አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.87K photos
25 videos
1.87K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
2003 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታሰብ መደረጉ ስህተት ነው፣ የስር 3ኛዋ ተከሳሽም ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እኩል ኃላፊነት እንዳላቸው ሊወሰን ሲገባ መታለፉ ያላግባብ ነው የሚሉትን ነጥቦችን ዘርዝረው ይግባኙን ለማቅረብ የከፈሉትን ዳኝነት፣ የጠበቃና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች የስር ተከሳሾች እንዲከፍሉ ሊወሰን ይገባል በማለት ዳኝነት መጠያቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ይግባኝ ሰሚው ችሎትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ መልስ ሰጪዎች ለይ/ባይ ሊከፍሉት የሚገባው የዶላር ምንዛሬ መቼ በነበረው ነው? የሚለው ጭብጥ በተመለከተከፍ/ብ/ህ/ቁ 1750 ጋር አመሳስሎ በመተርጎም የአሁኑ አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሏቸው የሚገባው የዶላር ምንዛሬ የስር ፍርድ ቤቱ ፍርድ በሰጠበት በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም በነበረው የዶላር የብር ምንዛሬ ተመን መሆን ይገባዋል በማለት የወሰነ ሲሆን አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱት ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ክስ እስከመሰረቱባቸው ድረስ ላለው ጊዜ ወለድ ሊከፍሉ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ ተጠሪ ገንዘባቸው ከእጃቸው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ገንዘብ ያገኙት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለ፣ በአንፃሩ ደግሞ የገንዘቡ ተጠቃሚዎች አመልካቾች የነበሩ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ ወለዱ የማይከፈልበት ምክንያት የለም ወደሚለው ድምዳሜ ደርሶ ተጠሪ በክሳቸው እንደጠየቁት 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በሚመለከት ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክስ ወደ ፍርድ ቤት እስከቀረበበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ ላለው ጊዜም 9% ወለድ ሊከፈላቸው ይገባል፤ በተመሳሳይም አመልካቾቹ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) ከተጠሪ ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ተጠሪ ክሱን በሬጅስትራር እስካስከፈቱበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ሊከፍሏቸው ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤቱ በዚህ ረገድ የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል፡፡ እንዲሁም የሥር 3ኛ ተከሳሽን በተመለከተም በባለቤታቸው በሁለተኛው አመልካች በቤተሰብ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂ ሊያደርጋቸው የሚችል ሁኔታ ካለ ከተጠያቂነት የማያመልጡበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ ለተጠሪ ክስ ግን በቀጥታ ፍርዱ ሊያርፍባቸው የሚያስችል ነገር የለም፣ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቱ በዚህ ረገድ የሰጠው ፍርድ የሚነቀፍ አይደለም በማለት በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡

የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን የአመልካቾች የሠበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተገቢውን ጭብጥ ለጉዳዩ ሳይዝና አግባብነት የሌለውን ድንጋጌን መሰረት አድርጎ  አመልካቾች ከኬንያ ናይሮቢ በአሜሪካን ዶላር ተልኮ በ2ኛ አመልካች ከአቢሲኒያ ባንክ በወቅቱ በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ለተወሰደው ገንዘብ ለተጠሪ ገንዘቡን ሊመልሱ የሚገባው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በሰጠበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው በማለት መወሰኑ አግባብነት የሌለው መሆኑን፣ ተጠሪ ወለድ የሚያገኙበት ሕጋዊ ምክንያትም የሌለ መሆኑን ዘርዝረው በዚህ ረገድ የተሰጠው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ በአንፃሩ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲፀናላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ነጥቦች፡-

አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሉት የሚገባው ገንዘብ በውጪ ምንዛሬ ነው? ወይስ በኢትዩጵያ ብር ነው?፣

አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱት ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ክስ እስከመሰረቱባቸው ድረስ ላለው ጊዜ ወለድ ሊከፍሉ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚሉት ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካቾች ለተጠሪ የኢትዩጵያ ብር 800,000 እና 150,000 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ ሊከፍሏቸው እንደሚገባ ክርክር ያቀረቡበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው አመልካቾች ለተጠሪ መክፈል ያለባቸው 150,000 ዶላር ይኼው ገንዘብ በ2ኛ አመልካች ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ ሲሆን በኢትዩጵያ ብር ተመንዝሮ በተሠጠበት መጠን ነው? ወይስ በዶላር ነው? የሚል ሲሆን ይህ ጭብጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 246፣ 247 እና 248 ድንጋጌዎች አግባብ ሊመሰረት የሚገባው እና ተጠሪ በዶላሩ ነው ሊከፈላቸው የሚገባው የሚል ምላሽ ከተሰጠ ደግሞ ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄው የዶላሩ ምንዛሬ መሆን ያለበት አመልካቾች ገንዘቡን በወሰዱበት ጊዜ ባለው የውጪ ምንዛሬ ተመን ነው?፣ ተጠሪ ክስ በመሰረቱበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው?፣ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በሰጠበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን? ወይስ አመልካቾች ገንዘቡን ለተጠሪ በሚከፈሉበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው? የሚሉትና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

ከክርክሩ መረዳት እንደተቻለው ተጠሪ ገንዘቡን ከኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ ለአመልካቾቹ የላኩላቸው አብረው የንግድ ማህበር ለማቋቋም በመዋጮነት ቢሆንም ማህበሩም አልተመሰረተም፣ ገንዘቡም ለአመልካቾች ጥቅም የዋለ ነው ከሚባል በስተቀር ተጠሪ በዚህ ገንዘባቸው ያገኙት እንዳችም ጥቅም የሌለ መሆኑን፣ ተጠሪ በገንዘባቸው ምንም አይነት ጥቅም ሳያገኙ በአንፃሩ ግን አመልካቾች ይህንን ገንዘብ ከተጠሪ ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ከፍተኛ ገቢ እንዳገኙበት የሚገመት መሆኑን፣ ተጠሪ ገንዘቡ ለራሳቸው ንግዳዊ ስራ ወይም ለሌላ አገልግሎት አውለውት ቢሆን ኖሮ በወቅቱ ከፍተኛ ጥቅም ሊያገኙበት ይችሉ እንደነበር የሚገመት መሆኑን፣ ተጠሪ የገንዘባቸው ዋጋ ሳይወርድ አቻው የብር ምንዛሬ እስካላገኙበት ድረስ ገንዘባቸውን በተሟላ ሁኔታ አግኝተዋል ሊባሉ የሚችሉ ያለመሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በምክንያትነት ይዞ የስር ፍ/ቤቱ አመልካቾች ለተጠሪ የብር ምንዛሬው መክፈል ያለባቸው ገንዘቡን ሲወስዱ በነበረው የብር ምንዛሬ ነው ማለቱ የተጠሪን ጥቅም የሚያጓድል፣ አመልካቾችን ደግሞ አላግባብ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ደምድሞ እና ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1750 ጋር አመሳስሎ በመተርጎም አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሏቸው የሚገባው የዶላር ምንዛሬ የስር ፍርድ ቤቱ ፍርድ በሰጠበት በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም በነበረው የዶላር የብር ምንዛሬ ተመን መሆን ይገባዋል በማለት መወሰኑን ነው፡፡ በመሰረቱ ተጠሪ እንዲመሰርት የፈለጉትና ጥቅም አገኝበታለሁ ብለው የነበሩት ድርጅት ባለመቋቋሙ አመልካቾች ገንዘቡን እንዲመልሱላቸው ዳኝነት መጠየቃቸው ግልጽ ሲሆን ዶላሩን ከኬንያ አገር ወደ ኢትዩጵያ ቢልኩም 2ኛ አመልካች ገንዘቡን ከባንክ ወጪ አድርገው ሲወስዱ የተከፈላቸው በወቅቱ በነበረው የምንዛሬ ተመን ወደ ኢትዩጵያ ብር ተለውጦ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ከውጪ አገር የተላከ የውጭ ምንዛሬ ኢትዩጵያ ውስጥ በጊዜው በነበረው ተመን ታስቦ ክፍያ የተፈፀመበት ከሆነ ዶላሩ ለተላከበት አላማ አልዋለም በሚል ክርክር ሲነሳ ገንዘቡ ሊመለስ የሚገባው ዶላሩ ሲላክ በነበረበት
የውጪ ምንዛሬ ተመን ሊሆን አይገባም የሚል የሕግ መሰረት የለም፡፡

ተጠሪ ከአመልካቾች ጋር ያለው ውል በመፍረሱ ምክንያት የደረሳባቸውን የጉዳት አይነትና መጠን በግልጽ ጠቅሰውም አልተከራከረም፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ ከገንዘብ እዳ ጋር ተይይዞ የሚነሳውን የውል አፈፃጸም ለመግዛት ታስቦ የወጣ ድንጋጌ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1749 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1749(1) ድንጋጌ ገንዘብን የሚመለከት እዳ ሲሆን እዳው የሚከፈለው በአገሩ መገበያያ ገንዘብ መሆኑን በመርህ ደረጃ የደነገገ ሲሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ ደግሞ እዳው በሚከፈልበት ቦታ ውሉ ሕጋዊ ዋጋ የሌለው ገንዘብ ጠቅሶ እንደሆነ ውሉ ቃል በቃል እውነተኛ ዋጋ ወይም ይህንኑ የመሰለ ቃል ከሌለበት በቀር እዳው በሚከፈልበት ቀን ዋጋ ልክ በአገሩ ገንዘብ ሊከፈል እንደሚችል የሚያስቀምጥ ነው፡፡ በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል ላለው ጉዳይ ቀጥታም ሆነ በማመሳሰል የትርጉም መርህ ተፈፃሚ የሚሆንበት አግባብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ የገንዘብ ክፍያ ውል መሰረት ያደረገ የገንዘብ እዳ ክፍያን የሚመለከት ካለመሆኑም በላይ አመልካቾች ከተጠሪ የተላከላቸውን የአሜሪካን ዶላር በቀጥታ የተቀበሉ ሳይሆን ዶላሩ በጊዜው በነበረው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ተሰልቶ ወደ ኢትዩጵያ ብር ተመልሶ አመልካቾች መቀበላቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነውና፡፡ በአገሪቱ የገንዘብ ስርዓት መሰረት መንግስትና ሕዝብ በጊዜው በነበረው የውጪ ምንዛሬው ተመን ላገኙት ጥቅም ደግሞ ወደ ኢትዩጵያ ብር የተመነዘረ ዶላር ለተጠሪ ሊያስገኝ ይችል የነበረው ጥቅም ግምት ውስጥ ገብቶ ምንዛሬው ተመን የሚታሰብበት የሕግ አግባብም የለም፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካቾች ያላግባብ ጥቅም ሊያገኙ የሚችሉበትን አጋጣሚ ግምት ውስጥ አስገብቶ ዶላሩ በተላከበት ጊዜ በኢትዩጵያ ብር ተመንዝሮ ለአመልካቾች መሰጠቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ ለተጠሪ  ዶላሩ ከተላከበት ጊዜ በኋላ ያለው የምንዛሬ ተመን በከፍተኛ ሁኔታ የተለዋወጠ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገባ ተመኑ ለተጠሪም የሚያስገኘው ጥቅም ሕጋዊ አድርጎ መውሰዱ አግባብነት የሌለው ነው፡፡ ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ጭብጥ ሳይመሰርትና በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠው ፍሬ ነገር በመተው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌን ያለቦታው ጠቅሶ አመልካቾች 150,000.0 የአሜሪካን ዶላር ለተጠሪ ሊመልሱ የሚገባው በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ባለው የውጪ ምንዛሬ ነው በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል፡፡ በዚህም ምክንያት አመልካቾች ይህንኑ ዶላር ለተጠሪ ሊከፍሉ የሚገባው 2ኛው ተጠሪ ከአቢሲኒያ ባንክ ሲወስዱ በተከፈላቸው የውጪ ምንዛሬ ተመን ሊሆን የሚገባ ሁኖ አግኝተናል፡፡ ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ተጠሪ ገንዘባቸው ከእጃቸው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ገንዘብ ያገኙት ምንም አይነት ጥቅም ያለመኖሩ፣ በአንፃሩ ደግሞ የገንዘቡ ተጠቃሚዎች አመልካቾች በመሆናቸው ተጠሪ ይህ ገንዘብ ከእጃቸው አላግባብ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያጡት ጥቅም በወለድ ክፍያ ሊካካስላቸው የሚገባ መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተቀበለው ጉዳይ ነው፡፡ አመልካቾች በዚህ ሰበር ደረጃ የሚከራከሩት ለተጠሪ ሕጋዊ ወለድ የሚታሰብበት አግባብ የለም በሚል ሲሆን ለዚህም እንደ ሕጋዊ ምክንያት የሚያቀርቡት ተጠሪ ለአመልካቾች ማስጠንቀቂያ ያልሰጡ መሆኑንና ጉዳዩ የገንዘብ ብድርን መሰረት ያላደረገ መሆኑን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይመሰረታል የተባለው ድርጅት ሳይመሰረት መቅረቱን አመልካቾች የሚክዱት ፍሬ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በተጠሪ ቋሚ ሃብት ወይም ጥቅም ላይ መቀነስን የሚያስከትል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ በተጠሪ ላይ ቀጥተኛ የሆነ የገንዘብ ኪሳራ የደረሰባቸው መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ተጠሪ ለአመልካቾች ማስጠንቀቂያ የሚሰጡበት ምክንያት የለም፡፡ አመልካቾች ያመኑትን ገንዘብ ያህል ተጠሪ ለመውሰድ ፈቃደኛ ሊሆኑ ያለመቻላቸውንም በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጡት ጉዳይ አለመሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ይመሰረታል በማለት የጠበቁት ድርጅት ሳይመሰረት ከቀረ ለአመልካቾች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1771 እና 1705 ድንጋጌዎች አግባብ ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ይገባ ነበር ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም፡፡ እንዲሁም የወለድ ገንዘብ በብድር ጊዜ ብቻ ተፈፃሚነት የሚሆን ነው በሚል የቀረበው የአመልካቾች ክርክር ሲታይም የሕግ መሰረት የሌለው ነው፡፡ ወለድ በሕጉ አግባብ የተዘረጋው ስርዓት እንደተጠበቀ ሁኖ በስምምነት ወይም ያለስምምነት ሊከፈል የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ ወለድ ተበዳሪ የወሰደውን ገንዘብ ወይም እቃ በወቅቱ ባለመመለሱየተነሳ የሚከፈል የገንዘብ ካሳ ነው፡፡ ሌላው አይነት ወለድ አንድ ሰው ግዴታውን ባለመፈፀሙ ወይም በማዘገየቱ የተነሳ የሚከፈለው ካሳ እኩያ ነው፡፡ ስለሆነም ወለድ ለገንዘብ ብድር ብቻእንዲከፈል የሚደረግ የካሳ አይነት አይደለም፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1803(3) ድንጋጌ አንፃር ሲታይም ተጠሪ አመልካቾች የውል ግዴታቸውን ባለመፈመፀማቸው የተነሳ የካሳ እኩያ የሆነው ወለድ የማያገኙበት የሕግ ምክንያት አላገኘንም፡፡

 

በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቱ ገንዘቡ ለተጠሪ ጥቅም ያለማዋሉን አረጋግጦ እያለ ገንዘቡን የላኩት ለንግድ ማህበር ማቋቋሚያ በመዋጮነት በመሆኑ ወለድ አይገባቸውም የሚል ምክንያት አሳማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያለመቀበሉ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ በክሳቸው እንደጠየቁት 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በሚመለከት 2ኛ ተጠሪ ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ አድርገው ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ክስ ወደ ፍርድ ቤት እስከቀረበበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ ላለው ጊዜም 9% ወለድ ሊከፈላቸው ይገባል፤ በተመሳሳይም አመልካቾቹ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) ከተጠሪ ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪ ክሱን በሬጅስትራር እስካስከፈቱበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ሊከፍሏቸው ይገባል በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የሌለበት ሁኖ አግኝተናል፡፡

 

ሲጠቃለልም ከላይ በተገለፁት ሕጋዊ ምክንያቶች የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ በከፊል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሊሻሻል የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል፡፡

ው  ሳ  ኔ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ 88280 ጥቅምት 08 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች 150,000 የአሜሪካን ዶላር ለተጠሪ ሊከፍሉ የሚገባው ይኼው ዶላር ከኬንያ ናይሮቢ ወደ ኢትዩጵያ ተልኮ በአቢሲኒያ ባንክ በኩል በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ በተሰጠው ተመን መሰረት ነው ብለናል፡፡

ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ለተጠሪ በሚከፍሉት ገንዘብ ላይ ክሱ ከቀረበበት ከሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ አክለው እንዲከፍሉ የሚለውን የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል የሠጠውን ውሳኔ ይህ ችሎትም በማሻሻል አመልካቾች 150,000 ዶላሩን በሚመለከት ከላይ በተራ ቁጥር 2 መሰረት በሚገኘው የብር
ስሌት ላይ ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ 9% ወለድ በማከል እንዲሁም ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) በሚመለከት ደግሞ አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዲከፍሏቸው ወስነናል፡፡

የሥር 3ኛ ተከሳሽን በሚመለከትይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ አልተነካም፡፡

በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ በሚመለከት አመልካቾች ለተጠሪ በዚህ ሰበር ችሎት በተወሰነው የገንዘብ መጠን መሰረት የዳኝነት ገንዘብ ይክፈሏቸው ብለናል፡፡ ሌሎች ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና በዚህ ችሎት ክርክር የወጡትን ወጪና ኪሳራዎችን የያራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

 

መዝገቡ ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት::

Share this:
https://t.me/lawsocieties
የተከበራችሁ መላዉ የሀገራችን ህዝቦች፡-
እንኳን ለ2013 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ፡፡ በ2012 ዓ.ም በሀገራችን በርካታ ዉጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰላማችንን የተፈታተኑ ጉዳዮች እንደነበሩ ግልጽ ነዉ፡፡ በመሆኑም በአዲሱ አመት በፍቅርና በመተሳሰብ በጋራ የምንኖርባትን ሀገር የምንገነባበት ለመጪዉ ትዉልድ ክፉዉን ሳይሆን መልካሙን ነገር የምናቆይበት ጊዜ እንዲሆንልን በተለይ የዜጎቻችን መብትና ጥቅም የምናስከብርበትና እዉነተኛ ፍትህ የሚረጋገጥበት በሁሉም አካባቢዎች የሕግ የበላይነት ተከብሮ በሰላም የምንኖርበት የደስታ የፍቅር አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡ ተቋማችን የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሙሉ ልብ በመወጣት ለሀገራችንና ለህዝባችን ዉጤታማ ስራ የምንከናዉንበት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡
ፈጣሪ ሀገራችንና ህዝባችንን ይጠብቅልን!!!
አምባሳደር ደግፌ ቡላ ዋቅጅራ
ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተመለከተ
****************************************************************
የንብረት ባለቤትነት ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ውጤታማ የሆነ የውል አፈጻጸም ሥርዓት በመዘርጋት ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥራ ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታዎች ለመፍጠር እንዲቻል በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው በኩባንያ እና ኪሳራ ሕግጋት (Company and Insolvency Law) ዙሪያ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚሰሩ ዳኞች የተዘጋጀ የአራት ቀን ሥልጠና መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአያት ሪጀንሲ ሆቴል ሲጀመር የፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

በሥልጠናው ላይ በፌደራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በንግድ እና ተያያዥ ችሎቶች ላይ የሚሰሩ 50 ዳኞች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን በንግግራቸው በተያዘው በጀት ዓመት የተጀመረውን የሪፎርም ስራ በማጠናከር የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት የታቀደ መሆኑን በመጥቀስ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ዳኞች በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማስቻል በቂ ሥልጠናዎች ማዘጋጀት አንዱ መሆኑንና የአሁኑ ሥልጠናም የዚህ ዕቅድ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስራን ቀለል ለማድረግ (Ease of Doing Business) በተለያዩ አካላት ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ሥራዎች በጥብቅ ዲሲፒሊን እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በዳኝነት ዘርፉ እየተካሄደ ያለውን የሪፎርም ሥራ ተፈጻሚ ለማድረግ በዕቅድ ከተያዙ ሥራዎች መካከል በንግድ ሕጉ ከተካተቱ ጉዳዮች በተጨማሪ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን የመለየት (Case Categorization) ሥራን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገኝበትም ጠቅሰዋል፡፡

የንግድ ችሎቶችን እንደገና የማደራጀት ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በተለየ ሁኔታ የሚቋቋም የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፍርድ ቤት የሚደራጅበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም በእነዚህ ፍርድ ቤቶች በችሎቶች ላይ የሚመደቡ ዳኞች ችሎታ እና ብቃትን መነሻ በማድረግ የመመደቢያ መስፈርት (Guideline) ማዘጋጀት የበጀት ዓመቱ የሪፎርም ሥራ አካል እንደሆንም ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ በፌደራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በንግድ እና ተያያዥ ችሎቶች ላይ የሚሰሩ 50 ዳኞች በመሳተፍ ይገኛሉ፡፡

ሥልጠናው የሚያተኩርባቸው ርዕሰ-ጉዳዮች የንግድ ማሕበራትን በተመለከቱ የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች እና የኪሳራ ጉዳዮችን በሚመለከቱ የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች እንዲሁም በተያያዥ ርዕሶች ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከመስከረም 6 – 9 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው የዚህ ስልጠናው ዓላማ ዳኞች በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በዚህ ረገድ የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎቶችን ውጤታማ፣ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ እንዲሁም ተገማች፣ ተጠያቂነት ያለበት እና የሕዝብ አመኔታን ያረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል ነው፡፡

ሥልጠናውን የሚሰጡት ደ/ር ታደሰ ሌንጮ እና አቶ ስዩም ዮሐንስ ሲሆኑ አሠልጣኞቹ የንግድ ሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት፣ በዩኒቨርሲቲ ንግድ ሕግ በማስተማር እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁ ጆርናሎች ላይ በማሳተም ዕውቅና ያላቸው ናቸው፡፡

ሥልጠናው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ተጠሪነቱ ለዓለም ባንክ በሆነው አይ.ኤፍ.ሲ (International Financial Corporation) ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን የሥልጠናው ሒደት በአሰልጣኞች ከሚደረግ ገለጻ በተጨማሪ የዳኞችን የቡድን ውይይት እንደሚያካትት ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties
መስከረም 6፣2013

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሰራር ለውጥ ማድረጉን ተናገረ።

እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፦

በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣
በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ነግሯል፡፡

ይህ አሰራርም ከነገ መስከረም 7፣2013 ይጀመራል ተብሏል።

በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውልን አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው እወቁልኝ ብሏል፡፡

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አሰራሩን የለወጠው ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ፣ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ነው ብሏል።

#Sheger Fm #Ethiopia #ሰነዶች_ማረጋገጫ_ምዝገባ_ኤጀንሲ

https://t.me/lawsocieties
የናይጄሪያዋ ግዛት ህፃናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜናዊ ናይጄሪያ የምትገኘው ካዱና ግዛት ህጻናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች በህክምና እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች፡፡

የካዱና ገዢ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ አዲሱ የወጣው ህግ ላይ ትናንት ማምሻውን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

አዲሱ ህግ ከ14 ዓመት በታች የሚገኙ ህጻናት ደፋሪዎችን በህክምና እንዲኮላሹ ከማድረግ በተጨማሪ የእድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው ናይጄሪያ አስገድዶ መድፈርን የሚቃወሙ ዘመቻዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ጠርጥሬያቸዋለው ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነግሯል፡፡

አዲሱን ህግ ያጸደቀችው ካዱና ግዛት ይህንን ውሳኔ ስታሳልፍ በናይጄሪያ ከሚገኙ ግዛቶች መካከል ብቸኛዋ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ source:- FBC

https://t.me/lawsocieties
#ብር_የመለወጡ_ቀጥተኛ_ጥቅም!
***
ብዙ ሰዎች በተደጋገሚ ብሩ በመለወጡ በቀጥታ ኢኮኖሚው ላይ የሚመጣውን ጥቅም ንገረን ብለው ጠይቀውኛል! ብር በመለወጡ የሚገኙት የአጭር ግዜ እና የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው!

የአጭር ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- በሀገራችን ከ113ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከፋይናንስ ገበያው ቁጥጥር ውጪ አለ! ስለዚህ የገንዘብ ለውጡ ይህንን ገንዘብ ወደ ብሄራዊ ባንክ የመለወጥ እድል ይፈጥራል!

#ለምሳሌ፡- ምንጩ ያልታወቀ በመሆኑ ወደ ባንክ ሳይመጣ ከሚበላሸው፤ ከሀገር ውጪ በጎረቤት ሀገር በመሸሹ ከማይመለሰው፤ የመቀየሪያ ወቅቱ ከሚያልፍበት፤ በጎርፍ፤ በቃጠሎ፤ ወዘተ ከወደመው ውጪ 100 ቢሊዮን ብር እንኳን ወደ ህጋዊ የባንክ ስርዓት ቢመጣ ከፍተኛ ገንዘብ ከገበያ የመሰብሰብ እድል ስለሚፈጠር የዋጋ ንረት በሚታይ መልኩ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል!

ምንጩ ያልታወቀ፤ በሙስና የተገኘ፤ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከፍተኛ ገንዘብ በገበያ በድርጅቶች እና በሰዎች እጅ እንደሚገኝ ይታወቃል! ስለዚህ የተቀመጠውን የጥሬ ገንዘብ ገደብ (1.5 ሚሊዮን ብር ለማለት ነው!) እና ከ5 ሺህ ብር በላይ በባለቤቶች እንዲቀመጥ የሚያዘውን መመሪያ ተከትሎ ህገወጦችን ለመለየት እድል ይፈጥራል፡፡

#ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሃብት ያከማቸ ሰው ወይም ድርጅት ህጋዊ ከሆኑት ሰዎች ተገቢ ያልሆነ Advantage እንደወሰደ ግልጽ ነው! ስለዚህ የብሩ መቀየር የተለየ እድል ያገኙ ሰዎችን በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ያሰችላል፡፡

የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- ኢትዮጲያ ውስጥ በባንክ ቤቶች ያለው የቁጠባ መጠን ማነስ እና ባንኮች ለባለሃብቶች የሚያቀርቡት የብድር መጠን ማነስ የታወቀ ጉዳይ ነው! ስለዚህ ለምሳሌ 100 ቢሊዮኑ ቢሰበሰብ እና የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ገደቡን ተከትሎ 80 ቢሊዮኑ በባንኮች ቢቀመጥ ተጨማሪ ቁጠባ እና ተጨማሪ የብድር አቅርቦት እንዲገኝ ያደርጋል፡፡

#ለምሳሌ፡- መንግስት ባወጣዊ አዲስ መመሪያ መሰረት የግል ባንኮች የመንግስትን የግምጃ ቤት ሰነድ የመግዛት እድል ተፈጥሮላቸዋል! ስለዚህ መንግስት ወደ ፊት ለሚያስበው የበጀት ጉድለትን በሀገር ውስጥ የመሙላት ፍላጎት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግለው ይችላል፡፡

ገንዘቦች በመሰብሰባቸው እና በግል ባንኮች ውስጥ በመቀመጣቸው የሚቀርበው ብድር የግል ሴክተሩን በማነቃቃት ተጨማሪ ምርት እንዲመረት፤ ተጨማሪ ሰራተኛ እንዲቀጠር፤ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች አድገው የውጪ ምንዛሬ ግኝት እንዲያድግ፤ የሀገር ውስጥ አምራቾች ተበረታተው ከውጪ የሚገቡትን የመተካት አቅም የሚፈጥሩ ከሆነ የውጪ ምንዛሬ እንዲቆጠብ፤ ወዘተ የማድረግ አቅም ይኖረዋል፡፡

ነገር ግን ብር መለወጡ ብቻውን ስር ነቀል ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም! ምክንያቱም ዋጋ ንረት፤ ስራ አጥነት፤ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ማነስ፤ የበጀት ጉድለት፤ ዝቅተኛ ምርት እና ምርታማነት መኖር፤ የንግድ ሚዛን መዛባት፤ ወዘተ በገንዘብ ምክንያት ብቻ የመጡም አይደሉም በገንዘብ ምክንያት ብቻም የሚፈቱ አይደሉም! ሌሎች ፖሊሲዎች እና ስራዎች በተጨማሪነት መሰራታቸው ግድ ነው!
via the Ethiopian economist view

https://t.me/lawsocieties
የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
----------------------------------------------------------------------- ይቀላቀሉን‼️
https://t.me/lawsocieties
የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-----------------------------------------------------------------------
ሁሉም የመንግስት ተቋማት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ተሳትፎ ጎን ለጎን የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ሀገራችንን ወደመልካም ጅማሮ ማሻገር እንደሚገባ የፍትሐ-ብሔር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ሄኖክ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

መንግስት በየዓመቱ ከሚበጅተው በጀት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ከሚይዙ ጉዳዮች መካከል ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር የሚገቡ ውሎች፣ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት አማራጭ የሙግት መፍቻ ማዕከላት ያሏቸው የድርድር እና የግልግል ዳኝነት ሂደቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ፍርድ ቤቶች ያሏቸው የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ክርክሮች መሆናቸውን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ ይህን የሚያህል የሀገር ውድ ሀብት በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት እንዳይባክኑና ተጨማሪ ወጪ እንዳያስወጡ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር የተለያዩ የግንባታ ሥራ፣ የእቃ ግዥ፣ የማማከር አገልግሎት እና ሌሎች ውሎችን ከወረርሽኙ አስቀድሞም ይሁን በአሁኑ ወቅት እየተዋዋሉ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እነዚህ ውሎች በባህሪያቸው ለተወሰነ ጊዜ የሚቆዩ እና አስቸኳይ ለሆነ ማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ በመሆናቸው በተለይ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ተገብተው ከነበሩ ውሎች የሚጠበቀው ውጤት በተቀመጠለት ጊዜ እንደሚደርስ ታሳቢ ተደርጎ የተፈፀመው ከወረርሽኙ በፊት በነበረው የሀገራችን የዕለት ከዕለት የስራ እንቅስቃሴ አንፃር እንደነበር በመግለጽ በወረርሽኝ ምክንያት እክል እየገጠማቸው ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ተቋማቱ የገቧቸውን ውሎች የአፈፃፀም ሂደት በዚህ ወቅት መገምገምና በውሉ ላይ የተመለከተው ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያትን የሚደነግገውን ክፍል በአግባቡ በመመርመር እንደየጉዳዩ አግባብ ወረርሽኙ ከአቅም በላይ የሆነባቸውን ተዋዋዮች ለይቶ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች መወያየትና ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተገቢ ነው ያሉት ዳይሬክተር ጄኔራሉ በአንፃሩ ወረርሽኙ ከአቅም በላይ የሆነ ክስተት ያልፈጠረባቸውን ተዋዋይ ወገኖች የውል አፈፃፀም ሂደቶችን በመለየት አፈፃፀሙን እንዲቀጥሉ የማሳሰብ እና ማስጠንቀቂያ የመስጠት አለፍ ሲልም ለውል አፈፃፀም ማስከበሪያ የተያዘን የዋስትና ገንዘብ የመውረስ እና ሌሎች በውሉ ውስጥ የተመለከቱ የመብት ማስከበሪያ መንገዶችን በመከተል እርምጃዎችን መውሰድ ተገቢ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የመንግስት ተቋማቱ በአሁኑ ወቅት ብዙ ትኩረት የሰጡት ወረርሽኙን መከላከል ላይ በመሆኑ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት አማራጭ የሙግት መፍቻ ማዕከላት ያሏቸው የድርድር እና የግልግል ዳኝነት ሂደቶችን ችላ የማለት ሁኔታ በመፈጠፉ የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት በግልግል ዳኝነት አመራር ሂደት ላይ መብታቸውን የሚያጣብቡ ተግባራትን ሲፈጽሙ እየተስዋለ ይገኛል፤ ለአብነትም የግልግል ዳኝነት መጠየቂያ መጥሪያ በኢ-ሜይል ደርሷቸው በ30 ቀናት ምላሽ እንዲሰጡበት ለሚሰጠው ትዕዛዝ ምላሽ ሳይሰጡ ጊዜው የሚያልፍ፤ ምላሽ ሲሰጡም በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ በመሆኑ ምላሽ መስጠት የማይችሉ መሆኑን መግለጽ፤ የተጀመረው የግልግል ዳኝነት ሂደት ወረርሽኙን መቆጣጠር እስኪቻል ታግዶ እንዲቆይ በመጠየቃቻ፤ ምላሽ የመስጠት መብታቸው የታለፈ እና በነሱ ሊመረጥ የሚገባውን የግልግል ዳኛ ሌላ አካል እንዲመርጠው ውሳኔ መተላለፉን የገለጹ ሲሆን ከክፍያ ጋር በተያያዘም በግልግል ዳኝነት ለተሰጠ የጥብቅና አገልግሎት ለተጠየቀ ክፍያ የተሰጡ ምላሾችና በኢ-ሜይል እንዲላኩ የተጠየቁ ማስረጃዎች ያለመላክ ለከፍተኛ ጉዳት ሊዳርጉ የሚችሉ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥቶ ማጤን አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የፍትሐ-ብሔር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሄኖክ ተስፋዬ ሌላውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት ጉዳል የፍትሐ-ብሔር ቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና የአፈፃፀም ክርክሮችን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በመሆናቸው በመደበኛው ሂደት ሲታዩ የነበሩ ጉዳዮች በቀጠሮ እየተላለፉ እንደሆነ አስታውሰው ይህ ሂደት የመንግስት ተቋማት የነበረባቸውን የክርክር ጫና በተወሰነ መልኩ የሚቀንስ መሆኑን እንደ አንድ አስቻይ ዕድል በመጠቀም የክርክር መዛግብቶቻቸውን በመፈተሽና በአግባቡ በማደራጀት፤ የተጓደሉ ማስረጃዎችና ሌሎች መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ካሉም በመለየትና የሚሟሉበትን መንገድ በመቀየስ፤ በክርክር አመራር የተፈፀመ ግድፈት ካለ የሚቃናበትን መንገድ በማጤንና ፍርድ ቤቶች ስራ ሲጀምሩ ሊቀርቡ የሚገባቸውን ማስረጃዎች፣ አቤቱታዎች እና ቃለ-መሀላዎችን በማዘጋጀት ክርክራቸው የህዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ እንደሆነ የገለጹት ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ ክርክር ባልተጀመሩባቸው ጉዳዮች ላይም ተገቢውን ማስረጃ በማሰባሰብ፣ የፍርድ ባለመብት ከሆኑ ፍርዱን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ንብረቶችን በማፈላለግ እና ተከሳሽ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ንብረቶችን እንዳያሸሹ ክትትል በማድረግና እንዳስፈላጊነቱም በፍርድ ቤት እንዲታገዱ አቤቱታ በማቅረብ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ በቀጣይ ስኬታማ ክርክር ለማድረግ ዝግጁ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/lawsocieties
new vacancy for inventory
#pce ventures manufacturing plc
sex: man
experience: 0
total: two
work place: Addis ababa
qualification: inventory
apply via email address: mikias@parkerclay.com
share to your friends
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አመለከቱ።

ምክር ቤቱምበቀረበው ሪፖርት ላይ እየተወያየ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ሊያ ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል
Forwarded from Abubeker Delil
Please can i get civil procedure teaching material?
👍ዛሬ አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ተሰጥቷል!‼️

የፀጥታ ኃይሎች ከ1.5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ የለባቸውም ተብሏል።

ዶ/ር ይናገር ደሴ (የብሄራዊ ባንክ ገዥ) ፦

- ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር ተፈጥሯል። በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ ነው ይህ ተገቢ አይደለም።

- እስከ1.5 ሚልየን ብር ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ ይችላሉ።
♦️
- ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን አይመለከትም። ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
🔺
- አንዳንዶች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ ነው መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትም እኩል የሚያገለግል ነው።

- በተለያዩ ባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ካሉ ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል ተቋቁሟል ፤ ይህንን ተግባር ፈጽሞ በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

- በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እና በሌላ ሰው ስም ገንዘብ ማስገባት አይቻልም።
🔺
- ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ ከጅቡቲ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ሁሉም ገንዘብ ህገ ወጥ ነው ተብሎ መያዝ የለበትም።

- አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት ይችላሉ፤ሲገቡ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ ይችላሉ-(ኤፍቢሲ)
https://t.me/lawsocieties
#Notice
All Year II and above Regular graduate students
This is to inform you that second year and above graduate students registration of first semester 2020/21 AY will be on September 21 and 22, 2020 and class will begin on September 23, 2020. This is therefore, to request your cooperation for effective implementation of the registrations.
http://www.aau.edu.et/blog/all-year-ii-and-above-regular-graduate-students/
AAU Registrar
Addis ababa university
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በቀን /መደበኛ/ ፕሮግራም ከ2005 እስከ 2012 ዓ.ም ተምረዉ ለተመረቁ አካል ጉዳተኛና ሴት ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) አዘጋጅቷል፡፡
የትምህረት አሰጣጡ የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል እና በኢለርኒግ የመማር ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡
1. ከመንግስት ዩኒቨርስቲ በቀን /መደበኛ /ፕሮግራም የተመረቀ/ች
2. የመጨረሻ የትምህርት ዉጤት (CGPA) 2.75 እና በላይ ያላቸዉ
3. ያለባቸዉን የወጪ መጋራት ክፍያ ከፍለዉ የጨረሱ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ማስላክ የሚችሉ
4. በገንዘብ ድጎማ (የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸዉ) ለሚወዳደሩ ከፍለዉ መማር እንደማይችሉ ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ለአካል ጉዳተኞች ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. ትምህርት ክፍሉ የሚያወጣዉን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ሲኖርባቸው
አመልካቾች
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር 600 /ስድስት መቶ/ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም  በቅርንጫፍ  አማካኝነት ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል (ክፍያ የሚፈጸምበትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 አጭር ኮዶች ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት በዩኒቨርሰቲው ድረ ገጽ እና በፌስቡክ እናሳውቃለን) 
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን እና ሌሎች መረጃዎችን አስገብተው ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ$ 
4. የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና ያለው CGPA ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡
ማሳሰቢያ
• ምዝገባው የሚከናወነው portal.aau.edu.et ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
• የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን ማስረጃ ዋናውን በተጠየቃችሁ ግዜ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
• የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (portal.aau.edu.et/aau.edu.et) መከታተል የምትችሉ ያሳውቃል፡፡
• ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን  Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ 
• የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
የመመዝገቢያ ቀን ከነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ 21 2012 ዓ.ም  

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
Addis ababa university
https://t.me/lawsocieties
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ-ወጥነት መያዝ እንደማይቻል ተገለጸ፡፡
*************************************

የፀጥታ ኃይሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ እንደሌለባቸው ተገለፀ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በዛሬው እለት አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር መፈጠሩን ገልጸዋል።

በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ መሆኑን እና ይህም ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው እስከ 1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን እንደማይመለከትም ተጠቅሷል።

ነገር ግን ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩትም አሳስበዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትም እኩል የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡

በተለያዩ በባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ካሉም ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል በመቋቋሙ ይህንን ተግባር ፈጽሞ በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስገንዝበዋል።

እንዲሁም በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እንዲሁም በሌላ ሰው ስም ገንዘብ ማስገባት እንደማይቻልም ተጠቅሷል።

ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ የጅቡቲ አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ ሁሉም ገንዘብ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ መያዝ እንደሌለበት በመግለጫው ተጠቅሷል።

አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት እንደሚችሉ፤ ሲገቡ ደግሞ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ የሚችሉ መሆኑም ታውቋል።

ሆኖም ግን በህገ-ወጥ መንገድ ብር በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ደብቀው ለማስገባት የሚመክሩ ካሉ እንደሚወረስባቸው ተጠቅሷል።

https://t.me/lawsocieties