መስከረም 6፣2013
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሰራር ለውጥ ማድረጉን ተናገረ።
እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፦
➖በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣
➖በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ነግሯል፡፡
ይህ አሰራርም ከነገ መስከረም 7፣2013 ይጀመራል ተብሏል።
በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውልን አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው እወቁልኝ ብሏል፡፡
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አሰራሩን የለወጠው ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ፣ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ነው ብሏል።
#Sheger Fm #Ethiopia #ሰነዶች_ማረጋገጫ_ምዝገባ_ኤጀንሲ
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/