አለሕግAleHig ️
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ የፌደረሽን ምክርቤት ሊሰበሰብ ነው ሲባል ለኢትዮጵያ ክብር የሚመጥን ውሳኔ ሊወስን የተጠራ መስሎን ነበር። የትግራይ ክልላዊ መንግስት አዋጆች ህጋዊነት ግምገማ ሪፖርት ስሰማ ግን እጢዬ ዱብ አለ። ጆሮዬም ማመን አቅቶን ህገመንግስቱን አገላበጥኩ። የፌደሬሽን ምክርቤት ህግ ይተረጉማል የሚል አንቀፅ ፈልጌ አጣሁ። ምናልባት ሌላ ህገመንግስት ይኖር ይሆን ብዬም አሰብኩ። እንደገናም…
ታ) አለው/አለበት እንጂ፣ ምርጫ የመከልከል ሥልጣን የለውም።
ለ)ምርጫ ቦርድ
በአዋጅ፣ "ጠቅላላ ምርጫ" (ማለትም ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ምርጫዎችን) የማስፈጸም ስልጣንና ግዴታ አለበት።
ሐ) ክልሎች፣ የትግራይ ክልል እንዳደረገው፣ ምርጫ እንዲያስፈጽምላቸው ሲጠይቁ፣ "አልችልም" ብሎ ከኃላፊነት መሸሹ የሚያስጠይቅ ነው። በምንም ምክንያት ይሁን "አልችልም ወይም አልፈልግም" ካለ ግን፣ ክልሎች ምርጫ እንዳያካሄዱ እንቅፋት መሆን አይገባውም፣ አይችልምም። ምርጫን ማደናቀፍ በወንጀል ያስጠይቃልና።
መ) ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን አለው ማለት፣ በአገሪቱ ውስጥ ብቸኛው የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም እርሱ ነው ማለት አይደለም። ምርጫን የሚመለከት ጉዳይ የሚመለከተው እርሱን ብቻ ነው ማለት አይደለም።
ሠ) 'የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ'፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን አለው ማለት፣ ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣን የፌደራል መንግሥት ሥልጣን ሥር ይወድቃል ማለት አይደለም። ሕገ-መንግሥቱ፣ የትም ቦታ፣ ምርጫን የማካሄድ ሥልጣን የፌደራል መንግሥት ሥልጣን መሆኑን አይደነግግም። ምርጫ ቦርድ፣ ሕገ-መንግሥቱን ጥሶና ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታውን ገፍቶ (ሥልጣኑን abdicate አድርጎ)፣ ምርጫ እንዳይካሄድ ስለወሰነ ብቻ፣ ክልሎቹ ምርጫ እንዳያደርጉ መከልከል ይችላል ማለት አይደለም። ክልሎች እንዲህ ያለውን ኢ-ሕገመንግሥታዊ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ በመቃወማቸው፣ "ፌደራል መንግሥቱን አላከበሩም" (አንቀጽ 50(8)) አያስብልም። ምክንያቱም፣ 'ብሔራዊ' ምርጫ ቦርድ፣ እራሱን የቻለ ሕገ-መንግሥታዊ ተቋም ነው እንጂ፣ የፌደራል መንግሥቱ አካል (ወይም ተቀጥላ) አይደለምና። የፌደራል መንግሥቱ፣ በምርጫ ጉዳይ ላይ (በተለይ በክልሎች ውስጥ በሚካሄድ ምርጫ ጉዳይ ላይ) አንዳችም ሥልጣን የለውም።
ረ) 'ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ'፣ እራሱን የቻለ ሕገ-መንግሥታዊ ተቋም ነው እንጂ፣ የፌደራል መንግሥት ተቋም አይደለም። የፌደራል መንግሥቱ ተላላኪ፣ የመንግሥቱ ሥራ አስፈጻሚ፣ ነው ማለት አይደለም። በአገሪቱ ክልሎች ውስጥ ምርጫ የማስፈጸም ግዴታውን ስለገፋ ብቻም፣ ክልሎች ምርጫ እንዳያደርጉ የማስገደድ አለው ማለት አይደለም።
ሰ)ክልሎች በሕገ-መንግሥቱ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ምርጫ ማካሄዳቸው (አሁን የትግራይ ክልል እያደረገ እንዳለው)፣ ሕገ-መንግሥቱን ያጸናል፣ ያስከብራል፣ እንጂ፣ በየትኛውም መስፈርት፣ ሕገ-መንግሥቱን አይጥስም፤ ወይም ሥርዓቱን ለአደጋ አያጋልጥም።
ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለአደጋ የሚያጋልጠው፣ በተጨባጭም እያጋለጠ ያለው፣ ምርጫን አለማድረግ ነው እንጂ፣ ምርጫን ማካሄድ አይደለም።
ምርጫን አላደርግም ያለው ሕገወጥ ቡድን፣ ምርጫን ለማካሄድ የሚንቀሳቀሱ ሕጋውያንን ለማስጠንቀቅ መሞከሩ፣ የኢፍትሓዊነት ጥግ ላይ መደረሱን ያረጋግጣል። It's a travesty of justice, pure and simple.
ተፃፈ በዶ/ር ፀጋዬ
የላከልን ጉማዬ ነው

ጉማዬ😷: ለዚ በቂ መልስ በቀድሞ የአ.አ ዩኒቨርስቲ የህገ መንስት አስተማሪ ስለ (ትግራይ) ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊነት እንደገና (26 August 2020) ======= 1. ምርጫ ማካሄድ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታን በተገቢው መንገድ መወጣት ነው። ምርጫን በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማካሄድ፣ የአንድን ሕዝብ የዴሞክራሲ መብት (ማለትም፣ ሕዝቦች መንግሥታቸውን የማቆም፣ የመቆጣጠርና፣ ካልፈለጉትም የመሻር…
ይሄንን ጽሑፍ የጻፉት የህገ-መንግስት አስተማሪ ናቸው መባሉ በራሱ ያሳፍራል። የፖለቲካውን ወሬ ትተን የምናወራው ስለ ህግ ከሆነ እነዚህ የህገ መንግሥት አንቀጾች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ምርጫን ማራዘም እንደሚቻል ያስረዳናል። የመጀመሪያው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የሚያበቃ ምክንያት መኖሩ ሁላችንንም የሚያስማማን ነገር እንደሆነ አምናለሁ። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚንስትሮች ምክር ቤት የዜጎችን መሠረታዊ የፖለቲካና የዲሞክራሲ መብቶችን አዋጁን ለማሳወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘው ደረጃ ማገድ እንደሚችል በህገ መንግስቱ አንቀጽ 93 (4) (ለ) በግልጽ ተቀምጦ ይገኛል። ምርጫ የዜጎች መሰረታዊ የፖለቲካ መብት ስለሆነ ሊታገድ እንደሚችል ግልጽ ነው። ሰዎች እንኩዋን እነዚህን መብቶችን መጠቀም ቀርቶ ከፈጣሪያቸው ጋርም በቤተ እምነታቸው እንዳይገናኙ ታግደዋል። እንግዲህ ህግ ሲቀረጽ መርህ(principle) ብቻ ሳይሆን exception (አሁን አቻ የአማርኛ ትርጉም ስላጣሁለት ነው) አብሮ እንደሆነ እንኩአን ለህግ አስተማሪ ለሌላው ዜጋም ብዙም ውስብስብ ነገር አይደለም። ምርጫ ዜጎች ያላቸውን ሉአላዊ የሆነ ስልጣን በውክልና ለመንግስት የሚያስተላልፉበት መንገድ ነው። ህገ መንግስት ደግሞ በመንግስት እና በህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ሰነድ ነው ማለት እንችላለን። እንግዲህ በየ አምስት አመቱ ምርጫ መካሄድ አለበት ብሎ የደነገገው ህገ መንግስቱ (መርህ/principle) በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደግሞ የዜጎችን ህገ መንግስታዊ የሆኑ መብቶችን ማገድ እንደሚቻል (exception) ራሱ ህገመንግስቱ እንደሚደነግግ አይተናል።
ከዚህም አልፎ ህገ መንግስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅትም ጭምር ሊሻሩ የማይችሉትን መብቶች ግልፅ በሆነ መልኩ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 93 (4) (ሐ) ላይ አስቀምጧል። እነዚህም አንቀፅ 1፣18፣25፣39(1) (2) መሆኑን ገልጿል። እነዚህ አንቀጾች ደግሞ ምርጫን ከማድረግ ጋር ሚገናኙ አይደሉም። ስለዚህም ህገ መንግስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የዜጎችን መሰረታዊ የፖለቲካ መብቶች መገደብ እንደሚችል ከመደንገጉም በላይ ምርጫ ህገ መንግሥቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሊገደቡ አይችሉም ካላቸው አንቀጾች ውጪ በመሆኑ ህገ መንግሥቱ ምርጫን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊገድበው እንደሚችል ግልፅ ነው።
እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም። በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ የህግ ተማሪ ነኝ። ይህንን ሃሳብ ህግን መሰረት ባደረገ መልኩ የምትቃረኑ ከሆነ እኔም የተሻለ መረዳት እንዲኖረኝ እይታችሁን አካፍሉኝ።
በደሳለኝ ንዳ ተጻፈ

ታ) አለው/አለበት እንጂ፣ ምርጫ የመከልከል ሥልጣን የለውም። ለ)ምርጫ ቦርድ በአዋጅ፣ "ጠቅላላ ምርጫ" (ማለትም ለፌደራልና ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚካሄዱ ምርጫዎችን) የማስፈጸም ስልጣንና ግዴታ አለበት። ሐ) ክልሎች፣ የትግራይ ክልል እንዳደረገው፣ ምርጫ እንዲያስፈጽምላቸው ሲጠይቁ፣ "አልችልም" ብሎ ከኃላፊነት መሸሹ የሚያስጠይቅ ነው። በምንም ምክንያት ይሁን "አልችልም ወይም አልፈልግም" ካለ…
These guys have completely forgotten the very objective of election in which people ascertain their democratic rights and bring to power those who care for their human rights issues including their rights to life. Elections should not be lifeless and mechanical and if it is expected to be carried out by the expense of the lives of the poor for the sake of putting some 'artful politicians in power', then that's what traversy of justice is all about since the so called politicians will have no one to represent and rule. Being written by a 'doctor' does not make an article always credible.
Sisay Degaga
Sisay Degaga
ስንሽከረከር እንዳንውል ለነገሩ ጭብጥ መኖሩ አግባብ መሆኑን አምናለሁ። በመሆኑም
1 ምርጫ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት መሆኑ
2 በአንቀፅ 93 ስር ከማይታገዱ የዜጎች መብት ስር አለመካተቱ
ለዚህ የምርጫ ጉዳይ በቂ ጭብጥ ነው የሚል እምነት አለኝ።
ሌላው የሚያሳዝነው ጉዳይ መንግስት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ ከሚገባባቸዉ ጉዳዮች
1 ህገመንግስታዊ ሥርዐቱን አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳይ ሲኖር
2 የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲኖር ነው
እናም አሁን ያሳዘነኝ ጉዳይ የህዝብ ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል ይህ ሁኔታ ተከስቶ ሳለ ምርጫ እንዲካሄድ በዝምታ ወይም ህጋዊ እውቅና የሌለው ምርጫ የሚል ውሳኔ በጣም አሳዛኝ ነው።
የክልከለው አላማ የህዝቡን ጤና እንዲጠበቅ ማስቻል በመሆኑ ነው። እናም የጤናቸው ጉዳይ አያሳስበኝም ስልጣኔን ግን አላስነካም ማለት ያስተዛዝባል።
የፌደራሉ መንግሰት ለህዝብ ቢቆም ኖሮ ይህንን ምርጫ ያስቆም ነበር።
ስለሆነም ከአዋጁ አላማ ውጭ ፖለቲካዊ ጉዳዩን ብቻ ማታየቱ ያሳዝነኛል።
እዚህ ላይ የፌደራል መንግስት በክልሎች ጉዳይ የሚገባበት ሁኔታ በአዋጅ መውጣቱን መገንዘብ ያሻል።
በ ∞

ህገ-መንግስት እንዲያኗኑረን እንጅ ለዕለት ህይወታችን ሆነ ለጥቅል ማህበራዊ ስሪታችን ጠንቅ እንዲሆን የተከተበ ሰነድ እንዳይደለ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ህገ-መንግስት የተቀመጠው የማህበረሰባችን ህይወት ሰበቃ ቀንሶ አብሮ መኖራችንን በመደላድል እንዲያመቻምች እንጅ ከድጡ ወደማጡ እንዲከት አይደለም፡፡የማህበረሰብ ህይወትን በህግ መሰረት ቃኝቶ ለማጽናት የተቀረጸው ይኸው ሰነድ ባለቤቱ የሆነው ህዝብ ያልተገመተ ፈተና ሲገጥመው በልሂቃን እየዳበረ ጊዜውን እየመጠነ የሚሄድ እንጅ ቆሞ ቀር መሆንም የለበትም፡፡
የህግ ምሁራን የፖለቲከኞች ቀላጤ ሲሆኑ የህግ ሥርዓቱ በጥልቅ ቀውስ ውስጥ እንደሚገኝ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርም ይኸው መሰለኝ እየተደረገ ያለው፡፡ የህግ ልሂቃን በተቻላቸው በራሳቸው ተፈጭተው ፣ተከራክረው እና ተሟግተው ለማህበረሰብ መተላለፊያ መንገድ ሊያበጁ ሲገባ ጎራ ለይተው ከመርህም ሆነ ከሞራል ባፈነገጠ አኳኋን ወገንተኛ የሆነ እና በፖለቲካ የታጀለ የህግ ትንተና ሲያቀርቡ ለህግ ስርዓታችን መጎልበት ምን ያህል ጠንቅ ሊሆን እንደሚችል መረዳት ይኖርብናል፡፡
ለመቀሌው ዩኒቨርሲቲ መምህር የማቀርበው
1. በዜጎች ጤናቸው ተጠብቆ የመኖር መብትን በተመለከተ ምን አስተያየት ይኖራቸው ይሆን?
2. ለህግ የበላይነት ያላቸው ምልከታስ እንዴት ይገለጽ ይሆን?
3. በፌዴሬሽን በአንድ ተጣምሮ የሚገኝ በባለ ሁለት ደረጃ መንግስታዊ አስተዳድር መርሆዎችና የስልጣን እና ተግባር ድልድሎችስ ላይ ምን ይነግሩናል?
4. የፍርድ ቤት ውሳኔ ሲጣፍጥ የሚከበር ሲመር ግን ወደ ጎን የሚደረግ ነው ወይ?
ህግ ስርዓታችንን በተመለከተ ብዙ ህጸጾች መዘርዘር አይደለም ለባለሙያ ለሰፊው ህዝብም የሚከብድ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡አሁን ደግሞ ከትላንት ዛሬ ከተደፋበት ለመቀናት ደንበር ገተር በሚልበት ወቅት እንዲህ ያለ ህግን እና ፖለቲካን ክፉኛ የደባለቀ ትንተና ለነገ ስምም አይበጅም፡፡ ያፈጠጠውን ለመከለለ እንዲህ የቃላት ድሪቶ ማድራት ነገ በትምህርት ክፍል የአሉታ ማጣቀሻ ከመሆን ያለፈ ሚና ይኖረዋል የሚል እምነት የለኝም፡፡
ቀና ቀናውን ያመላክተን፡፡
አንገት ከሚሰበር ……. እንዲል አቀንቃኙ ብኩርናን ለምስር ዳርጎት መለወጥ ነውር ነው በሉልኝ፡፡
በ ካbtaAmu

Forwarded from ⒻⒾⓇⒶ😉Ⓛ
Hige mengist zendiro taqayere new weyis teterogeme new linil minichilew?
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
07/09/2020
LEGAL AIDE
Tsehay Insurance
Addis Ababa, Ethiopia
FULL_TIME Insurance Jobs in Ethiopia Legal Jobs in Ethiopia
Job Description
JOB REQUIREMENT
Qualification: College Diploma in relevant field
Work Experience: 4 years of relevant experience
Place of Work: Head Office
HOW TO APPLY
Salary: As per the scale of the company with other benefit packages
Interested applicants, who fulfill the minimum requirements, can send their non-returnable application with CV and copies of relevant documents within 7 working days from the first date of this announcement to:
Tsehay Insurance S.C.
Manager, HR & Property Administration
P.O.Box 56144
Addis Ababa
@Ethiopian_Legal_Advocate

ለውድ የ #ALE # አለ የመገናኛ አውታር ተከታዮች 🌼🌼🌼እንኳን ለ2013ዓ.ም አደረሳችሁ🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼Happy New Year🌼🌼🌼
@lawsocieties
ባለፉት ዓመታት በALE (Alternative Legal Education) የቴሌግራም የመገናኛ አውታር ስንሰጣችሁ በነበረው ግልጋሎት እና ከአዲሱ ዓመት ጀምሮ አገልግሎታችንን በምን መልኩ እናድርገው በሚለው ነጥብ ላይ በማተኮር ያላችሁን ገንቢ አስተያየት ብትሰጡን አስተያየታችሁ ወደፊት የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ይረዳናል፡፡
አስተያየት ለመስጠት
@Alemwaza
ወይም
@Asratm27
አድራሻዎች ይጠቀሙ፡፡
🌻🌻🌻Happy New Year🌻🌻🌻
@lawsocieties
ሌሎች ወዳጆቻችሁንም የእዚህ የቴሌግራም አውታር ቤተሰብ እንዲሆኑ ይጋብዙ፡፡
🙏🏻🙏🏻🙏🏻እናመሰግናለን🙏🏻🙏🏻🙏🏻
አዲሱን ዓመት ፈጣሪ ወረርሽኙን አጥፍቶ ፤በተረጋጋ መንፈስና ስሜት የዘረኝነት አስተሳሰብ አስወግዶ ፤ በሰውነት መስፈርት ብቻ በቀደመው ኢትዮጵያዊ ማንነታችን ተከባብረን፣ በመተሳሰብ ፣በመደጋገፍ የምንኖርበት የተባረከ ዓመት ያድርግልን፡፡
🌼🌼🌼🌻🌻Happy New Year🌻🌻🌼🌼🌼
https://t.me/lawsocieties
@lawsocieties @lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

BERHANU. W:
ALE law Program?
ALE(አለ) የህግና ተያያዥ ጉዳዬች የሚቀርብበት በይነ መረብ የእስካሁን አቀራረብና ጥረት ታላቅ ምስጋና:ክብር እየሰጨሁ፣ቀጣይ መሆን ያለበት በዚህ ቀጥሎ መሻሻል አለበት እሚለውን አንተ ብጨምር።አንተን መረጃ እንድንጠይቅህ ብዙ ሳንደክም ቴሌግራም ቢኖርህ:ጥያቄውን ቶሎ ብታየው?በ2012 የት ጠፋህ?መረጃህ ቀንሶ ከረመ።በኮረና ይሆናል።ግን አይብዛ መጥፋት።አለን ሳላይ መረጃ ሳጣ በጣም እበሳጫለሁ።አንባቢ ነኝ።ህግ ነው የተማርኩት።ብሄር:ፖለቲካ: ገለመሌ አልወድም።አይመቼኝም።አመሠግናለሁ።(ብርሃኑ ወርቄ ወሎ ደሴ ኢትዮጵያ።)

BERHANU. W: ALE law Program? ALE(አለ) የህግና ተያያዥ ጉዳዬች የሚቀርብበት በይነ መረብ የእስካሁን አቀራረብና ጥረት ታላቅ ምስጋና:ክብር እየሰጨሁ፣ቀጣይ መሆን ያለበት በዚህ ቀጥሎ መሻሻል አለበት እሚለውን አንተ ብጨምር።አንተን መረጃ እንድንጠይቅህ ብዙ ሳንደክም ቴሌግራም ቢኖርህ:ጥያቄውን ቶሎ ብታየው?በ2012 የት ጠፋህ?መረጃህ ቀንሶ ከረመ።በኮረና ይሆናል።ግን አይብዛ መጥፋት።አለን…
እንዲህ እየመረጥን ለየት ያለ አስተያዬት እና መልዕክት #Share እናደርጋለን።
ግን ❓
ብዙ የአለ ቤተሰቦች ብዙ አስተያየት እና ምስጋና አድርሳችሁናል እናመሰግናለን‼️
Happy new year‼️

Forwarded from abyssinialaw.com
የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ መቁረጥ እና ሕጋዊነቱ
በ፡-አቤል ዘውዱ
ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነው ገበታ ለሃገር መርሃግብር የመንግሥት ሠራተኞች የወር ደሞዛቸውን ለገሱ የምትል ዜና በተደጋጋሚ በመስማቴ እና እውነት በዚህ የኑሮ ውድነት እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዛቸውን የሚለግሱት ጎርጎራ፣ ወንጪ አሊያም ኮይሻ ላይ ሆቴል መሰራቱ ከጊዚያዊ ችግሮቻችን ይበልጣል ብለው አምነው ወይስ በአለቆቻቸው ተፅዕኖ ሥር በመሆናቸው ተገድደው የሚለው ጥያቄ በተደጋጋሚ ውስጤ ሲመላለስ በመቆየቱ ነው፡፡
መልካም ንባብ
https://www.abyssinialaw.com/blog-posts/item/1954-the-legality-of-cutting-civil-servant-salary

ALE ዎች እንዴት ከረማችሁ ከሁሉም በማሰቀደም እንኳን ለ2013 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
የዚህ ቻናል አባል ከሆንኩበት ቅፅበት አንስቶ አያሌ ሕግ ሕግ የሚሸቱ ሰነዶችን፣ መረጃዎችን፣ እና ለህጉ ማህበረሰብ እሚጠቅሙ የተለያዩ ሀሳቦችን ስታካፍሉንና ስታሳትፉን ቆይታችዋል፤ በእውነቱ በርቱ ማለትን ፈልጋለው፡፡
በዚህ ላይ ማለት እምፈልገው የተለያዩ የህግ ሙህራን፣ የሕግ ትምህርት ቤቶች አመራሮች እንዲሁም ተማሪዎች እንደመኖራቸው መጠን በቀጣዩ አመት ሁሉም በሃላፊነት ቀለል ባለ አቀራረብ እውቀቱን ማካፈል ቢችልና በሳል የሆኑ ህግ ነክ ጉዳዮችን ማብላላት እሚቻለበት መደረክ አልያም መማማሪያ አይነት ነገር ማድረግ ቢቻል እና በዚህም ሁሉም መሳተፍ ቢችል በሃላፊነት ስሜት!!
ሌላኛው የተለያዩ ጥናቶችን፣ አርቲክሎችን፣ መፃህፍትን እና የህግ ሰነዶችን ማቅርብ ቢቻል በብዛትና ጥራት፡፡
የመጨረሻው ወቅታዊ የሆኑ ህግ ነክ መረጃዎችን እጅግ በፈጠነ መልኩ ማጋራት እምችሉበት ከበፊቱ በተሻለ ማቅርብ ብትሞክሩ፡፡
አመሰግናለሁ መልካም አዲስ ዓመት!!
(AN, ADAMA ETHIOPIA )

ALE ዎች እንዴት ከረማችሁ ከሁሉም በማሰቀደም እንኳን ለ2013 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የዚህ ቻናል አባል ከሆንኩበት ቅፅበት አንስቶ አያሌ ሕግ ሕግ የሚሸቱ ሰነዶችን፣ መረጃዎችን፣ እና ለህጉ ማህበረሰብ እሚጠቅሙ የተለያዩ ሀሳቦችን ስታካፍሉንና ስታሳትፉን ቆይታችዋል፤ በእውነቱ በርቱ ማለትን ፈልጋለው፡፡ በዚህ ላይ ማለት እምፈልገው የተለያዩ የህግ ሙህራን፣ የሕግ ትምህርት ቤቶች…
AN ከአዳማ ለሰጡን ገንቢ አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን🙏🏻🙏🏻🙏🏻፡፡ በሰጡን አስተያየት መሰረት በደንብ መክረንበት ለተሻለ አገልግሎት እንተጋለን፡፡አብሮነትዎ አይለየን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!!!
ይደግ እባላለሁ 5ኛ አመት የህግ ተማሪ ነኝ፡፡
በጣም ጥሩ እየተንቀሳቀሳቹ ነው፡፡ በርቱ፡፡
መረጃወችን በትኩስ በትኩሱ ተከታትላቹ ብታቀርቡልን፡ አንዳንድ መነበብ አለባቸው ምትሏቸውን ከአማርኛም ሆነ ከእንግሊዝኛ ስራወች(articles,books,journals, decisions) ብታካፍሉን እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ የህግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን ለክርክር እና ውይይት ብታቀርቡ እላለሁ፡፡
አመሰግናለሁ፡ እግዚአብሔር ይባርካቹህ

ይደግ እባላለሁ 5ኛ አመት የህግ ተማሪ ነኝ፡፡ በጣም ጥሩ እየተንቀሳቀሳቹ ነው፡፡ በርቱ፡፡ መረጃወችን በትኩስ በትኩሱ ተከታትላቹ ብታቀርቡልን፡ አንዳንድ መነበብ አለባቸው ምትሏቸውን ከአማርኛም ሆነ ከእንግሊዝኛ ስራወች(articles,books,journals, decisions) ብታካፍሉን እንዲሁም አንዳንድ ወሳኝ የህግ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን ለክርክር እና ውይይት ብታቀርቡ እላለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡ እግዚአብሔር…
ስለገንቢ አስተያየትዎ ከልብ እናመሰግናለን ወንድም ይደግ🙏🏻🙏🏻🙏🏻፡፡ በሰጡን አስተያየት መሰረት በደንብ መክረንበት የተሸለ አገልግሎት ለመስጠት እንተጋለን፡፡ አብሮነትዎ አይለየን፡፡ መልካም አዲስ ዓመት፡፡
Forwarded from 🇪🇹የሕግ ጉዳይ (Alemwaza)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የ2012 ዓ.ም የዳኝነት የስራ ዓመት መገባደድ እና የ2013 አዲስ ዓመት መባቻን አስመልክቶ ለዳኞች የምስጋና መግለጫ ልከዋል፡፡ የመግለጫው ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ክቡራንና ክቡራት ዳኞች
ባሳለፍነው የዳኝነት ዘመን በፍርድ ቤቶች ለተስተዋለው የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ያሳያነው የዳኝነት ኃላፊነት ስሜት፤ የሙያ ስነምግባርና ክብር የሚመሰገን ነው፡፡ ለተገኘው ውጤትም በፍርድ ቤቱ ከፍተኛ አመራር አካላት በኩል ለተፈጠረው የጋራ ራዕይ፣ ግልጽነት፣ የመተማመን መንፈስ እና የስራ ትጋር ያለኝን አድናቆት እገልጻለሁ!!
የዳኝነት ዘርፉን በተሟላ ቅርጽና ይዘት የማሻሻል አቅም የሚፈጥሩና የማዕዘን ድንጋይ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ የፌዴራሉ መንግስት የዳኝነት አካል ራሱን በሙሉ ነጻነት ማስተዳደር የሚያስችል እና የፍርድ ቤቶችን አደረጃጀትና ስልጣን የሚወስነውን አዋጅ በአዲስ መልክ የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጆች ተዘጋጅተው ለምክር ቤቱ ቀርበዋል፡፡ ምክር ቤቱም ላቀረባቸው የማብራሪያ ጥያቄዎች ዝረዝር ማብራሪያ በመስጠት በኮቪድ ምክንያት በሙሉ ዓቅሙ ስራ እንዳይሰራ ከማድረጉ በፊት የመጽደቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ማድረስ ተችሏል፡፡
ሌላው በዚህ ዓመት ከተከናወኑት ዓበይት ስራዎች መካከል በዓለማችን እንዲሁም በሃገራችን በተከሰተውና እስከአሁንም መፍትሄ ባልተገኘለት የኮቪድ 19 ወርሽኝ ምክንያት የዜጎችን የዳኝነት መብት እና በጤና በህይወት የመኖር መብት በአንድ ላይ ለማረጋገጥ ከገባንበት አጣብቂኝ ውስጥ ለመውጣት የሰራነው ስራ አንዱ ነው፡፡
ፍርድ ቤቶቻችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ማሰራጫ ማዕከል እንዳይሆኑ ለማድረግ በተወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ ፍ/ቤቶች ከመጋቢት እስከ ሐምሌ አጋማሽ በከፊል ዝግ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚሀም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤቶቻችን ሊመጣ የሚችል የመዛግብት ፍሰት የቀነሰ ቢሆንም ዳኞች በቤታችሁና በቢሯችሁ ለምርመራ ለደረሱ መዛግብት እልባት ለመስጠት ጊዜያችሁን በመጠቀማችሁ በፌዴራል ፍ/ቤቶች ደረጃ 140 ሺህ ለሚሆኑ መዛግበት እልባት መስጠት ተችሏል፡፡
በወረርሽኙ ምክንያት ፍ/ቤቶቸ በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩ በተደረጉበት ተመሳሳይ ጊዜ አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች በተረኛ ችሎት በማስተናገድ ለ7 ሺህ መዛግብት እልባት ተሰጥቷል፡፡ ይህም በአጣዳፊ ሁኔታ ዳኝነት ለሚሹ ወገኖቻችን ከራሳችሁ ደህንነት ይልቅ የእነርሱን በማስቀደም አወንታዊ ምላሽ ለመስጠት ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ የተጠቀማችሁበት ለመሆኑ ያሳያችሁበት ነው ለማለት ያስችላል፡፡
የዳኝነት የስራ ጫና ለመቀነስ ከ150 በላይ የረዳት ዳኞች ቅጥር በማከናወን የዳኞችን የስራ ሸክም ለማቃለልም ተችሏል፡፡ የሬጂስትራር ባለሙያዎቸን በበቂ ቁጥር በመሾምና የሙያ ብቃታቸውን የሚያጎለብት ስልጠና ተሰጥቷል፤ የአሰራር ለውጥ ተደርጓል፡፡ ከተገልጋዮቻችን ያገኘነው ግብረመልስ የሬጂስትራር አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናም መጨመሩን ጠቁሞናል፡፡
የተወደዳችሁ ዳኞች
የዳኝነት አንዱ መገለጫ ባህሪው ግልጽነት ነው፡፡ ዳኝነትን በግልጽ ችሎት ለመስጠት የማያስችሉ፤ ለዳኞችና ለተገልጋይ ምቾት የሌላቸውን ምድብ ችሎቶችን በመለየት የተሻለ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ህንጻዎችን በመከራየት ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ጥረትም አበረታች ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ከመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የመናገሻ እና የአራዳ ምድብ ችሎቶች እንዲሁም ከከፍተኛ ፍ/ቤት ጦሃይሎች ምድብ ችሎት ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
እንደምትገነዘቡት የዳኝነት ነጻነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያስመዘገብንባቸው አኩሪ እና ፈር ቀዳጅ ውጤቶችም አሉ፡፡ የዳኝነት አካሉን የበጀት ነጻነት ለማስጠበቅ በተሰራው ስራ በህገመንግስቱ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት የፍርድ ቤትን በጀት ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጥታ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ በማቅረብ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ምኒስቴር ከተቀመጠው የበጀት ጣሪያ በላይ በማስፈቀድ በጀቱን በውጤታማነት ጥቅም ላይ ማዋል ተችሏል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን የዳኞችን ግለሰባዊ ነጻነትና መብት አስከብሮ ገለልተኛ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታችን ለመፍጠር በተደረጉ ጥረቶች ዳኞች ያለባቸው የስራ ሃላፊነትና ጫና እነዲሁም የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከግንዛቤ ያስገባ የደመወዝ ማስተካከያም መደረጉ ይታወቃል፡፡ በእቅድ ከተያዘለት ጊዜ በላይ የወሰደው የዳኞች የጋራ መኖሪያ ሕንጻ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ከመንግስትና ከተቋራጩ ድርጅት ጋር በተደረጉ ያልተቋረጠ ክትትልና የአስተዳደር ድጋፍ ስራችን ፍሬ አፍርቶ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ችለናል፡፡ ዳኞች በቤት ኪራይ ሲደርስባቸው ከነበረው እንግልት የሚያወጣቸውና መኖሪያ ብቻ ሳይሆን እንደቢሮም የሚገለገሉባቸው 140 ባለ ሶስት እና 138 ባለ ሁለት መኝታ ክፍል ቤቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል፡፡
ከላይ የጠቀስናቸው አመርቂ ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም ያልተሸገርናቸውና ጉዳዮች አሉ፡፡ በጀመርነው አዲስ የዳኝነት ዓመት (2013 ዓ.ም) የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ስርዓታችን እንዱ በልዩ ትኩረት ልንሰራበት የሚገባ ዘርፍ ነው፡፡ በጀምር ላይ ያለውና የመደበኛ ፍርድ ቤቶቻችንን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል ፍርድ ቤት መር የአስማሚነት አገልግሎት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታን ማመቻቸት ያስፈልገናል፡፡
የምንሰጠው ዳኝነት ከቅልጥፍና አንጻር መልካም ደረጃ ላይ ደርሷል ሊባል የሚችል ቢሆንም ከምንሰጠው ዳኝነት ጥራት አኳያ ውስንነቶች እንዳሉ በተለያየ መንገድ የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የዳኝነት ነጻነት ሚዛን መጠበቂያ የሆነው የዳኝነት ተጠያቂነት ስርዓታችንንም እንደዚሁ የምንፈትሽና በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀን የዲሲፕሊንና ስነምግባር መመሪያ እንዲሁም የአፈጻጸም ምዘና መመሪያን በማጽደቅ ስራ ላይ የምናውል ይሆናል፡፡
ፍርድ ቤቶቻችን ለአራት ወራት በከፊል ዝግ ሆነው በመቆቀታቸው በወቅቱ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች ሳይታዩና መዝገብ ሳይከፈትላቸው በመቆየታቸው በጀመርነው አዲስ አመት የመዝገብ ፍሰቱ መጨመሩ የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም በተባበረ መንፈስ ጠንክረን በመስራት በፍርድ ቤቶቻችን እየታየ ያለውን ለውጥ በማስቀጠል አምና ያገኘነውን የሚያስመሰግን ውጤት ከፍ ባለ ደረጃ እንድንደግመው በጋራ ራዕያችን ላይ በጽናት እንድንቆም በዚሁ አጋጣሚ ልጠይቃችሁ አፈልጋለሁ፡፡
የአዲሱ አመት የመጀመሪያው ወር የእረፍት ጊዜያችሁ አንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤቶቻችን የተለመደ አሰራር አብዛኛዎቻችሁ ውዝፍ መዛግብትን በማጥራት ስራ ላይ በፈቃዳችሁ የምትቆዩ መሆናችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፡፡
ወድ ዳኞች በመጨረሻም
መጪው አዲስ ዘመን ቃል የገባንለት ህጋዊና ፍትሃዊ ዳኝነት የመስጠት ተልዕኳችንን በእውቀትና በሙያ፤ በገለልተኝነትና በሐቀኝት፤ በቅልጥፍናና በጥራት፤ በነጻነትና በተጠያቂነት የምንወጣበት፤ ህብረተሰቡ በፍርድ ቤቶቻችን ላይ ያለው ዓመኔታ ከፍ የሚልበት እና ለሌላ ተጨማሪ ስኬት የምንበቃበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!
ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ መንግስቱ
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት
ጷጉሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም