አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ለበጎ አድራጊ የአካባቢ ተቆርቋሪዎችና ለአካባቢ ሕግ ባለሙያዎች የቀረበ ግብዣ - ጥሪ
ድርጅታችን ቁም ለአካባቢ - Defend the Environment ሕግን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከ2ኛ ዲግሪ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ደረጃ በተማሩና በየዘርፋቸዉ ከፍተኛ ዉጤት ባስመዘገቡ ግለሰቦች የተመሰረተ እና በመልካሙ ኦጎ የሕግ ቢሮ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት /fully funded by Melkamu Ogo Law Office/ ቦርድ መር ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የሲቪል ማህበረሰብ - ድርጅት /NGO/ ነዉ፡፡
ይህ ጥሪ የተደረገዉ የትምህርት ዝግጅታቸዉ የአካባቢ ሕግ - Environmental Lawyers ወይም ለአካባቢ ተቆርቋሪ በመሆን አካባቢ እንዲጠበቅና እንዳይበከል በተለያዩ መንገድ ለሰሩ - Environmentalists እና ድርጅታችንን በበጎ አድራጊ ባለሙያነት /Volunteer Professionals/ ለማገልገል ለሚፈቅዱ ሰዎች ከዘርፉ ጋር በተገናኘ በሚሰራ ድርጅታችን ምስረታ መርሃ ግብር ላይ በሚቀርቡ የጥናት ጽሁፎችና የዉይይት መድረክ ላይ መገኘት የሚያስችል እና የበጎ አድራጊነት ስራ ግንኙነት እንዲፈጠር ዕድል ለማመቻቸት በማሰብ ነዉ፡፡
ለዚህ ድርጅት መመስረት ምክንያት የሆኑት ጉዳዮች በርካቶች ቢሆኑም በዋናነት:-
አከባቢን /Environment/፣ ብዝሃ ህይወትን /Biodiversity/ እና ተፈጥሮ ሀብትን /Natural Resources/ መንከባከብን፣ ጥበቃ ማድረግን፣
የአከባቢ ብክለት /Pollution/ መቀነስ/ማጥፋትን፣
የታዳሽ ኃይል /Renewable Resources/ አገልግሎት ማስተዋወቅን፣
ለአየር ንብረት ለዉጥ /Climate Change/ ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን መቀነስ/ማቆምን እና
መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ጥበቃ - Protection of Fundamental rights and freedoms ስራዎችን
በተመለከተ ጥናት እና ምርምር ማድረግ፣ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች/ባለሙያዎች ለአቅም ግንባታ የሚሆን የስልጠና፣ ትምህርት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ማዘጋጀት፣ ለአከባቢ ጥበቃ ምቹ የሆኑ የሕግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጁና በስራ ላይ ያሉትም ለዚሁ ተግባር እንዲመቹ ተደርገዉ እንዲሻሻሉና የማያስፈልጉ ሕጎች እንዲሻሩ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ እና አፈጻጸማቸዉን መከታተል /Legal Monitoring/፣
እንዲሁም በዋናነት አከባቢን በሚበክሉ፣ በተፈጥሮ ሃብት እና በብዝሃ ህይወት ላይ በማናቸዉም ሁኔታ ጉዳት በሚያደርሱ ሰዎች/ተቋማት ላይ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚቀርቡ የሙግት አቀራረብ/አመራር ስርዓት /Environmental Public Interest Litigation/ በመከተል ክሶችን በፍርድ ቤት እና በአስተዳራዊ አካላት ዘንድ በማቅረብ የህዝብን ከብክለት በጸዳ እና ንጹህ በሆነ አከባቢ በመኖር ጤንነቱን መጠበቅ የሚያስችለዉን ዕድል መፍጠር ነዉ፡፡
ከዚሁም ጋር በተገናኘ የድርጅቱ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ በሀገራችን በስፋት ባልተለመደዉ በዚህ አይነቱ የሙግት ስርዓት በመጠቀም አከባቢን ሲበክሉ በነበሩ ተቋማት ላይ ክሶችን/አቤቱታዎችን በፍርድ ቤት እና በሚመለከተዉ አስተዳደራዊ አካል ዘንድ በማቅረብ ለጉዳዩ የተለያየ ዉጤት ያስገኙና ሕዝብ ነገሩን እንዲገነዘብ እንዲሁም የመንግስት ትኩረት እንዲያገኝ አድርገዋል፡፡
በመሆኑም ይህ ድርጅት የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት ይረዳ ዘንድ ከተነሳንበት ጉዳይ ጋር በተገናኘ በዘርፉ ጥናት እና ምርምር ያደረጉ እዉቅ ምሁራን የጥናት ጽሁፍ በማቅረብ በዘርፉ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ክፍተት እንዲያሳዩ፣ የድርጅቱን መቋቋም ለህዝቡ በማሳወቅ ከአከባቢ ብክለት ጋር በተያያዘ ጥፋት ፈጻሚዎችን በመጠቆም መረጃ እንዲሰጡን ለማስቻል፣ ከድርጅቱ ጋር ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸዉ አካላት ጋር አብሮ ለመስራት ትዉዉቅ ለማድረግ እና ከተሳታፊዎች ጋር ገንቢ ዉይይቶችን በማድረግ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል መድረክ በግንቦት 07 ቀን 2013 ዓ.ም ቦሌ ኤድናሞል ጀርባ በሚገኘዉ Best western international Plus Hotel ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 ሰዓት በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ድፕሎማቶች፣ ምሁራን፣ የሕግ ባለሙዎች እና ሌሎችም ተጋባጅ እንግዶች በሚገኙበት ለማሰናዳት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
በመሆኑም፡-
የትምህት ዝግጅታቸዉ ከአካባቢ ሕግ /Environmental Law/ ጋር በእጅጉ የተገናኘ ወይም
ከአካባቢ ጋር በተገናኘ በፍርድ ቤት እና/ወይም በአስተዳራዊ አካላት ላይ ከሶስት ባላነሱ ክሶች/አቤቱታዎች /Environmental litigation/ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ወይም
የአካባቢ ተቆርቋሪ በመሆን በማናቸዉም መንገድ የሚታይ አበርክቶት ያላቸዉ /Environmentalists/ እና
ድርጅታችን ለህዝብ ጥቅም ሲባል በሚያቀርባቸዉ ክሶች/አቤቱታዎ ላይ በበጎ አድራጊ /volunteer/ ባለሙያነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆኑ 4/አራት ሰዎችን በዕለቱ መድረክ ላይ እንዲገኙ የሚያስችል ዕድል ተመቻችቷል፡፡
ስለሆነም ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 ከተጠቀሱት መስፈርቶች አንዱን እና 4ተኛዉን ማሟላት የምትችሉ ሰዎች የድርጅቱ መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ ለሆኑት አቶ መልካሙ ኦጎ (የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ) ሥም እና አድራሻችሁን ከስር ከሚቀመጡ አድራሻዎች በአንዱ በቅድሚያ በመላክ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ትችላላችሁ፡፡ ቀድሞ የደወለ/የጠየቀ ዕድሉን ቀድሞ የሚያገኝ መሆኑ ይታወቅ፡፡

Melkamu Ogo – Cellphone - +251 911 02 71 03, E-Mail - andiracha16@gmail.com or info@melkamuogo.com, Website – www.melkamuogo.com

ፍትህ ለአካባቢ - Justice for the Envirnment
Via Abyssinia law.com

🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
An unexamined life is not worth living! At this point, examine your life. Take personal inventory of your life and see how much of your time you spend on your personal development. Sometimes the weight that holds us down from flying are of our own manufacture. We stretch ourselves too thin on unnecessary things; sometimes even on things that is none of our business! It's time to focus on you. Cut off the unnecessary things. Count out the negative people and begin to associate yourself with like-valued people. If you really want to fly, then you must let go of the weight that prevents you from flying.
Have a sucess-filled day
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎትን በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ባለው መልኩ ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ነው
******************************************************************
ሕጻናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ነጻ የህግ ምክር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች እስካሁን ድረስ በተለያዩ ተቋማት ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂ እየተዘጋጀ ነው፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጊዜያዊ አስተባባሪ ዳኛ ልዑለስላሴ ሊበን ይህን የገለጹት በረቂቅ ደረጃ ላይ በሚገኘው ነጻ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ ላይ በተለይ ከሴቶችና ሕጻናት አንጻር የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ይዘት ለማዳበር እንዲረዳ ከሚያዚያ 29-30 ቀን 2013 ዓ.ም በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሔደው የግብአት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረክ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

አገልግሎቱን ለመስጠት ፈቃድ ያላቸው አካላት በአሁኑ ጊዜ በመሰላቸው መንገድ ተፈጻሚ እያደረጉት እንደሚገኙ በመግለጽም ስትራቴጅው ፀድቆ ሥራ ላይ መዋሉ አገልግሎቱን ወጥነት ባለው መልኩ ተፈጻሚ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

በተለይ በሕጻናት ጉዳይ ሲሰጥ የነበረው የሕግ ድጋፍ አገልግሎት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየ መሆኑን በመጥቀስ፣ ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎቱ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ባለው መልኩ ተፈጻሚ ሊሆን የሚችልበት አሠራር መዘርጋቱ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሕጻናት ፍትሕ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ያዘጋጀውና ነጻ የህግ ምክር ድጋፍ ከሚሰጡና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት የተውጣጡ ከ40 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በነጻ የሕግ ድጋፍ ረቂቅ ስትራቴጂ፣ በሕግ ድጋፍ አገልግሎት ላይ በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ በወጣት ጥፋተኞች ዙሪያ የተደረገ የዳሰሳ ሪፖርት ቀርቦም ውይይት ተካሒዶበታል፡፡

በውይይቱ ላይ ከተሳታፊዎች የቀረቡና ረቂቅ ስትራቴጅውን ለማሻሻል ይረዳሉ የተባሉ ግብአቶች ተለይተው በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት በኩል ለሚመለከተው አካል እንዲቀርቡም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ ከፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የተከላካይ ጠበቃ ጽ/ቤት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ሕጻናት አድን ድርጅት (UNICEF)፣ ከአፍሪካ ሕጻናት ፖሊሲ ፎረም (Africa Child Policy Forum)፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር፣ ከአዲስ አበባ ሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ቢሮ እንዲሁም ነጻ የሕግ ድጋፍ ከሚሰጡ ጠበቆች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ነጻ የሕግ ድጋፍ ረቂቅ ስትራቴጂው በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ በ2011 ዓ.ም ለሚኒስትሮች ም/ቤት የቀረበ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ረቂቅ ስትራቴጂው በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ ፀድቆ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅም ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
Legal Manager

JTI (Japan Tobacco International) Ethiopia

Required Skills And Experience • LLB Degree in Law, Proficient English language skill and MS Office confident user • At least 8 years of proven track record and hands-on experience
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሬጅስትራርነት ለተመዘገባችሁ አመልካቾች በሙሉ ቅዳሜ ግንቦት 07 ቀን 2013ዓ.ም ጠዋት 2፡00 ላይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አዳራሽ የጽሁፍ ፈተና የሚሰጥ ስለሆነ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ የጽሁፍ ፈተናውን እንድትወስዱ ተብላችኋል፡፡
ግንቦት 04/2013 ዓ.ም የወጣ

Federal City Job creation and Food Security Agency
2 ቦታዎች በ0አመት 7 ቦታዎች ልምድ ላላቸው

Professions: Law, Information System , Information Technology , Information Science , Computer Science , Office Administration , Secretary , Record Management , Sociology , Statistics , Geography , Economics , Driver , Mechanical Engineering , Automotive Engineering , Auto-Mechanic , Marketing , Business Management , Accounting , Human Resource Management , Management .
Deadline: May 26, 2021
Location:Addis Ababa,
#Full_Time

ሙሉ ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👉 https://ethiopage.com/jobs/21826/
Federal Urban Job Creation and Food Security Agency


Position: Lawyer III

Job Time: Full-Time

Job Type: Permanent

Place of Work: Addis Ababa, Ethiopia

Salary: 7,071.00

Application Deadline: May, 26/2021 (14 days left)

Federal Urban Job Creation and Food Security Agency is looking to hire qualified applicants who fulfill the following requirements 

Level XII

Requirement

First Degree in Law

Experince

4 years of work experience in various legal matters

Required Number 

1

Initial Salary 

7,071.00

How to apply

Qualified applicants who fulfill the above requirements should submit all the necessary credentials such as educational background, work experience along with an unreturnable photocopy to the following address:

Federal Urban Job Creation and Food Security Agency

On the road from Mexico square to kera

down the road from Kkare building, in front of Shew Bakery 

Seman Building 1st floor, Human Resource Management Office number 102,

Addis Ababa 

Tel 0115575061 or 0115575031

 

Applicants with work experience from a non-governmental institute should bring proof of tax payment,

Female applicants are highly encouraged. 


🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
If you could ask all members of this channel a question, what would that question be? (comment below)

⭐️ Great questions will be posted on the channel.
research assistant terms of reference

1: Purpose
Support and facilitate data collection for a doctoral research to be done mainly in Addis Ababa.

2: Tasks to be carried out by the research assistant.

The research assistant will be assigned to carry out the following activities:
Contact selected governmental and nongovernmental offices and schedule meetings for interview
Search and obtain certain research materials/documents specified and recommended by the researcher Organize focus group discussion venues in line with the general guideline and specification of the researcher
Assist in audio_video recording at meetings.

3: Duration
The assignment will last for three months. It may, however, be extended for some additional time if necessary.

4: Service fee
The service fee amount to be paid to the research assistant and the method of calculation will be negotiable.

5: Condition of assignment
The research assistant may not be engaged in the assignment fulltime unless agreed otherwise.

6. requirements
Graduates of law or sociology
interested in feminist jurisprudence or feminist ideas.

Special interest in women’s and girls’ right advocacy
Cooperative and supportive
Interview.

There may be an online interview either by phone or Zoom as may be necessary.

Apply now‼️🔴
via @LawsocietiesBot

🟩 @lawsocieties
🟨 @lawsocieties
🟥 @lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
#ጣልቃ #ገብ
• በፍትሃ ብሔር ክርክር ተካፋይ ያልነበረ ሰው የክርክሩ ተካፋይ የሚሆንበትና መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር ተገቢውን ክርክር እንዲያቀርብ በህጉ የተዘረጋ ስርዓት

ጣልቃ ገብ ወደ ክርከሩ የሚገባው በተከሳሽ ጠያቂነት ወይም በራሱ አነሳሽነት ሊሆን እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል፡፡ በዚህ ድንጋጌ እንደተመለከተው ሌሎች ወገኖች በሚከራከሩበት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሶስተኛ ወገን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር እንዲፈቀድለት ሊከራከር ይችላል፡፡ ሆኖም የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብ ለመሆን ሌሎች ሰዎች በሚከራከሩበት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የሚነካ መሆኑን የማስረዳት ግዴታውን መወጣት አለበት፡፡ በሌላ አገላለፅ ጣልቃ ልግባ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲኖረው ውሳኔው የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ሰው መብትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ በቀጥታ የሚፈጸም መሆኑንና ሌላ አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላል፡፡

ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጣልቃ ገብ ልሁን በሚል ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ውሳኔው በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የማይጎዳ ከሆነ እና አዲስ ክስ በማቅረብ ማስቀረት የሚቻልበት ሁኔታ ያለው ከሆነ ጥያቄው በህግ ፊት ተቀባይነት የሚያገኝበት ሁኔታ የሌለ መሆኑን ነው፡፡

ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ መብቱን በምን አግባብና መልኩ ሊነካ እንደሚችል ማሳየት እንደአለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41(2) ድንጋጌ ያሳያል፡፡ በመሆኑም አመልካቹ ዝርዝር ምክንያቱን በማስፈር ይህንኑ የማስረዳት ግዴታ አለበት፡፡ የጣልቃ ገብነቱ አቤቱታ ሊቀርብ የሚገባውም ጊዜ ለማራዘም፣ ክርክሩን ለማጓተት ሊሆን እንደማይገባው ከተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ከፍትሃ ብሔር ስነ ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ.95934 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41

በአንድ ክስ ሌሎች ተከራካሪ ወገኖች በክርክር ላይ ባሉበት ጊዜ ማናቸውም ሶስተኛ ወገን በጉዳዩ ያገባኛል የሚል ሲሆን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብ ሆኖ ለመከራከር እንደሚችል እና የጣልቃ ገብነት ማመልከቻው በክሱ ውስጥ ያገባኛል የሚልበትን ምክንያት የሚዘረዝርና በተለይም የመብቱን ሁኔታ የሚገልጽ መሆን እንዳለበት፣ እንዲሁም የጣልቃ ገብነት ጥያቄ አቅራቢው በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር የሚያስችል መብት ያለው መሆን አለመሆኑ በቅድሚያ ሊወሰን እንደሚገባው፣ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል መብት የለውም በተባለ ጊዜ መሰናበት እንደሚገባው እና መብት አለው በተባለ ጊዜ ግን የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆን ከተደረገ በኃላ ከጣልቃ ገቡ መብት አንፃር ጭምር አጠቃላይ ክርክሩ ተመርምሮ ተገቢ ነው የሚባል ውሳኔ የሚሰጥ መሆኑን ከፍትሐብሔር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 41 (1)፣ (2) እና (3) ድንጋጌዎች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡

ቤትና ይዞታን በሚመለከት በሚደረግ ክርክር አንድ ጣልቃ ገብ አመልካች ክርክር በሚደረግበት ቤትና ይዞታ ላይ ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር መብት አለኝ በማለት መብቱን የሚያሳዩ ሰነዶችን አቅርቦ እያለ የባለይዞታነት ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አላቀረብክም ተብሎ ከወዲሁ ጣልቃ ገብተህ ልትከራከር አትችልም ተብሎ አቤቱታውን ውድቅ ማድረግ አግባብነት የለውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 90713 ቅጽ 17፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41
በ ሄኖክ ታዬ
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
የሰርብ ፅንፈኛ ብሔርተኞች ዩጎዝላቪያን እንዴት አፈራረሷት?
=========================
ታሪክ መስታወት ነው፣ በራሳችን ዓውድ ላይ ቆመን የሌሎችን ዓውድ እንድንቃኝ ያስችለናል፡፡ ዛሬ ላይ ሆነን ትናንትን እንድናይ ይረዳናል፣ ጠቃሚ ትምህርት ይገኝበታል።
""""
በአንደኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ የዩጎዝላቪያን ግዛት የመሠረቱ አድርያቲክ ባህር ዳርቻ የሚገኙ ስድስት ሪፐብሊኮችና ሁለት ራስ ገዝ ክልሎች፣ የሁለተኛው ዓለምጦርነት እንዳበቃ የዩጎዝላቪያን ሶሻሊስት ፌዴራል ሪፐብሊክ ፈጠሩ።
""""
ከአራት አሠርት ዓመታት የአብሮነት ቆይታ በኋላ፣ የጠንካራውን መሪ ጆሴፕ ቲቶን ሞት ተከትሎ፣ በቀዝቃዛው ጦርነት መጨረሻ ፌዴሬሽኑ ያልተጠበቀ አደጋ ገጠመው።
""""
በ1980ዎቹ ሁለተኛ አጋማሽ የፈዴሬሽኑ አንድ አካል በነበረችው የሰርቢያ ክልል አክራሪ ብሔርተኞች ተነሱ። ከገዥው የኮሙዩኒስት ፓርቲ የተገኘ ስሎቦዳን ሜሎሰቪች የተባለ ፅንፈኛ ሰርብ፣ ብሶት ተኮር ፖለቲካ ሠርቶ በርካታ ሰርቦች ወደ ቤልግሬድ አደባባይ እንዲወጡ አደረገ። ቤልግሬድ የፌዴራሉ መንግሥቱ መቀመጫና የሰርቦች ዋና ከተማ ነበረች። በመሆኑም ሜሎሰቪች በፌዴራል መንግሥቱ የማያባራ ሕዝባዊ ጫና (Mob Pressure) በመፍጠር፣ እሱ ወደ ሥልጣን ካልወጣ መንግሥት ሰላም እንደማያገኝ አስታወቀ፣ ተሳካለትም። በወራት ውስጥ ለከፍተኛ ሥልጣን በቃ። ችግሩ በዚህ አላበቃም። የሽንገላ ፖለቲካው ዘላቂ መፍትሔ አላመጣም። ሜሎሰቪች በሌሎች ክልሎች እየዞረ ለእሱ ፍላጎት ተገዥ የሆኑ አድርባዮችን ወደ ሥልጣን ማውጣት ጀመረ። በቮጅቮዲናና በሞንቴኔግሮ ግዛቶች ተሳካለት። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተጠቅሞ የብዙኃን አልባንያዎች መኖርያ በሆነችው ኮሶቮም የሰርቦችን የበላይነት አረጋገጠ። ሜሎሰቪች ‹‹በምድር ላይ አንዳችም ኃይል የሰርብን ሕዝብ ፍላጎት ሊገታ አይችልም›› በማለት በአደባባይ ደሰኮረ።
"""""
የሰርብ ፅንፈኛ ብሔርተኞች ህልም ግን ብዙም ሳይርቅ ፈተና ገጠመው። በሰሜን ጫፍ ያለችው የስሎቫንያ ክልል በቀላሉ እጅ አልሰጠችም። የነገሮች አካሄድ አላምር ቢላቸው የዢዠክ አገር ሰዎች በቶሎ ከኮሙዩኒስት ፓርቲው ራሳቸውን አገለሉ። የሰሜን ምዕራቧ የክሮሽያ ክልልም እንዲሁ ለሰርብ ስግብግብ ብሔርተኞች አልንበረከክም አለች። ይህን ውጥረት ተከትሎ በመላው አገሪቱ በስፋት ተሠራጭተው ይኖሩ የነበሩ ሰርቦች ደኅንነታቸው አደጋ ላይ ወደቀ።
""""""
ሜሎሰቪች ሁኔታውን እንደ መልካም አጋጣሚ ቆጠረው፡፡ ለሰርብ ብሔርተኞች ፍላጎት ያልተንበረከኩ ክልላዊ መንግሥታትን ለመምታት ሊጠቀምበት ወሰነ። የሜሎሰቪች ሰዎች የሰርብ ብሔር ተወላጆች በያሉበት እንዲደራጁና እንዲታጠቁ አደረጉ። የብሔርተኞቹ እንቅስቃሴ በዚህ ብቻ አላቆመም። የፌዴራል መንግሥት ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎችም በሰርቦች እጅ እንዲገቡ ተደረገ። እንደ ሞንቴኔግሮ የመሳሰሉ ክልሎችም የሰርቦች ጥቅመኞች ሆነው ለፅንፈኞቹ ያልተገደበ ድጋፍ ሰጪ ሆኑ። ሜሎሰቪች በተፈለገው ጊዜና ቦታ የሚታዘዝ የሰርብ ልዩ ኃይልም አደራጀ። የታሪክ ቁርሾ ጥሩ የጥፋት ግብዓት ሆኖ ተገኘ። የኮሶቮ አልባንያዎችና ክሮሺያውያን በተለያየ ዘመን በሰርቦች ላይ ፈጸሙት የተባለው በደል እንደ አዲስ በቴሌቪዥን መተረክ ጀመረ። ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ የክሮሺያ ክልል ፖለቲከኞች ሕገወጥ መሣሪያ ሲገዙ የሚያሳይ የተቀነባበረ የቪድዮ ምሥል በቴሌቪዥን ተለቀቀ። በሕግ ማስከበር ስም ክልሉን ለመምታት የሚደረግ ዝግጅት ነበር። በመቀጠል በፌዴራል መንግሥቱ ያላቸውን ቁልፍ ሥልጣን ተጠቅመው የሰርብ ብሔርተኞች፣ ‹‹በየትኛም ክልላዊ መንግሥት ሕገወጥ መሣሪያ የታጠቀ በአስቸኳይ እንዲፈታ›› የሚል አዋጅ አወጡ። አዋጁን በማያስፈጽሙ አካላት የማያወላውል ዕርምጃ እንደሚወስዱም አስጠነቀቁ። የተጀመረውን ለውጥ ለመቀልበስ ብሎም ዩጎዝላቪያን ለመበተን በሚንቀሳቀሱ ‹‹የነውጥ ኃይሎች›› ላይ የከፋ ቅጣት እንደሚጣል አስጠነቀቁ።
""""
የሌሎች ክልል መንግሥታትና ሕዝቦች ክስተቱን በሥጋትና በአንክሮ ይከታተሉ ነበር። ከሰርቢያ ጋር ድንበር የማያገናኛቸው ስሎቬንያዎች በቀላል ኪሳራ ከፌዴሬሽኑ መውጣት ቢችሉም፣ ሌሎቹ ክልሎች ግን ከፅንፈኛ ብሔርተኞቹ ጋር ደም አፋሳሽ ትግል ማድረግ ነበረባቸው።
""""""
ሰርቦች የመጀመርያውን ዘመቻ በክሮሽያ ላይ ከፈቱ። ነገር ግን የሰርቦች ብሔራዊ ጡዘት በክሮሽያ ተመጣጣኝ ኃይል ፈጠሮ ነበር። የጦርነት ነጋሪቱ ያሰጋቸው ክሮአቶች አክራሪ ብሔርተኞችን ወደ ሥልጣን አወጡ፡፡ እ.ኤ.አ. ሰኔ 1991 የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው በመወሰን ነፃ አገር ለመሆን ወሰኑ፡፡ ለሉዓላዊነታቸው እንደሚዋደቁ ቃል ገቡ። ይህን ተከትሎ ሜሎሰቪች ‹‹ከሰርቢያ ውጪ የሚኖሩ ሰርቦች ህልውና ያሳስበኛል›› በሚል ሰበብ በክሮሽያ ላይ ይፋ ጦርነት አወጀ። በፌዴራል መንግሥቱ ስም የጦር ኃይሉን ተጠቅሞ ገና በሁለት እግሮቿ ያልቆመችውን ክሮሽያ ክፉኛ አቆሰላት። ጥቃቱ በሒደት ወደ ቦስኒያና ኮሶቮ ሰፍቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎች ሕይወታቸውን አጡ። በርካቶች ቄዬአቸውን ጥለው ተሰደዱ። ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፉ የመጡ መተኪያ የሌላቸው ታሪካዊ ቅርሶች በእሳት ነደዱ።
"""""
በዚህ ሁሉ መሀል ‹‹የወንድማማችነታችን መገለጫ ዩጎዝላቪያ በጥቂቶች ሴራ አይፈርስም›› የሚሉ ተስፋቸው የፀና ዜጎች ነበሩ። የአውሮፓ ኮሚሽንም አሸማጋይ ሆኖ ‹‹አብሮ መኖር ቢሳናችሁ መጠፋፋት የለባችሁም›› ብሎ ተማፀነ።
ጥረታችው ግን ለውጥ አላመጣም። በፌዴራል መንግሥቱ ሽፋን የራሳቸውን ርዕይና ፍላጎት በሌሎች ላይ ለመጫን የሞከሩ ፅንፈኞቹ ሰርቦች ዕቅዳቸው ዕዉን አልሆነም፣ ህልማቸው ተራ ቅዠት ሆኖ ቀረ። ፌዴሬሽኑን የመሰረቱት ክልሎች ተገፍተው አገር ሆኑ። የዘውጌ ጡዘቱን መሸከም ያልቻለችው ዩጎዝላቪያም በአጭር ግዜ ውስጥ ተበታትና ከዓለም ካርታ ተፋቀች።
ፕሬዚዳንት ጆሴፕ ቲቶ እ.ኤ.አ. በ1974 የብሔሮችና ብሔረሰቦች የመገንጠል መብት በሕገ መንግሥት እንዲረጋገጥ ሲያደርግ፣ አገሩ ዩጎዝላቪያ ከ17 ዓመታት በኋላ እንዲህ እንደምትበተን አልተጠራጠረም።
"""""
የሰርቢያ አክራሪ ዘውጌዎችም ከውጭም ከውስጥም በደረሰባቸው የተባበረ የጦር ምት ተደቁሰው፣ ባሉበት ተወስነው ክልላቸውን አገር አድርገው ሊኖሩ ግድ ሆነባቸው።
"""""
የመገነጣጠል ጦሱ ዘላቂና የከፋ ነው። ከ30 ዓመታት በኋላ ዛሬም የኮሶቮ አልባንያዎችና ሰርቦች ሰላም የላቸውም። ድህነትም ሥር ሰዷል።
""""
ዩጎዝላቪያን ያፈረሳት ሁሉን ነገር የእኔ ብቻ፣ በሁሉም ጉዳይ እኔ ብቻ የሚል አልጠግብ ባይ የሰርብ ብሔርተኝነት ነው። በጥሞና ላስተዋለ የዛሬ 30 ዓመት በዩጎዝላቪያ የሆነው አሁን በእኛ አገር እያቆጠቆጠ ነው። ከወዲሁ በጥንቃቄ ካልታሰበበት በእኛም አገር ሜሎሰቪቾች በቅለዋል፣ በእኛም አገር ሰርቦች አሉ። ሁሉን የኔ ብቻ፣ ሁሉን እኔ ብቻ በሚል ይሉኝታ ቢስ ፖለቲካ አገር እያመሱ ያሉ የኛ ዘዉጌዎች መንገዳቸው የጥፋት መሆኑን በግዜ ይረዱ ይሆን?
የኢትዮጵያን ሉዑላዊነት አረጋግጦ፣ የቡድን ማንነትንና ጥቅም ሳይጋፋ ወደ ዜግነት ፖለቲካ የሚወስደን ፍኖተ ካርታ ያስፈልገናል። ለዚህ ደግሞ መሸነጋገሉን ትተን መወያየት ያለብን አሁን ነው።
በዶክተር በተበጀ ሞላ
""""""""""""""""""""""""""
@NegereFej
https://t.me/NegereFej
@NegereFej
https://t.me/NegereFej