አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ተገዶ_የመያዝ_Habeas_corpus_ስረ_ነገር_ስልጣን.pdf
320.7 KB
የሰበር መዝ/ቁ. 230167፣ 230168፣ 230169 /ያልታተሙ/
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5(1)(ኘ) መሰረት ተገድዶ የመያዝን ህጋዊነት ለማረጋገጥ የሚቀርብን አቤቱታ / Habeas corpus/ ተቀብሎ የማየት የመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣን ያለው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው እንጂ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አይደለም ።
#Click Ethiopian Laws
224876.pdf
1 MB
የውርስ ሀብት በእጁ አድርጎ ያልያዘ ወራሽ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) መሰረት የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት አይችልም።
የፍ/ብ/ህ/ቁ 1000(1) ከሳሹ መብቱንና የውርሱ ንብረቶች በተከሳሹ መያዛቸውን ካወቀ ሶስት አመት ካለፈ በኋላ ስለወራሽነት ጥያቄ የሚቀርበው ክስ ተቀባይነት ለማግኘት እንደማይችል ደንግጓል፡፡ ይህ ድንጋጌ በይዘቱ የይርጋ መቃወሚያ ማንሳት የሚችለው የውርስ ንብረቶቹን በእጁ የያዘው ሰው ብቻ ስለመሆኑ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
ሰ-መ-ቁ 224876 ቀን ጥቅምት 2 2015 ዓ.ም
#Click Ethiopian Laws
መልስ የማቅረብ መብት መታለፍ ውጤት ሰ/መ/ቁ. 188331

የመከላከያ መልስ የማቅረብ መብቱ የታለፈበት ተከራካሪ ክሱ በሚሰማበት ሆነ በሙግት ጊዜ ማስረጃ የማቅረብ መብቱን ያጣል።
#Click Ethiopian Laws
ሰ/መ/ቁጥር---228231 የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም
የተራ ዋስትና እና የአንድነት ዋስትና ልዩነት
በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብት ለመጠቀም መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1935(1) ዋሱ እንደ ተከሰሰ ወዲያውኑ ባለገንዘቡን ከባለዕዳው ጋር ተከራከር ካላለ በቀር ባለገንዘቡ ከዋናው ባለዕዳ ጋር ለመከራከር ግዴታ የለበትም በማለት ሲደነግግ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1936 ደግሞ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም እንደቅድመ ሁኔታ መሟላት ያለባቸው ነገሮች ያስቀመጠ ሲሆን ይኸውም ክርክሩን የሚጠይቀው ዋስ ለባለገንዘቡ የዋናውን ባለዕዳ ንብረቶች መምራትና ለዚሁም ክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ አስቀድሞ ለባለገንዘቡ መስጠት አለበት በማለት አስቀምጧል።
ይህም የሚያስገነዝበን ዋሱ በቅድሚያ ከባለዕዳው ጋር ተከራከር የሚለውን መብት ለመጠቀም፥
አንደኛ ክሱ እንደቀረበበት ወዲያውኑ በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር በማለት ማንሳት አለበት፤
ሁለተኛ በደፈናው ባለዕዳው ንብረቶች ማለት ብቻ ሳይሆን ከክርክር ነጻ የሆኑ የባለዕዳው ንብረቶችን ቆጥሮ ወይም መርቶ ማሳየት አለበት፤
ሦስተኛ ለክርክር የሚያስፈልገውን በቂ ወጪ መዴቦ ለባለገንዘቡ መስጠት ይኖርበታል፡፡
ከእነዚህ ሦስት መስፈርቶች ውስጥ አንዱ እንኳ ካልተሟላ ባለገንዘቡን በቅድሚያ ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን እንደሚያጣ በግልጽ ያሳያል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የክፍያው ጊዜ ደርሶ ገንዘቡ ያልተከፈለው ባለገንዘብ ቢፈልግ ባለዕዳውንና ዋሱን በአንድ ሊይ መክሰስ ወይም ባለዕዳውን ትቶ ዋሱን ብቻ መክሰስ የሚችል ሲሆን ተራ የሆነ ዋስትና ግዴታ የገባው ዋስ የአንድነት ዋስትና ከገባው ዋስ የሚለየው ከባለዕዳው ተከራከር የማለት መብቱን ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ በአግባቡ መጠቀም ሲችል ብቻ መሆኑን ነው፡፡
ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቶ ከባለዕዳው ጋር በቅድሚያ ተከራከር የማለት መብቱን ያልተጠቀመ ተራ ዋስ በተናጠልም ሆነ ከባለዕዳው ጋር በጋራ የዋስትና ግዴታ የገባውን ዕዳ አልከፍሌም ማለት የሚችልበት የሕግ አግባብ የለም፡፡
#Click Ethiopian Laws

👇👇👇👇👇👇
219862 - Stamped.pdf
828.9 KB
አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ በፈፀመው የድብደባ ድርጊት የአጥንት ስብራት መድረሱ ቢረጋገጥና ቆይቶ ስብራቱ መዳኑ ቢረጋገጥ ጉዳት ያደረሰው ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሳይሆን በቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነው። በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ለማለት ታሳቢ ሊደረግ የሚገባው ወንጀሉ ሲፈፀም የደረሰውን የጉዳት መጠን ሳይሆን በድብደባው ምክንያት የደረሰውን የመጨረሻ የጉዳት ውጤት ነው። ሰ/መ/ቁ.156521፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556
#Click Ethiopian Laws
👆👆👆👆👆👆