አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#አዲሱ_የካሳ_ህግ_ማብራሪያ

አዲሱ የካሳ አዋጅ ቁጥር 1161/2012 አንቀጽ 2(2) የንብረት ካሳ ማለት የመሬት ይዞታውን እንዲለቅ ለሚወሰንበት ባለይዞታ በመሬቱ ላይ ለሰፈረው ንብረት ወይም ላደረገው ቋሚ ማሻሻያ በዓይነት ወይም በገንዘብ ወይም በሁለቱም የሚከፈል ክፍያ ነው በማለት ይደነግጋል።
#ቋሚ ማሻሻያ ማለት በይዞታው ላይ የሚሰራ የምንጣሮ፣ ድልደላ እርከን ስራ፣ ውሃ የመከተር ስራ እና የግቢ ንጣፍና ማስዋብ የመሳሰሉት ስራዎች ይጠቃለላል በማለት ይደነግጋል ፡፡ በመሆኑም አዲሱ አዋጅ የተሻለ ነገር ይዞ የመጣው ካሳ የሚከፈለው ለሰፈረ ንብረት እና ለተደረገ ቋሚ ማሻሻል እንደሆነ ይደነግጋል፡፡
#ቋሚ ማሻሻል የሚለው አሁንም ሌላ ውዝግብ የሚያስነሳ ነው ምክንያቱም ከተዘረዘሩት ድርጊቶች ውጪ ያደረገው ለምሳሌ መሬት በተለያየ መንገድ ለም እንዲሆን፣ ምርታማ እንዲሆን የሰራው ስራ በየትኛው ነው ሚካተተው? ምንጣሮ ነው?
#አዲሱ_ አዋጅ_የያዛቸው_ትሩፋቶች
(1) #የቀዳሚነት መብት፡-
ቀድሞ በነበረው አዋጅ 455/97 ያልነበረ ነገር ግን አዲሱ አዋጅ ቁጥር 1161/11 አካቶ ያወጣው ሰዎች ቀድሞ ለፍተው ባለሙት የመሬት ይዞታቸው አቅም ያላቸው በሆኑ ጊዜ በከተማ ፕላን መሰረት ለብቻቸው ወይም በጣምራ ማልማት የሚችሉበት የቀዳሚነት መብት በአንቀጽ 7 ስር ማጎናፀፋ በጣም ጥሩ የሚባል ነው፡፡
(2) #ካሳ የማግኘት መብት:-
በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1161/11 አንቀፅ 8(1)(ሰ) ስር የልማት ተነሺውን ማስነሳት የሚቻለው ለተነሺው ካሳ ከተፈለ እና ምትክ ቦታ ወይም ቤት ከሰጠ በኋላ መሆን እንዳለበት አዋጁ ይደነግጋል፡፡በመሆኑም ሰዎች በይዞታቸው ካሳም ሳይከፈላቸው ምትክ ቦታም ሳይሰጣቸው እንዲነሱ ተደርጎ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው የነበሩ ባለይዞታዎች በጣም ብዙ የነበሩ በመሆኑ ይህ አዋጅ ህዝቡ ውስጥ የነበረው ችግር ለመፍታት ተነሺዎች ከመነሳታቸው በፊት አስቀድመው ካሳ እና ምትክ ቦታ ማግኘት እንዳለባቸው መደንገጉ በሕግ ደረጃም ቢሆን ጥሩ የሚባል ነው፡፡
(3) #ካሳ በወቅቱ ካልተከፈላቸው መልሶ የመያዝ መብት
ተነሺዎች የካሳ ግምት በጹሑፍ እንዲያውቁ ከተደረገ ቀን ጀምሮ በሶስት ወር ውስጥ ካሳ ካልተከፈላቸው በመሬት ይዞታቸው ከቋሚ ተክልና ግንባታ በስተቀር ሌሎች ስራዎች መስራት ይችላሉ በማለት ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪ በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ካሳ ካልተከፈው በፕላን የሚፈቀድ እና ቀጣይ የቦታውን የልማት ወጪ በመንግስት ላይ የማያበዛ በመሬቱ ላይ ማንኛውም ስራ መስራት ይችላል በማለት ይደነግጋል።
ቢሆንም ግን ይህ ድንጋጌ እጅግ አሻሚ ነው ምክንያቱም መንግስት ካሳ ካልከፈለ በፕላን መሰረት ባለይዞታ ማንኛውንም ዓይነት ስራ መስራት እንደሚችል ከተደነገገ በኋላ በመንግስት የልማት ወጪ የማያበዛ ስራ ማለቱ ምን ማለት ነው? እጅግ በጣም ግልጽ ነት የጎደለው ነው፡፡
(4) #ተመጣጣኝ ካሳ ክፍያና ምትክ ቦታ
አዲሱ አዋጅ በመሬቱ ላይ ለተፈራ ንብረት፣ ቋሚ ማሻሻያ ባለይዞታው ንብረቱን ማዘዋወር የሚችል ከሆነ የማዘዋወሪያ ወጪ ወይም የትራንስፖርት/የማጓጓዣ ወጪ ከመክፈሉ በተጨማሪ ከገጠር መሬት ይዞታ ለሚነሳ የመሬት በላይዞታ ተነሺ ከተወሰደበት መሬት ተመጣጣኝ የሆነ ምትክ መሬት እና መሬት ይዞታው ከመልቀቅ በፊት ባሉ ሶስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ምርት ያመረተበትን ምርት በወቅታዊ ዋጋ ተሰልቶ በ15 ተባዝቶ ይከፈላል በማለት ይደነግጋል፡፡
(5) #በአዋጅ አንቀጽ 2(4) የልማት ተነሽ ድጋፍ የመሬት ባለይዞታ ከመሬቱ በጊዜያዊም ሆነ በቋሚነት ሲነሳ ከአዲሱ አከባቢ ጋር መላመድ እንዲችል ከንብረት እና ከልማት ተነሽ ካሳ በተጨማሪ በዓይነት ወይም በገንዘብ የሚሰጥ ድጋፍ ነው፡፡ it is promising move አዲስ እና በጣም ጥሩ የሚባል ነው ነገር ግን ይህ ነገር የሚወሰነው በክልሎች መመሪያ ነው፣ መች ይሁን የሚወጣው? ባይወጣስ?
(6) #የወል ይዞታዎች ላይ ካሳ የሚከፈል መሆኑ
በእርግጥ ወል ይዞታና የመንግስት የወል የተቀላቀለ በመሆኑ በወል ይዞታዎች ላይ ካሳ ሲከፈል አይታይም፣ በዚህ አዋጅ የወል ይዞታ ማለት ከመንግስት ወይም ከግል ይዞታነት ውጭ የሚገኝና የአከባቢው ማህበረሰብ ለግጦሽ፣ ለደንና ለማህበራዊ አገልግሎት በጋራ የሚጠቀሙበት የመሬት ይዞታ ነው በማለት አንቀፅ 2(11) ይደነግጋል።
በመሆኑ የወል ይዞታዎች አገኘን ተብሎ በየ ደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካል መሸንሸን አይችሉም ማለት ነው፡፡ የወል መሬቱ የካሳ ስሌት የወል መሬቱ ይሰጥ የነበረው ጥቅም ወይም ጥቅሙ የቀረባቸውን የአኗኗር ዘይቤ ወይም መተዳደሪያ መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡ይሰጥ የነበረው ጥቅም ወቅታዊ የገበያ ዋጋ መሰረት ያደረገ ማለት ነው? አሁንም ግልፅነት ይጎድለዋል፡፡የወል መሬቱ የተወሰደባቸው የወል መሬቱ ተጠቃሚ አካል የተገኘው ገንዘብ ለማህበረሰቡ አባላት እኩል ሊካፈል ወይም በዓይነት ሊጠቀሙበት የሚችሉበትን መንገድ መቅረጽ አለበት በማለት አንቀፅ 13(3) ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም የወል መሬት ያለካሳ የሚወስድ የመንግስት አካል ከድርጊቱ መቆጠብ አለበት፡፡
(7) #የልማት ተነሺ ካሳ የሚከፈል መሆኑ
የከተማ መሬት ባለይዞታ ከይዞታው በቋሚነት ተነሽ በሚሆንበት ጊዜ የሚከፈለው የልማት ተነሺ ካሳ እና የሚሰጠው ምትክ ቦታ ነው በማለት ይደነግጋል፡፡
የልማት ተነሺ ካሳ ማለት ባለይዞታው የመሬት ይዞታውን ሲለቅ በመሬቱ ላይ የመጠቀም መብቱ በመቋረጡ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት ለማካካስ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ይህ አይነቱ ካሳ የመጠቀም መብት በመኖሩ ብቻ የሚገኝ የካሳ ዓይነት ነው፡፡ ለከተማ ተነሺ በአከባቢ ለነበረው የማህበራዊ ትስስር መቋረጥና ለሚደርሰው የስነ-ልቦና ጉዳት ማካካሻ ይከፈለዋል መጠኑ በደንብ ይወሰናል 13(4)(ሠ) በማለት ይደነግጋል፡፡
ግን ይህ ካሳ በተግባር ተከፍሎ አያውቅም። #የማህበራዊ ትስስር መቋረጥና የስ-ልቦና ጉዳት ካሳ ማለት ለተጎጂ ከነበረበት አከባቢ በመነሳቱ የነበረው ማህበራዊ ትስስር በመቋረጡ የሚከፈል የጉዳት ማካካሻ ክፍያ ነው፡፡
በመሆኑም በከተማ መሬት ይዞታ የሚነሳ ሰው የልማት ተነሺነት ካሳ፣ምትክ ቦታ፣ቤት ፈርሶበት ከሆነ የቤት መስሪያ ዋጋና በቦታው እስኪገባ ባለው 2 ዓመት የሚኖርበት ቤት ወይም የወቅታዊ የኪራይ ገንዘብ ግምት እና የማህበራዊ ትስስር መቋረጥና የስነ-ልቦና ጉዳት ካሳ ይከፍለዋል፡፡በመሆኑም እነዚህ መብቶች በቀድሞ አዋጅ ያልነበሩ በአዲሱ አዋጅ የተካተቱ ጥሩና ተስፋ ሰጪ የመሬት ካሳ መብቶች ናቸው፡፡
#መልሶ ማቋቋም ፡- በአዋጅ አንቀጽ 16 የክልል መንግስት ወይም የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ አስተዳደር ለካሳ ክፍያ እና ለመልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ያቋቁማል በማለት ይደነግጋል፡፡ መልሶ ማቋቋም ማለት በተወሰደው መሬት ምክንያት የሚያገኙት ጥቅም ለሚቋረጥባቸው ተነሺዎች ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ የሚያስችል የሚሰጥ ድጋፍ ነው ። ጥያቄው ግን መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ባይቋቋምስ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሰት እርከን ካሳን በሚመለከት አቤቱታ የሚሰማ ኮሚቴ አንኳን አላቋቋሙም መልሶ ማቋቋሚያ ፈንድ ያቁማሉ
ከ ኢትዮ ህግ ኧረ በህግ ገፅ ተገኘ
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ልዩ የውክልና ስልጣን/በተለምዶ ሙሉ ውክልና ይሉታል/
==========================
• በተወካዩ የሚፈጸሙ ተግባራትን እያንዳንዳቸውን በግልፅ የሚያመለክት የውክልና ስልጣን
የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ፣ የመለወጥና የንብረቱን ባለቤትነት ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ተወካይ ንብረት በመያዣ አስያዞ በወካዩ ስም ከባንክ የመበደር ስልጣን አለው፡፡ የውክልና ማስረጃ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን የሚሰጥ ከሆነ ሕጋዊ ውጤቱ በውክልና ማስረጃው ላይ ከተጻፉት ተግባራት በተጨማሪ በውክልና ማስረጃው የተገለፁትን ጉዳዮችና እንደ ጉዳዩ ክብደትና እንደ ልምድ አሰራር በውክልና ማስረጃው የተገለጹትን ጉዳዮች ተከታታይና ተመሣሣይ የሆኑ አስፈላጊ ተግባራትን የመፈፀም ስልጣንን የሚያካትት መሆኑ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2206 ንዑስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል፡፡ በመሆኑም በውክልና ማስረጃ ቤት የመሸጥ፣ የመለወጥና ለሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ስልጣን ያለው ሰው ከዚህ መለስ የሆኑ ተግባራትን የመፈፀም ችሎታ እንዳለውና በተለይም ንብረቱን በመያዣነት ለማስያዝ የሚያስችል ስልጣን እና ችሎታ እንዳለው “ለራሱ ዕዳ ዋስትና እንዲሆን አንዱን የማይንቀሣቀሥ ንብረትን በእዳ መያዣነት አድርጎ ለመስጠት የሚችለው የማይንቀሣቀሰውን ንብረት ለመሸጥ ችሎታ ያለው ሰው ነው” ከሚለው በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 3049 ንዑስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 17320 ቅጽ 5፣ ፍ/ህ/ቁ. 2026/1/፣ 3049/2/
ተወካዩ ከአስተዳደር ሥራ በቀር ሌላ ሥራ ለመስራት የሚያስፈልግ ሲሆን ልዩ ውክልና እንዲኖረው አስፈላጊ መሆኑንና ተወካዩ ልዩ የውክልና ሥልጣን ከሌለው በቀር የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ለመሸጥ ወይም አስይዞ ለመበደር የማይችል መሆኑ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 ንዑስ አንቀፅ 1 እና ንዑስ አንቀፅ 2 ተደንግጓል፡፡ በወካዩ ስም የሚዘዋወር ንብረት ማናቸውንም ፎርማሊቲ እያሟላ እንዲያዛውር፣ በስሙ እንዲዋዋል የውክልና ስልጣን የተሰጠው ተወካይ በወካዩ ስም የሚገኝ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመሸጥ የመለወጥ ስልጣን የለውም፡፡ በፍታብሔር ህግ ቁጥር 2205 መሠረት የሚሰጥ ልዩ ውክልና በይዘቱ በልዩ ውክልና የሚፈፀሙ እያንዳንዳቸውን ተግባሮች በግልፅ የሚያመለክት መሆን ይገባዋል፡፡ የውክልና ስልጣን የሚተረጎመው ሳይስፋፋ በጠባቡ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 50985 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2204፣ 2205፣ 2181/3/
የውክልና ሰነዱ ይዘት በግልፅ ውክልና ተቀባዩ የተሰጠው ስልጣን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ የሚያስችል ስለመሆኑ እየገለፀ ስለልዩ ውክልና አስፈላጊነት የተቀመጠው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2205 በውክልና ስልጣን ሰነዱ ያለመጠቀሱ ውክልናው ልዩ የውክልና ስልጣን አይደለም ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ስለመሆኑ የሚያሳይ የሕግ ድንጋጌ የለም፡፡ ዋናውና ቁልፉ ነገር ለውክልና ተቀባዩ የተሰጡት ተግባሮች በዝርዝርና ግልጽ ሁኔታ ተጠቅሰው በውክልና ሰነዱ ላይ መገኘት እንጂ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ያለመጠቀሳቸው አይደለም፡፡ የሰነዱ ይዘት ግልጽ መሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች በውክልና ስልጣን ሰጪውና በውክልና ስልጣን ተቀባዩ አልተጠቀሱም ተብሎ ሰነዱ ዋጋ እንዲያጣ ማድረግ የተዋዋዮችን ሐሳብ ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግ በመሆኑ በውል አተረጓጎም ደንቦችም ተቀባይነት የሌለው አካሄድ ነው የሚሆነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 72337 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 2199፣ 2055
ከፀጋዬ ደመቀ ገፅ ተገኘ
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Don't see others doing better than you, Beat your own records everyday because, Success is a fight between YOU & YOURSELF. @lawsocieties
If U can not find the Brighter side of Life, Polish the Darker side..
Attitude of Adjustment is the Only Instrument to Live a Happy Life..
Have a fun-filled weekend
@lawsocieties
ነፃ የህግ ድጋፍ እና ማማከር አገልግሎት .....................📶☎️📞
Free Legal Aid .......📶☎️📞...loading.
ሶስት ናቸው…
ትልቅ ሮቶ ይዘዋል …
ላዳ አስቆሙና ሮቶውን ከላይ ጭነው እነሱ ከውስጥ ገቡ…ኋላ ወንበር

ሹፌሩን ሩቅ መንገድ ይዘውት ሄዱ…ብዙ ጉራንጉር አስገቡትና የሆነ ቤት ጋር ሲደርሱ እዚህ ጋር ነን ብለው አስቆሙት እቃቸውንም ተሸክሞ አወረደና

…"ሂሳብ" ሲል ጠየቀ ...

"የለንም" አሉት…

ወርዶ ቢለምን ምን ቢል "ዝምብለህ ንካው" የሚል ምላሽ ሰጡት…

"ጭራሽ እንድንከፍልህ ከፈለክ ዝፈንልን" አሉት…
"ዘፈን አልችልም" አለ…

"በቃ እሺ ጩኸህ #እልልል በልና እንሰጥሃለን" አሉት …
"ሰርቼ እኮ ነው ለምን ታንገላቱኛላችሁ? ይህን የሚያክል ሮቶ ጭኜ መኪናዬን በኮሮኮንች መንገድ ጎድቼ ምንም አትከፍሉኝም ?"ቢልም

"ጮክ ብለህ #እልልል ካላልክ አንሰጥህም" አሉት…

ተናደደና "ተውት በቃ ፈጣሪ የስራችንን ይስጠን" ብሎ እሱ በብስጭት እነርሱ እየተሳሳቁ ሳይቀበላቸው መኪናውን አዞሮ ሄደ…

ትንሽ እንደተጓዘ ከኋላው ስልክ ጠራ… ዞር ሲል እጅግ ውድ የሆነ የአይፎን ስልክ አንሱኝ አንሱኝ እያለ ይጮሃል …

መኪናውን ዳር አስያዘና ስልኩን አንስቶት "ሃሎ" አለ…

"ይቅርታ ወንድሜ አንተ ታክሲ ውስጥ ስልክ ጥለን ነበር" የሚል ድምፅ ተከተለ…

ማን ልበል? አላቸው … አሁን ያወረድከን ሮቶውን የጫንክልን ልጆች ነን… እባክህን ስልኩን ተባበረን

ይሄኔ ይሄ ላዳ ሹፌሩ ምን ቢል ጥሩ ነው… …
"አሁን ነዋ #እልልል" ማለት ብሎ ቃሉን እየደጋገመ እልልል… በማለት ስልኩን ከደወለለት ጆሮ ላይ ዘጋው።

★በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም!!!የሰዎችን ሀቅ መከልከል የራስን ያሳጣል።

በያላችሁበት መልካም ቀን ለይሁንላችን
በዋሱ መሀመድ‼️
ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀምና ከባድ የእመነት ማጉደል ወንጀል በመፈፀም ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ለግል ጥቅሙ ያዋለው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወሰነበት።
-------------------------------------

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው የተከሳሹ ትክከለኛ ስም “ዳንኤል በላይ” ሲሆን ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እና የአሽከርካሪነት ፍቃድ ያወጣበት ስሙ ደግሞ “ነጅሙ አደም“ ይባላል ።

ተከሳሹ የወንጀል ህግ አንቀፅ 676 (2)(ሀ) እና አንቀፅ 378 ላይ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች በመተላለፍ
ተከሳሹ በንፋስ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሙሉጌታ ሃ/የተ/የግ/ማህበር በከባድ መኪና ሾፌርነት ለመቀጠር “ነጅሙ አደም” በሚል ስም ባቀረበው የስራ ልምድ፣ የት/ት ማስረጃና የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ በድርጅቱ የቀረበለትን ፈተና በማለፍ በካባድ መኪና ሾፌርነት ተቀጥሮ እየሰራ እያለ ጥቅምት 25/2012 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ሲሆን በድርጅቱ መጋዝን ውስጥ ወደ ውጭ አገር የሚላክ ደረጃ 5 ቡና ባለ 60 እና ባለ 30 ኪሎ የዋጋ ግመቱ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 760 ኩንታል ጭኖ ከወጣ በኋላ ጥቅምት 26 / 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን ለድርጅቱ ሰራተኞች ስልክ በመደወል መኪናው ስላስቸገረኝ ጉምሩክ አካባቢ አቁሜው ወደ ቤት ሄጃለሁ መኪናውን ውሰዱ በማለት ያሳውቃቸዋል ።

የድርጅቱ ሰራተኞችም ወደ ተባለው ቦታ ሄደው መኪናውን በማግኘት በውስጡ ተጭኖ የነበረውን ቡና ግን ሊያገኙት ባለመቻላቸው ምክንያት መርመራው ተጣርቶ ክስ የተመሰረተበት ሲሆን
ዐቃቤ ህግም የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽም በፍርድ ቤት ክሱ ተነቦለት ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ያመነ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ግንቦት 2/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል መሰል አጥፊዎችን ያስተምራል ሲል በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እና በሃምሳ ሺህ ብር እንዲቀጣ ወስኖበታል
ሰበር ዜና
በዛሬዉ እለት የዳዉንት ወረዳ ፍርድቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ሞገስ ሽዋፈራ ስራቸዉን በማከናወን ላይ እያሉ አንድ ባለጉዳይ ለዉሣኔ ተቀጥሮ ባለበት ሰአት ችሎት ቀድሞ በመግባት የተጠቀለለ ፌሥታል ደኛዉ ወንበር ፊትለፊት ላይ ያሥቀምጣል።በጉዳዩ ግራ የገባዉ ዳኛ የችሎት አስከባሪ ፖሊሥ ጠርቶ ፌስታሉ እንደፈታ አድርጎ በፌሥታሉ ዉሥጥ ግለሠቡ የደኛዉን ስም ለማበላሸትና የደኝነት ስርአቱን ለማዛበትና የተዛባ የፍትህ ስርአት እንድሰፍን በማሠብ ዛሬም እንደወትሮዉ በጉቦ የሚያምን ትዉልድ በመሆኑ 120 ብር ለዳኛዉ ማባባያ እንዳቀረበለት በችሎት ታይቷል። ዳኛዉም ባለጉዳዩ ያደረገዉ ድርጊት አሣፋሪና እስካሁን ድርስ ያልተቀረፈ ችግር መሆኑን ተረድቶ ግለሠቡን ያርማል ህዝቡን ያሥተምራል ያለዉን በኢፌደሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 449(1ለ) መሠረት ቀጠሮ መሥጠት ሣያሥፈልገዉ ወዳዉኑ የሁለት ወር ቀላል እስራት እንድቀጣ ወስኖበታል። በወቅቱ ያነጋገርኩት የሥራ ባለደረባየ ዳኛ ሞገስ ሽዋፈራ ቅጣቱ ሌሎች ግለሠቦችን ከነዚህ አይነት ድርጊት እራሣቸዉን ቆጥበዉ በእዉነትና በህግ የሚያምን ትዉልድ እንድኖር ያደርጋል ብለዋል። በሌላ በኩል ለፍትሕ ስርአት የቆሙ ደኞችና ሌሎች አጋር አካላት አስፈለጊዉን ጥንቃቄና የህዝብ አደራን በታማኝነት ና በቅንንነት በማገልገል ለፍትሕ ዘብ መቆም እንዳለባቸዉና ለዳኝነት ነጻነት ዋጋ ሠተዉ በመሥራት የገቡለትን የሕዝብ አደራ አንክሮ ሰተዉ የሕዝብ እንባ ጠራጊ ሊሆኑ ይገባል በማለት አሳስቧል።
በሀብታሙ በላይ።
@lawsocieties
የመቃወም አቤቱታ/የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 እስከ 360/ > ፍርድ ከተሰጠ በኋለ የሚቀርብ ሥርዓት
=======================
1 • ተካፋይ ባልሆነበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት አስቀድሞ ለአንድ ወገን የተሰጠውን ውሳኔ ለማሰረዝ በመቃወም አመልካች የሚቀርብ አቤቱታ
የመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ክርክሩ የሚካሄደው በመቃወም አመልካች እና አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተጠቃሚ በሆነው የመቃወም ተጠሪ በሚባለው ወገን መካከል ሲሆን የዚህ ዓይነቱ ክርክር የሚቀርብበት እና የሚመራበት ስርዓት እንዲሁም የዚህ ዓይነቱን ክርክር የሚሰማው ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ከቁጥር 358 እስከ 360 ተመልክቷል፡፡ የመቃወም አቤቱታው መቅረብ የሚገባው በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 222 እና 223 ድንጋጌዎች መሰረት ክስ እና የማስረጃ መግለጫ የሚቀርብበትን ስርዓት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጎአል፡፡
የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተለይም የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሠማበት ስነ ስርዓት መሰረት ስለመሆኑ በቁጥር 360(2) የተመለከተው አስገዳጅ ድንጋጌ በቀጥታ የቀረበ ክስ እና ክርክር የሚስተናገድበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች የመቃወሚያ ክርክርን በማስተናገድ ረገድም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ ሊደረጉ የሚገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው፡፡
በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ዓይነተኛ ዓላማ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው እና በተለይም የመቃወም አመልካች የሆነው ወገን የክርክሩ ተካፋይ ባልነበረበት ጊዜ የቀረበውን የመቃወም ተጠሪ ወገን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመስቀልኛ ጥያቄ እና በማስተባበያ ክርክር ጭምር የመፈተን ዕድል እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 86398 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 222፣ 223፣ 350-360
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 አንድ የክርክሩ ተካፋይ መሆን የሚገባው ሰው የክርክሩ ተካፋይ ሳይሆን ውሳኔ ተሰጥቶ ከሆነ እና ውሳኔውም ያረፈው በአንድ የክርክሩ ምክንያት በሆነ ንብረት ላይ ሁኖ ይህንኑ የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ወገንን መብትና ጥቅም የሚነካ መሆኑ ከተረጋገጠ ፍርዱ ይኸው ወገን ባለበት እንዲታይና በሕግና በማስረጃ የተደገፈ ሁኖ ሲገኝ እንዲነሳለት የሚደነግግ ነው፡፡ አቤቱታው የሚቀርብበት ሥርዓትም በቁጥር 359 ስር በተመለከተው መንገድ መሆን እንደአለበት የተቀመጠ ሲሆን ይህ ድንጋጌ የመቃወሚያ አቤቱታ አቀራረብ በክስ አመሰራረት አይነት ሁኖ ማስረጃ ዝርዝር ሁሉ ይህንኑ ስርዓት ማሟላት እንደአለበት ያስገነዝባል፡፡ የዚህ ድንጋጌ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ ክርክሩ መኖሩን ከጅምሩ እያወቀ ውጤቱን በመጠበቅ ከፍርዱ በኋላ የፍርድ መቃወሚያ የሚያቀርበውን ወገን አቤቱታውን በመቀበል ለማስተናገድ አስፈላጊ ያለመሆኑን ሁሉ ያስገነዝባል፡፡
ይህም የክርክር አቀራረብ በቅን ልቦና የተመሰረተ ሁኖ በአነስተኛ ወጪ፣ ጉልበትና አጭር ጊዜ ፍትሐዊነት ያለውን ውሳኔ ለመስጠት የሚቻልበት አግባብ እንዲኖር እና ሕግ አውጪ ከፈለገበት አላማ ጋር መጣጣም ያለበት መሆኑም የሚታመን ነው፡፡ እንግዲህ አቤቱታውን የሚያቀርበው ወገን የቅን ልቦና ተከራካሪ ሁኖ መሰረታዊ መብቱን ማስከበር የሚችልበት የስነ ስርዓት ሕግ አግባብ እንዲኖር ሕግ አውጪ የፈለገ ሲሆን ይህንኑ መመዘኛ የሚያሟላ አቤቱታ አቅራቢ የሚቃወመው ፍርድ ዋጋ ያለው፣ ያልተፈፀመ መሆን እንደአለበትም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ ይዘት ያስረዳል፡፡ በሌላ አገላለፅ የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት ፍርድ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ያልተሻረና አፈጻጸሙም ያልተጠናቀቀ ሊሆን እንደሚገባ ሕጉ ያሳያል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 93987 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ 359
የሟች ሀብት ተጣርቶ በክፍፍሉ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ውርሱ ሲጣራ ያልተሳተፈ የሟች ወራሽ ነኝ የሚል ወገን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረብ ያለበት በውርስ አጣሪው ሪፖርትና ሪፖርቱን ባፀደቀው ፍ/ቤት ሳይሆን የክፍፍሉን ጥያቄ አይቶ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ነው፡፡ የውርስ አጣሪ ሪፖርት በፍርድ ቤት መጽደቅ በራሱ ፍርድ ሁኖ ለአፈፃፀም የሚቀርብ ሣይሆን እንደማስረጃ የሚያገለግል ነው፡፡ በመሆኑም ሪፖርቱ የማስረጃነት ዋጋ አለው ከተባለ ደግሞ የክፍፍል ክርክር ሲቀርብ በማስረጃነቱ ላይ ክርክር ቢቀርብ ክርክሩ መቅረብ ያለበት በውርስ አጣሪና ሪፖርቱን በአፀደቀው ፍርድ ቤት ነው ተብሎ ውድቅ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 45905 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ ፍ/ህ/ቁ. 944፣ 946፣ 956፣ 960
ተከራካሪ ወገኖች በፍርድ ቤት የሚያካሂዱትን ሙግት በማቋረጥ የሚያደርጉት የእርቅ ስምምነት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ተረጋግጦና ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ መባሉ የፍርድ ያህል አስገጃጅነት ያለው በመሆኑ እርቁን ያፀደቀው ፍርድ ቤት እርቁ ለሕግና ለሞራል ተቃራኒ አይደለም በእርቁ መሠረት ይፈፀም በማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሰጠውን ትእዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358 መሰረት በእርቅ ስምምነቱ መብቴ ተነክቷል በሚል ወገን ተቃውሞ ሊቀርብበት የሚችል ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 83582 ቅጽ 15
2 • በአፈጻጸም ንብረት እንዳይያዝ፣ እንዳይታገድ በንብረቶቹ ላይ መብት አለኝ የሚል በክርክሩ ተሳታፊ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን የሚያቀርበው አቤቱታ
የፍ/ብ/ህ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 ድንጋጌ አስፈላጊነት የክርክሩ አካል ያልሆኑና ፍርድ ያላረፈባቸው የ3ኛ ወገን ንብረት ሳይረጋገጥ ለፍርዱ ማስፈፀሚያነት እንዳይውሉ ለመከላከልና ባንጻሩ ፍርዱን የመፈፀም ለማስተጓጉል (እንዳይፈፀም ለሚቀርቡት በቂ ላልሆኑ አቤቱታዎችም) እልባት የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም በተያዙት ንብረቶች ላይ መብት አለኝ የሚል ወገን የሚያቀርበውን መቃወሚያና አቤቱታ ተቀብሎ መመርመር እንዳለበት የተጠቀሰው ድንጋጌም በግልፅ ያሰፈረው ነው፡፡ ይህ ከሆነ የዚሁ አንቀጽ 418(3) የአራተኛው ቅጂ ባለይዞታነትን ለማስረዳት የፅሁፍ ማስረጃ መቅረብ እንዳለበት የሚደነግግ ቢሆንም የእንግሊዘኛው ቅጂ የስነ- ስርዓት ህጉ ደግሞ ይህንኑ አንቀጽ ሲገልጽ The Claimant or 0bjector Shall adduce evidence to Show that at the date of the attachment he had Some interest in, or was possessed of the property attached ይላል፡፡ እንግዲህ ከዚህኛው የእንግሊዘኛ ቅጂ የምንረዳው ማስረጃ በማቅረብ ለአፈጻጸም የቀረበውን ንብረት ማስረዳት እንደሚቻል የሚገልጽ ነው፡፡ የአማርኛው ቅጂም ቢሆን ከፍ/ህ/ቁ/1193 (1) እና (2) ድንጋጌዎች ጋር ተደምሮ ሲታይ ሌላውን የማስረጃ አይነት በግልጽ እንዳይቀርብ የከለከለው ሆኖ አይታይም፡፡
ሰ/መ/ቁ 97094 ቅጽ 17፣ ፍ/ህ/ቁ. 1193(1) (2)፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 418
በዋናው ክርክር የሚሰጠው ውሳኔ እና በውሳኔው መሠረት ለማስፈጸም የሚደረገው ሂደት የተለያዩ በመሆናቸው በሚቀርቡት መቃወሚያዎች ላይ የሚሰጡት ውሳኔዎችም የተለያዩ ናቸው፡፡ መቃወሚያ አቅራቢው መብቱ የተነካው በአፈጻጸም ሂደቱ ከሆነ ከአፈጻጸም ሂደቱ ጋር የተያያዘ መፍትሄ ነው የሚሰጠው፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 418 መሠረት በሚቀርብ መቃወሚያ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 419 ተመልክቶአል፡፡ በዚህ መሠረት መቃወሚያው ተቀባይነት ያገኘ ከሆነ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት በከፊል ወይም በሙሉ እንዲለቀቅ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ከዚህ አልፎ በአፈጻጸም የተያዘው ንብረት ለአንድ ወይም ለሌላው ተከራካሪ ወገን ይገባል የሚል ዳኝነት አይሰጥም፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ በዋናው ክርክር የተሰጠውን ውሳኔ የሚሽር ወይም የሚያሻሽል ውሳኔ አይሰጥም፡፡ የዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት የሚቻለው ዋናውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታ ሲቀርብ ነው፡፡ ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ የአቀራረብ ሥርዓት እና የክርክር አመራር ሂደት ያለው ነው፡፡ በዚህ ረገድ ተገቢው ድንጋጌም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 358 የተመለከተው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 53607 ቅጽ 12 ፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 358፣ 418፣ 419
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 አግባብ የተሟላ ክርክርና ማስረጃ ያቀረበ ወገን አቤቱታው በመደበኛ ሙግት እንዲከናወን እንዳይጠይቅ ሕጉ ግልጽ ክልከላ ያላደረገበት ሲሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 421 ስር የተጠበቀው መብትም በሕጉ አግባብ የሚቀርቡ መቃወሚያዎች እንደተጠበቁ ሁነው አመልካቹ በምርጫው እንዲጠቀምበት የተቀመጠ እንጂ ይህንኑ ስርዓት እንዲከተል የግድ የሚደረግበት ያለመሆኑ ድንጋጌው በፈቃደኝነት የአቀራረፅ ስርዓት መቀመጡ አስረጂ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ 86133 ቅጽ 15
የቀዳሚነት መብት አለኝ በሚል መቃወሚያ አቅርቦ ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ሰው በድጋሚ ክስ ማቅረብ የተፈቀደለት በአፈፃፀም ችሎት የንብረቱ ባለመብትነት በጭብጥነት ተይዞ በመደበኛው የሙግት ስርአት አይነት ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ አንፃር ተመርምሮ ውሳኔ የሚሰጥበት ባለመሆኑ ይህንን እድል ለመስጠት ነው፡፡ አመልካቹ ይህንን መብት የሚያስከብርለት ሌላ ክስ የመሰረተ ከሆነ ግን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 421 ክስ ለማቅረብ ስለሚፈቅድ ብቻ በተመሳሳይ ጉዳይ ዳግመኛ ክስ ማቅረብ የስነ-ስርአት ህጉ አላማ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 37214 ቅጽ 9፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 421
ለጊዜው ስለሚሰጡ ማገጃዎችና ሌሎች ትዕዛዞች
=================
1. ከፍርድ በፊት ስለሚሰጥ የእስራት ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 147-150)
1.1. ከሳሹ ወይም ተከሳሹ የተከሳሽ ከሳሽ በሚሆንበት ጊዜ ሌላኛው ወገን ዋስትና እንዲሰጥ ለፍ/ቤቱ ማመልከት ይችላል፡፡
1.2. ማመልከቻው በመኃላ ቃል የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
1.3. ማመልከቻው ተቀባይነት ሊያገኝ የሚችለው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 147 (1) (ሀ) ና (ለ) ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ሲረጋገጡ ነው፡፡ ሁኔታዎቹም ሀ/ ተከሳሹ በማንኛውም ሁኔታ የዳኝነት ሥርዓቱን የሚያስናክል ድርጊት ሲፈጽም ወይም ለ/ ተከሳሹ ከኢትዮጵያ ግዛት ለመውጣት ሲዘጋጅና መውጣቱም ፍርዱን እንዳይፈጽም የሚያደርገው ሲሆን ነው፡፡
1.4. ፍ/ቤቱ ጥያቄውን ከተቀበለ ተከሳሽ ታስሮ እንዲቀርብ ያዛል፡፡
1.5. ተከሳሹ የሚፈለግበትን ዕዳ በመያዣ ካስቀመጠ የእስር ትዕዛዙ ተፈፃሚ አይሆንም፡፡
1.6. ተከሳሹ መያዣውን ካላስቀመጠ ወይም ፍ/ቤት ቀርቦ በቂ ምክንያት ካልሰጠ በቂ መያዣ እንዲያስቀምጥ ወይም ዋስ እንዲጠራ ይታዘዛል፡፡
1.7. የዋስትናው ወይም የመያዣው ዓይነትና ልክ እንዲሁም ዋስትናው የሚቆይበት ጊዜ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 148(1) መሠረት ይወሰናል፡፡
1.8. ተከሳሹን ለማቅረብ ዋስ የሆነ ሰው ሳያቀርብ የቀረ እነደሆነ ተከሳሹ ሊከፍል የሚገባውን ገንዘብ እንዲከፍል ይገደዳል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 148(2))፡፡
1.9. በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 149 በተደነገገው መሠረት የዋስትና ግዴታ ሊወርድ ይችላል፡፡ ዋስትናው ሲወርድ ተከሳሹ ሌላ ዋስ ማቅረብ ወይም ተመጣጣኝ የሆነ መያዣ ማስቀመጥ አለበት፡፡
1.10. ተከሳሹ ይህን ግዴታ ለመፈፀም እምቢተኛ ከሆነ እንደሁኔታው እስከ ስድስት ወር በማረፍያ ቤት እንዲቆይ ለማዘዝ ይቻላል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 150)፡፡ ተከሳሹ አዲስ ዋስ ለመጥራት ወይም መያዣ ለማስጠት ዓቅም የሌለው ከሆነ ግን ይህ ትዕዛዝ መሰጠት የለበትም፡፡ ተከሳሹ በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዙን ከፈፀመ የማሰር ትዕዛዙ መነሳት አለበት፡፡
2. ከፍርድ በፊት ንብረትን ማስከበር (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151-153)
2.1 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(1) (ሀ) ና (ለ) ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች መኖራቸውን ከሳሹ ወይም የተከሳሽ ከሳሹ በመኃላ ቃል በተደገፈ አቤቱታ ወይም በሌላ ሁኔታ ማስረዳት ይችላል፡፡
2.2 ፍ/ቤቱ አቤቱታውን መርምሮ እውነት መሆኑን ካረጋገጠ ተከሳሹ ዋስትና እንዲሰጥ ወይም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ንብረት ወይም ግምቱ እንዲቀርብ በወሰነው ጊዜ እንዲያመጣ ወይም ደግሞ ከሚያዘው ገንዘብ ወይም ንብረት ላይ ለሚሰጠው ፍርድ ተመዛዛኝ የሚሆን መጠን ያለው ገንዘብ ወይም ንብረት በፍ/ቤቱ እንዲቀመጥ ወይም ይህን መያዣ የማይሰጥበትን ምክንያት ቀርቦ እንዲያስረዳ ያዛል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(1) (ለ)) ፡፡
2.3 የሚያዘው ንብረት የግድ ከሳሹ ያመለከተው ሁሉ ሳይሆን ከክሱ ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ መሆን አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 151(3) እና (1))፡፡ እንዲሁም በቁ. 404 እና በሌላ ሕግ እንዳይከበር የተወሰነ ንብረት መያዝ የለበትም፡፡
2.4 ተከሳሹ ዋስ ያልጠራበትን ምክንያት በሚገባ ካስረዳ ወይም የሚፈለግበትን መያዣ ከሰጠ ንብረቱ ይለቀቅለታል፡፡ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 152 (2) እና 153(4))፡፡
2.5 ንብረቱ በሚከበርበት ጊዜ የሦስተኛ ወገኖች መብት መጠበቅ አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 153(2)(3)፣ 428-421 እና 443)፡፡
3. ለጊዜው የሚሰጥ የማገድ ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 154-159)
1.1 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 154 (ሀ) ና (ለ) ሥር የተመለከቱት ሁኔታዎች በመኃላ በተደገፈ ቃል ወይም በሌላ መንገድ ሲረጋገጡ ነገሩ በፍርድ እስኪወሰን ድረስ ወይም ሌላ ትዕዛዝ እስኪሰጥ ድረስ ክርክር የተነሳበት ንብረት እንዳለ እንዲቆይ፣ ከመጥፋት እንዲድን እንዳይበላሽ ለሌላ ሰው ተላልፎ እንዳይሰጥ ወይም ሌላ ስፍራ እንዳይዘዋወር ወይም እንዳይባክን ፍ/ቤቱ አስፈላጊውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡
1.2 ውል ወይም ሌላ ግዴታ ተደጋግሞ እንዳይፈርስ ወይም ለማፍረስ የተወሰደው አርምጃ እንዳይቀጥል የሚሰጠው ያማገጃ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 155 መሠረት ይፈፀማል፡፡
1.3 የማገጃ ትዕዛዝ ያለማክበር የፍትሐብሔረና የወንጀል ኃላፊነትን ሊያስከትለ ይችላል (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 156)፡፡
1.4 የማገጃ ትዕዛዝ መሰጠት ያለበት ማመልከቻው ለሌላቸው ወገን ከደረሰው በኃላ ነው፡፡ ከዚህ ወጪ ትዕዛዙ ሊሰጥ የሚችለው መዘግየቱ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል መስሎ ሲታይ ብቻ ነው (ለምሳሌ ንብረቱ የሚጠፋ ወይም የሚበላሽ ሲሆን )
1.5 የማገጃ ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 158 በተደነገገው መሠረት ሊነሳ፣ ሊሠረዝ ወይም ሊሻሻል ይችላል፡፡
4. ከፍርድ በፊት ስለሚሰጥ ትዕዛዝ (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 160-165)
1.1 ለክርክሩ መነሻ የሆነው ወይም የተያዘው ንብረት ክርክሩ እስኪሰማ ቢቆይ የሚበላሽ መሆኑን ወይም መቆየቱ ሌላ ጉዳት ያለው መሆኑን ከተረዳው ፍርድ ቤቱ ንብረቱ እንዲሸጥ ማዘዝ ይችላል፡፡
1.2 ክርክር የተነሳበትን ሀብት በአንድ ስፍራ አኑሮ መጠበቅ፣ እንደይበላሽ የሚደረግ ጥንቃቄና የመቆጣጠር ምርምራ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 161 በተደነገገው መሠረት ይፈፀማል፡፡
1.3 በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 160 እና 161 መሠረት በሚቀርበው አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ከመሰጠቱ በፊት ለሌላኛው ወገን ማስታወቂያ መስጠት አለበት (ፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 162)፡፡
ከሌጋል ኮሰልቲንግ ሊምትድ
የውርስ ፅንሰ ሀሳብ በኢትዮጵያ ሕግ (ፍ/ሕ/ቁ 826-1025)
======================
ውድ አንባብያን የዚህ ርእሰ ጉዳይ ይዘት ሰፋ ያለ በመሆኑ በዚች አጭር ፅሑፍ ለመዳሰስ ስለማይቻል በሁለት ክፍሎች ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በዚህም መሰረት በመጀመሪያው ክፍል የውርስ ምንነትና ውርስ ማስተላለፍ፣ የውርስ መከፈት፣ ስለ ውርስ ማጣራት፣ በውርስ መተላለፍ ስለሚችሉ መብትና ግዴታዎች፣ ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ እና ያለኑዛዜ ውርስን እንመለከታለን፡፡ በሁለተኛው ከፍል ደግሞ የኑዛዜ ውርስ ምንነት፣ የኑዛዜ ዓይነቶች፣ የኑዛዜ ፎርሞች፣ የኑዛዜ መሻር እና ከወራሽነት መነቀልን በተመለከተ የምንዳስስ ይሆናል፡፡
1. የውርስ ምንነት፡- ውርስ ምንድን ነው የሚለውን ትርጉም በሀገራችን የውርስ ሕግ ውስጥ በቀጥታ ተተርጉሞ ባናገኘውም የአንድ በሞት የተለየን ሰው ንብረት እና ሀብት እንዲሁም ሊተላለፉ የሚችሉ መብት እና ግዴታዎች በሕይወት ላለ ሰው የሚተላለፍበት መንገድ መሆኑን ከሕጉ ጠቅላላ መንፈስ መረዳት እንችላለን፡፡
የውርስ ሕግ ማለት ደግሞ የሟች (አውራሽ) መብቶች እና ግዴታዎች በሕይወት ወዳሉት ወራሾቹ የሚተላለፍበት ደምብ/ስርዓት ነው፡፡ የሟች ውርስ መች እና እንዴት ይከፈታል፣ ወራሾች እነማን ናቸው፣ ወራሽነትን የሚያሣጡ ነገሮች ምንድን ናቸው፣ የሟች ኑዛዜ ምን ማሟላት አለበት፣ ዉርሱ እንዴት እና በማን ይጣራል፣ የውርስ ክፍያ እንዴት እና በማን ይፈፀማል እና የመሳሰሉት ጉዳዮች የሚመሩት በውርስ ሕግ ነው፡፡
ውርስ ማለት የሟችን መብቶች እና ግዴታዎችን ወደ በሕይወት ያሉ ወራሾች ማስተላለፍ ከሆነ የማስተላለፍ ሂደት የተሟላ እንዲሆን ወራሾችን ማጣራት (መውረስ የሚችሉ እነማን እንደሆኑ ማወቅ)፣ ውርስ ማጣራት እና የውርስ ክፍፍል የሚሉትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ይሆናል፡፡
2. ስለ ውርስ መከፈት፡- የሟች ሀብትና ንብረት እንዲሁም ወራሾች በተለያየ ቦታ ሊገኙ ስለሚችሉ ሁሉንም በአንድ ቦታ አጠቃሎ ለማየት እንዲያመችና በውርስ ላይ ክርክር ቢነሳ ጉዳዩን የመዳኘት ስልጣን ያለውን ፍ/ቤት ለይቶ ለመወሰን እንዲቻል የሟች ውርስ የሚከፈተው ሟች በሞተበት ጊዜ ዋና መኖሪያው ስፍራ በሆነበት ቦታ ነው (ፍ/ሕ/ቁ 862/1/)፡፡
3. በውርስ መተላለፍ የሚችሉ መብትና ግዴታዎች፡- የሟች ንብረት እንዲሁም መብትና ግዴታዎቹ በውርስ ሕግ መሰረት ለወራሾች የሚተላለፉ ናቸዉ፡፡ ይህ አጠቃላይ ደንብ ሲሆን በባሕሪያቸው አንዳንድ መብቶች እና ግዴታዎች ደግሞ ግለሰባዊ በመሆናቸው ሁሉም መብትና ግዴታዎች ሊወረሱ ወይም ለወራሾች ሊተላለፉ አይችሉም፡፡ በመሆኑም በውርስ የሚተላለፉት መብትና ግዴታዎች ከሟች መሞት ጋር አብረው ቀሪ የማይሆኑ እና መተላለፍ የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡
4. ወራሽ ለመሆን የሚያስፈልግ ችሎታ፡- ለወራሽነት ብቁ የሚያደርጉ በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ሳያሟሉ እንዲሁም በስመ ወላጅነት ወይም ተወላጅነት ብቻ ወራሽ መሆን አይቻልም፡፡ በሕጉ የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎች ያላሟላ ወራሽ በኑዛዜ ስሙ ቢጠቀስም ወይም በሕግ ወራሽነቱ ቢገለፅም ከውርሱ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ለወራሽነት ብቁ ለመሆን የሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች በሕይወት መኖርና ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ናቸው (በፍ/ሕ/ቁ 830)፡፡
በህይወት መኖር፡- አንድ ሰው ወራሽ ለመሆን አውራሹ በሚሞትበት ወቅት በህይወት ያለ መሆን አለበት፡፡ አውራሽ ሲሞት ያልነበረ ወይም እሱን ቀድሞ የሞተ መውረስ አይችልም፡፡ ነገር ግን በልዩ ሁኔታ ሟች በሚሞትበት ወቅት ተፀንሶ የነበረ ህፃን ተወልዶ 48 ሰዓት በሕይወት ከቆየ ውርስ ሲከፈት እንደነበረ ተቆጥሮ የመውረስ መብቱ ይጠበቅለታል (ፍ/ሕ/ቁ 834)፡፡
ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን፡- ወራሽ ለመሆን ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች ሌላኛው ለወራሽነት የማይገባ አለመሆን ነው፡፡ አንድ ወራሽ ለወራሽነት የማይገባ የሚሆነው በአውራሹ ወይም ወደ ታች የሚቆጠሩ ተወላጆች ወይም ወደ ላይ የሚቀጠሩ ወላጆች ወይም ባል ወይም ሚስት አስቦ በመግደል የተፈረደበት ወይም በመግደል ሙከራ የተቀጣ ወይም በሀሰት በመወንጀል ወይም በመመስከር አንደኛውን የሞት ፍርድ ወይም ከአስር ዓመት በበለጠ የፅኑ እስራት ቅጣትን ለማስከተል የሚያሰጋ ሆኖ የተቀጣ ከሆነ ነው (ፍ/ሕ/ቁ 838)፡፡
ሌላው ለወራሽነት የማይገባ የሚያደርገው ምክንያት አውራሽ ከመሞቱ በፊት ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ የአውራሽን ሁኔታ ከግምት አስገብቶ ኑዛዜ እንዳያደርግ፣ እንዳይለውጥ ወይም እንዳይሽር የከለከለ እንደሆነ ወይም አስቦ ያለ ሟች ፍቃድ የመጨረሻውን ኑዛዜ ያበላሸ፣ እንዳይገኝ ያደረገ፣ ያጠፋ ወይም ጉዳዩን በማወቅ በሐሰት ኑዛዜ የተጠቀመ እንደሆነ ነው (በፍ/ሕ/ቁ 840)፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንድ ሰው ከጥፋቱ መጠቀም የለበትም ከሚለው የሕግ መርህ በመነሳት ነው፡፡
5. የውርስ ዓይነቶች፡- ሁለት ዓይነት የውርስ ማስተላለፊያ መንገዶች ያሉ ሲሆን እነርሱም፡- ያለኑዛዜ ውርስ (Intestate Succession) እና የኑዛዜ ውርስ (Testate Succession) ናቸው፡፡
ያለ ኑዛዜ ውርስ፡- አውራሽ (ሟች) ኑዛዜ ሳያደርግ ሲሞት ወይም ያደረገው ኑዛዜ ፈራሽ በሚሆንበት ጊዜ የአውራሽ ንብረት ለወራሾች የሚከፋፈለው በሕጉ በተቀመጠው መሰረት ያለ ኑዛዜ ውርስ መሰረት ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ውርስ የሚካሄደው በአውራሽ ፍላጎት ሣይሆን በሕጉ መሰረት ነው፡፡ የሟች ልጆች ለመውረስ ብቁ የሚያደርጓቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን እስካሟሉ ድረስ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ናቸው (በፍ/ሕ/ቁ 842)፡፡
አውራሽ ልጆች ከሌሉት ወይም ልጆቹን ተክቶ የሚወርስ ከሌለ የአውራሽ አባትና እናት 2ኛ ደረጃ ወራሽ ይሆናሉ (ፍ/ሕ/ቁ 843)፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አውራሽ ልጆችም ወላጆችም የሌሉት ከሆነ ወይም አነሱን ተክቶም የሚወርስ ከሌለ የአውራሽ አያቶች 3ኛ ደረጃ ወራሾች ይሆናሉ (በፍ/ሕ/ቁ 845)፡፡ የ3ኛ ደረጃ ወራሾች የሌሉ እንደሆነም የአውራሽ ቅድመ አያቶች 4ኛ ደረጃ ወራሾች ይሆናሉ (በፍ/ሕ/ቁ 847)
አባት ወይም እናት ወይም ሁለቱም ቀድመዉ የሞቱ እንደሆነ የነሱን ፋንታ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጆቻቸዉ ተተክተው ይወርሳሉ፡፡ በአባት ወይም በእናት መስመር /አንዱ መስመር/ የሚወርስ ከሌላ ወደ ሌላኛው መስመር ሙሉ ውርሱ ይተላለፋል፡፡
ዘመዶች እስከ አራተኛ ደረጃ ተለይቶ ያልተገኘ እንደሆነ የሟችን ንብረት ለመንግስት እንደሚተላለፍ የ/ፍ/ሕ/ቁ 852 ላይ ተደንግጓል፡፡
ያለኑዛዜ ውርስ ሲሆን ውርሱ ለሁሉም ወራሾች በእኩል የሚከፋፈል ሆኖ ከአባት ወይም ከእናት ወገን የአንደኛው መስመር ከሌለ ውርሱ ወደ ሌላኛው መስመር ይተላለፋል፡፡ ነገር ግን በልዩ ሀኔታ ንብረቱ ከመጣበት መስመር ህጋዊ ወራሽ ካለ፣ ንብረቱ የማይንቀሳቀስ ከሆነ፣ ንብረቱ በውርስ ወይም በስጦታ የመጣ ከሆነ፣ የአውራሽ ተወላጆች ወይም ወላጆች በሕይወት ካሉ ካንዱ ወደሌላው መስመር መተላለፍ አይችልም (በፍ/ሕ/ቁ 849)፡፡ ይህም የሆነው የቤተሰብ ቅርስ የሆነ ንብረት በቤተሰብ እጅ እንዲቀር ነው፡፡
ምንጭ :- ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ 0አቃቤ ህግ ገጽ
Legal Assistant

Dagnachew & Mahlet Law Office (DMLO)

Addis Ababa

The ideal candidate will ensure smooth running of the office and effective case management by providing legal services under the supervision of an attorney. This individual will communicate frequently with the clients in order to serve them adequately. Additionally, this candidate will conduct necessary case research to aid the legal proceedings. Responsibilities • Provide administrative support to lawyer • Handle communication with clients • Handle court and government office tasks Qualifications • Bachelor's degree or equivalent experience • Experience in legal assistance • Familiarity with law, legal procedures, and protocols

How to Apply
Apply on LinkedIn
https://et.linkedin.com/jobs/view/legal-assistant-at-dagnachew-mahlet-law-office-dmlo-2547593705?utm_campaign=google_jobs_apply&utm_source=google_jobs_apply&utm_medium=organic
ግንቦት 12 /2013 ዓ.ም የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች

🔴 Ministry of Labor and Social Affairs
9 ቦታዎች በ0አመት 100+ ቦታዎች ልምድ ላላቸው

Professions: #Law, Environmental Science , Leadership , Federalism , Auto-Mechanic , Library and Information Science , Office Administration , Secretary , Record Management , Gender , Anthropology , Social Work , Sociology , Supplies Management , Automotive Management , Education Planning Management , Development Management , Natural And Social Science , Health Science , Journalism , Language and Literature , Statistics , Economics , Information System , Information Science , Purchasing , Law , Management Information System (MIS) , Information Technology , Computer Science , Human Resource Management , Political Science , International Relations , Business Management , Public Administration , Management , Business Administration , Accounting , Finance Management
Deadline: May 28, 2021
Location: Addis Ababa
#Full_Time

ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ 👇
https://ethiopage.com/jobs/21885/
____________
✔️ Minstry of Transport
5 ቦታዎች በ0አመት 9 ቦታዎች ልምድ ላላቸው

Professions: #Law, Business Management , Information System , Law , Videography , Photography , Cinematography , Material Management , Supplies Management , Accounting , Management , Purchasing , Motor Driver , Record Management , Library and Information Science , Software Engineering , Management Information System (MIS) , Computer Science , Information Science , Information Technology , Office Administration , Secretary

Deadline: June 1, 2021
Location: Addis Ababa,
#Full_Time

ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👉 https://ethiopage.com/jobs/21876/
____________
✳️ Ethiopian Institution of the Ombudsman (EIO)
2 ቦታዎች ልምድ ላላቸው

Professions: #Law, Development Management , Human Resource Management , Psychology , Leadership , Information Technology , Graphic Design , Computer Science .


Deadline: June 4, 2021
Location: Addis Ababa,
#Full_Time

ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👉 https://ethiopage.com/jobs/21892/
____________
የተሻሻለው_የፌዴራል_ፍ_ቤቶች_አዋጅ_ቁ_1234.pdf
2.9 MB
አዲሱ የተሻሻለው የፌደራል ፍ/ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013
የተሻሻሉት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እና የዳኝነት አስተዳደር አዋጆች መጽደቃቸው ለፍርድ ቤቱ የሪፎርም ሥራ መሠረት መሆናቸው ተገለጸ
******************************************************************
የተሻሻለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ እና የዳኝነት አስተዳደር አዋጆች በቅርቡ መጽደቃቸው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለጀመሩት የሪፎርም ሥራ መሠረት መሆናቸው ተገለጸ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ይህን የገለጹት የፍርድ ቤቱ አመራሮችና ዳኞች በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2013 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ግንቦት 14 ቀን 2013 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ሲወያዩ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

የፍርድ ቤቶች ተቋማዊ ነጻነትም ሆነ የዳኞች ነጻነት በአሁኑ ጊዜ የተረጋገጠ መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ፕሬዜዳንትዋ ይህም ዳኞች ሕግን ብቻ መሠረት አድርገው ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችላቸው መሆኑን በመጥቀስ ዳኞች ይህን ነጻነት ከሙያዊ ሥነምግባር (Integrity) ጋር አቀናጅተው ወደተግባር ሊተረጉሙት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የፌደራል ፍርድ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የዳኝነት አገልግሉት ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነትን ከማሳደግ፤ የዳኝነት ጥራት፣ የዳኝነት ግልጽነትና ቅልጥፍና ከማሻሻል እንዲሁም የዳኝነት ተደራሽነትን ከማሳደግ አንጻር የተከናወኑ ሥራዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የዳኝነት አገልግሎት ነጻነትን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር በየደረጃው በዳኝነት መርሆዎች ላይ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮች መመቻቸታቸው፣ የበጀት ነጻነት የሚከበሩባቸው አሠራሮች መጀመራቸው እንዲሁም የጸደቁ የፍርድ ቤቱ አዋጆችን ጨምሮ የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች መሻሻላቸውና በመሻሻል ላይ መገኘታቸው እንደስኬት ተጠቅሷል፡፡

የዳኝነት አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልም የአሠራር ሥርዓቶችና አደረጃጀቶች ተሻሽለው ለዳኝነትም ሆነ ለቅድመና ድህረ ዳኝነት ጥራት የሚያስፈልግ የሰው ኃይል ፍላጎትና የግብዓት አቅርቦቶች እንዲሟላ መደረጉ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን ጨምሮ የባለሙያዎችን ዕውቀትና ክህሎት የሚያጎለብቱ የትምህርትና ሰልጠና መርሐግብሮች እንዲዘጋጁ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡ በሥር ፍ/ቤት የአንድ መስኮት አገልግሎት እንዲጀመር መደረጉ፣ የተከማቹ ውዝፍ መዛግብት እንዲጠሩ ለማስቻል ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ እንዲሁም ጽዱና ምቹ የሥራ አካባቢዎች እንዲዘጋጁ መደረጋቸው የአገልግሎት ጥራትን ከማሳካት አንጻር ከተከናወኑ ተግባራት መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በሆኑት በፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዲሁም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የዘጠኝ ወር የመዛግብት አፈጻጸም በተጠቃለለ መልኩ ሲታይ በተጠቀሰው ጊዜ 118,417 መዛግብት ዕልባት እንዲያገኙ ዕቅድ ተይዞ 119,413 መዛግብት ዕልባት በማግኘታቸው አፈጻጸሙ 100.84 በመቶ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ የዳኝነት አገልግሎትን ለማሳደግ እንዲረዳ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አምስት ተጨማሪ የቪዲዮ ኮንፍረንስ ማዕከላትን በመክፈት በኢፋይሊንግ ከ9 ክልሎች የተላኩ 1,456 መዝገቦችን ለማስተናገድ የተቻለ ከመሆኑም በላይ በ1801 መዝገቦች 2,232 ባለጉዳዮችን በቪዲዮ ኮንፍረንስ ለማከራከር የተቻለ መሆኑም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል፡፡

በዘጠኝ ወር ውስጥ ለፍ/ቤቶች ከቀረቡ መዛግብት አንጻር በሶስቱም ፍርድ ቤቶች ካለፈው ተሻግረው፣ አዲስና እንደገና ተከፍተው ከቀረቡ 162,615 መዛግብት መካከል 119,413 መዛግብት ዕልባት አግኝተው 43,202 በመሻገራቸው የፍርድ ቤቶችን የማጥራት አቅም 97.91%፣ የመጨናነቅ ሁኔታ 1.36 እና የክምችት ምጣኔ 0.36 ለማድረስ እንደተቻለም በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

የፍርድ አፈጻጸም ቅልጥፍናን ከማሳደግ አኳያም 35,471 መዛግብትን መመርመር እና 3,374 ፍርዶችን/ውሳኔዎችን ማጣራት እንደተቻለና 5,618 የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ከዕዳ ዕገዳ ነጻ መሆናቸውን አረጋገግጦ የሀራጅ ሽያጭ በማካሄድ ከተለያዩ ገቢዎች ብር 322,175,918.32 በማሰባሰብ ለፍርድ ባለመብትና ለመንግሥት ብር 453,109,694.59 ለመክፈል እንደተቻለም ተገልጿል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ችሎቶች እና ዳኞች የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም በተናጠል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
@lawsocieties @lawsocieties
@lawsocieties https://t.me/lawsocieties