አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት አራዘሙ
***
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ፍርድ ቤቶቹ ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ መወሰናቸውን ለኢቢሲ በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩና አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲመለከቱ መደረጉ ይታወቃል፡፡
የወረርሽኙ ስርጭት እየተስፋፋ በመምጣቱ ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረና የስርጭት አድማስም እየሰፋ መምጣቱን የጤና ጥብቃ ሚኒስቴር በየጊዜው ከሚያስራጫቸው መረጃዎች የፍርድ ቤቱ አመራር መገንዘብ ችሏል፡፡
አመራሩ ባካሄደው ስብሰባ የዳኝነት አገልግሎት ለማግኘት ከክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተሞች ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ባለጉዳዮች ቁጥራቸው በርካታ በመሆኑና የእነዚህ ባለጉዳዮች ለቫይረሱ ስርጭት ያላቸወን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ዳኞችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ ወስኗል፡፡
ፍ/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩበት ጊዜ በተረኛ ችሎት እንዲታዩ ከተለዩት ጉዳዮች በተጨማሪ አነስተኛ የተገልጋይ ቁጥር ያላቸው ሌሎች የዳኝነት አገልግሎት ሊሰጥባቸው የሚችሉ የጉዳዮችን በመለየት አገልግሎቱን በየጊዜው ቀስ በቀስ ለባለጉዳዮች ክፍት እየተደረገ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም በአመራሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜ፡-
1. ከሰኔ 30/2011 ዓ/ም በፊት የተከፈቱ ዉዝፍ ይግባኝ መዝገቦችን ለመወሰን በችሎት ባለጉዳዮችን የመስማት አስፈላጊነት የታመኑባቸው ጉዳዮች ተለይተው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
2. የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተከራካሪ ወገኖች ይሰማሉ፤ እንደየሁኔታው ከባለጉዳዮች ጋር በመነጋገር የቃል ክርክራቸውን በጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን ወሳኔ እንዲያገኙም ይደረጋል፡፡
3. የፍታብሔር ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ባለጉዳዮችን መስማት አስፈላጊነቱ በዳኞች ከታመነባቸው ጉዳዮች ውጭ የሆኑ መዛግብት እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል።
4. አስቸኳይ በሆኑ ጉዳችዮች በተረኛ ችሎት የተሰጠውን ትዕዛዝ፣ ብይን እና ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ የይግባኝ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት የሚሰጣቸው ይሆናል፣
5. አስቸኳነት ያላቸው ጉዳዮች ማለትም ከህጻናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፣ የዋስትና ጉዳይ፣ የአሰሪና ሰራተኞች ጉዳይ፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይሆናሉ፡፡
6. የፌዴራልና የክልል ጉዳዮች ውሳኔን መሰረት በማድረግ ተከፍተው በሂደት ላይ የነበሩ የአፈጻጸም ጉዳዮች የስራና አፈጻጸም አቅጣጫ እስከሚሰጥባቸው ጊዜ ድረስ በደረሱበት ደረጃ ቆመው የሚቆዩ ይሆናል፡፡
7. በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ተዘጋጅቶ በሚገለጸው መርሃ-ግብር መሰረት የውሳኔ፣ የትዕዛዝ፣ የብይንና የመዝገብ ግልባጭ የመስጠት ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ የሚገቡና የሚስተናገዱት ባለጉዳዮቹ ብቻ ይሆናሉ፡፡
ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ እንዲሁም በመግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ እጅ መታጠቢያ እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የእርስ በእርስ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንዲስተናገዱ የፍርድ ቤቱ አመራር አሳስቧል፡፡ የመከላከያ ጥንቃቄዎችን በአግባቡ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያደርሰው አስከፊ ጥቃት ህብረተሰቡ አራሱን እንዲከላከል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
#EBC
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው የሚቆዩበትን ጊዜ

ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት አራዘሙ፡፡

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2012 ዓ.ም በከፊል ዝግ ሆነው እንዲቆዩና አስቸኳይነት ያላቸውን ጉዳዮች ብቻ በተረኛ ችሎት እንዲመለከቱ መደረጉ ይታወቃል፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፕሬዝደንቶችና ም/ፕሬዝደንቶች በፍርድ ቤቶች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ወቅታዊ ሁኔታ ባካሄዱት ስብሰባ ገምግመዋል፡፡

የወረርሽኙ ስርጭት እየተስፋፋ በመምጣቱ ምክንያት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረና የስርጭት አድማስም እየሰፋ መምጣቱን የጤና ጥብቃ ሚኒስቴር በየጊዜው ከሚያስራጫቸው መረጃዎች የፍርድ ቤቱ አመራር መገንዘብ ችሏል፡፡

አመራሩ ባካሄደው ስብሰባ የዳኝነት አገልግሎት ለማግኘት ከክልሎች፣ ከአዲስ አበባና ከድሬዳዋ ከተሞች ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ባለጉዳዮች ቁጥራቸው በርካታ በመሆኑና የእነዚህ ባለጉዳዮች ለቫይረሱ ስርጭት ያላቸወን ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ዳኞችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ደህንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከሰኔ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እስከ ሀምሌ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ለተጨማሪ 30 የስራ ቀናት በከፊል ዝግ ሆነው አንዲቆዩ ወስኗል፡፡

ፍ/ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩበት ጊዜ በተረኛ ችሎት እንዲታዩ ከተለዩት ጉዳዮች በተጨማሪ አነስተኛ የተገልጋይ ቁጥር ያላቸው ሌሎች የዳኝነት አገልግሎት ሊሰጥባቸው የሚችሉ የጉዳዮችን በመለየት አገልግሎቱን በየጊዜው ቀስ በቀስ ለባለጉዳዮች ክፍት እየተደረገ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም በአመራሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህን መሰረት በማድረግም ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ጊዜ፡-

1. ከሰኔ 30/2011 ዓ/ም በፊት የተከፈቱ ዉዝፍ ይግባኝ መዝገቦችን ለመወሰን በችሎት ባለጉዳዮችን የመስማት አስፈላጊነት የታመኑባቸው ጉዳዮች ተለይተው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡

2. የወንጀል ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ከማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጋር የቪዲዮ ኮንፈረንስ መርሃ ግብር በማዘጋጀት ተከራካሪ ወገኖች ይሰማሉ፤ እንደየሁኔታው ከባለጉዳዮች ጋር በመነጋገር የቃል ክርክራቸውን በጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን ወሳኔ እንዲያገኙም ይደረጋል፡፡

3. የፍታብሔር ይግባኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ባለጉዳዮችን መስማት አስፈላጊነቱ በዳኞች ከታመነባቸው ጉዳዮች ውጭ የሆኑ መዛግብት እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

4. አስቸኳይ በሆኑ ጉዳችዮች በተረኛ ችሎት የተሰጠውን ትዕዛዝ፣ ብይን እና ውሳኔ መሰረት በማድረግ የሚቀርቡ የይግባኝ ጉዳዮች በአፋጣኝ እልባት የሚሰጣቸው ይሆናል፣

5. አስቸኳነት ያላቸው ጉዳዮች ማለትም ከህጻናት ቀለብና አስተዳደግ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች፣ የዋስትና ጉዳይ፣ የአሰሪና ሰራተኞች ጉዳይ፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈጸሙ የቤት ውስጥ ጥቃቶች እና ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያ ወይም ደንብ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይሆናሉ፡፡

6. የፌዴራልና የክልል ጉዳዮች ውሳኔን መሰረት በማድረግ ተከፍተው በሂደት ላይ የነበሩ የአፈጻጸም ጉዳዮች የስራና አፈጻጸም አቅጣጫ እስከሚሰጥባቸው ጊዜ ድረስ በደረሱበት ደረጃ ቆመው የሚቆዩ ይሆናል፡፡

7. በየደረጃው ባሉ ፍርድ ቤቶች ተዘጋጅቶ በሚገለጸው መርሃ-ግብር መሰረት የውሳኔ፣ የትዕዛዝ፣ የብይንና የመዝገብ ግልባጭ የመስጠት ተግባር የሚከናወን ይሆናል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በሆኑባቸው ጊዜያት ወደ ፍርድ ቤቶቹ ቅጥር ጊቢ የሚገቡና የሚስተናገዱት ባለጉዳዮቹ ብቻ ይሆናሉ፡፡ ባለጉዳዮች ለአገልግሎት ወደ ፍርድ ቤት ሲመጡም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መልበስ እንዲሁም በመግቢያ በር ላይ በተዘጋጀ እጅ መታጠቢያ እጃቸውን መታጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የእርስ በእርስ ርቀታቸውንም ጠብቀው እንዲስተናገዱ የፍርድ ቤቱ አመራር አሳስቧል፡፡

የመከላከያ ጥንቃቄዎችን በአግባቡ በመተግበር ወረርሽኙ ከሚያደርሰው አስከፊ ጥቃት ህብረተሰቡ አራሱን እንዲከላከል የፌዴራል ፍርድ ቤቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
Hi Ale, investment, human rights, teaching materials laklign ebakh
Selam.sele yerga tinish maberareya felege neber
አለመፍራታችን ያስፈራል!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

የኮሮና ቫይረስ ወደ ሃገራችን ከገባ ድፍን ሶስት ወር ሊሞላው ተቃርቧል። ነገር ግን ከዛሬ ሶስት ወር በፊት እና አሁን ላይ ያለን የማህበራዊ ህይወት እምብዛም ልዩነቱ አይታይበትም።

ያኔ ገና አንድ ብለን ስንጀምር በብዙ መሸበር እና ግራ መጋባት እንዳልነበርን አሁን ላይ በቀን ውስጥ በመቶዎች ስናስቆጥር ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነን ደንገጥ አለማለታችን ያስፈራል። ጉዳዩን የቁጥር አድርገነዋል። ዛሬ ላይ የምንሰማው ከትላንቱ በአንድ እንኳን ካነሰ 'የዛሬውስ ይሻላል' እያልን ጥንቃቄያችንን በቁጥር ላይ መሰረት አድርገን እየተዘናጋን ነው። ጉዳዩ ግን የቁጥር እና የንፅፅር አይደለም።

በየቦታው የተሰቀሉት የእጅ መታጠቢያ ጄሪካኖች አሁን ላይ ከቦታቸው ተነስተዋል፣ አካላዊ እርቀቱ ተረስቶ እንደቀድሞው ሆነናል፣ የፊት ጭምብል ለአገጭ እና ለግንባር የተሰራ አስመስለነዋል፣ባጠቃላይ የመጀመሪያው ፍርሃታችን እና ጥንቃቄያችን የለም።

አንድ ሲባል እንዳልደነገጥን አሁን ላይ 100 በላይ ሲባል ምንም አልመስል ብሎናል፥ በፊት የምንወስዳቸው ጥንቃቄዎች ወረት ሆኖብን መድሃኒቱን ያገኘነው እስኪመስል ድረስ ቸልተኞች ሆነናል።

ነገር ግን የመጀመሪያውን ፍርሃታችንን ልንመልሰውና ወደ ጥንቃቄ ልንቀይረው ይገባል። ኮሮና ቫይረስን በምናብ የተሳለ ተረት አናድርገው፣ሲደርስብን ብቻ ለመንቃት አንሞክር።

መዘናጋታችን አሁንም ከዚህ በላይ ዋጋ ሳያስከፍለን ነቅተን አንዳችን ለአንዳችን ዘብ ልንቆም ይገባል። አሁን በደጉ ጊዜ ካለንበት ከቁጥር ዓለም እንንቃ እና ጥንቃቄ እናድርግ።

ፍርሃታችንን ወደ ጥንቃቄ በመለወጥ አድርጉ የተባልነውን ብቻ በማድረግ ሃገራችንን ከዚህ አስከፊ በሽታ እንታደጋት።

''የአንተ/ያንቺ ጥንቃቄ ነገ ለእኛ ህይወት ነው''
via Tikvah
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 190 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው ፤አምስት ተጨማሪ ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል፡፡
https://amharaweb.com/በኢትዮጵያ-ተጨማሪ-190-ሰዎች-የኮሮናቫይረስ/
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4 ሺህ 599 የላቦራቶሪ ምርመራ 190 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህም በሀገሪቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 2ሺህ 336 አድርሶታል፡፡

አምስት ተጨማሪ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንም የጤና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ አስታውቋል፤ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች መካከል 135 ወንዶች ናቸው፡፡ ዕድሜያቸው ከአንድ እስከ 89 ዓመት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

ቫይረሱ በአዲስ የተገኘባቸው…
Hello every body! Hopefully all you are fine ! Pealse could one of you help me in attaching the format of externship program. Thank u in advance!
የፍትህ ተደራሽነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ዌብነር የፊታችን ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡

***********************************************************

በኮቪድ -19 ወረርሽን ወቅት የፍትሕ ተደራሽነት ላይ ትኩረት የሚያደርግ በሕግ ባለሞያዎች የተዘጋጀ የዌብነር ፕሮግራም የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ይተላለፋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር በሀሳብ አቅራቢነት የሚሳተፉ ሲሆን ሌሎች ስመ ጥር የሕግ ባለሞያዎችም የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ይህን ፕሮግራም ለመከታተል እንዲችሉ የሚከተለው ሊንከ በመክፈት እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል፡፡

https://us02web.zoom.us/webinar/register/WN_f70NDwuJTvqYU3eQ2iDMUg
ህብረተሰቡ የፊት ጭምብሎችን በማድረግ የጀመረዉን በጎ ተግባር በሌሎች ተግባራትም ሊያስቀጥል ይገባል
-----------------------------------------
የኮቪድ-19 ወርርሽን ለመከላከልና ስርጭቱን ለመቀነስ ያስችላሉ ተብሎ በመንግስት ከወጡ መመሪያዎች ዉስጥ አንዱና አስገዳጅ የሆነዉ ከቤት ዉጭ በማንኛዉም ቦታ የፊት ጭምብል የማድረግ መመሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ የታየ መልካም ተግባርና ጅምር መሆኑ ከሰሞኑ የታየ ክስተት ሲሆን ህብረተሰቡ አሁንም ሳይዘናጋ በመንግስት የወጡ ህጎችን፣ ደንቦችን እና መመሪያዎችን ጠንቅቆ በማወቅና በባለድርሻ አካላት የሚሰጡ ምክሮችን በመተግበር ከዚህ አስከፊና ህይዎትን ከሚቀጥፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ራሱንና ሌሎችን ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡
አዲስ የተሻሻለው የንግድ ሕግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቀ

___________________

ሰኔ 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከ1952 ጀምሮ በሥራ ላይ የዋለው እና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የንግድ ሕግ በአዲስ ተሻሽሎ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቋል፡፡

በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይሁን ይርጋን ስለጉዳዩ ባነጋገርንበት ወቅት እንደተናገሩት የንግድ ሕጉ በ1952 ከወጣ በኃላ ለግማሽ ምዕተ አመታት ሳይሻሻል የቆየ በመሆኑ አሁን ካለው ዘመናዊ የንግድ ሥርዓት ጋር አብሮ የማሄድ የሕግ ድንጋጌ ያሉት በመሆኑና በሌሎች ምክንያቶች የንግድ ሕጉን ማሻሻል አስፈልጓል ብለዋል፡፡

በ1952 ዓ.ም ጀምሮ የወጣው የንግድ ህግ ይዛቸው የነበሩት 5 መጸሐፍት ሲሆኑ መጽሐፍ 1 ስለ ንግድ ስራ፣ መጽሐፍ 2 ስለንግድ ማህበራት፣ መጽሐፍ 3 ስለማጓጓዣ እና ኢንሹራንስ፣ መጽሐፍ 4 ስለ ባንክና ተላላፊ ሰነዶች እና መጽሐፍ 5 ስለ ኪሳራ ህግ የተጻፉ ድንጋጌዎች መሆናቸውን ጠቁመው በተደረገው ጥናት መጸሐፍት 3 እና 4 የንግድ አካል ሳይሆኑ ራሳቸውን ችለው የፋይናስ አገልግሎት መድብል (code) እንዲሆኑ የተወሰነ መሆኑን እና መጽሐፍት 1፣ 2 እና 5 የንግድ ሕግ ተብሎ እንዲረቀቅ በተስጠው አቅጣጫ መሰረት ረቂቁ ተዘጋጂቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁን ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም የንግድ ሕጉን የማርቀቅ ሂደት ከ18 አመት በላይ የፈጀ መሆኑን ጠቁመው በማርቀቅ ሂደቱ ሲሳተፉ የነበሩ ባለሙያዎች፣ ድጋፍ ላደረጉ የተለያዩ አካላት እና ሂደቱን ለመሩት የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ FDRE Attorney General የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
አለዎች ስለ ዝግጅታች ሁለ አመሰግናለሁ
please send me short note on
• Legal writing
• Evidence and
• conflict of law
CCI_ለፌደሬሽን_ምክር_ቤት_ያቀረበው_የውሳኔ_ሃሳብ.pdf
3 MB
CCI ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ፡፡
Hi selam nwu? Adisun draft Commercial code, engikizegna tirkgum kaleh lakegne
አለ ሰላም ላንተ ይሁን!! እስቲ ይህን ነገር ፓስትልኝ? እድሌ ከሆነ ይገኝ ይሆናል proclamation № 44/2001 Amhara region: proc to control proliferation and miss use of small arms
የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ዳኛ የሆኑት ወዳጃችን ዳዊት በዛብህ በአማርኛ የተፃፌ የጁሪስፕሩደንስ መፅሀፍ ይኸው ሼር አድርገው
"መከላከል ከመታከም ይቀላል፣ ቤት መቆየት ሆስፒታል ከመተኛት ይሻላል፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርጎ መተንፈስ በማሽን ከመተንፈስ ይልቃል፣ ስለሆነም እነዚህን እንዲሁም ሌሎችን የመከላከያ መንገዶችን ሳንዘናጋ በመተግበር እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንጠብቅ።"
ዶ/ር ሊያ ታደሰ (የኢፌዲሪ የጤና ሚኒስትር)
@MoHE_News @MoHE_News
10ኛው የኢትዮጵያ ክልል 'ሲዳማ ክልል' !

የደቡብ ክልልና አዲሱ የሲዳማ ክልል በዛሬው ዕለት በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ፊት ቀርበው የስልጣን ርክክብ አካሂደዋል።

ውሳኔውን ተከትሎ ሲዳማ በሀገሪቱ 10ኛው ክልል የሚሆን ሲሆን ፥ የምክር ቤቱ አባላት ለሲዳማ ክልል ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia