳራ ለደረሰበት ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት ይህ የህግ ክፍል ያስገድዳል፡፡
አጠቃላይ መርሆዎች
የዚህ ህግ ዋንኛ አላማ ሰዎች በገንዘባቸው፣ በንብረታቸው እና በጉልበታቸው ላይ ሚኖራቸውን ህጋዊ መብት መጠበቅ ነው፡፡
ይቀጥላል..... 👇👇👇👇👇👇
አለአግባብ መበልጸግ በኢትዮጵያ ህግ
=============================⤵️የቀጠለ👆👆👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

ስለሆነም የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2162 ስር ማንኛውም ሰው በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም የሌላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ እና ባለሀብቱ ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ጥቅም ባገኘበት ልክ ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡ ይህ ድንጋጌ በስሩ የያዛቸው ነጥቦችን ስንመለከት ያለአግባብ የመበልጸግ ህግ ማንኛውም ሰው (ማለትም የተፈጥሮ ወይም የህግ ሰውነት ያለው ሰው) ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን እንደመጀመሪያ ቅድመ ሁኔታ በዚህ ህግ ተጠያቂ የሚሆን ሰው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም ሊያገኝ ይገባል፡፡ ይህም ማለት ጥቅሙ በንብት ላይ የተቋቋመ (right in rem) ወይም ከሌላ ሰው የሚጠየቅ መብት (right in personam) ወይም የነበረ እዳ የመሰረዝ፣ ግዴታ የመቅረት አይነት ወይም የኪሳራ መቅረት አይነት ጥቅም ሊሆን የሚችል ሲሆን ይህ ጥቅም ያለአግባብ የመበልፀግ የህግ ክፍል ስር ሊያስቀጣ የሚችለው ጥቅሙ የህሊና እርካታ ሊያስገኝ የሚችል ብቻ ሳይሆን በገንዘብ ሊለካ የሚችል ሲሆን ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ የተገኘው የገንዘብ ወይም የንብረት ጥቅም በሌላ ሰው የሚንቀሳቀስ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ወይም ስራ ምክንያት የተገኘ መሆን ያለበት ሲሆን ጥቅሙን ያገኘው ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስለሆንም በዚህ የህግ ክፍል ተጠያቂ የሚያደርግ ክስ የቀረበበት ሰው ጥቅሙን ላገኘበት ማንኛውም ህጋዊ ምክንያት ያቀረበ እንደሆነ ካሳ መክፈል ግዴታ አይኖርበትም፡፡ ሌላው በህጉ የተቀመጠው ቅድመሁኔታ በተከሳሽ ድርጊት ምክንያት ከሳሽ የሚታወቅ ኪሳራ ወይም ድህነት ሊደርስበት ሚገባ ሲሆን የከሳሽ ጥቅም ማጣት (ኪሳራ) እና የተከሳሽ ጥቅም ማግኘት ምክንያት አንድ መሆን አለበት፡፡ ይህም ማለት በደረሰው ኪሳራ እና በተገኘው ጥቅም መካከል የውጤት እና የምክንያት ግንኝነት መኖር አለበት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩ ሁኔታዎች ከተሟሉ በኋላ ሃላፊነትን የሚወስድ ሰው በምን ያህል መጠን ከሳሽን የመካስ ግዴታ አለበት የሚለውን በተመለከተ የተገኘው ጥቅም እና የደረሰው ኪሳራ እኩል በሚሆንበት ግዜ ምንም አይነት ችግር ሊገጥም አይችልም ምክንያቱም ተከሳሽ አለአግባብ የበለፀገበት መጠን እና ከሳሽ ላይ የደረሰው ጉዳት እኩል ስለሆነ በዚሁ ልክ ካሳ እንዲከፍ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ሁኔታዎች ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት ሊያንስ ወይም ሊበልጥ ይችላል፡፡ እንዲህ አይነት ሁኔታ በሚያጋጥምበት ግዜ ምንም እንኳን የደረሰው ጉዳት ከተገኘው ብልፅግና የሚያንስ ቢሆንም ህጉ በግልፅ ተከሳሽ መክፈል ያለበት ኪሳራ ያለአግባብ ባገኘው ብልፅግና መጠን መሆን እንደሚገባው ያስቀምጣል፡፡ በተመሳሳይ ያለአግባብ የተገኘው ብልፅግና ከደረሰው ጉዳት የሚያንስ ከሆነ ወይም ጉዳቱ ከብፅግናው የሚበልጥ በሚሆንበት ግዜ የተከሳሽ ተጠያቂነት መጠን በተገኘው ብልፅግና ልክ ብቻ በመሆኑ ካሳ እንዲከፍል የሚገደደውም በዚሁ መጠን ብቻ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ ያአለአግባብ መበልፀግ በመሰረታዊነት ሶስት ሁኔታዎችን ያካተተ ሲሆን አንድን ሰው በዚህ የህግ ክፍል በመክሰስ ካሳ ለማስከፈል እነዚህ ሶስት ሁኔታዎች በድምር መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የመጀመሪያው ተከሳሽ በገንዘብ ሊለካ የሚችል ጥቅም ያገኘ መሆኑ ሁለተኛው ይህ ጥቅም የተገኘው በከሳሽ ኪሳራ ወይም ጉዳት ምክንያት መሆኑ እንዲሁም ሶስተኛው የተገኘበት መንገድ አለአግባብ ወይም ምንም አይነት ህጋዊ መንገድ/ምክንያት የማይቀርብበት መንገድ መሆኑ ናቸው፡፡
ያለአግባብ የመበልፅ ክሶችን ይበልጥ ለመረዳት ፌዴራል ሰበር ሰሚ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 34406 የሰጠውን ውሳኔ መመልከት ይቻልል፡፡ በዚህ መዝገብ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ሰዎች ባለቤት እና አባት የሆኑት ግለሰብ መኖሪያ ቤታቸውን ያከራዩት ሰው ለተከሳሽ ቤቱን አስረክቦ ይጠፋል፡፡ የቤቱ ህጋዊ ዋራሽ ከሳሾች ቤቱን ለተረከቡት ግለሰብ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቧቸው ቢጠይቋቸውም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲያስረክቡ እና ንብረቱን በያዙበት ወቅት ያለክራይ በመኖር ያገኙትን ያለአግባብ ብልፅግና እንዲከፍሉ ክስ አቅርበዋል፡፡ ተከሳሽም በሰጡት መልስ ቤቱን ያለአግባብ ይዛለች ከተባለ እንኳን ይህን ካወቁ 10 ዓመት በላይ ስለሆነ በይርጋ ይታገዳል፣ የደረሰባቸው የጥቅም ጉዳት ከውል ውጪ እንደመሆኑ የኪራይ ማስከፈል ጥያቄአቸው ሁለት አመት ካለፈው በይርጋ ይታገዳል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን ከመረመሩ በኋላ ተከሳሽ ያለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲመልሱ እና ከንብረቱ ያለአግባብ የተጠቀሙትን መጠን ካሳ እንዲከፍሉ ወስነው ተከሳሽም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለሰበር ሰሚ ችሎቱ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ የሰበር ሰሚ ችሎቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በስር ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት ግለሰቦች ይዞታችን በሃይል ተወስዷል ወይም በይዞታችን ላይ ሁከት ተፈጥሯል በማለት ያቀረቡት ክስ የለም ክሣቸው በኪራይ የተረከቡትን ቤት ተከሳሽ መብት ሣይኖራቸው ገብተው አልወጣም ብለዋልና አለአግባብ የያዙትን ንብረት እንዲለቁ የቀረበ ክስ ስለሆነ 10 ዓመት ቢያልፈው እንኳን በይርጋ አይታገድም፡፡ በጨማሪም ተከሳሽ የቀረበው የካሣ ጥያቄም ቢሆን በይርጋ ቀሪ ይሆናል በሚል ያቀረቡት ክርክር በተመለከተ ማንኛውም በሌላ ሰው የስራ ድካም ወይም በሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሣራ መክፈል እንዳለበት በፍ/ህ/ቁ. 2162 ሥር ተመልክቷል፡፡ በመሆኑም ከሳሽ በቤቱ አላግባብ በበለፀጉበት መጠን ኪሣራ እንዲከፈላቸው መጠየቃቸው ህጉን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የካሣ ጥያቄ ሊቀርብ የሚገባበት የጊዜ ገደብ በተመለከተ ክርክር ቀርቧል፡፡ ያለአግባብ ስለመበልፀግ የሚናገረው ምእራፍ የካሣ ጥያቄ የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ አይናገርም፡፡ ነገር ግን አላግባብ ስለመበልፀግና ከውል ውጪ ስለሚደርስ ሃላፊነት የሚናገሩት ድንጋጌዎች በአንድ አንቀጽ ውስጥ ተካትተው መገኘታቸው እንዲሁም ያለአግባብ መበልፀግም ከውል ውጪ የሚደርስ ሃላፊነት በመሆኑ ከውል ውጭ የሚደርስ ሃላፊነት ሥር የተመለከተው የይርጋ ዘመን በተመሣሣይ አላግባብ መበልፀግ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በዚህ መሰረት ከውል ውጭ ሃላፊነትን በተመለከተ ተበዳዩ ክስ ማቅረብ የሚችለው ካሣ የሚጠይቅበት ጉዳት ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 2 አመት ድረስ መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 2143/1/ ሥር ተመልክቷል፡፡ ስለሆነም ተከሳሽ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ኋላ ላሉት ሁለት አመታት አላግባብ በቤቱ በተገለገሉበት መጠን እንዲከፈሉ የተጠየቁት ካሣ በይጋ የሚታገድ አይሆንም:: ሆኖም ከዛ በፊት ያሉት ግዜያት የተጠቀሙት ክፍያ ግን በይርጋ ቀሪ የሚሆኑ ናቸው በማለት ወስኗል፡፡
ሌላው መታየት ያለ ጉዳይ አንድ ሰው ያለአግባብ በልፅጓል ተብሎ ክስ በሚቀርብበት ወቅት ይህ አለመሆኑን ስለሚያሳይበት መንገድ ነው፡፡ የፍታብሔር ህጋችን በቁጥር 2163 ያለአግባብ መበልፀግ ስለሚቀርበት ሁኔታዎች የሚደነግግ ሲሆን በዚህም መሰረት ያለአግባብ በልፅገሃል ተብሎ የተከሰሰ ሰው ንብረቱን መልስ በሚባልበት ግዜ ላለመበልፀጉ ማስረጃ ያቀረበ እንደሆነ ማሰረጃ ባቀረበበት ልክ ኪሳራ እንዲከፍል አይጠበቅበትም፡፡ ይህም ማለት ምንም እንኳን ከሳሽ ተከሳሽ በእርሱ ኪሳራ መበልፀጉን ማስረዳት ቢችልም ተከሳሽ ክሱ በቀረበበት ወቅት የተገኘው ብልፅግና ከእርሱ ጋር እንደሌለ (ወይም ለሌላ ሰው የተላለፈ መሆኑን) ማስረዳት ከቻለ ካሳ መክፈል ላይኖርበት ይችላል፡፡ ሆኖም ተከሳሹ በክፉ ልቦና ተነሳስቶ ወይም መመለስ እንዳለበት እያወቀ ንብረቱን ወይም ዕቃውን ሌላ ሰው አስተላልፎ ከሆነ ምንም እንኳን የተገኘው ብልፅግና እርሱ ጋር የሌለ ቢሆንም ካሳ የመክፈል ግዴታ እንደሚኖርበት የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2163(2) ስር ያስቀምጣል፡፡ ነገር ግን ተከሳሽ ያለአግባብ የበለፀገበትን ሀብት ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈው ያለ ዋጋ እንደሆነ ከሳሽ ይህን ሶስተኛ ወገን ያለ ዋጋ የወሰደውን ንብረት እንዲመልስለት ሊጠይቀው ይችላል፡፡
መክፈል የማይገባውን ክፍያ ስለመክፈል
ማንኛውም ሰው ሊከፍል የማይገባውን ነገር የከፈለ እንደሆነ ያለአግባብ የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም ማለት ማንም ሰው በስዕተት ሊከፍል የማይገባውን ክፍያ የፈፀመ እንደሆነ ይህ የከፈለው ገንዘብ እንዲመለስልት ካሳ መጠየቅ የሚችል ሲሆን ክፍያውን የተቀበለው ሰው በእምነት ማጉደል ሀሳብ ተነሳስቶ የተቀበለ እንደሆነ ክፍያውን የፈፀመው ሰው ክፍያው ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ የከፈለው ነገር የሰጠውን ፍሬ ወይም ህጋዊ ወለድ ጨምሮ መጠየቅ እንደሚችል ህጉ ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ሰውየው የከፈለው መክፈል የማይጠበቅበትን ክፍያ ቢሆንም እንኳን በሚከተሉት ሁኔታዎች የከፈለው ክፍያ እንዲመለስለት መጠየቅ አይችልም፡-
• ክፍያውን የፈፀመው ዕዳ እንደሌለበት እያወቀ ወይም ይህን ሁኔታ በግልፅ እየተረዳ በፍቃደኝነት ከሆነ፤
• ግለሰቡ የሚከፈለውን ነገር ያለዋጋ የመስጠት የህግ ችሎታ ያለው ሆኖ ክፍያውን የፈፀመው በይርጋ የታገደውን ዕዳውን ወይም የሕሊና ግዴታውን እና የበጎ አድራጎት መንፈሱን ተከትሎ እንደሆነ፤
ክፍያውን ከፈፀመለት ሰው የከፈለው እንዲመለስለት መጠየቅ እንደማይችል የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2165 እና 2166 ስር ያስቀምጣል፡፡
በሌላ በኩል ያለአግባብ የተከፈለውን ክፍያ የተቀበለ ሰው የተከፈለውን ነገር ከመመለስ የሚድንበት መንገድ ህጉ በቁጥር 2168 ስር ያስቀመጠ ሲሆን በዚህም መሰረት የማይገባውን ገንዘብ የተቀበለ ሰው በሌላ ሰው ላይ ያለው ገንዘቡ የተከፈለው መስሎት በቅን ልቦና የብድሩን ሰነድ አበላሽቶ ወይም ዋሶቹን ከዕዳው ነፃ አድርጎ ወይም ከእውነተኛ ባለዕዳ ሊቀበል የሚገባውን ገንዘብ በይርጋ አሳልፎ እንደሆነ፤ ያለአግባብ የተቀበለውን ገንዘብ የመመለስ ግዴታ ማይኖርበት ሲሆን እንዲህ ባለው ሁኔታ ክፍያውን ያለአግባብ የከፈለው ግለሰብ ክፍያው እንዲመለስለት ለመጠየቅ የሚችለው ከዋናው ባለዕዳ ብቻ ነው፡፡
በሌላ ሰው ንብረት ላይ የወጣ ወጪን ስለማስመለስ
ይህ የህግ ክፍል የሌላ ሰው ንብረት ያየዘ ሰው ንብረቱ በሚመልስበት ግዜ ንብረቱን ለመጠበቅ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ስለሚጠይቅበት አግባብ ወይም ንብረቱ በግለሰቡ ቁጥጥር በነበረበት ወቅት ያስገኘውን ጥቅም የራሱ ስለሚያደርግበት መንገድ የሚደነግግ የህግ ክፍል ነው፡፡ ዋናው ያለአግባብ መበልፀግ ህግ አላማ ማንኛውም ሰው መክፈል የማይገባውን ክፍያ እንዳይከፍል ወይም ማውጣት የሌለበትን ወጪ እንዳያወጣ ይህን ካደረገም ተገቢው ካሳ ተከፍሎት ፍትሀዊነት እንዲሰፍን ማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው የራሱ ባልሆነ ንብረት ላይ በቀና ልቦና ያወጣው ወጪ ሳይቀናነስ ንብረቱን ለባለቤቱ መልስ መባሉ ተገቢ አይደለም፡፡ የፍታብሔር ህጉ በቁጥር 2168 ስር አንድ ሰው ለተወሰነ ግዜ በእጁ የቆየውን ዕቃ እንዲመለስ የተገደደ እንደሆነ የሕግ ወይም የውል ተቃራኒ የሚሆን ድንጋጌ ከሌለ በቀር ይህ ሰው የተባለውን ዕቃ ከመለዋወጥ የተነሳ ያሉት መብቶችና ግዴታዎች በዚህ የህግ ክፍል እንደሚገዛ ያደነግጋል፡፡
በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው በእጁ የነበረውን የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ በሚገደድበት ወቅት ዕቃው እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣውን ወጪ እንዲመለስለት ለመጠየቅ እንደሚችል በቁጥር 2168 ስር ተቀምጧል፡፡ ሆኖም ይህ ወጪ የወጣው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ወይም እርሱ ሃላፊነትን በሚወስድለት ሰው ጥፋት ምክንያት ከሆነ ወጪው እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው በውል ህግ መሰረት በተቃራኒው ካልተዋዋሉ ወይም ወጪው አላስፈላጊ ካልሆነ ወይም ወጪው ዕቃውን እንዲመልስ በተገደደው ሰው ጥፋት ምክንያት የተፈፀመ እስካልሆነ ድረስ የሌላን ሰው ንብረት እንዳይጠፋ ወይም እንዳይበላሽ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ህጉ ያስቀምጣል፡፡
ነገርግን ይህ የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ የተገደደ ሰው በውል በሌላ መልኩ ካልተዋዋሉ በስተቀር በማንኛውም መልኩ ለዕቃው አጠባበቅ ያወጣው ወጪ ወይም በንብረቱ ይዞታ ምክንያት የከፈለው ግብር እንዲመለስለት ለመጠየቅ አይችልም፡፡ ይህ መርህ መሰረት ያደረገው ህጉ የሌላ ሰው ንብረትን የያዘ ሰው ንብረቱን በእጁ በሚያስገባበት ወቅት ምንም አይነት መብት የሌለው መሆኑን የሚያውቅ ካልሆነ በስተቀር ንብረቱ ከሚያፈራው ፍሬ እንዲጠቀም መብት የሚሰጥ በመሆኑ ይህ ግለሰብ ፍሬ ያፈራለትን ንብረት ለመጠበቅ ያወጣው ወጪ ይመለሰልኝ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ ስለሆነም በእጁ ያለው ዕቃ እንዲመልስ የተገደደ ሰው የተቀበለው ዕቃ ያፈራውን ፍሬ የማስቀረት ህጋዊ መብት ያለው ሲሆን ዕቃውን በይዞታው ስር ባደረገበት ወቅት በዕቃው ላይ ምንም ዓይነት የውልም ሆነ የህግ መብት እንደሌለው እያወቀ ድርጊቱን ከፈፀመ ግን ይህን የንብረቱን ፍሬ ለራሱ የማስቀረት መብቱ ቀርቶ ለትክክለኛው የንብረቱ ባለቤት ዕቃው በእሱ ይዞታ ስር በነበረበት ወቅት ያፈራው ፍሬ ግምት ልክ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
ሌላው የሌላ ሰው ንብረት እንዲመልስ ከተገደደ ሰው መብት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ይህ ግለሰብ ንብረቱ በእጁ በነበረበት ወቅት በቅን ልቦና በመነሳሳት ወጪ አውጥቶ የዕቃውን ዋጋ ከፍ በሚያደርግበት ግዜ ስለሚኖረው ህጋዊ መብት ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2171 ስር በሌላ ሰው ዕቃ ላይ የተደረገ ወጪ የዕቃውን ግምት ከፍ አድርጎት ከሆነ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ለዚሁ ጉዳይ ያወጣው ወጪ የዕቃውን ዋጋ ከፍ ባደረገው መጠን ብቻ ሊመለስለት እንደሚገባ ያስቀምጣል፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ንብረቱን እንዲመልስ የተገደደ ሰው የዕቃውን ዋጋ ከፍ ለማድረግ ያወጣው ወጪ እንዲመለስለት የሚከተሉትን ነገሮች ማስረዳት ይጠበቅበታል፡-
• በዕቃው ላይ ወጪ ያወጣ መሆኑን፤
• የዕቃውን ዋጋ መጨመሩን እና የዕቃው ዋጋ የጨመረው እሱ ባወጣው ወጪ ምክንያት መሆኑን፤
• የዕቃው ዋጋ መጨመር ንብረቱ እንዲመለስ በተጠየቀመት ግዜ የሚታይ መሆኑን፡፡
ነገር ግን እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተሟሉ ማለት ሰውየው በዕቃው ላይ ያወጣው ወጪ በእርግጠኝነት ይመለስለታል ማለት አይደለም፡ ከነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች በተጨማሪ የቅን ልቦና መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳን ወጪውን በማውጣት ሂደት ቅን ልቦና አለ የሚለው ግምት የሚወሰድበት ቢሆንም ይህ ግን ተቃራኒ ማስረጃ ሊቀርብበት የሚችል ነው፡፡ የፍታብሔር ህጉም በቁጥር 2172 ስር ወጪው በተፈፀመበት ግዜ ዕቃውን እንዲመልስ የተገደደው ሰው ዕቃውን የመመለስ ግዴታ ያለበት መሆኑን ያውቅ እንደነበር ወይም የማወቅ ግዴታ ያለበት መሆኑን ማስረዳት ከተቻለ የወጪው ኪሳራ እንዳይከፈል ወይም የንብረቱ ባለቤት ኪሳራውን የመክፈያ እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ግዜ እንዲሰጠው ዳኞች ለመወሰን እንደሚችሉ አስቀምጧል፡፡
Via lawyer Tsegaye Demeke
https://t.me/lawsocieties
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምንጭ ጥበቃ

የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ለመገናኛ ብዙሃን ማንነቱ እንዳይገለጽ (ሚስጥራዊ መረጃ) በመስማማት መረጃ የሰጠውን ምንጭ እንዲገልጹ አይገደዱም፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ፍርድ ቤት ግን የተፈጸመ ከባድ ወንጀል ላይ ክስ ለመመስረት ወይም መከላከያ ለማቅረብ፣ ወይም በሀገር ጸጥታ ላይ ግልጽና የማይቀር አደጋን ለመከላከል ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ሲሆን እና ክስ ለመመስረት ወይም መከላከያ ለማቅረብ አስፈላጊና ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ከሆነ እና የማይቀር የሆነውን አደጋ ለመከላከል ሌላ አማራጭ የሌለ ሲሆን የመረጃ ምንጭ እንዲገለጽ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።

(የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1238/2013፤ አንቀጽ 49 (1እና2)
https://t.me/lawsocieties
የማስረጃ ሕግ በኢትዮጵያ ሕግ (ክፍል ሁለት)
የማስረጃ ሕግ የማስረጃን አግባብነት፣ የማስረጃን ተቀባይነት እንዲሁም የማስረጃን ክብደትና ብቃት የሚገዙ ደንቦችና መርሆች ስብስብ ነው፡፡ በክፍል አንድ በተለያዩ ህጎች የሚገኙ የማስረጃ ደንቦች የተመለከትን ሲሆን በክፍል ሁለት ፅሁፍ ደግሞ በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት፣ በፀረ-ሙስና ልዩ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃሕግ እና በመሰል ልዩ ህጎች ያሉ የማስረጃ ደንቦችን እንመለከታለን፡፡

የማስረጃ ሕግ በኢ.ፌዲ.ሪሕገ-መንግስት

ህገ መንግስት በባህሪው ሀገሮች መርህ የሚሏቸውን ዋና ዋና ነገሮች የሚያካትት እና ለሌሎች ህጎች መሰረት የሚያስቀምጥ ህግ ነው፡፡ በሀገራችንም በሥራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ዋና ዋና ነገሮችን በመደንገግ ለሚወጡ ዝርዝር ህጎች መነሻ አስቀምጧል፡፡ ከወንጀል ምርመራ፣ ክስ ሂደት እና ከማስረጃ ጋር በተያያዘ ሁለት ዋና ነጥቦችን አካቷል፡፡

የመጀመሪያው በወንጀል ተጠርጥረው የሚያዙ ሰዎች እና የሚካሄድባቸውን ምርመራ በተመለከተ ሲሆን የተያዙ ሰዎች በፍፁም ፈቃደኝነት የሚሰጡት የእምነት ቃል ማስረጃ ሊሆን እንደሚችል ነገር ግን በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት እንደሌለው የደነገገበት ነው፡፡ ይህ በሁሉም የወንጀል ምርመራ እና ክርክር ሂደት ገዢ የሆነ መርህ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት እንዳይኖረው በማድረግ በምርመራው ሂደት የእምነት ቃል ለማግኘት ሲባል የሚደረግን ማስገደድ ፍሬ አልባ በማድረግ ማስገደድን ለማስቀረት ይጠቅማል፡፡

ሁለተኛውየተከሰሱ ሰዎች በፍርድ ሂደት ባሉበት ጊዜ በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር (presumption of innocence) ሲሆን ይህም በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ማስረጃዎች በፍ/ቤት ተሰምተው ጥፋተኝነቱ ካልተረጋገጠ በስተቀር መጠርጠሩ ወይም መከሰሱ ብቻ ወንጀለኛ እንደማያደርገው የደነገገበት ነው፡፡

የማስረጃ ሕግ በሌሎች አዋጆች

1. የማስረጃ ሕግ በፀረ-ሙስናልዩ የሥነ-ሥርዓት እና የማስረጃሕግ

አዋጅ ቁጥር 434/1997 (በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለዉ) የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግን ለመደንገግየወጣ አዋጅ ነው፡፡አዋጅ ቁጥር 434/1997 በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለዉ ማስረጃን አስመልክቶ በደነገገበት ክፍል ስድስት በኮንምፒውተር በተገኘ ሰነድ ማስረጃ ሊሆን ስለሚችልበት ሁኔታ፣ የግል ግንኙነትንና ደብዳቤን በመጥለፍ እንዲሁም ግንኙነትን በመቅዳት ማስረጃ ማሰባበሰብ ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎች አዋጁ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 እንደተሻሻለዉ አንቀጽ 43፣44 እና 45 ላይ እንደቅደም ተከተላቸው ደንግጐ እናገኛለን፡፡በዚህም የኮምፒውተሩ በተገቢው ሁኔታ መስራት እና የፅሁፍ ትክክለኛነትንየሚያጠራጥሩ ምክያንቶች እስከሌሉ ድረስ የኮምፒውተር ሰነዶች፣ አግባብ ባለው አካል የበላይ ሀላፊ ትዕዛዝ በካሜራ፣ በድምፅ መቅረጫ እና በመሳሰሉት ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ህጉን ተከትለው የተሰበሰቡ ማስረጃዎች የሙስና ወንጀልን ለማስረዳት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ማለት ነው፡፡

በቴሌኮሚዩኒኬሽን ወይም በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች የሚደረግን ግንኙነት በመጥለፍ ማስረጃ ለማሰባሰብ የሚሰጥ ትዕዛዝ ለጠለፋው ምክንያት የሆነውን ወንጀል እና ጠለፋው የሚቆይበትን ጊዜ፣ የሚጠለፈው ስልክ ከሆነ ደግሞ ጠለፋው የሚመለከተውን የግንኙነት መስመር መግለፅ አለበት፡፡ አግባብ ያለው አካል በተለየ ሁኔታ ካልወሰነ በስተቀር ትዕዛዙ የሚፀናው ከ4 ወር ለማይበልጥ ጊዜ ይሆናል፡፡ ትዕዛዙ ተግባራዊ ሲደረግም ፈፃሚው በእያንዳንዱ ጠለፋ የተቀዳውን፣ ጠለፋው የተጀመረበትን እና የተጠናቀቀበትን ሰአት መመዝገብ የሚጠበቅበት ከመሆኑም በተጨማሪ በጠለፋው ከተቀዳው ውስጥ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ እውነቱን ለማወቅ የሚረዳ ፅሁፍ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. የማስረጃ ሕግ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን መከላከልና መቆጣጠርበወጣው አዋጅ

ይህን ወንጀል ለመከላከል በሥራ ላይ የዋለው አዋጅ ቁጥር 780/2005 በአንቀጽ 25 በባንክ ሂሳቦችና ሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ ክትትል ማድረግ፣ የኮምፒውተር ሥርአቶችን፣ መረቦችን እና ሰርቨሮችን ማየት፣ መገናኛዎችን በክትትል ሥር ማዋል ወይም መጥለፍ እና የመሳሰሉት ልዩ የምርመራ እና ማስረጃ የማፈላለጊያ ዘዴዎች ጥቅም ላይ በማዋል ማስረጃ ስለሚሰበሰብባቸውሁኔታዎች በዝርዝር የደነገገ ሲሆን እነዚህ የምርመራ ዘዴዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ በወንጀሉ የተሳተፉ ሰዎች እየተጠቀሙባቸው እንደሆነ ወይም ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ጠቋሚ አስተማማኝ ምክንያት ሲኖር ብቻ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪምየማስረጃ ተቀባይነት አስመልክቶበአዋጁ መሠረት የተያዘን መረጃ የሚመለከት ሰነድ ወይም የሰነዱ የተረጋገጠ ግልባጭ ወይም የተረጋገጠ የኤለክተሮኒክ ህትመት በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ላለ ጉዳይ በማስረጃነት ተቀባይነት እንዳለው በአንቀፅ 52 ተመልክቷል፡፡

3. የማስረጃ ሕግ የሽብር ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር የወጣው አዋጅ

ሽብርተኝነት በሀገርና በአለም ሰላምና ደህንነት ላይ ጉዳት የሚያስከትል፣ በሰው ልጆች መብቶችና ነፃነቶች ላይ የሚቃጣና በሰላምና ያለስጋት የመኖር ሁኔታን የሚያሳጣ ከባድ ወንጀል ነው፡፡በሀገራችን የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 መሰረት በሀገር እና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል የሽብር ወንጀል ስጋት ሲኖር ፖሊስ በመደበኛው የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ማስረጃ ማሰባሰብ ሳይቻለው ሲቀር
ሀ. ተጠርጣሪው በፖስታ፣ በደብዳቤ፣ በቴሌፎን፣ በፋክስ፣ በራድዮ፣ በኢንተርኔት እና በሌሎች የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች የሚያደርጋቸውን ልውውጦች ወይም ግንኙነቶች በመመርመር ወይም በመጥለፍ፤
ለ. ክትትል በማድረግ ወይም ድምጽ ወይም ፎቶግራፍ ወይም ተንቀሳቃሽ ምስል መቅረጽ የሚያስችል መሣሪያ በመጠቀም፤
ሐ. ሠርጎ በመግባትና አብሮ በመሆን የተጠርጣሪዎችን እንቅስቃሴና ድርጊት በመከታተል፤
መ. የይምሰል ግንኙነቶችን በመፍጠር በልዩ የምርመራ ዘዴዎች ማስረጃ ለመሰብሰብ እንደሚችል ደንግጓል፡፡

ፖሊስ ልዩ የማስረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለው ፍርድ ቤት የምርመራውን አስፈላጊነት አምኖ ሲፈቅድ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም ፖሊስ አስቸኳ ይሁኔታ ካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ህግ ተቋም ኃላፊ በማስፈቀድ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በልዩ የምርመራ ዘዴ ማስረጃ ሊሰበስብ ይችላል፡፡ ነገር ግን ፖሊስ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በልዩ የምርመራ ዘዴ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ48 ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዐቃቤ ህግ የተሰጠውን ጊዚያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

ፍርድ ቤት በዚህ አንቀጽ መሰረት በልዩ የምርመራ ዘዴ ማስረጃ ለማሰባሰብ የሚፈቅደው ጊዜ ከ90 ቀናት መብለጥ የለበትም፡፡ ፖሊስ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለገውን ማስረጃ ያላገኘ እና ልዩ የምርመራውን ዘዴ መጠቀሙ ተጨማሪ ጊዜ አስፈላጊ ለመሆኑ በቂ ምክንያት ያለው ከሆነ ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ለመጠየቅ ይችላል፡፡ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያከናወነውን ተግባር፣ የተፈቀደው ዘዴ እያስገኘ ያለውን ውጤት በማገናዘብ እና ተጨማሪ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በመመርመር ከ30 ቀናትያልበለጠ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ ይችላል፡፡