አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Live stream finished (1 hour)
እጅግ በጣም አሪፍ የሆነ ውይይት ነበረን።
ስለ አደረግነው ውጤታማ የሀሳብ ልውውጥ ለተሳታፊዎች በሙሉ
#አለ_ህግ ከልብ የሆነ ምስጋና ያቀርባል።

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
ለመንግሥት ሠራተኞች የሚሰጥ የወሊድ ፈቃድ
#አለ_ህግ
==================
ለአንድ የመንግስት ሰራተኛ የተለያዩ ዕረፍት ዓይነቶች ያሉ ስሆን በፌደራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” አንቀጽ 43 ላይ የተደነገገው የወሊድ ፈቃድ ነው።
ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ፣ ከእርግዝናዋ ጋር የተያያዘ ምርመራ ለማድረግ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ደመወዝ የሚከፈልበት ፈቃድ ይሰጣታል፤
1. ከመውለዷ በፊት ዕረፍት እንድታደርግ ሐኪም ካዘዘ ደመወዝ የሚከፈልበት ዕረፍት ይሰጣታል፡፡
2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) የተመለከተው ፈቃድ እንደ ህመም ፈቃድ አይቆጠርም፡፡
3. ነፍሰጡር የሆነች የመንግሥት ሠራተኛ መውለጃዋ ሲደርስ እወልዳለሁ ብላ ከገመተችበት ቀን በፊት 30 ተከታታይ ቀናት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ፣ እንዲሁም ስትወልድ ከወለደችበት ቀን ጀምሮ 90 ተከታታይ ቀናት፣ በአጠቃላይ 120 ተከታታይ ቀናት ደመወዝ የሚከፈልበት የወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት ሠራተኛዋ የተሰጣት የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከማለቁ በፊት ከወለደች ያልተጠቀመችበትን ቀሪ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወለደች በኋላ እንድትጠቀምበት ይደረጋል፡፡
5. ሠራተኛዋ የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ሲያልቅ ያልወለደች እንደሆነ እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የምትቆይበት ዕረፍት በበጀት ዓመቱ ካላት የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ወይም በበጀት ዓመቱ የዓመት ፈቃድ የሌላት እንደሆነ ከሚቀጥለው የበጀት ዓመት የዕረፍት ፈቃዷ ይተካል፡፡
6. ሠራተኛዋ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተወሰነውን የወሊድ ፈቃድ ከጨረሰች በኋላ ብትታመምና ተጨማሪ ፈቃድ የሚያስፈልጋት መሆኑ በሀኪም ከተረጋገጠ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 43(1) በተደነገገው መሠረት የሕመም ፈቃድ መውሰድ ትችላለች፡፡
7. ማንኛዋም ስድስት ወር የሞላት ነፍሰጡር የሆነች የመንግስት ሠራተኛ የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከመውሰዷ በፊት ጽንሱ የተቋረጠባት ከሆነ ይህንኑ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ ስታቀርብ የ60 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
8. የቅድመ ወሊድ ፈቃድ ከወሰደች በኋላ የጽንስ መቋረጥ ካጋጠማት የወሰደችው የቅድመ ወሊድ ፈቃዷ ተቋርጦ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) የተመለከተው የ90 ቀን የድህረ ወሊድ ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
9. ከሦስት እስከ ስድስት ወር ባለው የእርግዝና ጊዜ ውስጥ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚከፈልበት 30 ተከታታይ ቀን ፈቃድ ይሰጣታል፡፡
10. ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡
Via Tsegaye Demeke Lawyer

#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com
#አለ_ህግ
ፍርድ ቤት፣
በችሎት ውስጥ መደረግ ያለባቸው ተግባራት


• ዳኞች ወደ ችሎት ሲገቡም ሆነ ሲወጡ ችሎት ውስጥ ያሉ ስዎች ከተቀመጡበት መነሳት፤
• ባለጉዳዮች የተስተካከለና የሰዎችን አትኩሮት ሊሰብ የማይችል አለባበስ ልበስ ይኖርባቸዋል፤
•የዳኞችን ትዕዛዝ ብቻ ጠብቆ መናገር ይኖርባቸዋል፤

• የተጠየቁ ጥያቄዎችን ግልፅና አጭር በሆነ መልኩ መግለፅ አለባቸው!

• ዳኛን ለማናገር የአክብሮት ቃል ማለትም ክቡር ዳኛ/ክብርት ዳኛ የተከበረው ችሎት የሚሉትን በጠቀም መናገር ይኖርባቸዋል፤

• አላስፈላጊ ፍርሃት፣ መጨናነቅ፣ መሸማቀቅና መርበትበትን በማስወገድ ሀሳብን ያለፍርሃት መግፅ ያስፈልጋል፤
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ
#አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.co
የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸው የባንክ ሒሳቦች በሙሉ እንዲዘጉ ታዘዙ
👉ትዕዛዙን ያልፈጸመ መሥሪያ ቤት በጀት አይለቀቅለትም ተብሏል
ሰኞ ሚያዝያ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች በተለያዩ የግል ባንኮች የከፈቷቸውን ሒሳቦች በአስቸኳይ እንዲዘጉ፣ ይህንንም ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ፡፡
የገንዘብ ሚኒስቴር በግል ባንኮች ውስጥ አካውንት ከፍተው ገንዘብ እያንቀሳቀሱ ነው ለተባሉ መሥሪያ ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ፣ በግል ባንኮች ውስጥ ያላቸውን ሒሳብ ካልዘጉ ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠንቅቋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተጻፈው ይኸው ደብዳቤ፣ በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅና የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ መሠረት፣ የመንግሥት ገንዘብ ወይም ገቢ የሚደረገው በብሔራዊ ባንክ ወይም ብሔራዊ ባንክ በሚወክለው ባንክ እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በዚህ ድንጋጌ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሰየመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ብቻ መሆኑን የሚኒስትር ዴኤታው ደብዳቤ ያመለክታል ሲል ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
ሆኖም በአሁኑ ወቅት በርካታ የመንግሥት ባለበጀት መሥሪያ ቤቶች የመንግሥት ገንዘብ ለማንቀሳቀስ በግል ባንኮች ሒሳብ በመክፈት ላይ መሆናቸውንና ይህንን ማቋረጥ እንደሚኖርባቸው በመታመኑ ዕርምጃው እንደተወሰደ ታውቋል፡፡
_____
አዲስ ማለዳ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.co
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
የሰብዓዊ_መብቶች_ዓለም_አቀፍ_ቃል_ኪዳኖች_በአማርኛ፣_2001_ዓ_ም.pdf
621.5 KB
International Covenant on Civil and Political Rights (የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳኖች) በ2001 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (በቀድሞ አጠራር የአትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን) በአማርኛ የተዘጋጀ
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇👇
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
ሉሲ ኢንሹራንስ በሚከተሉ የስራ መደቦች ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
Position:-
1 - Engineering Officer
2 - Board Secretary
📚ትምህርትዓይነትእናደረጃ:-
BSc in Mechanical or Automotive Engineering or directly related field of study, BA/LLB Degree in Management, Law or relevant field of study.
🇪🇹 የስራ ቦታ ፡ አዲስ አበባ
🧭የምዝገባ ጊዜ ፡ እስከ ማያዚያ 09 /2014 ዓ.ም
🔔ስለ ስራው ሙሉ መረጃ ለማየት እና ለማመልከት ቀጣዩን ሊንክ ይጠቀሙ
https://jobs.amazonethiopia.com/job/lucy-insurance-s-c-3/

https://t.me/LawyerEthiopia
#Selale University#

▪️Required No - 38 positions 0 EXP
▪️Professions - agribusiness-management,animal-science,anthropology,business-law,commercial-law,communication,dairy-and-meat-technology,development-evaluation,doctor-of-veterinary-medicine,ecology, 🔴environmental-and-land-law, forest-science,forestry,journalism,law,natural- resource-management,peace-security,philosophy,psychology,social-anthropology,soil-and-water-conservation-engineering,special-need-education,tax-and-investment-law,veterinary-pathology,veterinary-pharmacology
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3qXjKaH

▪️Deadline - Apr 12/2022
የወራሽነት የምስክር ወረቀትን በተለከተ የሚቀርብ የተቃውሞ አቤቱታ፣ የማስረጃውን ትክክለኛነት እና ህጋዊነት ከማረጋገጥ ያለፈ አንድምታ የሌለው መሆኑ ከተረጋገጠ ማስረጃውን የሰጠው ፍርድ ቤት የማስረጃው ይሰረዝልኝ ጥያቄን ማስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ፣
በሐሰት ለተገኘ የወራሽነት ማስረጃ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ተፈጻሚነት የሚኖረው፣

የይርጋ ጊዜ የአስር አመት የይርጋ ጊዜ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1000፣
1677 1845 እና 1846
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 እና 359
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና
👇👇👇👇 Join and #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
አለ_ህግ Ale Hig, Ale Law Societies #አለ_ህግባለሙያ፣ ነፃ የህግ ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ የውልና የክስ ቅፆች (ፎርሞች) ፤ የህግ ጉዳዮችን 🔴ሁሉንም ሕጎች በአንድ ላይ ያገኙበታል 🔴 All in one, for All. #አለ_ህግ መሰረታዊ የህግ መረጃና እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው።
ይህን ሊንክ በመጫን በቴሌግራም ተቀላቀሉን https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties
email us: lawsocieties@gmail.com
contact us via telegram Bot @LawsocietiesBot

follow us on Facebook page
https://www.facebook.com/lawsocieties/
238_ባንኰች_ባገኙት_ንፋስ_አመጣሽ_ገቢ_ላይ_ግብር_የሚከፈልበትን_ሁኔታ_ለመወሰን_የወጣ_መመሪያ_ቁጥር.pdf
192.5 KB
ባንኮች ባገኙት ንፋስ አመጣሽ ገቢ ላይ ግብር የሚከፈልበትን ሁኔታ
ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 238/2013 #አለ_ህግ #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
#አለ_ህግ #Ale_Hig Lawsocieties

በፌስቡክ Facebook
https://www.facebook.com/lawsocieties/

በቴሌግራም Telegram
https://t.me/lawsocieties

በ ቲክቶክ Tiktok
tiktok.com/@lawsocieties

በዩቲዩብ YouTube
https://youtube.com/channel/UCXYKAPt4crrhEx62KvcPzBw
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና በአክስዮን ማኅበር መካከል ያላቸዉ መሰረታዊ አንድነት እና ልዩነት
1. አባልነት/Membership: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የሚያስፈልጉ ሁለት/2/ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ አክሲዮን ማኅበር ደግሞ ለመጀመር ቢያንስ አምስት/5/ አባላት ያስፈልጋሉ ፡፡
በአክሲዮን ማህበር ውስጥ በከፍተኛው የአባላት ብዛት ላይ ገደብ የለም ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ቢበዛ 50 አባላት ብቻ ሊኖሩት ይችላል ፡፡
2. ዳይሬክተሮች/ Directors፡ -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአንድ ወይም በብዙ ሥራ አስኪያጆች የሚተዳደር ሲሆን አክሲዮን ማኅበሩ ደግሞ አነስተኛ ቁጥራቸው ሦስት በሚሆኑ ዳይሬክተሮች የሚተዳደር ነው ፡፡
3. ፕሮስፔስተስ/ Prospectus: -
አንድ አክሲዮን ማኅበር ለአክሲዮኖቹና ለዕዳ ወረቀቶቹ ደንበኝነት እንዲመዘገብ ህዝቡን መጋበዝ ይችላሉ ፣ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ካፒታሉን ለማሳደግ ወደ ሕዝብ መሄድ አይችልም ፡፡
4. አነስተኛ ምዝገባ /Minimum subscription:-
በአክሲዮን ኩባንያ ውስጥ ሁሉም ካፒታል መፈረም አለባቸው እና ከምዝገባ በፊት የካፒታልው 25% መከፈል አለበት። ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሙሉ በሙሉ በተከፈለ ካፒታል ይመዘገባል ፡፡
5. የማህበሩ ዋና ገንዘብ / capital፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ዋና ገንዘብ ከ15,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡ በአክሲዮን ኩባንያ ደግሞ መነሻ ካፒታሉ ከ50,000 ብር በታች መሆን አይችልም፡፡
6. የተገደበ ሀላፊነት/Limited liability: -
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሆነ በአክስዮን ማህበር በማህበሩ ባዋጡት/ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ሀላፊነት አላቸዉ፡፡ ማህበርተኞቹም ለማህበሩ ግዴታዎች አላፊ የሚሆኑት ባላቸዉ ድርሻ ልክ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም በተገደበው የኃላፊነት ደንብ መሠረት የኩባንያው አበዳሪዎች በድርጅቱ በራሱ ንብረት ላይ ብቻ የይገባኛል ጥያቄ ለማቅረብ የተገደቡ ሲሆን የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በግል በያዙት ንብረት ላይ ምንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ የላቸውም ፡፡
7. የህግ ስዉነት/Legal personality፡-
ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርም ሆነ አክስዮን ማህበር የራሳቸዉ የሕግ ሰዉነት ያላቸዉ ሲሆን በስማቸዉ የመክሰስ ሆነ የመከሰስ እንዲሁም ማንኛዉንም ስራ የመስራን ሰፊ መብት ተጎናፀፈዋል፡፡
8. የአክስዮኖችን ማስተላለፍን በተመለከተ/Transferable shares፡-
አክስዮን ማህበር ምንም እንኳን በማኅበሩ አንቀጾች ውስጥ የአክሲዮን ነፃ ዝውውርን መገደብ ቢቻልም (አንቀጽ. 333 (1) የአክሲዮን ኩባንያ አጠቃላይ መርሆዎች በነፃነት የሚተላለፉ በመሆናቸው በአክሲዮን ገበያ ሊሸጡ ወይም ሊገዙ ይችላሉ ፡፡ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአባላቱ መካከል በነፃነት የሚተላለፉ ሲሆን ለሌሎች ግን እንደ አክስዮን ማህበር እንደፈለጉ በነፃነት የሚተላለፍ አይደለም ምክንያቱም ሲመሰረትም ቤተሰባዊ እና ቅርርብን መሰረት ተደርጎ የሚመሰረት ማህበር በመሆኑ ነው፡፡
☞ሰናይ ጊዜ
© Yilkal
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Entrust🔷ETC)
የአክስዮን ማህበር መመስረት የሚያስገኙ ጥቅሞች፡-
የአባላቱ ሀላፊነት የተወሰነ መሆኑ፤
የአክስዮን አባላቱ ቢሞቱም በወራሾች በቀላሉ መቀጠል ስለሚችል የማይሞት መሆኑ፤
አክስዮን ማህበር ትልቅ ካፒታል የሚጠይቅ ስለሆነ ግዙፍ ኢንተርፐራይዞች እንዲኖሩ ማድረግ መቻሉ፤
ጠንካራ የገንዘብ አቅም መኖሩ፤
ድርሻዉ በቀላሉ የሚተላለፍበት እና የአባላትም ቁጥር የሚቀያየር መሆኑ፤
ቦንድ/የብድር ሰነድ/መሸጥ የሚችል መሆኑ፤
የተለያየ የአስተዳደር አካላት ማለትም የዳይሬክቶሮች ቦርድ፤ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ እና የዉጪ ኦዲተር ያሉት መሆኑ፤
የመስፋፋት እድል መኖሩ፤
የተበተነ አደጋ መኖሩ/Diffused risk/
ከ50 በላይ አባላት ያሉት ማቋቋም ሲፈለግ፤
መዋጮ ከህዝብ መሰብሰብ መቻሉ ማለትም ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለማቋቋም የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ለህዝብ አስነግሮ ካፒታል መሰብሰብ አይችልም ፡፡ በመሆኑም ብዙ ገንዘብ በሚጠይቁ ዘርፎች ለመሰማራት ካፒታልን ከህዝብ መሰብሰብ የሚያስችል ስለሆነ አክስዮን ማህበር ተመራጭ ያደርገዋል፡፡
ለሶስተኛ ወገኖች የበለጠ አስተማማኝ እና ተቋማዊ ቅርፅ የያዘ መሆኑ፤ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አሰራሩ ቀላል፤ በህግ የሚደረግበት ቁጥጥር የላላ፤ የአስተዳደር ስርዓቱ በአንፃራዊነት የማያስተማምን ስለሆነ 3ኛ ወገኖችን ብዙ አያስተማምንም፡፡ በተቃራኒዉ አክስዮን ማህበር አሰራሩ ዉስብስብ፤ዝርዝር የህግ ቁጥጥር ያለበት፤ አስተዳደሩ በብዙ አካላት የተደራጀ ስለሆነ ለአባላትም ሆነ ከአክስዮኑ ጋር ግኑኙነት የሚፈጥ የ3ኛ ወገኖች መብት ለማስጠበቅ አስተማማኝ ነው፡፡
አንዳንድ የስራ ዘርፎች በህግ በግልጽ በአክስዮን ማህበር ብቻ የሚሰሩ መሆናቸዉ፤ ምሳሌ ባንክ እና ኢንሹራንስ ስራ በሀላፊነቱ የጠወሰነ የግል ማህበራት የማይሰራ መሆኑ፤
ስለሆነም የአክስዮን ማህበር ከላይ ባየናቸዉ ባህሪያት ያሉት ከአባላቱ የተለየ ሀላፊነት ያለበት ራሱን የቻለ የህግ ሰዉነት ያለዉ ድርጅት መሆኑ ተመራጭ የሚያደርገዉ ቢሆንም የራሱ ሆነ ድክመቶች ያሉት ሲሆን እንደሚከተለዉ እናያለን፡፡
የአክስዮን ማህበር መመስረት ያሉት ጉዳቶች፡-
አክስዮን ማህበር ለመመስረት ዉስብስብ እና አስቸጋሪ ስነ ስርዓት መጠየቁ፤
በምስረታ ሂደት የተለያዩ ባለሙያዎች አስፈላጊ መሆናቸዉ ምሳሌ መመስረቻ ፁሁፍን እና መተዳሪያ ደንቡን ለማዘጋጀት የህግ ባለሙያ ማስፈለጉ፤ በአይነት የሚደረገዉን መዋጮ ለመወሰን የሂሳብ ሰራተኛ እና ማህንዲስ አስፈላጊ መሆኑ በምስረታ ሂደትን ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፤
በቀጥታ የንብረቱ ባለቤት ያለመሆን፤
የዉሳኔ መዘግየት መኖሩ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ወሳኝ ጉዳይ ላይ የጠቅላላ አባላትን እና የተለያዩ አካላትን ዉሳኔን የሚያስፈልግ መሆኑ፤
በጥቂት እጅ የወደቀ እና የተንኮል አስተዳደር የመፈጠር እድሉ ሰፊ ነው ምክንያቱም ባላክስዮኖቹ በየሀገሩ የተበታተኑ እና የማይተዋወቁ በመሆናቸዉ በቀላሉ ለመቆጣጠር እና መብታቸዉን በተደራጀ መልኩ ለማስከበር ይቸገራሉ፡፡ ምሳሌ፡- የባንክ አባሎች የማይተዋዉ ብዙ ቁጥር ያለቸዉ በመሆኑ ቦርድ እና ስራ አስኪያጆችን በየቀኑ ለመቆጣጠር ያስቸግራል፡፡
ሚስጢር ያለመጠበቅ ችግር

ሰናይ ጊዜ 👏
YilkalG.
#አለ_ህግ #አለ_ስራ #አለ_ዜና #አለ_መዝናኛ #አለ_ጤና #አለ_መረጃ #አለ_ትምህርት #አለ_ሁሉም #Ale_Law #አለ_ጠበቃ #አለ_ህግአማካሪ #አለ_ነገረፈጅ
#አለ_Share..... 👇👇👇👇👇👇
#Share #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት ጠበቆች በሙሉ

በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 59 (1) መሰረት የኢትዮጵያ የፌደራል ጠበቆች ማህበር የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ የአመራር አባላት ተመርጠው ወደ ስራ የተገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በአዋጁ አንቀጽ 57 (4) መሰረት ማንኛውም ጠበቃ ወይም የጥብቅና ድርጅት የጥብቅና ፈቃድ ሲሰጠው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የማህበሩ አባል እንደሚሆን የተደነገገ በመሆኑ ለማህበሩ አባልነት ምዝገባ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000469494218 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን SLIP በማቅረብ በአካል ባምቢስ በሚገኘው የፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ወይም አራዳ የፍትሕ አካላት ህንጻ 9ኛ ፎችቅ በሚገኘው የማህበሩ ቢሮ በመቅረብ ምዝገባ ማከናወን የሚገባችሁ ሲሆን በአካል መቅረብ የማትችሉ በኦንላይን ከዚህ በታች በተመለከተው የዌብ አድራሻ በመጠቀም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

https://www.eag.gov.et/am-et/አገልግሎታችን
ማሳሰቢያ፡-
• ምዝገባው የሚካሄደው በፍትህ ሚኒስቴር ዋናው መስሪያ ቤት ባለው ቢሮ እና አራዳ በሚገኘው የፍትሕ አካላት ህንጻ 9ኛ ፎች የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ቢሮ ብቻ ነው፤
• ምዝገባው የሚካሄደው ከሚያዝያ 7 ቀን እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ብቻ ነው፤
• በኦን ላይን ሲመዘገቡ የጥብቅና ፍቃድ ደብተራችሁ ፎቶዎቹ የሚገኝበትን ገጽ እና የመጨረሻ የታደሰበትን ገጽ ስካን በማድረግ ማያያዝ ይኖርባችኋል፣
• ለምዝገባ ክፍያ ገቢ ተደረገበት ደረሰኝ በኦን ላይን መያያዝ ሲኖርበት በአካል ለሚደረግ ምዝገባ ደግሞ ኮፒው መቅረብ ይኖርበታል፣
• እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ያልተመዘገበ ማንኛውም ጠበቃ የማህበሩ አባል እንዳልሆነ ተቆጥሮ የጥብቅና አገልግሎት ከመስጠት ይታገዳል፣

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ከ11 ዓመት በፊት የፈረመችውን የቤት ሰራተኞች መብት ህግ እንድታጸድቅ ተጠየቀች

ኢትዮጵያ ስምምነቱን ብትፈርምም እስካሁን ህግ አድርጋ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አላጸደቀችውም፡፡
https://am.al-ain.com/article/ethiopia-requested-to-ratify-domestic-labor-law-signed-11-years-ago