አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#ብር_የመለወጡ_ቀጥተኛ_ጥቅም!
***
ብዙ ሰዎች በተደጋገሚ ብሩ በመለወጡ በቀጥታ ኢኮኖሚው ላይ የሚመጣውን ጥቅም ንገረን ብለው ጠይቀውኛል! ብር በመለወጡ የሚገኙት የአጭር ግዜ እና የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው!

የአጭር ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- በሀገራችን ከ113ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከፋይናንስ ገበያው ቁጥጥር ውጪ አለ! ስለዚህ የገንዘብ ለውጡ ይህንን ገንዘብ ወደ ብሄራዊ ባንክ የመለወጥ እድል ይፈጥራል!

#ለምሳሌ፡- ምንጩ ያልታወቀ በመሆኑ ወደ ባንክ ሳይመጣ ከሚበላሸው፤ ከሀገር ውጪ በጎረቤት ሀገር በመሸሹ ከማይመለሰው፤ የመቀየሪያ ወቅቱ ከሚያልፍበት፤ በጎርፍ፤ በቃጠሎ፤ ወዘተ ከወደመው ውጪ 100 ቢሊዮን ብር እንኳን ወደ ህጋዊ የባንክ ስርዓት ቢመጣ ከፍተኛ ገንዘብ ከገበያ የመሰብሰብ እድል ስለሚፈጠር የዋጋ ንረት በሚታይ መልኩ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል!

ምንጩ ያልታወቀ፤ በሙስና የተገኘ፤ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ከፍተኛ ገንዘብ በገበያ በድርጅቶች እና በሰዎች እጅ እንደሚገኝ ይታወቃል! ስለዚህ የተቀመጠውን የጥሬ ገንዘብ ገደብ (1.5 ሚሊዮን ብር ለማለት ነው!) እና ከ5 ሺህ ብር በላይ በባለቤቶች እንዲቀመጥ የሚያዘውን መመሪያ ተከትሎ ህገወጦችን ለመለየት እድል ይፈጥራል፡፡

#ለምሳሌ፡- በህገወጥ መንገድ ሃብት ያከማቸ ሰው ወይም ድርጅት ህጋዊ ከሆኑት ሰዎች ተገቢ ያልሆነ Advantage እንደወሰደ ግልጽ ነው! ስለዚህ የብሩ መቀየር የተለየ እድል ያገኙ ሰዎችን በተወሰነ መልኩ ለመቆጣጠር ያሰችላል፡፡

የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- ኢትዮጲያ ውስጥ በባንክ ቤቶች ያለው የቁጠባ መጠን ማነስ እና ባንኮች ለባለሃብቶች የሚያቀርቡት የብድር መጠን ማነስ የታወቀ ጉዳይ ነው! ስለዚህ ለምሳሌ 100 ቢሊዮኑ ቢሰበሰብ እና የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ገደቡን ተከትሎ 80 ቢሊዮኑ በባንኮች ቢቀመጥ ተጨማሪ ቁጠባ እና ተጨማሪ የብድር አቅርቦት እንዲገኝ ያደርጋል፡፡

#ለምሳሌ፡- መንግስት ባወጣዊ አዲስ መመሪያ መሰረት የግል ባንኮች የመንግስትን የግምጃ ቤት ሰነድ የመግዛት እድል ተፈጥሮላቸዋል! ስለዚህ መንግስት ወደ ፊት ለሚያስበው የበጀት ጉድለትን በሀገር ውስጥ የመሙላት ፍላጎት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግለው ይችላል፡፡

ገንዘቦች በመሰብሰባቸው እና በግል ባንኮች ውስጥ በመቀመጣቸው የሚቀርበው ብድር የግል ሴክተሩን በማነቃቃት ተጨማሪ ምርት እንዲመረት፤ ተጨማሪ ሰራተኛ እንዲቀጠር፤ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች አድገው የውጪ ምንዛሬ ግኝት እንዲያድግ፤ የሀገር ውስጥ አምራቾች ተበረታተው ከውጪ የሚገቡትን የመተካት አቅም የሚፈጥሩ ከሆነ የውጪ ምንዛሬ እንዲቆጠብ፤ ወዘተ የማድረግ አቅም ይኖረዋል፡፡

ነገር ግን ብር መለወጡ ብቻውን ስር ነቀል ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም! ምክንያቱም ዋጋ ንረት፤ ስራ አጥነት፤ የውጪ ምንዛሬ ክምችት ማነስ፤ የበጀት ጉድለት፤ ዝቅተኛ ምርት እና ምርታማነት መኖር፤ የንግድ ሚዛን መዛባት፤ ወዘተ በገንዘብ ምክንያት ብቻ የመጡም አይደሉም በገንዘብ ምክንያት ብቻም የሚፈቱ አይደሉም! ሌሎች ፖሊሲዎች እና ስራዎች በተጨማሪነት መሰራታቸው ግድ ነው!
via the Ethiopian economist view

https://t.me/lawsocieties
የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
----------------------------------------------------------------------- ይቀላቀሉን‼️
https://t.me/lawsocieties
የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
-----------------------------------------------------------------------
ሁሉም የመንግስት ተቋማት የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከሚያደርጉት ተሳትፎ ጎን ለጎን የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊፈትኑ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው በመስራት ሀገራችንን ወደመልካም ጅማሮ ማሻገር እንደሚገባ የፍትሐ-ብሔር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጄኔራል አቶ ሄኖክ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡

መንግስት በየዓመቱ ከሚበጅተው በጀት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ከሚይዙ ጉዳዮች መካከል ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር የሚገቡ ውሎች፣ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት አማራጭ የሙግት መፍቻ ማዕከላት ያሏቸው የድርድር እና የግልግል ዳኝነት ሂደቶች እንዲሁም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ፍርድ ቤቶች ያሏቸው የፍትሐ-ብሔር ጉዳዮች ክርክሮች መሆናቸውን የገለጹት ጄኔራል ዳይሬክተሩ ይህን የሚያህል የሀገር ውድ ሀብት በወቅታዊ የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት እንዳይባክኑና ተጨማሪ ወጪ እንዳያስወጡ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት ግለሰቦች እና ድርጅቶች ጋር የተለያዩ የግንባታ ሥራ፣ የእቃ ግዥ፣ የማማከር አገልግሎት እና ሌሎች ውሎችን ከወረርሽኙ አስቀድሞም ይሁን በአሁኑ ወቅት እየተዋዋሉ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሄኖክ ተስፋዬ እነዚህ ውሎች በባህሪያቸው ለተወሰነ ጊዜ የሚቆዩ እና አስቸኳይ ለሆነ ማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ በመሆናቸው በተለይ ወረርሽኙ ከመከሰቱ በፊት ተገብተው ከነበሩ ውሎች የሚጠበቀው ውጤት በተቀመጠለት ጊዜ እንደሚደርስ ታሳቢ ተደርጎ የተፈፀመው ከወረርሽኙ በፊት በነበረው የሀገራችን የዕለት ከዕለት የስራ እንቅስቃሴ አንፃር እንደነበር በመግለጽ በወረርሽኝ ምክንያት እክል እየገጠማቸው ነው ብለዋል፡፡

ስለሆነም ተቋማቱ የገቧቸውን ውሎች የአፈፃፀም ሂደት በዚህ ወቅት መገምገምና በውሉ ላይ የተመለከተው ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያትን የሚደነግገውን ክፍል በአግባቡ በመመርመር እንደየጉዳዩ አግባብ ወረርሽኙ ከአቅም በላይ የሆነባቸውን ተዋዋዮች ለይቶ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች መወያየትና ግልጽ የሆነ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተገቢ ነው ያሉት ዳይሬክተር ጄኔራሉ በአንፃሩ ወረርሽኙ ከአቅም በላይ የሆነ ክስተት ያልፈጠረባቸውን ተዋዋይ ወገኖች የውል አፈፃፀም ሂደቶችን በመለየት አፈፃፀሙን እንዲቀጥሉ የማሳሰብ እና ማስጠንቀቂያ የመስጠት አለፍ ሲልም ለውል አፈፃፀም ማስከበሪያ የተያዘን የዋስትና ገንዘብ የመውረስ እና ሌሎች በውሉ ውስጥ የተመለከቱ የመብት ማስከበሪያ መንገዶችን በመከተል እርምጃዎችን መውሰድ ተገቢ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

እንዲሁም የመንግስት ተቋማቱ በአሁኑ ወቅት ብዙ ትኩረት የሰጡት ወረርሽኙን መከላከል ላይ በመሆኑ በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት አማራጭ የሙግት መፍቻ ማዕከላት ያሏቸው የድርድር እና የግልግል ዳኝነት ሂደቶችን ችላ የማለት ሁኔታ በመፈጠፉ የተወሰኑ የመንግስት ተቋማት በግልግል ዳኝነት አመራር ሂደት ላይ መብታቸውን የሚያጣብቡ ተግባራትን ሲፈጽሙ እየተስዋለ ይገኛል፤ ለአብነትም የግልግል ዳኝነት መጠየቂያ መጥሪያ በኢ-ሜይል ደርሷቸው በ30 ቀናት ምላሽ እንዲሰጡበት ለሚሰጠው ትዕዛዝ ምላሽ ሳይሰጡ ጊዜው የሚያልፍ፤ ምላሽ ሲሰጡም በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ በመሆኑ ምላሽ መስጠት የማይችሉ መሆኑን መግለጽ፤ የተጀመረው የግልግል ዳኝነት ሂደት ወረርሽኙን መቆጣጠር እስኪቻል ታግዶ እንዲቆይ በመጠየቃቻ፤ ምላሽ የመስጠት መብታቸው የታለፈ እና በነሱ ሊመረጥ የሚገባውን የግልግል ዳኛ ሌላ አካል እንዲመርጠው ውሳኔ መተላለፉን የገለጹ ሲሆን ከክፍያ ጋር በተያያዘም በግልግል ዳኝነት ለተሰጠ የጥብቅና አገልግሎት ለተጠየቀ ክፍያ የተሰጡ ምላሾችና በኢ-ሜይል እንዲላኩ የተጠየቁ ማስረጃዎች ያለመላክ ለከፍተኛ ጉዳት ሊዳርጉ የሚችሉ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥቶ ማጤን አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የፍትሐ-ብሔር ፍትህ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ሄኖክ ተስፋዬ ሌላውና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት ጉዳል የፍትሐ-ብሔር ቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና የአፈፃፀም ክርክሮችን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በመሆናቸው በመደበኛው ሂደት ሲታዩ የነበሩ ጉዳዮች በቀጠሮ እየተላለፉ እንደሆነ አስታውሰው ይህ ሂደት የመንግስት ተቋማት የነበረባቸውን የክርክር ጫና በተወሰነ መልኩ የሚቀንስ መሆኑን እንደ አንድ አስቻይ ዕድል በመጠቀም የክርክር መዛግብቶቻቸውን በመፈተሽና በአግባቡ በማደራጀት፤ የተጓደሉ ማስረጃዎችና ሌሎች መሟላት የሚገባቸው ነገሮች ካሉም በመለየትና የሚሟሉበትን መንገድ በመቀየስ፤ በክርክር አመራር የተፈፀመ ግድፈት ካለ የሚቃናበትን መንገድ በማጤንና ፍርድ ቤቶች ስራ ሲጀምሩ ሊቀርቡ የሚገባቸውን ማስረጃዎች፣ አቤቱታዎች እና ቃለ-መሀላዎችን በማዘጋጀት ክርክራቸው የህዝብ እና የመንግስትን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ እንደሆነ የገለጹት ዳይሬክቶሬት ጄኔራሉ ክርክር ባልተጀመሩባቸው ጉዳዮች ላይም ተገቢውን ማስረጃ በማሰባሰብ፣ የፍርድ ባለመብት ከሆኑ ፍርዱን ለማስፈፀም የሚያስችሉ ንብረቶችን በማፈላለግ እና ተከሳሽ ሊሆኑ የሚችሉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ንብረቶችን እንዳያሸሹ ክትትል በማድረግና እንዳስፈላጊነቱም በፍርድ ቤት እንዲታገዱ አቤቱታ በማቅረብ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ በቀጣይ ስኬታማ ክርክር ለማድረግ ዝግጁ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡
https://t.me/lawsocieties
https://t.me/lawsocieties
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/lawsocieties
new vacancy for inventory
#pce ventures manufacturing plc
sex: man
experience: 0
total: two
work place: Addis ababa
qualification: inventory
apply via email address: mikias@parkerclay.com
share to your friends
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ሲሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አመለከቱ።

ምክር ቤቱምበቀረበው ሪፖርት ላይ እየተወያየ ነው፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት አጭር ሪፖርት ኮቪድ-19ኝ መከላከልን ከግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነምግባር፣ ደንብና ማስፈፀሚያ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሃገራዊ ምርጫ ማካሄድ ይቻላል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የወረርሽኝ ስርጭት ከተከሰተ በተለየ ሁኔታ መታየት ሊያስፈልገው እንደሚችል ታሳቢ በማድረግ መዘጋጀት እንደሚያስፈልግም ዶ/ር ሊያ ባቀረቡት ሪፖርት አመልክተዋል
Forwarded from Abubeker Delil
Please can i get civil procedure teaching material?
👍ዛሬ አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ተሰጥቷል!‼️

የፀጥታ ኃይሎች ከ1.5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ የለባቸውም ተብሏል።

ዶ/ር ይናገር ደሴ (የብሄራዊ ባንክ ገዥ) ፦

- ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር ተፈጥሯል። በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ ነው ይህ ተገቢ አይደለም።

- እስከ1.5 ሚልየን ብር ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ ይችላሉ።
♦️
- ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን አይመለከትም። ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
🔺
- አንዳንዶች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ ነው መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትም እኩል የሚያገለግል ነው።

- በተለያዩ ባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ካሉ ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል ተቋቁሟል ፤ ይህንን ተግባር ፈጽሞ በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።

- በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እና በሌላ ሰው ስም ገንዘብ ማስገባት አይቻልም።
🔺
- ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ ከጅቡቲ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ሁሉም ገንዘብ ህገ ወጥ ነው ተብሎ መያዝ የለበትም።

- አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት ይችላሉ፤ሲገቡ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ ይችላሉ-(ኤፍቢሲ)
https://t.me/lawsocieties
#Notice
All Year II and above Regular graduate students
This is to inform you that second year and above graduate students registration of first semester 2020/21 AY will be on September 21 and 22, 2020 and class will begin on September 23, 2020. This is therefore, to request your cooperation for effective implementation of the registrations.
http://www.aau.edu.et/blog/all-year-ii-and-above-regular-graduate-students/
AAU Registrar
Addis ababa university
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በቀን /መደበኛ/ ፕሮግራም ከ2005 እስከ 2012 ዓ.ም ተምረዉ ለተመረቁ አካል ጉዳተኛና ሴት ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) አዘጋጅቷል፡፡
የትምህረት አሰጣጡ የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ እስከሚሻሻል ድረስ በቨርቹዋል እና በኢለርኒግ የመማር ማስተማር መንገድ በተጨማሪም እንደ አስፈላጊነቱ በገጽ ለገጽ የሚካሄድ መሆኑን እያሳወቀ የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡
1. ከመንግስት ዩኒቨርስቲ በቀን /መደበኛ /ፕሮግራም የተመረቀ/ች
2. የመጨረሻ የትምህርት ዉጤት (CGPA) 2.75 እና በላይ ያላቸዉ
3. ያለባቸዉን የወጪ መጋራት ክፍያ ከፍለዉ የጨረሱ እና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ ማስላክ የሚችሉ
4. በገንዘብ ድጎማ (የኪስ ገንዘብ እየተከፈላቸዉ) ለሚወዳደሩ ከፍለዉ መማር እንደማይችሉ ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. ለአካል ጉዳተኞች ከሚኖሩበት ወረዳ የተመሰከረ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. ትምህርት ክፍሉ የሚያወጣዉን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ሲኖርባቸው
አመልካቾች
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻው ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ለመመዝገቢያ ብር 600 /ስድስት መቶ/ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም  በቅርንጫፍ  አማካኝነት ክፍያ መፈጸም ያስፈልጋል (ክፍያ የሚፈጸምበትን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 አጭር ኮዶች ምዝገባው ከመጀመሩ በፊት በዩኒቨርሰቲው ድረ ገጽ እና በፌስቡክ እናሳውቃለን) 
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ የወጪ መጋራት ሰነድዎትን እና ሌሎች መረጃዎችን አስገብተው ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ$ 
4. የBA/BSc ዲግሪ/ጊዜያዊ ዲግሪ እና ያለው CGPA ትራንስክሪፕት ማያያዝ ይጠበቅብዎታል፡፡
ማሳሰቢያ
• ምዝገባው የሚከናወነው portal.aau.edu.et ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ማስገባት አይቻልም፡፡
• የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን ማስረጃ ዋናውን በተጠየቃችሁ ግዜ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
• ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1176 ያላስላከ አመልካች ቀጣይ የምዝገባ ሂደቶች እንደማይከናወኑለት እናሳስባለን፡፡
• የፈተና ግዜውን በተመለከተ ከትምህርት ክፍሉ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ (portal.aau.edu.et/aau.edu.et) መከታተል የምትችሉ ያሳውቃል፡፡
• ጤና ላይ ለሚያመለክቱት አመልካቾች ዲግሪያቸዉን ሲጨርሱ ከጤና ጥበቃ ወይም ከተማሩበት ዩኒቨርስቲ የሚሰጣቸዉን ደብዳቤ ወይም በየሴምስተሩ የሚሰጣቸዉን  Grade report ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡ 
• የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
የመመዝገቢያ ቀን ከነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ 21 2012 ዓ.ም  

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
Addis ababa university
https://t.me/lawsocieties
ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ-ወጥነት መያዝ እንደማይቻል ተገለጸ፡፡
*************************************

የፀጥታ ኃይሎች ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በታች የሆነን ገንዘብ በህገ ወጥነት መያዝ እንደሌለባቸው ተገለፀ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ በዛሬው እለት አዲሱን የብር ኖት ለውጥ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ከብር ኖት ለውጡ ጋር በተያያዘ የተወሰነ ውዥንብር መፈጠሩን ገልጸዋል።

በዚህም የፀጥታ ሀይሎች በመቶ ሺዎች ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እየያዙ መሆኑን እና ይህም ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው እስከ 1 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ያላቸው ሰዎች ያለመሳቀቅ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ መያዝን የሚከለክለው መመሪያ እንደ ነዳጅ ማደያ እና ሌሎች ከፍተኛ ሽያጭ የሚያከናውኑ ተቋማትን እንደማይመለከትም ተጠቅሷል።

ነገር ግን ባለሀብቶች በእነዚህ ተቋማት በኩል ገንዘባቸውን በዚህ መንገድ እናስገባለን ብለው ከሞከሩ የንግድ ተቋማቱ የሽያጭ ታሪካቸው ክትትል ስለሚደረግበት እንዳይሞክሩትም አሳስበዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች መመሪያው ባንክ ብቻን የሚመለከት ነው በሚል በርከት ያለ ገንዘብ በማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል ለማስገባት ሙከራ እያደረጉ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን መመሪያው ለባንኮችም ለማይክሮ ፋይናስ ተቋማትም እኩል የሚያገለግል ነው ተብሏል፡፡

በተለያዩ በባንኮች ሂሳብ በመክፈት ገንዘብ በትኖ ለማስቀመጥ የሚሞክሩ ካሉም ይህንን የሚቆጣጠር ግብረ ሀይል በመቋቋሙ ይህንን ተግባር ፈጽሞ በተገኙት ላይ ብራቸውን እስከ መውረስ የሚደርስ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስገንዝበዋል።

እንዲሁም በተለያዩ ሰዎች አማካኝነት ገንዘብ ማስቀመጥ እንዲሁም በሌላ ሰው ስም ገንዘብ ማስገባት እንደማይቻልም ተጠቅሷል።

ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘም ከጎረቤት ሀገራት በተለይ የጅቡቲ አሽከርካሪዎች ገንዘብ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ፤ ሁሉም ገንዘብ ህገ-ወጥ ነው ተብሎ መያዝ እንደሌለበት በመግለጫው ተጠቅሷል።

አሽከርካሪዎች ከሀገር ሲወጡ እስከ 30 ሺህ ብር ይዘው መውጣት እንደሚችሉ፤ ሲገቡ ደግሞ እስከ 10 ሺህ ብር መያዝ የሚችሉ መሆኑም ታውቋል።

ሆኖም ግን በህገ-ወጥ መንገድ ብር በተሽከርካሪያቸው ውስጥ ደብቀው ለማስገባት የሚመክሩ ካሉ እንደሚወረስባቸው ተጠቅሷል።

https://t.me/lawsocieties
public dissatisfaction in the Ethiopian Judiciary
Before two years, the Federal Supreme Court promises to establish public trust in the Ethiopian judiciary. Is that promise fulfilled? The court in different communiqués asserted that public trust is regained. That bold assertion of success is without conducting a scientific public survey or study.
The ability of courts to fulfill their mission and perform their functions is based on the public’s trust and confidence in the system. In large part, the judiciary earns that trust and confidence by faithfully performing its duties, adhering to ethical standards, and effectively carrying out internal oversight, review, and governance responsibilities. However, public perceptions of the judiciary are also often colored by misunderstandings about the institutional role of the federal courts and the limitations of their jurisdiction, as well as attitudes toward federal court decisions on matters of public interest and debate.
The judiciary is still staggering in four major areas
Ø Access to Justice
Ø Timeliness
Ø Equality, Fairness and quality
Ø Lack of independence and sound inter branch relation.
Under access to justice: complexity of the court process, lack of understanding of court rulings, inadequate attorney representation, judges and court personnel’s unfriendly behavior are deterrent factors for accessible Justice.
There is a progress in timely disposition of cases regardless of its qualities. However courts don’t monitor the progress of cases adequately.
As regards equality, fairness and quality, the following factors are still rampant.
Ø When a person sues government body or corporation, courts generally favor over person.
Ø Wealthy are treated better than other groups.
Ø Decisions are not well considered and unpredictable
In the area of independence and accountability,
Ø Judges decisions are influenced by political considerations, particularly the trial of prominent political or public figures.
Ø Courts don’t make sure that their orders are enforced. Police officers refuse to effect court orders. Some regions refuse to enforce court orders and some arrest judges.
Ø Corruption is still on the air.
All these deficiencies greatly affect the relation of the public and courts. The main object of administration of justice should be to give public satisfaction. As the famous Chief Justice Rehnquist of USA once said the search for greater public trust must be pursued consistently with the idea of judicial independence.
In the current New Year, I hope that the court will work on its deficiencies and regained public trust as envisioned. The public is highly critical of these aspects of the Justice system. These negative views have eroded confidence in courts. The court can curve such critical perceptions by improving communication with the public. I remember once the court used to air a TV show focused on its work. Actually the mission of a court is not to gain popularity. However, the court must explain to the public in a language they all understand that the judicial system is different from the political branches of government. Politicians revere what is popular while judges protect constitutional rights of all people, even the despised. Judges must remain independent of politicians, even independent of the ones who appoint them and confirm their appointment. The court should assure high standard of conduct and integrity for judges and staffs. At the same time, improving the sharing and delivery of information about the judiciary will help to minimize some wrong perception of the public towards the Judiciary.
Yoseph shiferaw
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የፌደራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን ሊያሾም ስለመሆኑ ተገለጸ፡፡
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
የፌደራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞችን በነገዉ እለት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ለማሾም ቅድመ ዝግጅት ስለመጠናቀቁ የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ የጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ዘሪሁን ጌታሁን ተናገሩ፡፡
ሃላፊዉ አያይዘዉም ለፈተና ከተቀመጡ እጩ ዳኞች መካከል 50 የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና 40 የከፍተኛ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞች ስለመቅረባቸዉ ጠቁመዉ ምክር ቤቱም ሹመቱን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡
ምክር ቤቱ ለዕጩ ዳኞች ሹመት እንደሚሰጥ ይጠበቃል
******************************************
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተመለመሉ ዕጩ ዳኞችን መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም በሚያካሒደው ስብሰባ እንደሚሾም ይጠበቃል፡፡

በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ተመልምለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ለሹመት ለምክር ቤቱ የሚቀርቡት ዕጩ ዳኞች ቁጥር 90 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 40 ዕጩ ዳኞች ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ 50 ዕጩ ዳኞች ደግሞ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንደሚሾሙ ታውቋል፡፡

ዕጩ ዳኞቹ የተመለመሉት ከበርካታ ተወዳዳሪዎች መካከል በጽሑፍ እና በቃለ-መጠይቅ ፈተና ተፈላጊውን የመመዘኛ መስፈርት በማሟላታቸውና የሕዝብ አስተያየትን መሠረት በማድረግ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል፡፡

የዕጩ ዳኞቹ ሹመት በፌደራል ፍርድ ቤቶች ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘውን የሪፎርም ሥራ ለማሳካት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው የታመነበት ሲሆን በተለይም በፍርድ ቤቶች የዳኛና የመዝገብ ቁጥርን በማመጣጠን የዳኝነት ቅልጥፍናን ለመጨመር እንደሚያስችል ታውቋል፡፡

ምክር ቤቱ የሚሰጠው ሹመት የዳኞችን የሥራ ጫና (Case Load) በመቀነስ የዳኝነት ጥራትን ለማሳደግ የሚያስችል በመሆኑ በፍርድ ቤቶች የተጀመረውን የሪፎርም ሥራ ከግብ ለማድረስ የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ለመረዳት ተችሏል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Request for Proposal (RFP) Provision of Legal Service on Retainer Fee Basis
Addis Ababa Full–time
Information about TechnoServe (TNS) Today, TechnoServe works with enterprising people in the developing world to build competitive farms, businesses and industries. We have worked in more than 40 (forty) countries across Africa, Latin America and Asia, assisting thousands of businesses and improving the incomes of millions of people. True to Ed’s vision, we provide business solutions to poverty by linking people to information, capital and markets. With more than five decades of proven results, we believe in the power of private enterprise to transform lives. Dear Sir/Madam, 1. TNS requests that you submit a proposal for the Provision of Legal Service on Retainer Fee basis. Fees shall be quoted in Birr. 2. The purpose of this RFP is to conclude a Long Term Agreement (LTA) for the period of 3 (three) years. The successful Offeror shall be contracted initially for 1 (one year), with the contract to be renewed annually thereafter, subject to a satisfactory performance each year. 3. To enable you to submit a proposal, come and get a twelve pager documents, which holds the below information’s before/on September 30 th , 2020 from our office: General Information · Memo to Offerors (Annex I) · Instructions to Offerors (Annex II) · Terms of Reference (TOR) (Annex III) Forms and Formats · Acknowledgement Form (Attachment 1) · Proposal Submission form (Attachment 2) · Technical Submission form (Attachment 3) · Price Schedule Form (Attachment 4) 4. If you request additional information, please send it to email below in writing: Contact person: Tsion Admassu Address: TechnoServe Inc. Ethiopia (TNS) Haile G/Selassie Street, Rebecca Building, 8 th floor P. O. Box 100589 Addis Ababa, Ethiopia Telephone: 251-116 630017/18/19 Email: Tadmassu@tns.org We will endeavor to provide additional information expeditiously, but any delay in providing such information will not be considered a reason for extending the submission date of your proposal. BIDS SENT TO THIS EMAIL ADDRESS WILL BE REJECTED.

Educational Requirements:

Required Experience:
Senior Level (5+ years experience
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሕግ መዝገበ ቃላት ለማዘጋጀት የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ!

ሥምምነቱን የተፈራረሙት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ምርምርና ሥልጠና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ጀስቲስ ፎር ኦል የተባለው ግብረ ሠናይ ድርጅት ናቸው።

መዝገበ ቃላቱን ለማዘጋጀት አራት ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ሲሆን በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

የሚዘጋጀው መዝገበ ቃላት በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች የአገሪቱ ቋንቋዎች የሚዘጋጅ መሆኑም ተጠቁሟል።

#ENA|📸FBC
ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ተሾሙ
**************************************
በኢ.ፌ.ድ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት 50 የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መስከረም 12/2013 ዓ.ም ተሾሙ፡፡ የዳኞች ሹመት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከጸደቀ በኃላ ዳኞቹ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ጋር ተዋውቀዋል፡፡
ከትውውቅ ፕሮግራሙ በመቀጠል ከተሾሙት ዳኞች የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የምሳ ግብዣ ያካሄደ ሲሆን በዚሁ ፕሮግራም ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ክብርት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ ባስተላለፉት መልዕክት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በለውጥ ሂደት ላይ የሚገኙ በመሆናቸው አዲስ የተሾሙ የፍርድ ቤቱ ዳኞች የዳኝነት ነጻነት ከተጠያቂነት ጋር ሚዛኑን አስጠብቀው በመስራት የሕዝብ አመኔታ ለማረጋገጥ ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በዚህ መድረክ ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ክቡር አቶ ፋአድ ኪያር እንደተናገሩት የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ የዳኝነት ስራዎችን ጥራት ባለው፣ ውጤታማ እና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ለማከናወን እንዲያስችል ሞያው የሚፈልገውን ገለልተኝነት፣ ፍትሀዊነት፣ ቅንነት፣ ታታሪነት ከፍተኛ የስነ ምግባር እሴት መኖር እና የመሳሰሉትን በስራዎቻቸው ውስጥ ሊያንጻባረቁ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመራሮች፣ ዳኞች እና ሰራተኞች አዲስ ለተሾሙት የፍርድ ቤቱ ዳኞች መልካም የስራ ዘመን ይመኛሉ፡፡

https://t.me/lawsocieties