አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Draft Registration and Licensing Directive - 01.25.2014.docx
4.2 MB
በአገራችን በ1952 ዓ.ም. ወጥቶ ለረዥም ጊዜ ሥራ ላይ የነበረው የንግድ ሕግ በዘርፉ ካለው ለውጥና ዕድገት ጋር እንዲጣጣም ባለፈው ዓመት በአዲስ መልክ በአዋጅ ቁ 1243/2013 ሆኖ እንዲወጣና ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። በሚኒስቴር መ/ቤታችን በኩልም የንግድ ሕጉ ያመጣቸውን ለውጦች ታሳቢ በማድረግ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 አንቀጽ 52 ንዑስ አንቀጽ 2 እና በንግድ ሕጉ የመግቢያ ድንጋጌ አንቀጽ 5 መሠረት የተሻሻል የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ረቂቅ ተዘጋጅቷል።

ረቂቅ መመሪያውን ላይ ያላችሁን አስተያየት በዚህ ቻናል ኮመንት ላይ ወይም በኢምል አድራሻ jiratenemera@yahoo.com ይላኩልን።
#የሊዝ_መብትን_ስለማስተላለፍ_በዋስትና_ስለማስያዝ_እና_መሠረታዊ_የሊዝ_ህግ_ድንጋጌዎች

የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት/Federal Justice and Law Institute
#የሊዝ_መብትን_ስለማስተላለፍ_በዋስትና_ስለማስያዝ_እና_መሠረታዊ_የሊዝ_ህግ_ድንጋጌዎች
ከሊዝ ሥሪት ውጪ ቦታ መያዝና መፍቀድ ስለመከልከል
ማንኛውም ሰው የከተማ መሬትን በሊዝ አዋጅ 721/2004 ከተደነገገው የሊዝ ሥረዓት ውጪ መያዝ አይችልም፡፡
ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳይገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አሰፋፍቶ መከለልና መጠቀም አይችልም፡፡
ማኝውም ከልል ወይም የከተማ አስተዳደር በሊዝ አዋጅ 721/2004 ከተደነገገው ውጪ የከተማ መሬትን መፍቀድ ወይም ማስተላለፍ አይችልም፡፡
ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ሥሪት ስለሚቀየሩበት ሁኔታ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
በነባር ይዞታ ላይ የሰፈረ ንብረት ባለቤትነት ከውርስ በስተቀር በማንኛውም መንገድ ለሌላ ሰው ከተላለፈ ንብረቱ የተላለፈለት ሰው የቦታው ባለይዞታ ሊሆን የሚችለው በሊዝ ሥሪት መሰረት ይሆናል፡፡
ነባር ይዞታና የሊዝ ይዞታ እንዲቀላቀል ጥያቄ ቀርቦ ይዞታው እንዲቀላቀል ከተፈቀደ ጠቅላላ ይዞታው በሊዝ ሥሪት ይተዳደራል፡፡
በሊዝ የተያዘ የከተማ ቦታ አጠቃቀም እና ግንባታ ስለመጀመር
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
የከተማ ቦታ ሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል አለበት፡፡ ነገር ግን ባለይዞታው የቦታውን አጠቃቀም መለወጥ ከፈለገ አግባብ ላለው አስቀድሞ በማመልከት ፈቃድ ሊያገኝ ይገባል፡፡
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታ መጀመር አለበት ነገር ግን በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ካልጀመረ ቦታውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሊዝ ክፍያና የጠቅላላውን የሊዝ ዋጋ ሰባት በመቶ መቀጮ እንዲከፍል ተደርጎ ቦታውን አግባብ ያለው አካል መልሶ ይረከባል፡፡
ግንባታ ስለማጠናቀቅ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባውን ማጠናቀቅ አለበት፡፡
የግንባታ ማጠናቀቅያ የጊዜ ገደብ እንደ ሚከተለው ይሆናል፡-
ለአነስተኛ ግንባታ 24 ወራት
ለመካከለኛ ግንባታ 36 ወራት፤
ለከፍተኛ ግንባታ 48 ወራት፡፡
ከላይ የተመለከተው ቢኖርም እንደ ግንባታው ውስብስብነት እየታየ የግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡ ሆኖም ለግንባታ ማጠናቀቅያ የሚሰጠው ጠቅላላ ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ፡- ለአነስተኛ ግንባታ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር ለመካከለኛ ግንባታ ከአራት ዓመት እና ለከፍተኛ ግንባታ ከአምስት ዓመት መብለጥ አይችልም፡፡ በተጨማሪም የሊዝ ባለይዞታ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ግንባታውን ካላጠናቀቀ አግባብ ያለው አካል የሊዝ ውሉን በማቋረጥ ቦታውን መልሶ መረከብ ይችላል፡፡
የሊዝ ውል የተቋረጠበት ሰው በራሱ ወጪ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ የሠፈረ ንብሩን ማንሳት አለበት፡፡ የሊዝ ባለይዞታው ንብረቱን በወቅቱ ካላነሳ አግባብ ያለው አካል ጀምሮ ግንባታው በፕላኑ መሰረት የተገነባ መሆኑን አረጋግጦ ግንባታውን ማጠናቀቅና መጠቀም ለሚችል ሰው በግልፅ ጨረታ ንብረቱን በመሸጥ ማስተላለፍ ይችላል፡፡
የሊዝ መብትን ስለማስተላለፍና በዋስትና ስለማስያዝ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግት ጥቅም ላይ የማንዋል ግዴታ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ መብቱን ለማስተላለፍ ወይም በከፈለው የሊዝ ክፍያ መጠን በዋስያዝ ወይም በካፒታል አስተዋፆነት ለመጠቀም ይችላል፡፡
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ ባላይዞታ የሊዝ መብቱን ግንባታ ከመጀመሩ ወይም ግንባታውን በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት ከውርስ በስተቀር ማስተላለፍ የሚችለው አግባብ ባለው አካል ቁጥጥር የሚደረግበት ግልጽ የሽያጭ ሥርዓትን በመከተል ይሆናል፡፡
በሌላ አኳኳን ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር በመሬት የመጠቀም መብት በዋስትና ሲያዝ ወይም ሲተላለፍ በመሬቱ ላይ የተገነባው ህንፃና ከህንፃው ጋረር የተያያዙ መገልገያዎች መብት አብሮ ይያዛል ወይም ይተላለፋል እንዲሁም ሕንፃና ከሕንፃው ጋር የተያያዙ መገልገያዎች በዋትና ሲያዙ ወይም ሲተላለፉ በመሬት የመጠቀም መብቱም አብሮ ይያዛል ወይም ይተላለፋል፡፡
---------------------
ግንባታ መጀመር ማለት በቦታው ላይ ለመስራት ከተፈቀደው ግንባታ ወይም ሕንፃ ቢያንስ የመሠረት ሥራ መሥራትና የኮለን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችሉ የኮለን ብረቶች የማቆም ሥራ ማጠናቀቅ ነው
ግንባታ በግማሽ ማጠናቀቅ ማለት
ሀ/ ቪላ ሲሆን የመሠረቱን የኮለኖችና ለጣሪያ ውቅር የሚስፈልጉ ቢሞችን ሥራ ማጠናቀቅ ፤
ለ/ ፎቅ ሲሆን የመሠረቱንና ከጠቅላላው ወለሎች ውስጥ 50 የሚሆኑትን የስሌት ስራ ማጠናቀቅ ፣
ሐ/ሪል ስቴት ሲሆን የሁሉንም ብሎኮች ግንባታ እንደአግባቡ ማጠናቀቅ ነው፤
ግንባታ ማጠናቀቅ ማለት በሊዝ የተፈቀደ ቦታ ላይ እንዲገነባ የተፈቀደ ቦታ ላይ እንዲገነባ የተፈቀደን ግንባታ በተሰጠው የግንባታ ፈቃድ መሰረት ሙሉ በሙሉ መሥራትና ዋና ዋና አገልግሎቶች ተሟልተውለት ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡
ነባር ይዞታ ማለት የከተማ ቦታ በሊዝ ስርዓት መተዳደር ከመጀመሩ በፊት በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ወይም ሊዝ ተግባራዊ ከሆነ በኃላ ለነባር ይዞታ ተነሺ በምትክ የተሰጠ ቦታ ነው፡፡
የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት/Federal Justice and Law Institute
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#Commercial Bank Of Ethiopia#🚩Call for Written Exam - Legal Attorney Applicants
==================

Dear Applicants,

Thank you for your application for the position of Legal Attorney for Commercial Bank of Ethiopia.

We are pleased to invite you to take a written exam on Saturday August 13, 2022 at 02:00 local time (Morning) at CBE’s Zagwe Building, Lideta, Addis Ababa.

N.B. You are required to provide your ID card or Passport. Using a mobile phone is prohibited.

Please check name lists of applicants to seat for the written exam using the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Exam_Legal_Attorny_27e81ba84c.pdf
2022_የንግድ_ምዝገባ_ፈቃድ_እና_ድኅረ_ፈቃድ_ኢንስፔክሽን_መመሪያ_ቁጥር_23_2014.pdf
888.8 KB
የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 23/2014

መመሪያው ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የንግድ ስምን ስለማጣራት የወጣውን መመሪያ ቁጥር 003/2007 እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ እና የድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 010/2009 የሚሽር ሲሆን በአባሪ የሚከተሉትን ይዟል :-

ሀ.የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መጠየቂያ የማመልከቻ ቅጾች
ለ.የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት የምስክር ወረቀቶች
ሐ.የድርጅት እና የንግድ ስም ማብራሪያ
መ.የድኅረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መረጃ ማሰባሰቢያ ቼክ ሊስትና ቅጽ
2022_Draft_Regulation_to_Amend_The_Federal_Income_Tax_Regulations.pdf
2.5 MB
የፌደራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ ደንብ

Draft Regulation to Amend The Federal Income Tax Regulations
በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ በማውጣት ወንጀል የተከሰሰችው ግለሰብ በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣች
-------------------/////////////-----------------
https://t.me/lawsocieties
-------------------/////////////-----------------
ፍጥረት አማረ ያዘው የተባለችው ተከሳሽ በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 693/1/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፉ ክስ ተመስረቶባታል፡፡

ተከሳሽ የምታዝበት በቂ ስንቅ ሳይኖራት ሚያዚያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ በግምት 5፡00 ሰዓት አካባቢ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታው ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ከግል ተበዳይ አቶ ተክሌ ፀሀዬ ለገዛችው የቤት ዕቃ ክፍያ ለመፈፀም 10,000›000 /አስር ሚሊዮን/ ብር እንዲሁም ከግል ተበዳይ ኤፍሬም ወንድሙ በብድር መልክ ለወሰደችው ገንዘብ ክፍያ የሚሆን በሚል 600,000 /ስድሰት መቶ ሺህ/ ብር ደረቅ ቼክ ፅፋና ፈርማ ከሰጠች በኋላ የግል ተበዳዮች ለመመንዘር ቼኩን ለባንክ ሲያቀርቡ ተከሳሽ በቂ ስንቅ ሳይኖራት በተደጋጋሚ ጊዜ ቼክ በማውጣቷ ሂሳቡ ከቀን 27/11/2013 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋ መሆኑን የተረጋገጠ በመሆኑ ለግል ተበዳይዮች ክፍያ ሳይፈፀም ቼኩ የተመለሰ ስለሆነ፤ በፈፀመችው በቂ ስንቅ ሳይኖር ቼክ ማውጣት ወንጀል ተከሳለች፡፡
ተከሳሽ በችሎት ቀርባ ክሱ ደርሷትና ተነቦላት የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ”እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ”ስትል ቃሏን ሰጥታለች።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር ሶስት የምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎች በበቂ ሁኔታ ለችሎቱ በማስረዳቱ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን እንድትከላከል ብይን ቢሰጥም ተከሳሽ በችሎት ቀርባ መከላከያ ምስክር ማቅረብ አልቻለችም፤ ስለሆነም የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ላይ በሁለቱም ክሶች የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለባት መሆኑ እንደ አንድ የቅጥት ማቅለያ ተይዞላት ሐምሌ 27/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችንም ያስተምራል በማለት ተከሳሽ በሌለችበት በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና ሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ተወስኖባታል።
ከፍትህ ሚኒስቴር
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ሠበር በ7 ዳኞች የተሰጠ ውሳኔ ።።።።።።።።።**።።።።።።።።።።።።።።።።።።። https://t.me/lawsocieties ።።።።።።።።።።።**።።።።።።።።።።።።።።።።።ሠሰ/መ/ቁ. 190307 ( ያልታተመ) ህዳር 29 ቀን 2014 ዓ.ምየአ/አ/ክትማ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በፍርድ ቤት ክርክር በማድረግ የከተማዉ ነዋሪዎችን/የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም ለማስከበር ያለዉመብት/ስልጣን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣንና ኃላፊነት ባለዉ ሌላ የከተማዉ አስተዳደር አካል ክርክር ተደርጎበት ዉሳኔ ያረፈበት ጉዳይ በድጋሚ እንዲታይ በፍ/ብ/ሥ/ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ ያስችለዋል ወይ?ሦስተኛ ወገን በክርክሩ ተሳታፊ ካልሆነ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ፍትሐዊ ዉሳኔ ለመስጠት የማይችል ዓይነት (indispensable party) ከሆነ በፍርድ ቤቱ አነሳሽነት ወይም መብት ባለዉ ሰዉ አቤቱታ አቅራቢነት፣ እንዲሁም ዉጤቱ መብቴን ሊነካ ይችላል በሚል ወገን (interested party) አቤቱታ አቅራቢነት ሦስተኛ ወገን በተጀመረ ክርክር ተሳታፊ የሚሆንበትን ሥርዓት የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ ይዘረጋል (አንቀጽ 40 እና 41 ይመለከቷል)፡፡ ዓላማዉም የጉዳዩ አመራር ፍትሐዊ እንዲሆንና በሥርዓት እንዲከናወን ለማስቻል ሲባል ነዉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይሁንናበተለያዩ ምክንያቶች ከላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ በክርክሩ ተሳታፊ ሆኖ መብቱን ማስከበር ይችል የነበረ ሰዉ ተሳታፊ ባልሆነበት መብቱን የሚነካ ዉሳኔ ሊሰጥ የሚችልበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል፡፡ ስለሆነም በፍርድ ቤት ወይም በህግ የዳኝነት ስልጣን ባለዉ አካል በተሰጠ ዉሳኔ መብቴ ተነክቷል የሚል ሦስተኛ ወገን አቤቱታዉን በማቅረብ ዉሳኔዉን በመቃወም መብቱን ሊያስከብር የሚችልበትን ሥርዓት በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 ላይ ተመልክቷል ።በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የሚቀርብ አቤቱታ የክርክሩ ተሳታፊ ባልሆነበት በተደረገ ክርክር የተሰጠ ዉሳኔ መብቱን የሚነካበት ሦስተኛ ወገን የመቃወም አቤቱታዉን አቅርቦ የክርክሩ ተሳታፊ በመሆን ተከራክሮ መብቱን ማስከበር እንዲችል ታስቦ የተዘረጋ ነዉ፡፡ በመሆኑም አቃቤ ህግ ወኪል ሆኖ ሊከራከር የሚችልበት መብትና ጥቅም ክርክር በማድረግ ተመሳሳይ መብትና ጥቅም ለማስከበር ስልጣን ባለዉ ጉዳዩ በሚመለከተዉ መስሪያ ቤት ክርክር ቀርቦበት ዉሳኔ ከተሰጠ በኋላ አቃቤ ህግ ዉሳኔዉን በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት ሊቃወም የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም፡፡የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 37502 (ቅጽ 8 ላይ እንደታተመዉ) የሰጠዉ የህግ ትርጉም ተለዉጧል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (በየደረጃዉ ያሉ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤቶችን ይጨምራል) ወኪል ሆኖ ክርክር በማቅረብ የነዋሪዉን መብትና ጥቅም እንዲያስከብር በአስፈፃሚ አካላት ማቋቋሚያ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 5 ስልጣን የተሰጠዉ ቢሆንም፣ ይህ ስልጣኑ ብቻዉን ተመሳሳይ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣን ያለዉ የሚመለከተዉ የከተማዉ አስተዳደር አካል የክርክሩ ተሳታፊ በሆነበት ታይቶ ዉሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ መሠረት አድርጎ እንደገና ክርክር ለማድረግ በፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ህጉ አንቀጽ 358 መሠረት የመቃወም አቤቱታ እንዲያቀርብ ምክንያት አይሆንም፡፡

#ዳንኤል ፍቃዱ
#Phison Real Estate#🚩for experienced

▪️1 - Senior Secretary
▪️2 - Senior Accountant
▪️3 - Senior Auditor
▪️4 - Safety & Health Officer(Nurse)
▪️5 - Junior Legal Officer
▪️6 - Excavator Operator
▪️7 - Mobile Crane Operator
▪️8 - Construction ,Machinery,Equipment & Maintainance Department Head
▪️Click the link below for details
👇👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3drJYhZ

▪️Deadlin - August 15/22