አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.88K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Tips of the Day Wisdom
Be mindful. Be grateful. Be positive. Be true. Be kind. So Let us be grateful to the people who make us happy; they are the charming gardeners who make our souls blossom.
Note.
When a new day begins, dare to smile gratefully. When there is darkness, dare to be the first to shine a light. When there is injustice, dare to be the first to condemn it. When something seems difficult, dare to do it anyway. When life seems to beat you down, dare to fight back. When there seems to be no hope, dare to find some. When you’re feeling tired, dare to keep going. When times are tough, dare to be tougher. When love hurts you, dare to love again. When someone is hurting, dare to help them heal. When another is lost, dare to help them find the way. When a friend falls, dare to be the first to extend a hand. When you cross paths with another, dare to make them smile. Always Dare to Be. Good morning. Danrabi
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ የዐቃቤ ሕግ ሚና‼️‼️🔴
=========================
ዐቃቤ ሕግ በሕግ ጠባቂነቱ መንግስት የሚያወጣቸውን የተወሰኑ ሕጐች መከበራቸውን የሚያረጋግጥ የመንግስት አካል ነው፡፡ ሕግን የተላለፉ ሰዎችን ለሕግ በማቅረብ ሕግና ስርዓት በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲሰፍን ማድረግ ዋነኛ የዐቃቤ ሕግ ተግባር ነው፡፡ ይህ የመንግስት አካል እንደሌሎች የመንግስት ተቋማት ሁሉ የእለት ተዕለት ስራውን ሲያከናውን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት የተረጋገጡ የዜጐች ሰብአዊ መብቶችና መሠረታዊ ነፃነቶች የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት አለበት፡፡

በመሆኑም በመንግስት ተቋምነቱ ከሌሎች የመንግስት አካላት ጋር ያለው ህገ መንግስቱን የማክበርና የማስከበር የወል ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ ዐቃቤ ሕግ በሕግ አስከባሪነቱ እና ጠባቂነቱ ለሕግ የበላይነት እና ለሰብአዊ መብቶች ጥበቃ በወንጀል ፍትህ አስተዳደር ውስጥ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይኖርበታል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ እኤአ ሴፕቴምበር 1990 ባወጣው የዐቃብያነ ሕግ ሚናን በሚመለከት መመሪያ(UN Guidelines on the Role of prosecutors) በወንጀል ፍትህ ሂደት ያላቸውን ከፍተኛ ሓላፊነት በተመለከተ በአንቀጽ 12 ስር አቃብያነ ህግ በህጉ መሰረት ግዴታቸውን ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ መወጣት እንዳለባቸው ከማስቀመጡ በተጨማሪ ሰብዓዊ ክብርን የመጠበቅ፣ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና እንከን የሌለው የወንጀል የፍትህ ስርአት እንዲኖር አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚኖርባቸው አስቀምጧል፡፡

ከተጠቀሰው የተባበሩት መንግስታት መመሪያ በሚቀራረብ ሁኔታ ዐቃቤ ሕግ ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚያደርገው አስተዋፅጾ ከምርመራ አንስቶ የተጠርጣሪው ጥፋተኝነት ተረጋግጦ ቅጣት እስኪጣልበት ወይም ንፁህ መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችል በብሄራዊ ህጎችም ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ይህንንም እንደሚከተለው በዝርዝር እናያለን፡፡

1. #ዐቃብያነ ሕግ ከፖሊስ ምርመራ ጋር በተያያዘ ስላለባቸው ኃላፊነት

በሕብረተሰብ ውስጥ ሰላምን የሚያደፈርስ እንቅስቃሴ ወይም ሕገወጥ ተግባር ተፈጽሞ ሲገኝ አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ የወንጀል ምርመራ ስራ በዋነኛነት በፖሊስ አካላት እንደሚካሄድ የታወቀ ነው፡፡ የወንጀል ምርመራ ስራ ሂደት በባህሪው የዜጐችን መብት የመገደብ ወይም የመንካት ሁኔታ የሚያስከትል በመሆኑ ከዜጐች የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ አንፃር በጥንቃቄ ሊከናወን የሚገባው ተግባር ነው፡፡

የወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 8/2/ ዐቃቤ ሕግ ተግባሩን በሚያከናውንበት ጊዜ አስፈላጊ የሆነውን ትዕዛዝና መመሪያ ለፖሊስ የመስጠትና ፖሊስ በሕጉ መሠረት ግዴታውን መወጣቱን ማረጋገጥ እንዳለበት መደንገጉ ፖሊስ የምርመራ ስራውን ሲያከናውን የግለሰቦችን ሰብአዊ መብቶች ባከበረና በሕግ በተወሰኑ ስርዓቶች መሰረት ኃላፊነቱን መወጣቱን ዐቃቤ ሕግ እንዲቆጣጠር የታለመ እንደሆነ ይታመናል፡፡

በቅርብ አመታት ወጥተው በፌዴራል መንግስት ተፈፃሚ ከሆኑ ሕጐች መካከልም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር 313/95 እና የኢፌዲሪ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 471/98 ዐቃቤ ሕግ የፖሊስን ተግባር ሕጋዊነት የሚቆጣጠርበት ድንጋጌ አካተዋል፡፡ በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አዋጅ ቁጥር 313/95 አንቀፅ 7/9/ ፌዴራል ፖሊስ “የወንጀል ምርመራን በተመለከተ ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ የሚሰጠውን ትዕዛዝ” እንደሚፈፅም የተደነገገ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 471/98 አንቀፅ 23/3/ ስር ደግሞ ፍትህ ሚኒስቴር (ፌዴራል ዐቃቤ ሕግ)

“በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቁ ወንጀል ተፈፅሟል ብሎ ሲያምን ምርመራ እንዲደረግ ያዛል፣ በቂ ምክንያት ሲኖር የተጀመረ ምርመራ እንዲቆም ወይም ተጨማሪ ምርመራ
እንዲከናወን ያደርጋል...”

በማለት ደንግጓል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ከተለያዩ አካላት ወንጀል ስለመፈፀሙ ጥቆማ ሲደርሰው፣ ፖሊስ አላግባብ ምርመራ አላጣራም አለኝ የሚል አቤቱታ ሲቀርብለት ወዘተ ምርመራ እንዲጀመር ለፖሊስ ትዕዛዝ የሚሰጥ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ከሕግ ውጪ ምርመራ እየተጣራብኝ ነው የሚል አቤቱታ ሲቀርብለት እና በሌሎች ምክንያቶች አላግባብ በፖሊስ የተጀመሩ ምርመራዎች መኖራቸውን ካረጋገጠ የተጀመረ ምርመራ እንዲቋረጥ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡ የክልል ዐቃቤ ሕግ ተቋማትም የክልል ፖሊሶች ከሚፈፅሙት የምርመራ ተግባር ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ስልጣን እንዳላቸው ይታመናል፡፡

ከላይ ከቀረቡት ዝርዝር ድንጋጌዎች ዐቃቤ ህግ በራሱ ህግ አስፈጻሚ ብቻ ሳይሆን የፖሊስ አባላትም የዜጐችን ሰብአዊ መብቶች የሚመለከቱ ሕግጋት በትክክል ማክበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት እና በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ቁልፍ የሆነ ድርሻ እንዳለው ለመረዳት ይቻላል፡፡

2. #ዐቃብያነ ህግ ከክስ ጋር በተያያዘ ስላለባቸው ኃላፊነት ዐቃቤ ሕግ በፖሊስ ተጣርቶ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ በማየት
የዜጐችን የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብት ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ፡-

ተጨማሪ ደጋፊ ማስረጃ ሊገኝ ይችላል ብሎ ካመነ ተጨማሪ ምርመራ እንዲደረግ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 38/ሐ/ መሠረት ለፖሊስ ትዕዛዝ የማስተላለፍ፣
ተጠርጣሪን ጥፋተኛ ለማድረግ የሚያስችል በቂ ማስረጃ የለም ብሎ ካመነ ደግሞ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 42/1/ሀ/ መሠረት ክስ ያለማቅረብ ወይም
ክስ ለመመስረት እና ተከሳሽን ለማስቀጣት የሚያስችል በቂ ማስረጃ አለ ብሎ ካመነ ደግሞ ክስ በማዘጋጀት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት በማቅረብ ተገቢውን ክርክር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ላይ ክስ የሚያቀርበው ሕዝብን በመወከል ስለሆነ፣ የሕዝብ ጥቅም የሚጠበቀው ጥፋተኞች ሲቀጡ እና ንፁህ የሆኑ ሰዎች ከክስ ነፃ ሲሆኑ በመሆኑ በመጀመርያ ክስ ለመመስረት በቂ ማስረጃ መኖሩን የማረጋገጥ፣ በክሱ መሰማት ሂደት የተከሳሽን ንፁህ መሆን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ካገኘ ወይም ጥፋተኛ ሊያስደርጉ የሚችሉ ማስረጃዎች በሂደት የጠፉ ከሆነ ወዘተ ደግሞ ክሱን ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡ፀጋዬ ደመቀ ሎየር ገፅ ተገኘ
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
👍1
Attorney I

Nyala Insurance S.C


Position: Attorney I

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: Competitive and Attractive

Application Deadline: Aug, 2/2021 (7 days left)

Nyala Insurance Share Company (NISCO) wants to hire a qualified, competent and motivated candidate for the following position on a permanent basis.

Position: Attorney I

Qualification and Experience:

LLB Degree

Minimum of 1 year experience as an attorney, preferably in financial industry

Post available: 2 (Two)

Duty Station: Addis Ababa

Remuneration: Nyala Insurance offers a competitive and attractive remuneration package

Age: Not more than 35

How to apply

Interested applicants who fulfill the above requirements are invited to submit their application with a non-returnable copy of CV and credentials to the under-mentioned postal address or in person at our HO (Protection House) 3rd floor, Room No. 307 located around 22 Mazorial Mickey Leland Road.

NYALA INSURANCE S.C. (NISCO)

Protection House

P.O.Box: 12753

Addis Ababa

Only shortlisted applicants will be contacted and invited for an interview
#join #join #Share #Share #Share
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Senior Attorney

Nyala Insurance S.C

Position: Senior Attorney

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: Competitive and Attractive

Application Deadline: Aug, 2/2021 (7 days left)

Nyala Insurance Share Company (NISCO) wants to hire a qualified, competent and motivated candidate for the following position on a permanent basis. 

Position: Senior Attorney

Qualification and Experience:

LLB Degree

4 years experience as an attorney, preferably in the financial industry

Post available: 1 (One)

Duty Station: Addis Ababa

Remuneration: Nyala Insurance offers a competitive and attractive remuneration package

Age: Not more than 35

How to apply

Interested applicants who fulfill the above requirements are invited to submit their application with a non-returnable copy of CV and credentials to the under-mentioned postal address or in person at our HO (Protection House) 3rd floor, Room No. 307 located around 22 Mazorial Mickey Leland Road.

NYALA INSURANCE S.C. (NISCO)

Protection House

P.O.Box: 12753

Addis Ababa

 

Only shortlisted applicants will be contacted and invited for an interview

#join #join #Share #Share #Share
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Explanatory_Note_for_the_Provisions_of_Federal_Administrative_Procedure.pdf
2 MB
#join #join #Share #Share #Share
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
በቅርቡ በወጣው የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 1183/2012) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ጉባዔ የማብራሪያ ሰነድ በአማርኛ እና እንግለዝኛ አዘጋጅቷል።

ለተረቀቁ ሕጎች የተሟላ የማብራሪያ ሰነድ እንዲኖር የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ጉባዔ የጀመረው እንቅስቃሴ የሚበረታታ ነው። ለአዘጋጆቹ ምስጋናችን ይደረሳቸው።
.........‼️እናመሰግናለን‼️
#lawsocieties............
Attorney I Job at Hibret Bank - Career Opportunity in Ethiopia New

Job Category: Legal

Job Type: Full-Time

Deadline of this Job: 31 July 2021

Duty Station: Addis Ababa

Posted: 26-07-2021

Start Publishing: 26-07-2021

Stop Publishing (Put date of 2030): 26-07-2065

Job Description

Vacancy title: Attorney I
Category: Legal 

Jobs at: Hibret Bank

Deadline of this Job:
31 July 2021  

Duty Station:
Within Ethiopia , Addis Ababa , Horn of Africa

Summary
Date Posted: Monday, July 26, 2021 , Base Salary: Not Disclosed

JOB DETAILS:
Job Type: Full Time
Location: Hiber Tower, 14 floor, Head Office Building around Senga Tera area Bahir Dar, West
Category: Banking & Insurance - Legal
Job Overview
Salary Offer: As per Company Scale
Experience Level: Junior
Total Years Experience: 2

Job Requirement
Educational Qualification: LLB Degree in Law
Work Experience: 2 years as Junior Attorney or equivalent experience in the Banking Industry OR 2 years as Attorney I or equivalent experience
Place of work: For North West District Office Based in Bahir Dar
Experience in Months: 24

Level of Education: Bachelor Degree

Job application procedure
Interested applicants should apply in person along with non-returnable updated CV and copies of relevant credentials from the date of this vacancy announcement until July 30, 2021 to:
Hibret Bank S.C. Human Capital Business Partnering Department P.O.Box 19963 Hiber Tower, 14 floor, Head Office Building around Senga Tera area Addis Ababa
#join #join #Share #Share #Share
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መቁረጥ እና ሕጋዊነቱ
የመንግሥት ሠራተኛ ማነው ?
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ፌደራሊዝም ሥርዓትን በሚከተሉ ሃገራት ሁለት መንግሥታት አሉ፡፡ እነዚህም የፌደራል እና የክልል መንግሥታት ይሰኛሉ፡፡ እንዲህ ባለው ሁኔታ የመንግሥት ሠራተኛ ስንል በእነዚህ መንግሥታት ሥር ተቀጥረው የሚሰሩትን የሚያካትት ነው፡፡ ፌደራል መንግሥቱም ሆነ ክልሎች ቀጥረው የሚያሰሯቸውን ሠራተኞች የሚያስተዳድሩባቸው አዋጆች አውጥተው ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ ለዚህ ጽሑፍ አላማ ስንል የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 እናያለን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በመንግሥት ባለቤትነት ሥር የሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ሥር የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ይሰኛል፡፡ እነዚህ ሠራተኞች በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ ከመንግሥት አስተዳደራዊ ቁጥጥር ውጪ ባለመሆናቸው እና ቀጣሪያቸው መንግሥት በመሆኑ ለዚህ ጽሑፍ አላማ ሲባል የመንግሥት ሠራተኛ ልንላቸው እንችላለን፡፡
የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚቆረጠው በምን አግባብ ነው?
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በፌደራል መንግሥቱ ሥር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ ነው፡፡ በዚህ ህግ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በምን አኳኋን ሊቆረጥ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል፡፡ የአዋጁ አንቀፅ 9 (2) የደመወዝ ክፍያ በሚለው ርዕስ እንዲህ ይነበባል፡፡
የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት፣
ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም፡፡.....................................................ይቀጥላል
https://www.facebook.com/Negerefej/
👍3
Law Part 2.pdf
7.3 KB
Share 'Law Part 2.pdf'
👍1
LAW part 1.pdf
180 KB
Share 'LAW part 1.pdf'
PART 3 LAW.pdf
22 KB
Share 'PART 3 LAW.pdf'
Part 4.pdf
5.7 KB
Share 'Part 4.pdf'
በዚህ መሰረት ለዝግታችሁን እንዲረዳችሁ በጥያቄያችሁ መሠረት ወደ ተግባር የተቀየረ ነው።
Exit Exam‼️🔴❗️
በዚህ መሰረት ለዝግታችሁን እንዲረዳችሁ በጥያቄያችሁ መሠረት ወደ ተግባር የተቀየረ ነው።
በዚህ መሰረት ለዝግታችሁን እንዲረዳችሁ በጥያቄያችሁ መሠረት ወደ ተግባር የተቀየረ ነው።
#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
Attorney I x2 at Nyala Insurance Share Company (NISCO)

Company: Nyala Insurance Share Company (NISCO)

Location: Ethiopia

State: Addis Ababa Jobs

Job type: Full-Time

Job category: Legal
Job Description

Position: Attorney I

– Post available: 2 (Two)
– Duty Station: Addis Ababa
– Remuneration: Nyala Insurance offers a competitive and attractive remuneration package
– Age: Not more than 35

Qualifications/Skills
Qualification and Experience:
• LLB Degree
• Minimum of 1 year experience as an attorney, preferably in financial industry


Method of Application

Interested applicants who fulfill the above requirements are invited to submit their application with a non-returnable copy of CV and credentials to the under-mentioned postal address or in person at our HO (Protection House) 3rd floor, Room No. 307 located around 22 Mazorial Mickey Leland Road.

NYALA INSURANCE S.C. (NISCO)
Protection House
P.O.Box: 12753
Addis Ababa

Closing Date: August 2, 2021

#join #join #Share #Share #Share
https://t.me/lawsocieties
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
የግልግል ዳኝነት አሠራር ሥርዓት በኢትዮጵያ ከአዋጅ ቁጥር 1237/2013 አኳያ (ክፍል አንድ)
----------------------------------------------

• የግልግል ዳኝነት ምንነት
በአዋጁ ቁጥር 1237/12 ስር ለግልግል ዳኝነት ግልጽ የሆነ ትርጉም ተሰጥቶት አይገኝም፡፡ ይሁንና የብላክስ ሎ (arbitration)ግልግል ተብሎ በአማርኛ ለሚጠራው ቃል የሰጠው ትርጉም ስንመለከት ግልግል ማለት አንድ እና ከዛ በላይ በሆኑ ገለልተኛ እና የሚሰጡት ውሳኔ የአስገዳጅነት ውጤት በሚኖረው ዳኞች አማካኝነት ግጭት ውስጥ የገቡ ሰዎች ጉዳያቸውን በስምምነት የሚፈቱበት ሂደት እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ ይህ የግጭት መፍቻ መንገድ ከመደበኛው የፍርድ ቤት ስርአት ጋር የተቀራረበ ሲሆን ገለልተኛ የሆነ ሶስተኛ ወገን በዳኝነት ተሰይሞ አለመግባባቱንም ለመፍታት በሙሉ ስልጣን እና ሀላፊነት የሚሰራበት ስርአት ነው፡፡ ዳኛው የሁለቱንም ወገን መከራከሪያ ነጥብ እና ማስረጃ ሰምቶ በመመዘን አስገዳጅ ውሳኔ የመስጠት ሀላፊነት አለበት፡፡ ከመደበኛው ፍርድ ቤት የሚለየው ገላጋይ ዳኛው በተከራካሪዎች ነጻ ፍቃድ የሚመረጥ መሆኑ እና በሚወሰነው ውሳኔ ላይ ይግባኝ የማይጠየቅበት መሆኑ ነው፡፡በግልግል ዳኝነት ዉስጥ ያሉ ተከራካሪ ወገኖች ዳኞችን፣ የክርክር ቦታዉን፣ በክርክሩ ተፈፃሚነት ያለዉን ህግ የመምረጥ ነፃነቶች አሉዋቸዉ፡፡ በመሆኑም ይህ ሂደት ከፍርድ ቤት በተለየ ሁኔታ ተከራካሪ ወገኖች በጉዳያቸው የተሻለ ተሳትፎ ለማድረግ የሚስችላቸው ፣ ጉልበት፤ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ የግጭት አፈታት ስርአት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

አዋጁ ለግልግል ዳኝነት ትርጉም ያልሰጠ ቢሆንም "የግልግል ዳኝነት ስምምነት" ማለት ከውል ወይም ከውል ውጭ ባለ ሕጋዊ ግንኙነት ሊፈጠር የሚችልን ወይም የተፈጠረን አለመግባባት በሙሉ ወይም በከፊል በግልግል ዳኝነት ለመፍታት የሚፈፀም ስምምነት እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ እንዲሁም "የግልግል ዳኝነት ውሳኔ” ማለት አለመግባባቶችን ለመፍታት በቋሚነት በተደራጀ የግልግል ተቋም(arbitration insitution ) ወይም በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት በጊዜያዊነት በሚቋቋም የግልግል አካል( ad hoc arbitral body) የሚሰጥ ውሳኔ እንደሆነ ሲያስቀምጥ “የግልግል ዳኛ” ማለት በተዋዋይ ወገኖች ወይም በሦስተኛ ወገን የሚሰየም ገለልተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሰው እንደሆነ ይደነግጋል፡፡

በሌላ በኩል ፍርድ ቤቶች በአዋጁ ተለይቶ ከተሰጣቸው ሥልጣን ለምሳሌ የግልግል ዳኝነት ውሳኔን ማስፀም፣ ጊዜያዊ የመጠባበቂያ እርምጃ ትዕዛዝ መስጠትን የመሳሰሉትን ከማድረግ በስተቀር ፣ በግልግል ዳኝነት በሚታዩ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንደማይገቡ አዋጁ ይደነግጋል፡፡

• የግልግል ዳኝነትና የእርቅ አስፈላጊነት
የግልግል ዳኝነትና የዕርቅ አሠራር ሥርዓት መዘርጋት የአለመግባባት መፍቻ አማራጮችን በማስፋት ፍትሕ የማግኘት መብትን ለማሟላት አጋዥ በመሆኑና በተለይም የኢንቨስትመንትና ንግድ ነክ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና በዘርፉ እድገት አስተዋፅኦ ያለው መሆኑ ፣የተዋዋይ ወገኖችን ወጪ በመቀነስ፣ ምስጢርን በመጠበቅና ልዩ ሙያ ያላቸው ባለሙያዎች በዳኝነት እንዲሳተፉ በማድረግ እንዲሁም ቀላልና ለተዋዋይ ወገኖች ነፃነት ያለው ሥነ ሥርዓት ለመጠቀም በመፍቀድ የተቀላጠፈ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ የግልግል ዳኝነትና የዕርቅ አስፈላጊነትን የሚያመለክቱ መሆናቸውን ከግልግል ዳኝነትና የዕርቅ አሰራር ስርዓት አዋጅ መግቢያ መገንዘብ ይቻላል፡፡

በህገ መንግስቱ ፍትህ የማግኘት መብት በተመለከተ አንቀጽ 37 ስር እንደተደነገገው ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም በሌላ ህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት እንዳለው ያመለክታል፡፡ በዚሁ መሰረት አዋጁ ከህገ መንግስቱ ድንጋጌ ጋር የሚጣጣም እና ባለጉዳዮች ጉዳያቸውን በአማራጭ የሙግት መፍቻ መንገድ እንዲፈቱ የሚያስችላቸው ነው፡፡

በመሆኑም የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በግልግል ዳኝነት የሚታዩ ጉዳዮችን ለመለየት ፣ሂደቱ የሚመራበትን እና ውሳኔ የሚፈጸምበትን አጠቃላይ ማዕቀፍ ለመደንገግ እና ከግልግል ዳኝነትና ከዕርቅ ጋር በተያያዘ የዳበሩ ዓለም አቀፍ አሠራሮችንና መርሆችን ታሳቢ በማድረግ በሥራ ላይ ያለ ሕጎችን ማሻሻል ይህ አዋጅ በስራ ላይ ውሏል፡፡

• የግልግል ዳኝነት አይነቶች
የግልግል ዳኝነትን ከሚገዛበት ህግ (governing law) እና ከሚያስተዳድራቸው አካላት ማለት ተከራካሪ ወገኖች (parties to dispute) የንግድ ስፍራ ወይም ዜግነት አንፃር በመመልከት በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡

1. ብሄራዊ የግልግል ዳኝነት(domestic arbitration)
በግልግል ዳኝነት ሂደት የሚሳተፉ ተከራካሪ ወገኖች የሀገር ውስጥ ብቻ ከሆኑ ማለትም የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ሰው ወይም ድርጅት በጉዳዩ ላይ ከሌለበት እና ለግልግሉ መፍቻ በአገልግሎት ላይ የሚውለው የሀገር ውስጥ ህግ((domestic or national law) ከሆነ የግልግል ዳኝነቱ ብሄራዊ የግልግል ዳኝነት ሊባል ይችላል፡፡
2. አለምአቀፍ የግልግል ዳኝነት(international arbitration)
የግልግል ዳኝነቱ አለም አቀፍ የሚሆነው ተዋዋይ ወገኞች የግልግል ስምምነት በሚፈጽሙበት ወቅት ዋነኛ የቢዝነስ ቦታቸው በሁለት በተለያየ ሀገራት የነበረ ሲሆን፣ በግልግል ዳኝነት ስምምነቱ የተመረጠ የግልግል ዳኝነቱ ሕጋዊ መቀመጫ ወይም፣ በንግድ ወይም በውል ግንኙነቱ ውስጥ ያለ ዋነኛ ግዴታዎች የሚፈፀሙባቸው ወይም አለመግባባቱ የተከሰተበትና የተያያዘበት የተዋዋይ ወገኞች ዋነኛ የቢዝነስ ቦታ ውጭ ሀገር ሲገኝ እና ተዋዋይ ወገኞች የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ ጉዳይ ከአንድ በላይ በሆኑ ሀገሮች ጋር የተያያዘ መሆኑን በግልፅ ሲስማሙ ነው፡፡

• የግልግል ዳኝነት ስምምነት (arbitration agreement)
የግልግል ዳኝነት ስምምነት ህጋዊ ግንኙነት ያላቸው አካላት የተፈጠረን ወይም ወደፊት የሚፈጠር ያለመግባባት ፍርድ ቤት ሳይሄዱ በግልግል ለመፍታት የሚስማሙበት የስምምነት ሰነድ እንደመሆኑ መጠን የህግ ስርዓትን ወይም ፎርምን መከተል እንዳለበት አዋጁ ያስቀምጣል፡፡ይሀውም፡- በዋናነት የግልግል ዳኝነት ስምምነት በጽሁፍ መሆን ያለበት ሆኖ የግልግል ዳኝነት በጽሁፍ እንደተደረገ የሚቆጠረው በቃል፣ በድርጊት ወይም በሌላ አኳኋን የተደረገ ቢሆንም ይዘቱ ተመዝግቦ የሰፈረ፣ በሁሉም ተዋዋይ ወገኖች እና ሁለት ምስክሮች ሲፈረምበት፡ በኤሌክትሮኒክ መገናኛ ዘዴ የተደረገ ከሆነ መረጃውን በተፈለገ ጊዜ ጥቅም ላይ ለማዋል ተደራሽ ሆኖ የሚገኝ ሲሆን የጽሁፍ ፎርም እንዳሟላ ይቆጠራል፡፡
ተከራካሪዎች የግልግል ዳኝነት ስምምነት ማድረጋቸው የሚኖረው ህጋዊ ውጤትን ስንመለከት ከተከራካሪዎች አንዱ ይህን ስምምነት ባለማክበር ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ቢወስደው ሌላኛው ወገን በመጀመረያ ደረጃ መቃወሚያነት በማንሳት ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ እንዳያይ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ፍርድ ቤቱም ይህንን ተቃውሞ በመመርመር ጉዳዩን ከማየት ተቆጥቦ ተከራካሪዎች አለመግባባታቸውን በግልግል እንዲፈቱ ሊያሰናብታቸው ይችላል፡፡ይሁንና የግልግል ዳኝነት ስምምነቱ የማይፀና ወይም ተፈፃሚ የማይሆን በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ይችላል፡፡ በሌላ በኩል የግልግል ዳኝነት ስምምነቱን መኖር በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አለማንሳት የግልግል ዳኝነት ስምምነቱን ቀሪ እንደሆነ ያስቆጥረዋል፡፡
👍1
• ለግልግል ዳኝነት የማይቀርቡ ጉዳዮች
ተከራካሪዎች ጉዳያቸውን በግልግል ለመፍታት ሙሉ ነፃነት ያላቸው ቢሆንም በግልግል ዳኝነት መፈታት የማይችሉ ጉዳዮች በአዋጁ ተዘርዝረው ይገኛሉ፡፡እነዚህም፡-
• የፍች፣ የጉዲፈቻ፣ የአሳዳሪነት፣ የሞግዚትነት እና የውርስ ጉዳዮች፣
• የወንጀል ጉዳዮች፣
• የግብር ጉዳዮች፣
• መክሰር ላይ የሚሰጥ ውሳኔ፣
• የንግድ ማሕበራት መፍረስ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ፣
• የሊዝ ጉዳይን ጨምሮ አጠቃላይ የመሬት ጉዳዮች፣
• አስተዳደራዊ ውሎች በልዩ ሁኔታ በሕግ ካልተፈቀደ በስተቀር፣
• የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ፤
• በሕግ ለሚመለከታቸው አስተዳደራዊ አካላት በተሰጠ ሥልጣን ሥር የሚሸፈኑ አስተዳደራዊ አለመግባባቶች፤ እና በግልግል እንዳይታዩ በሕግ የተከለከሉ ሌሎች ጉዳዮች ናቸው፡፡

ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ተከራካሪዎች ገዳያቸውን መፍታት የሚችሉት በፍርድ ቤት ሂደት ብቻ ይሆናል ማለት ነው፡፡

• በግልግል ዳኝነት ስምምነት ላይ ተፈፃሚ ስለሚሆኑ ሕጎች
የግልግል ዳኝነትን ከፍርድ ቤት ስርዓት ከሚለየው ስርዓት የግልግል ዳኝነቱ የሚገዛበትን ህግ የመምረጥ ነፃነት አንዱ መሆኑን ተመልክተናል፡፡በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ ተፈፃሚነት የሚኖረው ህግ ተዋዋይ ወገኖች የመረጡት የግልግል ዳኝነት ህግ ይሆናል ማለት ነው፡፡ይህ ሳይሆን ቀርቶ መቀመጫውን በኢትዮጵያ ባደረገ የግልግል ዳኝነት ስምምነት ላይ ተዋዋይ ወገኖች ህግ ያልመረጡ እንደሆነ የግልግል ዳኝነትና ዕርቅ አሰራር ሥነ ስርዓት ቁጥር 1237/12 ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
ይሁንና ስምምነቱን በራሱ ለመፈጸም የማይቻል ሆኖ ሲገኝ ወይም የአዋጁ አስገዳጅ ድንጋጌዎችን የሚጻረር ሲሆን የተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ በዚህ መሠረት ተፈጻሚ ሊሆን የማይችል የተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ሲያጋጥም ተዋዋይ ወገኖች በሚመርጡት ሌላ የግልግል ሕግ ወይም በአዋጁ ድንጋጌዎች መሠረት ግልግሉ ይታያል፡፡

ዓለም አቀፍ በሆኑ የግልግል ዳኝነት ጉዳዮች ላይ ተዋዋይ ወገኖች ተፈፃሚ እንዲሆን የመረጡትን መሠረታዊ ሕግ ጉባዔው(የግልግል ዳኞች) የመጠቀም ግዴታ አለበት፡፡ ግልጽ የሆነ ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በስተቀር በተዋዋይ ወገኖች የሚደረግ የትኛውም የሕግ ምርጫ ስምምነት ከጉዳዩ ጋር የተገናኘውን የሌላ ሀገር መሠረታዊ ሕግ የሚመለከት እንጂ የግጭት ሕግ እንዳልሆነ ይገመታል፡፡

በተዋዋይ ወገኖች በስምምነት የተመረጠ ሕግ ከሌለ ጉባዔው ከጉዳዩ ጋር ቅርበትና አግባብነት ያላቸውን ሕጎች በመምረጥ ተፈፃሚ ያደርጋል፡፡ ጉዳዩ ዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ይዘት የሌለው ከሆነ ጉባዔው የኢትዮጵያን ሕግ ብቻ ተፈፃሚ የሚያደርግ ሆኖ በርትዕ ወይም የታወቁ የንግድ ልምዶችን መሠረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት የሚቻለው ተዋዋይ ወገኖች ለጉባዔው ይህንን ዓይነት ሥልጣን በግልጽ ከሰጡ ወይም ተፈፃሚው ሕግ ይህን ለማድረግ ሥልጣን የሚሰጠው ከሆነ ብቻ ነው፡፡

• ስለ ግልግል ዳኞች ብዛት እና አሰያየም
ተዋዋይ ወገኖች የግልግል ዳኞቹን ብዛት በስምምነት መወሰን ይችላሉ፤ይሁንና የዳኞቹ ብዛት ጎዶሎ ቁጥር መሆን አለበት፡፡

የዳኞችን ብዛት በስምምነት መወሰን ያልቻለ እንደሆነ የግልግል ዳኞች ብዛት ሦስት እንደሚሆን በአዋጁ እንቀፅ 11 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በአዋጁ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በስተቀር ተዋዋይ ወገኖች የግልግል ዳኞች አሰያየም ሥነ-ሥርዓትን በስምምነት ሊወስኑ፣ የግልግል ዳኝነት ተቋማት ወይም ሶስተኛ ወገን የግልግል ዳኞችን እንዲሰይሙላቸው ሊስማሙ ይችላሉ፡፡ በዚህ መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልረሱ በአዋጁ አንቀፅ 12 የተደነገጉ ዝርዝር ሁኔታዎች እንደየአግባብነቱ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

• የግልግል ዳኞች መብትና ግዴታ

ማንኛውም ሰው ዳኛ እንዲሆን ጥያቄ ሲቀርብለት የጥቅም ግጭት፣ ገለልተኛነቱን እና ነፃነቱን ሊያውክ የሚችል ወይም ምክንያታዊ ጥርጣሬ ሊያሳድር በሚችል ደረጃ የቤተሰብ፣ የብድር፣ የንግድ ወይም የንብረት ባለቤትነት ግንኙነት ከተዋዋይ ወገኖች ጋር ካለው ወይም ካጋጠመው ወዲያውኑ ማሳወቅ አለበት፡፡

የግልግል ዳኛ ለሥራው መሰየሙን የተቀበለ እንደሆነ መስማማቱን በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት፡፡ የግልግል ዳኛ የአገልግሎት ክፍያ የማግኘት እና ለወጣው ወጪ የመካስ መብት አለው፡፡ የግልግል ዳኛ ሥራውን በቅልጥፍና መስራትና የግልግል ሂደቱ ያለአግባብ እንዳይራዘም ወቅቱን ጠብቆ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ ለግልግል በቀረበው ጉዳይ ላይ ጠበቃ፣ አማካሪ፣ አስማሚ ወይም በፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ከዚህ በፊት የተሳተፈ ሰው በዛው ጉዳይ ላይ የግልግል ዳኛ ሆኖ ማገልገል አይችልም፡፡ በግልግል ዳኝነት ሂደቱ አግባብ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር የግልግል ዳኛ ተዋዋይ ወገኖችን በተናጠል ማግኘት አይችልም፡፡ የግልግል ዳኞች ከተዋዋይ ወገኞች ማንኛውንም ዓይነት ስጦታ መቀበል አይችሉም፡፡

በሌላ በኩል የግልግል ዳኞችን መቃወም ስለሚቻልበት ሁኔት አዋጁ ያስቀመጠ ሲሆን ይህም የአንድን ዳኛ መመረጥ መቃወም የሚቻለው ገለልተኛነቱን እና ነፃነቱን ወይም በግልግል ስምምነቱ ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን የማያሟላ መሆኑን አሳማኝ ጥርጣሬ ውስጥ የሚከቱ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ብቻ ነው፡፡

በተጨማሪ አንድ ወገን ራሱ በመረጠው ዳኛ ወይም በምርጫው ሂደት በተሳተፈበት ዳኛ ላይ ተቃውሞ ማቅረብ የሚችለው ዳኛው ከተመረጠ በኋላ በሚያውቀው ምክንያት ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም የግልግል ዳኛው ስራውን ባግባቡ ማከናወን ካልቻለ ወይም ያለበቂ ምክንያት ካዘገየ በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ከሀላፊነት ይነሳል፡፡በዚሁ መሰረት ዳኛው በራሱ ፍቃድ ካልተነሳ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ላይ ካልደረሱ ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ማመልከት የሚቻል ሲሆን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ይግባኝ የሚቀርብበት አይደለም፡፡
(ክፍል ሁልት ይቀጥላል)
Source:- FDRE Attorney General
👍2