አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የ2012 ዓ.ም የዳኝነት የስራ ዓመት መገባደድ እና የ2013 አዲስ ዓመት መባቻን አስመልክቶ ለዳኞች የምስጋና መግለጫ ልከዋል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ክቡራንና ክቡራት ዳኞች

ባሳለፍነው የዳኝነት ዘመን በፍርድ ቤቶች ለተስተዋለው የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ያሳያነው የዳኝነት ኃላፊነት ስሜት፤ የሙያ ስነምግባርና ክብር የሚመሰገን ነው፡፡ ለተገኘው ውጤትም በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራር አካላት በኩል ለተፈጠረው የጋራ ራዕይ፣ ግልጽነት፣ የመተማመን መንፈስ እና የስራ ትጋር ያለኝን አድናቆት እገልጻለሁ!!

የዳኝነት ዘርፉን በተሟላ ቅርጽና ይዘት የማሻሻል አቅም የሚፈጥሩና የማዕዘን ድንጋይ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ የፌዴራሉ መንግስት የዳኝነት አካል ራሱን በሙሉ ነጻነት ማስተዳደር የሚያስችል እና የፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚወስነውን አዋጅ በአዲስ መልክ የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጆች ተዘጋጅተው ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም ላቀረባቸው የማብራሪያ ጥያቄዎች ዝረዝር ማብራሪያ በመስጠት በኮቪድ ምክንያት በሙሉ ዓቅሙ ስራ እንዳይሰራ ከማድረጉ በፊት የመጽደቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡

ሌላው በዚህ ዓመት ከተከናወኑት ዓበይት ስራዎች መካከል በዓለማችን እንዲሁም በሃገራችን በተከሰተውና እስከአሁንም መፍትሄ ባልተገኘለት የኮቪድ 19 ወርሽኝ ምክንያት የዜጎችን የዳኝነት መብት እና በጤና በህይወት የመኖር መብት በአንድ ላይ ለማረጋገጥ ከገባንበት አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣት የሰራነው ስራ አንዱ ነው፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ማሰራጫ ማዕከል እንዳይሆኑ ለማድረግ በተወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ ፍ/ቤቶች ከመጋቢት እስከ ሐምሌ አጋማሽ በከፊል ዝግ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚሀም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤቶቻችን ሊመጣ የሚችል የመዛግብት ፍሰት የቀነሰ ቢሆንም ዳኞች በቤታችሁና በቢሯችሁ ለምርመራ ለደረሱ መዛግብት እልባት ለመስጠት ጊዜያችሁን በመጠቀማችሁ በፌዴራል ፍ/ቤቶች ደረጃ 140 ሺህ ለሚሆኑ መዛግበት እልባት መስጠት ተችሏል፡፡

በወረርሽኙ ምክንያት ፍ/ቤቶቸ በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ በተደረጉበት ተመሳሳይ ጊዜ አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች በተረኛ ችሎት በማስተናገድ ለ7 ሺህ መዛግብት እልባት ተሰጥቷል፡፡ ይህም በአጣዳፊ ሁኔታ ዳኝነት ለሚሹ ወገኖቻችን ከራሳችሁ ደህንነት ይልቅ የእነርሱን በማስቀደም አወንታዊ ምላሽ ለመስጠት ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ የተጠቀማችሁበት ለመሆኑ ያሳያችሁበት ነው ለማለት ያስችላል፡፡

የዳኝነት የስራ ጫና ለመቀነስ ከ150 በላይ የረዳት ዳኞች ቅጥር በማከናወን የዳኞችን የስራ ሸክም ለማቃለልም ተችሏል፡፡ የሬጂስትራር ባለሙያዎቸን በበቂ ቁጥር በመሾምና የሙያ ብቃታቸውን የሚያጎለብት ስልጠና ተሰጥቷል፤ የአሰራር ለውጥ ተደርጓል፡፡ ከተገልጋዮቻችን ያገኘነው ግብረመልስ የሬጂስትራር አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናም መጨመሩን ጠቁሞናል፡፡
የተወደዳችሁ ዳኞች

የዳኝነት አንዱ መገለጫ ባህሪው ግልጽነት ነው፡፡ ዳኝነትን በግልጽ ችሎት ለመስጠት የማያስችሉ፤ ለዳኞችና ለተገልጋይ ምቾት የሌላቸውን ምድብ ችሎቶችን በመለየት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ህንጻዎችን በመከራየት ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ጥረትም አበረታች ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመናገሻ እና የአራዳ ምድብ ችሎቶች እንዲሁም ከከፍተኛ ፍ/ቤት ጦሃይሎች ምድብ ችሎት ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

እንደምትገነዘቡት የዳኝነት ነጻነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያስመዘገብንባቸው አኩሪ እና ፈር ቀዳጅ ውጤቶችም አሉ፡፡ የዳኝነት አካሉን የበጀት ነጻነት ለማስጠበቅ በተሰራው ስራ በህገመንግስቱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት የፍርድ ቤትን በጀት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ በማቅረብ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ምኒስቴር ከተቀመጠው የበጀት ጣሪያ በላይ በማስፈቀድ በጀቱን በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነትና መብት አስከብሮ ገለልተኛ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታችን ለመፍጠር በተደረጉ ጥረቶች ዳኞች ያለባቸው የስራ ሃላፊነትና ጫና እነዲሁም የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከግንዛቤ ያስገባ የደመወዝ ማስተካከያም መደረጉ ይታወቃል፡፡ በእቅድ ከተያዘለት ጊዜ በላይ የወሰደው የዳኞች የጋራ መኖሪያ ሕንጻ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ከመንግስትና ከተቋራጩ ድርጅት ጋር በተደረጉ ያልተቋረጠ ክትትልና የአስተዳደር ድጋፍ ስራችን ፍሬ አፍርቶ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ችለናል፡፡ ዳኞች በቤት ኪራይ ሲደርስባቸው ከነበረው እንግልት የሚያወጣቸውና መኖሪያ ብቻ ሳይሆን እንደቢሮም የሚገለገሉባቸው 140 ባለ ሶስት እና 138 ባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡

ከላይ የጠቀስናቸው አመርቂ ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም ያልተሸገርናቸውና ጉዳዮች አሉ፡፡ በጀመርነው አዲስ የዳኝነት ዓመት (2013 ዓ.ም) የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ስርዓታችን እንዱ በልዩ ትኩረት ልንሰራበት የሚገባ ዘርፍ ነው፡፡ በጀምር ላይ ያለውና የመደበኛ ፍርድ ቤቶቻችንን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል ፍርድ ቤት መር የአስማሚነት አገልግሎት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታን ማመቻቸት ያስፈልገናል፡፡

የምንሰጠው ዳኝነት ከቅልጥፍና አንጻር መልካም ደረጃ ላይ ደርሷል ሊባል የሚችል ቢሆንም ከምንሰጠው ዳኝነት ጥራት አኳያ ውስንነቶች እንዳሉ በተለያየ መንገድ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የዳኝነት ነጻነት ሚዛን መጠበቂያ የሆነው የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓታችንንም እንደዚሁ የምንፈትሽና በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀን የዲሲፕሊንና ስነምግባር መመሪያ እንዲሁም የአፈጻጸም ምዘና መመሪያን በማጽደቅ ስራ ላይ የምናውል ይሆናል፡፡

ፍርድ ቤቶቻችን ለአራት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው በመቆቀታቸው በወቅቱ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች ሳይታዩና መዝገብ ሳይከፈትላቸው በመቆየታቸው በጀመርነው አዲስ አመት የመዝገብ ፍሰቱ መጨመሩ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም በተባበረ መንፈስ ጠንክረን በመስራት በፍርድ ቤቶቻችን እየታየ ያለውን ለውጥ በማስቀጠል አምና ያገኘነውን የሚያስመሰግን ውጤት ከፍ ባለ ደረጃ እንድንደግመው በጋራ ራዕያችን ላይ በጽናት እንድንቆም በዚሁ አጋጣሚ ልጠይቃችሁ አፈልጋለሁ፡፡

የአዲሱ አመት የመጀመሪያው ወር የእረፍት ጊዜያችሁ አንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤቶቻችን የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቻችሁ ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ በፈቃዳችሁ የምትቆዩ መሆናችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፡፡

ወድ ዳኞች በመጨረሻም

መጪው አዲስ ዘመን ቃል የገባንለት ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የመስጠት ተልዕኳችንን በእውቀትና በሙያ፤ በገለልተኝነትና በሐቀኝት፤ በቅልጥፍናና በጥራት፤ በነጻነትና በተጠያቂነት የምንወጣበት፤ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለው ዓመኔታ ከፍ የሚልበት እና ለሌላ ተጨማሪ ስኬት የምንበቃበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!

ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ መንግስቱ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት
ጷጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም
🎤የተከበራችሁ ክቡራት እና ክቡረን የ ALE channel ቤቸሰቦች ስላማችሁ ይብዛ በያላችሁበት ።

አህመድ እንድሪስ እባላለው በ ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት የ 4ኛ ዓመት ተማሪ ነኝ።

1⃣በቅድሚያ እንኳን (ለ ሀበሻዎች የዘመን መለወጫ ለሆነው)ለ ዓዲሱ ዓመት 2013 ዓ.ም በስላም አደረሳችሁ አደረስን።

2⃣በመቀጠል ይህ ቻናል(channel) ከተከፈተበት ቀን አንሰቶ እሰካሁን ደረስ ጥሩና የወሳኝ የሆኑ ሕግ ነክ መረጃዎችን: አጋዥ ማቴሪያሎችን እና ሌሎች ተዛመጅነት ያላቸው ጠቃሚ መረጃዎችን እያደረሰን ይገኛል።
↪️ስለሆነም መስጋናችን በጣም የላቀ ነው አሁንም ትብብረዎን እንሻለን መለገሰዎን ቢቀጥሉ።

🔵አዲሱን ዓመት የሰላም የፍቅር የደግነት የብሩህ ተሰፋ የጤና ያደርግልን ዘንድ ትልቅ ምኞቴ ነው ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️Happy new year 2013 EC.

@wulsu
እንኳን ለዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ!
አዲሱ 2013 ዓመት የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንልን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመላው ኢትዮጵያውያን ይመኛል!
የፌደራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር በከፊል ዝግ ሆነው ይቆያሉ
********************
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
ይህም ፍርድ ቤቶች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከመጋቢት 10 - እስከ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው ከቆዩብ ሁኔታ ለመውጣትና ተቋርጦው የነበሩት አገልግሎቶችን ደረጃ በደረጃ ለማስጀመር ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው መመሪያ መሰረት ዳኞች በመስከረም ወር እረፍት አንዲያደርጉ በመወሰኑ ነው ተብሏል፡፡
ዳኞች ዓመታዊ እረፍታቸውን በነሃሴ እና በመስከረም ወር የሚወስዱ በመሆኑ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎቶች በማስተናገድ በከፊል ዝግ ሆነው እንደሚቆዩ ማድረግ የተለመደ አሰራር መሆኑን ያስታወሰው ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ በዚህ ዓመት ዳኞች አጭር የእረፍት ጊዜ እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡
ፍርድ ቤቶቹ በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው የመስከረም ወር 20 የስራ ቀናት አስቸኳይና ጊዜ የማይሰጡ ከዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲሁም ከአገር ሰላምና ፀጥታ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጉዳዮች እንደሚመለከቱ ተገልጿል፡፡
ለአብነትም እንደ የጊዜ ቀጠሮ፣ የዋስትናና የዕግድ ጥያቄዎች፣ የመያዣና የብርበራ ትዕዛዞች፣ በተፋጠነ ስነ-ስርዓት የሚታዩ የእጅ ከፍንጅ ወንጀሎች እንዲሁም ከቤተሰብና ከሕፃናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር የተያያዙ አጣዳፊ መሰረታዊ ጉዳዮች በተረኛ ችሎቶች የሚስተናገዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡
የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያው ወር ለዳኞች የእረፍት ጊዜያቸው አንዲሆን የተወሰነ ቢሆን በፍርድ ቤቶች የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቹ ዳኞች በፈቃዳቸው ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ የሚቆዩ መሆናቸውን ከፕሬዝደንት ጽ/ቤት ከተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤ ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ለዳኞች በስተላለፉት የምስጋና መግለጫ “መጪው አዲስ ዘመን ቃል የገባንለት ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የመስጠት ተልዕኳችንን በእውቀትና በሙያ፤ በገለልተኝነትና በሐቀኝት፤ በቅልጥፍናና በጥራት፤ በነጻነትና በተጠያቂነት የምንወጣበት፤ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለው ዓመኔታ ከፍ የሚልበት እና ለሌላ ተጨማሪ ስኬት የምንበቃበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!” ብለዋል፡፡
የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Legal Expert
#ethiopian_national_accreditation_office
#legal_services
#law
#legal_expert
Addis Ababa
LLB in Law with relevant work experience in related legal service
Minimum Years Of Experience: #6_years
Deadline: September 16, 2020
How To Apply: In person to the following address: Bole sub city Ethiopian National Accreditation Office 3rd floor to the HR office no. 304. Tel: 011667- 0994/011833-3770
Forwarded from ...
Selam ye robert allen sadler "Ethiopian civil procedure law" yemilew metsihaf pdf kale share bitareguln .Thank you in advance.
please share me exit exams for 2007, 2008,and 2011 EC.
Thankyou in advance.
አለሕግAleHig ️
Robert Allen Sendler 2.pdf
Thank for sending Robert Allen sendler. I want to finish the reading after the interrupt of teaching by causes of covid 19. I searched everywhere but impossible to find except WSU university library
የገንዘብ ይመለስልኝ ክርክር-የእሽሙር ማህበር ሰ/መ/ቁ. 95069 ቅፅ 17


ByAbrham Yohannes

 SEP 13, 2020

የሰ/መ/ቁ. 95069

ህዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም

                           ዳኞች፡- አልማው ወሌ

ዓሊ መሐመድ

  ሡልጣን አባተማም

 ሙስጠፋ አህመድ

                                 ተኽሊት ይመሰል

አመልካች፡- 1. ሴፍሜት አግሪ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

አቶ ወንድምአንተነህ መሸሻ ጠበቃ ውቤ አለነ ቀረቡ    ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ብረቱ ሱኬሱ ጠበቃ ወንድአወክ አየለ ቀረቡ  መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ፍ  ር  ድ

ጉዳዩ የገንዘብ ይመለስልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኗ  ተጠሪ የአሁኑ አመልካቾችን እንደቅደምተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች፣ ወ/ሮ ትግስት ድረስ የተባሉትን ግለሰብ ደግሞ 3ኛ ተከሳሽ በማድረግ መጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡ የተጠሪ የክስ ይዘትም፡- 2ኛው ተከሳሽ 1ኛ ተከሳሽን በአሽሙር ማህበር በመመስረት የጥቁር ድንጋይ ማምረቻ እናቋቁም በማለት ተጠሪዋን ባግባቧቸው መሰረት በሚኖሩበት ከኬኒያ ናይሮቢ ከተማ ሆነው በተለያዩ ጊዜያት ማለትም ነሐሴ 06 ቀን 2001 ዓ.ም 10,000 የአሜሪካ ዶላር፣ ነሐሴ 07 ቀን 2001 ዓ/ም 70,000 የአሜሪካ ዶላር፣ ነሐሴ 11 ቀን 2001 ዓ.ም ደግሞ 67,000 የአሜሪካ ዶላር በ1ኛ አመልካች ስም ናይሮቢ ከተማ በሚገኘው ዲያመንድ ትረስት ባንክ አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው በአቢሲኒያ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ በኩል እንደላኩና ለእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ለተላኩት ገንዘቦች ደግሞ በተከታታይ 204 ዶላር፣ 1429 ዶላር፣ 1367 ዶላር ኮሚሽን እንደከፈሉባቸውና በአጠቃለይም 150,000 የአሜሪካን ዶላር ልከው 2ኛው አመልካችም ይህን ገንዘብ መቀበላቸውን በደረሰኝ ያረጋገጡላቸው መሆኑን እንዲሁም እርሳቸው ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት የአሽሙር ማህበሩን ለማቋቋም ተጨማሪ ገንዘብ መስጠት አለብሽ በማለት 2ኛው አመልካች በጠየቋቸው መሰረት ጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ደረሰኝ አማካኝነት ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር) የሰጧቸው መሆኑን፣ ከዚህ ጊዜ በኋላ ግን 2ኛ አመልካችን ለማግኘት እንደተቸገሩና ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ አግኝተዋቸው ሲጠይቋቸው ገንዘቡን ለሌላ ፕሮጀክት እንዳዋሉት እንደገለፁላቸው፣ እርሳቸውን በደንብ የሚያውቋቸውን የ2ኛ አመልካች ባለቤት የሆኑትን የሥር 3ኛ ተከሳሽ የነበሩትን ግለሰብ ሲጠይቋቸውም “ገንዘብሽን አንክድሽም፤ ጊዜ ስጭንና ከባንክ ተበድረን እንሰጥሻለን” እንዳሏቸውና እርሳቸውም ባዶ እጃቸውን ወደ ኬኒያ እንደተመለሱ እና አመልካቾችም ሆነ የሥር 3ኛ ተከሳሽ ገንዘባቸውን ሊመልሱላቸው እንዳልቻሉ በመዘርዘር አመልካቾች የወሰዱትን 150,000 የአሜሪካ ዶላር ክስ በቀረበበት ከመጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም በነበረው የአንድ ዶላር ምንዛሬ ብር

16.7293 ሂሳብ ብር 2,509,395 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሶስት መቶ ዘጠና አምስት ብር) እንዲሁም የዚህን ገንዘብ የመጨረሻ ክፍያ (67,000 ዶላር) ከተከፈለበት ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት እስከ መጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ብር 368,159.20  ተጨምሮበት እንዲከፈላቸው፣ እንዲሁም ብር 800,000.00 (ስምንት መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር) እና ይህ ገንዘብ ከተወሰደበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት እስከ መጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ብር 112,636.60 (አንድ መቶ አስራ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከስልሳ ሳንቲም) እንዲከፈሏቸው ጠቅሰው በአጠቃላይም ከላይ የተዘረዘረውን ገንዘብ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ያለው ብር 3,790,189.82 (ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠና ሺ አንድ መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከሰማኒያ ሁለት ሳንቲም) ክሱ ከቀረበበት ከመጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ወለድ ጋር በውጭ ምንዛሬ የወሰዱትም በሚከፍሉበት ወቅት በሚኖረው ምንዛሬ ታስቦ እንዲከፍሏቸው፣  የጠበቃ አበል በውላቸው መሰረት፣ ሌሎች ወጪና ኪሳራዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ዝርዝር መሰረት እንዲወሰንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የአሁኑ አመልካቾች ለክሱ በሰጡት መልስም፡- ከሳሿ የክስ ምክንያት የሌላቸው መሆኑን፣ ከሳሿ ገንዘቡን ያዋጡት ለአሽሙር ማህበር መዋጮ በመሆኑ 1ኛ አመልካችን የሚመለከት ክስ ከሚሆን በስተቀር 2ኛ አመልካችን እና የሥር 3ኛ ተከሳሽን በሚመለከት የመክሰስ ጥቅም እንዳላቸው ያለማረጋገጣቸውን፣ ገንዘቡ ገቢ የተደረገውና በ2ኛ አመልካች ወጪ የሆነው በኢትዮጵያ ብር በመሆኑ እርሳቸው ባሉበት የዶላር ምንዛሬ ሊጠይቁ እንደማይገባ፣ ገንዘቡን የላኩት በመዋጮ መልክ በመሆኑ ወለድ ሊታሰብላቸው እንደማይገባ፣ ከሳሽ በአጠቃላይ ያዋጡት ገንዘብ ብር 2,634,089.73 ሁኖ ከዚህ ገንዘብ ውስጥም ብር 139,200.75 ከሳሿ መልሰው የወሰዱ በመሆናቸው ይህ ተቀንሶ የሚቀራቸው ብር 2,494,888.98 መሆኑንና ይህን ገንዘብ ብቻ ለመውሰድ ፈቃደኛ ባለመሆን በመሰረቱት ክስ ወጪና ኪሳራ ሊከፍሉ እንደማይገባ ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ የሥር 3ኛ ተከሳሻም የአሁኑ 2ኛ አመልካች ባለቤት ከመሆናቸው ውጪ ለክሱ ኃላፊ የሚሆኑበት ሕጋዊ ምክንያት የሌለ መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም አመልካቾች ያቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ አድርጎ ፍሬ ነገሩን በተመለከተም ጉዳዩን መርምሮ ከሳሿ (ተጠሪ) በዶላር የላኩት ገንዘብ 2ኛ ተከሳሽ (የአሁኑ 2ኛ አመልካች) የተቀበሉት በብር ስለሆነ አሁን ባለው የብር ምንዛሬ እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ክስ ውድቅ ነው፣ ከሳሿ ገንዘቡን የላኩት በራሳቸው ፈቃድ የአሽሙር ማህበር ለመመስረት አስበው ስለሆነ የወለድ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም፣ ተከሳሾቹ ባቀረቡት ክርክር ከሳሿ ብር 139,200.75 መልሰው ወስደዋል የሚለውም ተቀባይነት የለውም፣ 3ኛዋ ተከሳሽ ለከሳሿ ገንዘብሽን እንመልስልሻለን ከማለት ውጭ በክሱ ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ነገር ስላልተገኘ ከክሱ በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል፣ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ግን ከከሳሽ የተቀበሉትንና የወሰዱትን ብር 2,634,089.43 ዳኝነት ከፍለው መዝገቡን ካስከፈቱበት ከሚያዝያ 10/2003 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር በአንድነትና በነጠላ ለከሳሽ እንዲከፍሏቸው በማለት ወስኗል፣ እንዲሁም ከሳሿ በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ 3ኛዋ ተከሳሽ ደግሞ በከሳሿ ላይ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብትም ጠብቋል፡፡

በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ በከፊል በመቃወም ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ይግባኛቸው መሰረታዊ ነጥብም፡- በኬኒያ አገር ናይሮቢ ከተማ ሆነው በዶላር የላኩላቸው ገንዘብ ለእኔ ጥቅም ባላገለገለበት ማለትም ለአሽሙር ማህበሩ በመዋጮ መልክ ባልዋለበትና እቃም ባልተገዛበት በወቅቱ በነበረው የብር ምንዛሬ ብቻ እንዲከፈላቸው ተብሎ መወሰኑ የደረሰባቸውን ጉዳት ያላገናዘበ ነው፤ የሥር ተከሳሾችም ገንዘቡን ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ወለድ ሊታሰብልኝ እየተገባ ክሱ ከቀረበበት ከሚያዝያ 10 ቀን
2003 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታሰብ መደረጉ ስህተት ነው፣ የስር 3ኛዋ ተከሳሽም ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እኩል ኃላፊነት እንዳላቸው ሊወሰን ሲገባ መታለፉ ያላግባብ ነው የሚሉትን ነጥቦችን ዘርዝረው ይግባኙን ለማቅረብ የከፈሉትን ዳኝነት፣ የጠበቃና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች የስር ተከሳሾች እንዲከፍሉ ሊወሰን ይገባል በማለት ዳኝነት መጠያቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ይግባኝ ሰሚው ችሎትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ መልስ ሰጪዎች ለይ/ባይ ሊከፍሉት የሚገባው የዶላር ምንዛሬ መቼ በነበረው ነው? የሚለው ጭብጥ በተመለከተከፍ/ብ/ህ/ቁ 1750 ጋር አመሳስሎ በመተርጎም የአሁኑ አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሏቸው የሚገባው የዶላር ምንዛሬ የስር ፍርድ ቤቱ ፍርድ በሰጠበት በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም በነበረው የዶላር የብር ምንዛሬ ተመን መሆን ይገባዋል በማለት የወሰነ ሲሆን አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱት ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ክስ እስከመሰረቱባቸው ድረስ ላለው ጊዜ ወለድ ሊከፍሉ ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለውን ጭብጥ በተመለከተ ደግሞ ተጠሪ ገንዘባቸው ከእጃቸው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ገንዘብ ያገኙት ምንም አይነት ጥቅም እንደሌለ፣ በአንፃሩ ደግሞ የገንዘቡ ተጠቃሚዎች አመልካቾች የነበሩ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ ወለዱ የማይከፈልበት ምክንያት የለም ወደሚለው ድምዳሜ ደርሶ ተጠሪ በክሳቸው እንደጠየቁት 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በሚመለከት ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ክስ ወደ ፍርድ ቤት እስከቀረበበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ ላለው ጊዜም 9% ወለድ ሊከፈላቸው ይገባል፤ በተመሳሳይም አመልካቾቹ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) ከተጠሪ ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ተጠሪ ክሱን በሬጅስትራር እስካስከፈቱበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ሊከፍሏቸው ይገባል በማለት የስር ፍ/ቤቱ በዚህ ረገድ የሰጠውን ውሳኔ በማሻሻል ወስኗል፡፡ እንዲሁም የሥር 3ኛ ተከሳሽን በተመለከተም በባለቤታቸው በሁለተኛው አመልካች በቤተሰብ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ተጠያቂ ሊያደርጋቸው የሚችል ሁኔታ ካለ ከተጠያቂነት የማያመልጡበት ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ ለተጠሪ ክስ ግን በቀጥታ ፍርዱ ሊያርፍባቸው የሚያስችል ነገር የለም፣ በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቱ በዚህ ረገድ የሰጠው ፍርድ የሚነቀፍ አይደለም በማለት በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል፡፡

የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመቃወም ሲሆን የአመልካቾች የሠበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተገቢውን ጭብጥ ለጉዳዩ ሳይዝና አግባብነት የሌለውን ድንጋጌን መሰረት አድርጎ  አመልካቾች ከኬንያ ናይሮቢ በአሜሪካን ዶላር ተልኮ በ2ኛ አመልካች ከአቢሲኒያ ባንክ በወቅቱ በነበረው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ለተወሰደው ገንዘብ ለተጠሪ ገንዘቡን ሊመልሱ የሚገባው የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በሰጠበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው በማለት መወሰኑ አግባብነት የሌለው መሆኑን፣ ተጠሪ ወለድ የሚያገኙበት ሕጋዊ ምክንያትም የሌለ መሆኑን ዘርዝረው በዚህ ረገድ የተሰጠው የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሽሮ በአንፃሩ ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲፀናላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል፡፡

የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል፡፡ እንደመረመረውም የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ነጥቦች፡-

አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሉት የሚገባው ገንዘብ በውጪ ምንዛሬ ነው? ወይስ በኢትዩጵያ ብር ነው?፣

አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱት ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ክስ እስከመሰረቱባቸው ድረስ ላለው ጊዜ ወለድ ሊከፍሉ ይገባል? ወይስ አይገባም? የሚሉት ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- አመልካቾች ለተጠሪ የኢትዩጵያ ብር 800,000 እና 150,000 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ ሊከፍሏቸው እንደሚገባ ክርክር ያቀረቡበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው አመልካቾች ለተጠሪ መክፈል ያለባቸው 150,000 ዶላር ይኼው ገንዘብ በ2ኛ አመልካች ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ ሲሆን በኢትዩጵያ ብር ተመንዝሮ በተሠጠበት መጠን ነው? ወይስ በዶላር ነው? የሚል ሲሆን ይህ ጭብጥ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 246፣ 247 እና 248 ድንጋጌዎች አግባብ ሊመሰረት የሚገባው እና ተጠሪ በዶላሩ ነው ሊከፈላቸው የሚገባው የሚል ምላሽ ከተሰጠ ደግሞ ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄው የዶላሩ ምንዛሬ መሆን ያለበት አመልካቾች ገንዘቡን በወሰዱበት ጊዜ ባለው የውጪ ምንዛሬ ተመን ነው?፣ ተጠሪ ክስ በመሰረቱበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው?፣ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በሰጠበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን? ወይስ አመልካቾች ገንዘቡን ለተጠሪ በሚከፈሉበት ጊዜ ባለው የውጭ ምንዛሬ ተመን ነው? የሚሉትና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

ከክርክሩ መረዳት እንደተቻለው ተጠሪ ገንዘቡን ከኬኒያ ወደ ኢትዮጵያ ለአመልካቾቹ የላኩላቸው አብረው የንግድ ማህበር ለማቋቋም በመዋጮነት ቢሆንም ማህበሩም አልተመሰረተም፣ ገንዘቡም ለአመልካቾች ጥቅም የዋለ ነው ከሚባል በስተቀር ተጠሪ በዚህ ገንዘባቸው ያገኙት እንዳችም ጥቅም የሌለ መሆኑን፣ ተጠሪ በገንዘባቸው ምንም አይነት ጥቅም ሳያገኙ በአንፃሩ ግን አመልካቾች ይህንን ገንዘብ ከተጠሪ ከተቀበሉበት ጊዜ ጀምሮ ለራሳቸው ጥቅም በማዋል ከፍተኛ ገቢ እንዳገኙበት የሚገመት መሆኑን፣ ተጠሪ ገንዘቡ ለራሳቸው ንግዳዊ ስራ ወይም ለሌላ አገልግሎት አውለውት ቢሆን ኖሮ በወቅቱ ከፍተኛ ጥቅም ሊያገኙበት ይችሉ እንደነበር የሚገመት መሆኑን፣ ተጠሪ የገንዘባቸው ዋጋ ሳይወርድ አቻው የብር ምንዛሬ እስካላገኙበት ድረስ ገንዘባቸውን በተሟላ ሁኔታ አግኝተዋል ሊባሉ የሚችሉ ያለመሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በምክንያትነት ይዞ የስር ፍ/ቤቱ አመልካቾች ለተጠሪ የብር ምንዛሬው መክፈል ያለባቸው ገንዘቡን ሲወስዱ በነበረው የብር ምንዛሬ ነው ማለቱ የተጠሪን ጥቅም የሚያጓድል፣ አመልካቾችን ደግሞ አላግባብ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን ደምድሞ እና ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1750 ጋር አመሳስሎ በመተርጎም አመልካቾች ለተጠሪ ሊከፍሏቸው የሚገባው የዶላር ምንዛሬ የስር ፍርድ ቤቱ ፍርድ በሰጠበት በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም በነበረው የዶላር የብር ምንዛሬ ተመን መሆን ይገባዋል በማለት መወሰኑን ነው፡፡ በመሰረቱ ተጠሪ እንዲመሰርት የፈለጉትና ጥቅም አገኝበታለሁ ብለው የነበሩት ድርጅት ባለመቋቋሙ አመልካቾች ገንዘቡን እንዲመልሱላቸው ዳኝነት መጠየቃቸው ግልጽ ሲሆን ዶላሩን ከኬንያ አገር ወደ ኢትዩጵያ ቢልኩም 2ኛ አመልካች ገንዘቡን ከባንክ ወጪ አድርገው ሲወስዱ የተከፈላቸው በወቅቱ በነበረው የምንዛሬ ተመን ወደ ኢትዩጵያ ብር ተለውጦ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ከውጪ አገር የተላከ የውጭ ምንዛሬ ኢትዩጵያ ውስጥ በጊዜው በነበረው ተመን ታስቦ ክፍያ የተፈፀመበት ከሆነ ዶላሩ ለተላከበት አላማ አልዋለም በሚል ክርክር ሲነሳ ገንዘቡ ሊመለስ የሚገባው ዶላሩ ሲላክ በነበረበት
የውጪ ምንዛሬ ተመን ሊሆን አይገባም የሚል የሕግ መሰረት የለም፡፡

ተጠሪ ከአመልካቾች ጋር ያለው ውል በመፍረሱ ምክንያት የደረሳባቸውን የጉዳት አይነትና መጠን በግልጽ ጠቅሰውም አልተከራከረም፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ ከገንዘብ እዳ ጋር ተይይዞ የሚነሳውን የውል አፈፃጸም ለመግዛት ታስቦ የወጣ ድንጋጌ መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1749 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1749(1) ድንጋጌ ገንዘብን የሚመለከት እዳ ሲሆን እዳው የሚከፈለው በአገሩ መገበያያ ገንዘብ መሆኑን በመርህ ደረጃ የደነገገ ሲሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ ደግሞ እዳው በሚከፈልበት ቦታ ውሉ ሕጋዊ ዋጋ የሌለው ገንዘብ ጠቅሶ እንደሆነ ውሉ ቃል በቃል እውነተኛ ዋጋ ወይም ይህንኑ የመሰለ ቃል ከሌለበት በቀር እዳው በሚከፈልበት ቀን ዋጋ ልክ በአገሩ ገንዘብ ሊከፈል እንደሚችል የሚያስቀምጥ ነው፡፡ በመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌ በአመልካቾችና በተጠሪ መካከል ላለው ጉዳይ ቀጥታም ሆነ በማመሳሰል የትርጉም መርህ ተፈፃሚ የሚሆንበት አግባብ የለም፡፡ ምክንያቱም ጉዳዩ የገንዘብ ክፍያ ውል መሰረት ያደረገ የገንዘብ እዳ ክፍያን የሚመለከት ካለመሆኑም በላይ አመልካቾች ከተጠሪ የተላከላቸውን የአሜሪካን ዶላር በቀጥታ የተቀበሉ ሳይሆን ዶላሩ በጊዜው በነበረው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት ተሰልቶ ወደ ኢትዩጵያ ብር ተመልሶ አመልካቾች መቀበላቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነውና፡፡ በአገሪቱ የገንዘብ ስርዓት መሰረት መንግስትና ሕዝብ በጊዜው በነበረው የውጪ ምንዛሬው ተመን ላገኙት ጥቅም ደግሞ ወደ ኢትዩጵያ ብር የተመነዘረ ዶላር ለተጠሪ ሊያስገኝ ይችል የነበረው ጥቅም ግምት ውስጥ ገብቶ ምንዛሬው ተመን የሚታሰብበት የሕግ አግባብም የለም፡፡ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካቾች ያላግባብ ጥቅም ሊያገኙ የሚችሉበትን አጋጣሚ ግምት ውስጥ አስገብቶ ዶላሩ በተላከበት ጊዜ በኢትዩጵያ ብር ተመንዝሮ ለአመልካቾች መሰጠቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ ለተጠሪ  ዶላሩ ከተላከበት ጊዜ በኋላ ያለው የምንዛሬ ተመን በከፍተኛ ሁኔታ የተለዋወጠ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገባ ተመኑ ለተጠሪም የሚያስገኘው ጥቅም ሕጋዊ አድርጎ መውሰዱ አግባብነት የሌለው ነው፡፡ ስለሆነም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ጭብጥ ሳይመሰርትና በክርክሩ ሂደት የተረጋገጠው ፍሬ ነገር በመተው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1750 ድንጋጌን ያለቦታው ጠቅሶ አመልካቾች 150,000.0 የአሜሪካን ዶላር ለተጠሪ ሊመልሱ የሚገባው በታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ባለው የውጪ ምንዛሬ ነው በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል፡፡ በዚህም ምክንያት አመልካቾች ይህንኑ ዶላር ለተጠሪ ሊከፍሉ የሚገባው 2ኛው ተጠሪ ከአቢሲኒያ ባንክ ሲወስዱ በተከፈላቸው የውጪ ምንዛሬ ተመን ሊሆን የሚገባ ሁኖ አግኝተናል፡፡ ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ተጠሪ ገንዘባቸው ከእጃቸው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ገንዘብ ያገኙት ምንም አይነት ጥቅም ያለመኖሩ፣ በአንፃሩ ደግሞ የገንዘቡ ተጠቃሚዎች አመልካቾች በመሆናቸው ተጠሪ ይህ ገንዘብ ከእጃቸው አላግባብ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ያጡት ጥቅም በወለድ ክፍያ ሊካካስላቸው የሚገባ መሆኑን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተቀበለው ጉዳይ ነው፡፡ አመልካቾች በዚህ ሰበር ደረጃ የሚከራከሩት ለተጠሪ ሕጋዊ ወለድ የሚታሰብበት አግባብ የለም በሚል ሲሆን ለዚህም እንደ ሕጋዊ ምክንያት የሚያቀርቡት ተጠሪ ለአመልካቾች ማስጠንቀቂያ ያልሰጡ መሆኑንና ጉዳዩ የገንዘብ ብድርን መሰረት ያላደረገ መሆኑን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይመሰረታል የተባለው ድርጅት ሳይመሰረት መቅረቱን አመልካቾች የሚክዱት ፍሬ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ በተጠሪ ቋሚ ሃብት ወይም ጥቅም ላይ መቀነስን የሚያስከትል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ በተጠሪ ላይ ቀጥተኛ የሆነ የገንዘብ ኪሳራ የደረሰባቸው መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ተጠሪ ለአመልካቾች ማስጠንቀቂያ የሚሰጡበት ምክንያት የለም፡፡ አመልካቾች ያመኑትን ገንዘብ ያህል ተጠሪ ለመውሰድ ፈቃደኛ ሊሆኑ ያለመቻላቸውንም በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጡት ጉዳይ አለመሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል፡፡ በመሆኑም ተጠሪ ይመሰረታል በማለት የጠበቁት ድርጅት ሳይመሰረት ከቀረ ለአመልካቾች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1771 እና 1705 ድንጋጌዎች አግባብ ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ይገባ ነበር ለማለት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም፡፡ እንዲሁም የወለድ ገንዘብ በብድር ጊዜ ብቻ ተፈፃሚነት የሚሆን ነው በሚል የቀረበው የአመልካቾች ክርክር ሲታይም የሕግ መሰረት የሌለው ነው፡፡ ወለድ በሕጉ አግባብ የተዘረጋው ስርዓት እንደተጠበቀ ሁኖ በስምምነት ወይም ያለስምምነት ሊከፈል የሚችል ገንዘብ ነው፡፡ ወለድ ተበዳሪ የወሰደውን ገንዘብ ወይም እቃ በወቅቱ ባለመመለሱየተነሳ የሚከፈል የገንዘብ ካሳ ነው፡፡ ሌላው አይነት ወለድ አንድ ሰው ግዴታውን ባለመፈፀሙ ወይም በማዘገየቱ የተነሳ የሚከፈለው ካሳ እኩያ ነው፡፡ ስለሆነም ወለድ ለገንዘብ ብድር ብቻእንዲከፈል የሚደረግ የካሳ አይነት አይደለም፡፡ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1803(3) ድንጋጌ አንፃር ሲታይም ተጠሪ አመልካቾች የውል ግዴታቸውን ባለመፈመፀማቸው የተነሳ የካሳ እኩያ የሆነው ወለድ የማያገኙበት የሕግ ምክንያት አላገኘንም፡፡

 

በመሆኑም የስር ፍርድ ቤቱ ገንዘቡ ለተጠሪ ጥቅም ያለማዋሉን አረጋግጦ እያለ ገንዘቡን የላኩት ለንግድ ማህበር ማቋቋሚያ በመዋጮነት በመሆኑ ወለድ አይገባቸውም የሚል ምክንያት አሳማኝ ሆኖ ባለመገኘቱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያለመቀበሉ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል፡፡ ስለሆነም ተጠሪ በክሳቸው እንደጠየቁት 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር) በሚመለከት 2ኛ ተጠሪ ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ አድርገው ከወሰዱበት ጊዜ ጀምሮ ክስ ወደ ፍርድ ቤት እስከቀረበበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ ላለው ጊዜም 9% ወለድ ሊከፈላቸው ይገባል፤ በተመሳሳይም አመልካቾቹ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) ከተጠሪ ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪ ክሱን በሬጅስትራር እስካስከፈቱበት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ድረስ 9% ወለድ ሊከፍሏቸው ይገባል በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የሌለበት ሁኖ አግኝተናል፡፡

 

ሲጠቃለልም ከላይ በተገለፁት ሕጋዊ ምክንያቶች የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ በከፊል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሊሻሻል የሚገባው ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል፡፡

ው  ሳ  ኔ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ 88280 ጥቅምት 08 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሏል፡፡

1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች 150,000 የአሜሪካን ዶላር ለተጠሪ ሊከፍሉ የሚገባው ይኼው ዶላር ከኬንያ ናይሮቢ ወደ ኢትዩጵያ ተልኮ በአቢሲኒያ ባንክ በኩል በኢትዮጵያ ብር ተመንዝሮ በተሰጠው ተመን መሰረት ነው ብለናል፡፡

ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ አመልካቾች ለተጠሪ በሚከፍሉት ገንዘብ ላይ ክሱ ከቀረበበት ከሚያዝያ 10 ቀን 2003 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ አክለው እንዲከፍሉ የሚለውን የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል የሠጠውን ውሳኔ ይህ ችሎትም በማሻሻል አመልካቾች 150,000 ዶላሩን በሚመለከት ከላይ በተራ ቁጥር 2 መሰረት በሚገኘው የብር
ስሌት ላይ ከነሐሴ 13 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ 9% ወለድ በማከል እንዲሁም ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) በሚመለከት ደግሞ አመልካቾች ገንዘቡን ከወሰዱበት ከጳጉሜ 4 ቀን 2001 ዓ/ም ጀምሮ ገንዘቡ ተከፍሎ እስኪያልቅ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዲከፍሏቸው ወስነናል፡፡

የሥር 3ኛ ተከሳሽን በሚመለከትይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ አልተነካም፡፡

በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ በሚመለከት አመልካቾች ለተጠሪ በዚህ ሰበር ችሎት በተወሰነው የገንዘብ መጠን መሰረት የዳኝነት ገንዘብ ይክፈሏቸው ብለናል፡፡ ሌሎች ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና በዚህ ችሎት ክርክር የወጡትን ወጪና ኪሳራዎችን የያራሳቸውን ይቻሉ ብለናል፡፡

 

መዝገቡ ዘግተን ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል፡፡

የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት::

Share this:
https://t.me/lawsocieties
የተከበራችሁ መላዉ የሀገራችን ህዝቦች፡-
እንኳን ለ2013 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ፡፡ በ2012 ዓ.ም በሀገራችን በርካታ ዉጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሰላማችንን የተፈታተኑ ጉዳዮች እንደነበሩ ግልጽ ነዉ፡፡ በመሆኑም በአዲሱ አመት በፍቅርና በመተሳሰብ በጋራ የምንኖርባትን ሀገር የምንገነባበት ለመጪዉ ትዉልድ ክፉዉን ሳይሆን መልካሙን ነገር የምናቆይበት ጊዜ እንዲሆንልን በተለይ የዜጎቻችን መብትና ጥቅም የምናስከብርበትና እዉነተኛ ፍትህ የሚረጋገጥበት በሁሉም አካባቢዎች የሕግ የበላይነት ተከብሮ በሰላም የምንኖርበት የደስታ የፍቅር አመት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡ ተቋማችን የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሙሉ ልብ በመወጣት ለሀገራችንና ለህዝባችን ዉጤታማ ስራ የምንከናዉንበት እንዲሆንልን እመኛለሁ፡፡
ፈጣሪ ሀገራችንና ህዝባችንን ይጠብቅልን!!!
አምባሳደር ደግፌ ቡላ ዋቅጅራ
ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተመለከተ
****************************************************************
የንብረት ባለቤትነት ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ውጤታማ የሆነ የውል አፈጻጸም ሥርዓት በመዘርጋት ለንግድ እና ኢንቨስትመንት ሥራ ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታዎች ለመፍጠር እንዲቻል በፌደራል ፍርድ ቤቶች የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው በኩባንያ እና ኪሳራ ሕግጋት (Company and Insolvency Law) ዙሪያ በፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሚሰሩ ዳኞች የተዘጋጀ የአራት ቀን ሥልጠና መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም በአያት ሪጀንሲ ሆቴል ሲጀመር የፍርድ ቤት ም/ፕሬዚደንት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው፡፡

በሥልጠናው ላይ በፌደራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በንግድ እና ተያያዥ ችሎቶች ላይ የሚሰሩ 50 ዳኞች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡

ክቡር አቶ ሰለሞን በንግግራቸው በተያዘው በጀት ዓመት የተጀመረውን የሪፎርም ስራ በማጠናከር የተለያዩ ሥራዎችን ለመሥራት የታቀደ መሆኑን በመጥቀስ ከእነዚህ ሥራዎች መካከል በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ዳኞች በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ለማስቻል በቂ ሥልጠናዎች ማዘጋጀት አንዱ መሆኑንና የአሁኑ ሥልጠናም የዚህ ዕቅድ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስራን ቀለል ለማድረግ (Ease of Doing Business) በተለያዩ አካላት ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ሥራዎች በጥብቅ ዲሲፒሊን እየተሰሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በዳኝነት ዘርፉ እየተካሄደ ያለውን የሪፎርም ሥራ ተፈጻሚ ለማድረግ በዕቅድ ከተያዙ ሥራዎች መካከል በንግድ ሕጉ ከተካተቱ ጉዳዮች በተጨማሪ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮችን የመለየት (Case Categorization) ሥራን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገኝበትም ጠቅሰዋል፡፡

የንግድ ችሎቶችን እንደገና የማደራጀት ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በተለየ ሁኔታ የሚቋቋም የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፍርድ ቤት የሚደራጅበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንዲሁም በእነዚህ ፍርድ ቤቶች በችሎቶች ላይ የሚመደቡ ዳኞች ችሎታ እና ብቃትን መነሻ በማድረግ የመመደቢያ መስፈርት (Guideline) ማዘጋጀት የበጀት ዓመቱ የሪፎርም ሥራ አካል እንደሆንም ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ በፌደራል ጠቅላይ፣ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች በንግድ እና ተያያዥ ችሎቶች ላይ የሚሰሩ 50 ዳኞች በመሳተፍ ይገኛሉ፡፡

ሥልጠናው የሚያተኩርባቸው ርዕሰ-ጉዳዮች የንግድ ማሕበራትን በተመለከቱ የንግድ ሕግ ድንጋጌዎች እና የኪሳራ ጉዳዮችን በሚመለከቱ የንግድ ሕጉ ድንጋጌዎች እንዲሁም በተያያዥ ርዕሶች ላይ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከመስከረም 6 – 9 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው የዚህ ስልጠናው ዓላማ ዳኞች በንግድ እና ኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በዚህ ረገድ የሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎቶችን ውጤታማ፣ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ እንዲሁም ተገማች፣ ተጠያቂነት ያለበት እና የሕዝብ አመኔታን ያረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል ነው፡፡

ሥልጠናውን የሚሰጡት ደ/ር ታደሰ ሌንጮ እና አቶ ስዩም ዮሐንስ ሲሆኑ አሠልጣኞቹ የንግድ ሕግ ረቂቅ በማዘጋጀት፣ በዩኒቨርሲቲ ንግድ ሕግ በማስተማር እንዲሁም የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን በአገር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁ ጆርናሎች ላይ በማሳተም ዕውቅና ያላቸው ናቸው፡፡

ሥልጠናው በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ተጠሪነቱ ለዓለም ባንክ በሆነው አይ.ኤፍ.ሲ (International Financial Corporation) ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን የሥልጠናው ሒደት በአሰልጣኞች ከሚደረግ ገለጻ በተጨማሪ የዳኞችን የቡድን ውይይት እንደሚያካትት ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
https://t.me/lawsocieties
መስከረም 6፣2013

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል እንዲሁም የብድር ውሎችን ሰነድ አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላይ የአሰራር ለውጥ ማድረጉን ተናገረ።

እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት የሽያጭ ዋጋ ወይም የብድሩ ገንዘብ አከፋፈልን በተመለከተ ክፍያው መፈጸም ያለበት፦

በሽያጭ ውል ጊዜ የሽያጭ ዋጋው ባንክ ከሚገኝ የገዢ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ሻጭ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት፣
በብድር ውል ጊዜ የብድሩ ገንዘብ ባንክ ከሚገኝ የአበዳሪ ሂሳብ ተቀናሽ ሆኖ ወደ ተበዳሪ የባንክ ሂሳብ የተላለፈ (Transfer) መሆን አለበት ሲል የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ለሸገር ነግሯል፡፡

ይህ አሰራርም ከነገ መስከረም 7፣2013 ይጀመራል ተብሏል።

በተጨማሪም ህገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውልን አረጋግጦ የመመዝገብ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ኤጀንሲው እወቁልኝ ብሏል፡፡

የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አሰራሩን የለወጠው ከባንክ ውጪ የሚንቀሳቀስ ጥሬ ገንዘብን ሥርዓት ለማስያዝ ፣ህገወጥነትን ለመከላከል እና ዘመናዊ አሰራርን ለማስፈን ነው ብሏል።

#Sheger Fm #Ethiopia #ሰነዶች_ማረጋገጫ_ምዝገባ_ኤጀንሲ

https://t.me/lawsocieties
የናይጄሪያዋ ግዛት ህፃናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜናዊ ናይጄሪያ የምትገኘው ካዱና ግዛት ህጻናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች በህክምና እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች፡፡

የካዱና ገዢ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ አዲሱ የወጣው ህግ ላይ ትናንት ማምሻውን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

አዲሱ ህግ ከ14 ዓመት በታች የሚገኙ ህጻናት ደፋሪዎችን በህክምና እንዲኮላሹ ከማድረግ በተጨማሪ የእድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው ናይጄሪያ አስገድዶ መድፈርን የሚቃወሙ ዘመቻዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ጠርጥሬያቸዋለው ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነግሯል፡፡

አዲሱን ህግ ያጸደቀችው ካዱና ግዛት ይህንን ውሳኔ ስታሳልፍ በናይጄሪያ ከሚገኙ ግዛቶች መካከል ብቸኛዋ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ source:- FBC

https://t.me/lawsocieties