አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#የሊዝ_መብትን_ስለማስተላለፍ_በዋስትና_ስለማስያዝ_እና_መሠረታዊ_የሊዝ_ህግ_ድንጋጌዎች

የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት/Federal Justice and Law Institute
#የሊዝ_መብትን_ስለማስተላለፍ_በዋስትና_ስለማስያዝ_እና_መሠረታዊ_የሊዝ_ህግ_ድንጋጌዎች
ከሊዝ ሥሪት ውጪ ቦታ መያዝና መፍቀድ ስለመከልከል
ማንኛውም ሰው የከተማ መሬትን በሊዝ አዋጅ 721/2004 ከተደነገገው የሊዝ ሥረዓት ውጪ መያዝ አይችልም፡፡
ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው አካል ፈቃድ ሳይገኝ በህጋዊነት ከያዘው ይዞታ ጎን ያለን የከተማ ቦታ አሰፋፍቶ መከለልና መጠቀም አይችልም፡፡
ማኝውም ከልል ወይም የከተማ አስተዳደር በሊዝ አዋጅ 721/2004 ከተደነገገው ውጪ የከተማ መሬትን መፍቀድ ወይም ማስተላለፍ አይችልም፡፡
ነባር ይዞታዎች ወደ ሊዝ ሥሪት ስለሚቀየሩበት ሁኔታ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
በነባር ይዞታ ላይ የሰፈረ ንብረት ባለቤትነት ከውርስ በስተቀር በማንኛውም መንገድ ለሌላ ሰው ከተላለፈ ንብረቱ የተላለፈለት ሰው የቦታው ባለይዞታ ሊሆን የሚችለው በሊዝ ሥሪት መሰረት ይሆናል፡፡
ነባር ይዞታና የሊዝ ይዞታ እንዲቀላቀል ጥያቄ ቀርቦ ይዞታው እንዲቀላቀል ከተፈቀደ ጠቅላላ ይዞታው በሊዝ ሥሪት ይተዳደራል፡፡
በሊዝ የተያዘ የከተማ ቦታ አጠቃቀም እና ግንባታ ስለመጀመር
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
የከተማ ቦታ ሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግሎት ጥቅም ላይ ማዋል አለበት፡፡ ነገር ግን ባለይዞታው የቦታውን አጠቃቀም መለወጥ ከፈለገ አግባብ ላለው አስቀድሞ በማመልከት ፈቃድ ሊያገኝ ይገባል፡፡
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባታ መጀመር አለበት ነገር ግን በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ካልጀመረ ቦታውን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሊዝ ክፍያና የጠቅላላውን የሊዝ ዋጋ ሰባት በመቶ መቀጮ እንዲከፍል ተደርጎ ቦታውን አግባብ ያለው አካል መልሶ ይረከባል፡፡
ግንባታ ስለማጠናቀቅ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ በሊዝ ውሉ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ መሠረት ግንባውን ማጠናቀቅ አለበት፡፡
የግንባታ ማጠናቀቅያ የጊዜ ገደብ እንደ ሚከተለው ይሆናል፡-
ለአነስተኛ ግንባታ 24 ወራት
ለመካከለኛ ግንባታ 36 ወራት፤
ለከፍተኛ ግንባታ 48 ወራት፡፡
ከላይ የተመለከተው ቢኖርም እንደ ግንባታው ውስብስብነት እየታየ የግንባታ ማጠናቀቅያ ጊዜው ሊራዘም ይችላል፡፡ ሆኖም ለግንባታ ማጠናቀቅያ የሚሰጠው ጠቅላላ ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ፡- ለአነስተኛ ግንባታ ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር ለመካከለኛ ግንባታ ከአራት ዓመት እና ለከፍተኛ ግንባታ ከአምስት ዓመት መብለጥ አይችልም፡፡ በተጨማሪም የሊዝ ባለይዞታ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ግንባታውን ካላጠናቀቀ አግባብ ያለው አካል የሊዝ ውሉን በማቋረጥ ቦታውን መልሶ መረከብ ይችላል፡፡
የሊዝ ውል የተቋረጠበት ሰው በራሱ ወጪ ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በቦታው ላይ የሠፈረ ንብሩን ማንሳት አለበት፡፡ የሊዝ ባለይዞታው ንብረቱን በወቅቱ ካላነሳ አግባብ ያለው አካል ጀምሮ ግንባታው በፕላኑ መሰረት የተገነባ መሆኑን አረጋግጦ ግንባታውን ማጠናቀቅና መጠቀም ለሚችል ሰው በግልፅ ጨረታ ንብረቱን በመሸጥ ማስተላለፍ ይችላል፡፡
የሊዝ መብትን ስለማስተላለፍና በዋስትና ስለማስያዝ
➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠➠
ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግት ጥቅም ላይ የማንዋል ግዴታ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ መብቱን ለማስተላለፍ ወይም በከፈለው የሊዝ ክፍያ መጠን በዋስያዝ ወይም በካፒታል አስተዋፆነት ለመጠቀም ይችላል፡፡
ማንኛውም የሊዝ ባለይዞታ ባላይዞታ የሊዝ መብቱን ግንባታ ከመጀመሩ ወይም ግንባታውን በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት ከውርስ በስተቀር ማስተላለፍ የሚችለው አግባብ ባለው አካል ቁጥጥር የሚደረግበት ግልጽ የሽያጭ ሥርዓትን በመከተል ይሆናል፡፡
በሌላ አኳኳን ስምምነት ካልተደረገ በስተቀር በመሬት የመጠቀም መብት በዋስትና ሲያዝ ወይም ሲተላለፍ በመሬቱ ላይ የተገነባው ህንፃና ከህንፃው ጋረር የተያያዙ መገልገያዎች መብት አብሮ ይያዛል ወይም ይተላለፋል እንዲሁም ሕንፃና ከሕንፃው ጋር የተያያዙ መገልገያዎች በዋትና ሲያዙ ወይም ሲተላለፉ በመሬት የመጠቀም መብቱም አብሮ ይያዛል ወይም ይተላለፋል፡፡
---------------------
ግንባታ መጀመር ማለት በቦታው ላይ ለመስራት ከተፈቀደው ግንባታ ወይም ሕንፃ ቢያንስ የመሠረት ሥራ መሥራትና የኮለን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችሉ የኮለን ብረቶች የማቆም ሥራ ማጠናቀቅ ነው
ግንባታ በግማሽ ማጠናቀቅ ማለት
ሀ/ ቪላ ሲሆን የመሠረቱን የኮለኖችና ለጣሪያ ውቅር የሚስፈልጉ ቢሞችን ሥራ ማጠናቀቅ ፤
ለ/ ፎቅ ሲሆን የመሠረቱንና ከጠቅላላው ወለሎች ውስጥ 50 የሚሆኑትን የስሌት ስራ ማጠናቀቅ ፣
ሐ/ሪል ስቴት ሲሆን የሁሉንም ብሎኮች ግንባታ እንደአግባቡ ማጠናቀቅ ነው፤
ግንባታ ማጠናቀቅ ማለት በሊዝ የተፈቀደ ቦታ ላይ እንዲገነባ የተፈቀደ ቦታ ላይ እንዲገነባ የተፈቀደን ግንባታ በተሰጠው የግንባታ ፈቃድ መሰረት ሙሉ በሙሉ መሥራትና ዋና ዋና አገልግሎቶች ተሟልተውለት ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡
ነባር ይዞታ ማለት የከተማ ቦታ በሊዝ ስርዓት መተዳደር ከመጀመሩ በፊት በሕጋዊ መንገድ የተያዘ ወይም ሊዝ ተግባራዊ ከሆነ በኃላ ለነባር ይዞታ ተነሺ በምትክ የተሰጠ ቦታ ነው፡፡
የፌዴራል የፍትህና የህግ ኢንስቲትዩት/Federal Justice and Law Institute
@lawsocieties @AleHig
https://t.me/lawsocieties
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆