አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የተጠናቀቀውን የበጀት አመት የግብር አከፋፈል ጋር የተፈጠሩ የአሰራር ችግሮች ጋር በተያያዘ መፍትሄ ለማምጣት እና ዘላቂ የአሰራር ስርአት እንዲኖር ከሀምሌ 01 ቀን 2014ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል:: የዚሁ አካል በሆነው 11 አባላት ያሉት ግብረ ሀይል (Task force) አቋቁሞ በርካታ ተግባራትን በየእለቱ ሲያከናውን ቆይቷል::

በዚሁ መሰረት ለአጭርና ለረጅም ጊዜ ስራዎች እቅድ በማውጣት ለአጭር ጊዜ መፍትሄው ቅድሚያ በመስጠት ሲሰራ ቆይቷል::

በዚህም የጠበቆች ማህበሩ በጉዳዩ ላይ ያለውን አቋም ከነማብራሪያው በይፋ ለሚመለከታቸው አካላት በፅሁፍ ከማሳወቅ ጀምሮ አማራጭ መፍትሄዎችን አቅርቧል:: በተመሳሳይ ከሚመለከታቸው የፍትህ ሚ/ር; የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ቢሮ እና ሌሎች ተቋማት የበላይ ሀላፊዎች ተከታታይ ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል:: በዚህም የአጭር ግዜ መፍትሄው በመልካም ውጤት ተጠናቋል::

በመሆኑም ግብር ከፋይ ጠበቆች;
1. ሂሳብ መዝገብ የያዙ ጠበቆች ካሉ በዛው መሰረት እንዲስተናገዱ;
2. በአማራጭ ደረሰኝ የሚስተናገዱ በቆረጡት ደረሰኝ መሰረት ታክሳቸውን አሳውቀው እንዲስተናገዱ;
3. ሁለቱምን ያልያዙ ወይም የሌላቸው ጠበቆች ደግሞ እንደከዚ ቀደሙ በቁርጥ ግብር/ወጪ እንዲስተናገዱ ለሁሉም የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቅርንጫፎች መመሪያ ተላልፏል::
4. በመሆኑም ከዛሬ ጀምሮ ጠበቆች በየግብር መክፈያ ቅርንጫፋቸው እየተገኙ ታክሳቸውን መክፈል መቀጠል የሚችሉ ይሆናል::

በዚህ ሂደት አስተዋፅኦ እና ቀና ትብብር ላሳያችሁ ለፍትህ ሚ/ር; የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የበላይ አመራሮችና የስራ ባልደረቦች እንዲሁም በሂደቱ ላይ በቀጥታ ለተሳተፋችሁ ግዜ እና እውቀታችሁን ጭምር አስተዋፅኦ ያደረጋችሁ የማህበሩን የአመራር አባላት እና የግብረሀይሉ አባላት ማህበሩ ምስጋናውን ያቀርባል::

ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተም ከኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር; ከገንዘብ ሚኒስቴር; ከገቢዎች ሚ/ር እና ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የተውጣጣ የጥናትና መፍትሄ አመንጪ ቡድን በማህበሩ አስተባባሪነት ተቋቁሞ ስራውን የሚጀምር መሆኑን እና የሚደረስባቸውን ውጤቶችም የሚያሳውቅ መሆኑን ማህበሩ ይገልፃል::

ከላይ ከተገለፀው በተቃራኒ እክል የሚፈጠርባችሁ ጠበቆች በማህበሩ አድራሻ ስማችሁን; ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱንና tin no በማስመዝገብ መፍትሄ እንድታገኙ የሚደረግ መሆኑን ማህበሩ ያሳስባል::


የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሀምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት የክልሉ ምክር ቤት አስታውቋል።

1. ቦንጋ ከተማ የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳደሩ መቀመጫ፣
2. ተርጫ የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ፣
3. ሚዛን አማን የዳኝነት አካል መቀመጫ
4. ቴፒ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ እንደሚሆኑም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።

የክልሉ ዋና ከተሞች አራት እንዲሆኑ የተደረገው ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ እንደሆነም የብዝኃ ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ ይጠቅሳል።

ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ በክልሉ ምክር ቤት ፀድቆ የሚተገበር ከሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች ያሉት የመጀመሪያው ክልል ይሆናል።
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
New_Investment Incentives Regulation_No 517_2022.pdf
4 MB
አዲሱ_የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ ቁጥር 517_2014

New _ Investment Incentive Regulation No.517_2022
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Regarding Exemption of Motor Vehicles from Customs Duties.jpg
1.5 MB
የተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ መሆን በተመለከተ
Regarding Exemption of Motor Vehicles from Customs Duties
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
የተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ መሆን በተመለከተ
Regarding Exemption of Motor Vehicles from Customs Duties
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Exit exam guide line.pdf
393.5 KB
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና አፈጻጸም መመሪያ*** ከ2015 ጀምሮ በሁሉም ዮኒቨርሰቲዎች ለሁሉም ዲፓርትመንቶች ተግባራዊ የሚደረግ ነው
ፍርድ ቤቱ ሐሰተኛ የቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር እንዲቀጡ ወሰነ
*****************************************************************
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሶስተኛ ሰበር ችሎት ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡ ባለጉዳይን በችሎት መድፈር ጥፋተኛ ናቸው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡
ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በደሀ ደንብ መስቀልኛ የሰበር አቤቱታ ለማቅረብ የዳኝነት ለመክፈል ምንም ሀብት እና ንብረት የሌላቸውና በቀበሌ ቤት የሚኖሩ መሆኑን በቃለ-መሐላ በማረጋገጥ አቤቱታቸውን በሀሰተኛ መንገድ በማቅረባቸው ነው፡፡
ሆኖም ግን የግለሰቡ ተከራካሪዎች ለችሎቱ ባቀረቡት አቤቱታ ግለሰቡ በስር ፍርድ ቤት እስከ ክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ የዳኝነት ከፍለው ሲከራከሩ የነበረ መሆኑን እና አሏቸው ያላቸውን ሀብትና ንብረት ጠቅሰው በችሎቱ እንዲጣራላቸው በመጠየቃቸው ምክንያት ግራ ቀኙ በችሎት ቀርበው እንዲሰሙ ሲደረግ ግለሰቡ ቀድሞ ባቀረቡት የቃለ-መሐላ አቤቱታ መሠረት በስማቸውም ሆነ በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ ምንም ዓይነት ሀብትና ንብረት እንደሌላቸው ለችሎቱ ማረጋገጣቸውን ችሎቱ በግለሰቡ ላይ ከሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስለግለሰቡ ሀብትና ንብረት አጣርቶ እንዲያቀርብ የታዘዘው የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከላይ በተመለከተው አግባብ ግለሰቡ በስማቸው የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ያላቸው መሆኑን እና በመጠጥ ችርቻሮ ንግድ ስራ ላይም ተሰማርተው በመስራት ላይ የሚገኙ ስለመሆኑ ለፍ/ቤቱ ማረጋገጡን የችሎቱ ውሳኔ ያስረዳል፡፡
ተጠሪ ሀብትና ንብረት እያላቸው እንዲሁም በንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው እያለ ምንም ዓይነት ንብረት እንደሌላቸው በቃለ-መሐላ አቤቱታ ከማረጋገጣቸውም በላይ ስለዚሁ ጉዳይ በችሎት በተጠየቁበት ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ መናገራቸው ሆነ ብለው ሀሰተኛ ፍሬ ነገርን ለችሎት መግለጻቸውን የሚያረጋግጥ መሆኑም በውሳኔው ላይ ተመልክቷል፡፡
ይህ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 481 እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 452 መሰረት የወንጀል ክስ ማቅረብ ሳያስፈለግ በቀጥታ በወንጀል ሊያስቀጣ የሚችል ለመልካም ችሎት አመራር ተቃራኒ የሆነ በፍትህ ስራ ላይ ሊደረግ የሚገባው በእውነተኝነት እና በታማኝነት ተግባር ላይ የሚፈፀም የወንጀል ተግባር መሆኑንም ችሎቱ በውሳኔው ላይ ዘርዝሯል፡፡
ግለሰቡ ጥፋተኛ በተባሉበት የወንጀል ህግ አንቀፅ ስር ያለው ቅጣት ከአንድ ዓመት የማይበልጥ ቀላል እስራት ወይም ድርጊቱ የተፈፀመው በወንጀል ክስ ሂደት በሆነ ጊዜ ከሶስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በመጥቀስም ከተፈፀመው ድርጊት አኳያ ግለሰቡንም ሆነ ሌሎች መሰል ድርጊት ለመፈፀም ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች ያስተምራል እንዲሁም ያስጠነቅቃል በማለት ለችሎቱ ሐሰተኛ ቃለ-መሐላ አቤቱታ ያቀረቡት አቶ ኃይለማርያም ወዳጆ በአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ቀላል እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የጤና ህግ (Health Law) ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት ምክክር ተካሄደ
***
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ግምገማ፣ የ2015 ዓ/ምን የስራ እቅድ ትውውቅና በኽልዝ ሎው ስርዓተ ትምህርት (Health Law curriculum) ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ሀምሌ 29/2014ዓ/ም በፍሎሪዳ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡

በመርሃ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት ተወካይ አቶ ልጃለም ጋሻው፣ የህግ ትምህርት ቤት ዲን አቶ አለሙ ታዬ፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተምረው በህግ መምህርነት ሲያገለግሉ የነበሩና በአሁኑ ሰአት በአሜሪካን ሀገር በሲያትል ዋሽንግተን ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ እዮብ ከበደና ሌሎች የትምህርት ቤቱ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፣ በቅድሚያ አቶ እዮብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን የጤና ህግ (Health Law curriculum) ፕሮግራም በዩኒቨርሲቲው በ2ኛ ዲግሪ ለመክፈትና ከዩኒቨርሲቲው ጋር ለመስራት ያላቸውን ፈቃደኝነትንና ተነሳሽነት በዩኒቨርሲቲው፣ በራሳቸውና በህግ ትምህርት ቤቱ ስም አመስግነዋል፡፡ ዶ/ር ካሳሁን አያይዘውም ፕሮግራሙ በዩኒቨርሲቲው መሰጠቱ የሚኖረውን ፋይዳና ተያያዥ ነጥቦችን በማንሳት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው፣ በሚቀርበው የስራ ሪፖርትና እቅድ ላይ ተሳታፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኽልዝ ሎው (Health Law curriculum) ፕሮግራምን በ2ኛ ዲግሪ ለማስጀመር ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደቆዩ የሚያነሱት አቶ እዮብ የፕሮግራሙን አስፈላጊነት አስመልክቶ፣ፕሮግራሙ ለዩኒቨርሲቲውና እንደ ሀገርም ያለውን ፋይዳ፣ በአጠቃላይ የፕሮግራሙን ጠቀሜታ እንዲሁም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ አጭር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ገለፃውን ተከትሎ በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመቀጠል የህግ ትምህርት ቤት ዲን በሆኑት በአቶ አለሙ ታዬ የ2014ዓ/ም የስራ ዘመን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተው ለጥያቄዎቹ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ እቅድ በመነሳት የህግ ትምህርት ቤቱ የ2015 ዓ/ም የስራ እቅድ መታቀዱንና በሚቀጥለው የስራ ዘመን ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወኑ ተግባራትንም አቶ አለሙ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
****
ለልህ
ቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሀምሌ 29/2014ዓ.ም
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
ኢትዮጵያ በምግብ ዋጋ ንረት ከተመቱ የዓለም ቀዳሚ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ኢትዮጵያን ያካተተው የዓለም ባንክ ሪፖርት ይፋ ሆኗል።
በከባድ የምግብ ዋጋ ንረት ተመተዋል በሚል በሪፖርቱ ከተካተቱት ቀዳሚ 10 ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች።
ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ወርሃ መጋቢት ወዲህ እስከ ሰኔ በነበሩት አራት ወራት ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ንረት አጋጥሟታል ተብሏል።
ንረቱ 38 በመቶ ሆኖ መመዝገቡም ነው በሪፖርቱ የተጠቀሰው።

በከባድ የብድር ጫና ውስጥ የሚገኙት ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ሊዳረጉ እንደሚችሉም ተገልጿል።

በሪፖርቱ ሊባኖስ በንረቱ ክፉኛ የተጎዳች ሃገር ነች ተብላለች።


https://am.al-ain.com/article/ethiopia-is-among-the-countries-worst-hit-by-the-food-inflation-crisis-wbg-said

#lawsocieties #AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
_የኢትዮጵያ_የንግዴ_ስራ_ፈቃዴ_መስጫ_መዯብ_መመሪያ_ቁጥር_17_201.pdf
3.1 MB
በኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዳሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ
የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር


የኢትዮጵያ የንግድ ስራ ፈቃድ መስጫ ደንብ መመሪያ ቁጥር
17/2011

ሰኔ/2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
በሽታን ሆን ብሎ ወደሌሎች ማስተላለፍ የሕግ ተጠያቂነት
Via health inovation
#New#Awash Bank#

▪️1 - Administrative Assistant I
▪️2 - Plumber
▪️3- IT Service Management Officer - Core & Interface
▪️4 - Legal Officer
▪️5 - Mobile & Internet Banking Officer I
▪️6 - Digital Channels Technical Support Officer II
▪️7 - Terminal Management Officer II
▪️8 - Agent Banking Officer II
▪️9 - Branch Manager Class II Branch
▪️Posted On - August 07, 2022
▪️🚩Deadline Date: August 13, 2022
▪️Find More Details here
💧💧💧💧💧
https://bit.ly/3P4CMW3
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን !

በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦

• መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

• ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው።

• የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ ጠይቀዋል።

• በመንግስት የተደረገው የደረጃ ማሻሻያ ረጅም ጊዜ በዩንቨርሲቲ ያስተማሩ መምህራንን ልምድ ያላገናዘበ በመሆኑና በመምህራን መካከል በቀጣይ ፍትሀዊ የደምወዝ ልዩነት እንዲኖር ስለማያስችል የደረጃ ማሻሻየው የመምህራንን ልምድ እና ማዕረግ ያገናዘበ እንዲሆን ጠይቀዋል።

• የረዳት ፕሮፌሰር የአካዳሚክ ማዕረግ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የ3ኛ ዲግሪ መደረጉን በተመለከተ ያለን ቅሬታ አላቸው።

• የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑ ላይ አቤቱታ አላቸው።

• የቺፍ ቴክኒካል ረዳት II የትምህርት ደረጃን ፒ ኤችዲ ዲግሪ መሆኑም ላይ አቤቱታ አላቸው።

ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጣቸው እያሉ የሚገኙት መምህራኑ ይህ ካልሆነ እስከ ስራ የማቆም አድማ መምታት ድረስ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።

👉 ትምህርት ሚኒስቴር ለሪፖርተር ፥ " ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ላይ ለውጦች ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ባለፈ የምንለው ነገር የለም። የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ አይደለም የሲቪል ሰርቪስ ጉዳይም ነው "

ያንብቡ : telegra.ph/ETH-08-07-2
via #tikvahethiopia