አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
178:2016-2025-02-03-67a109eecb426.pdf
1.1 MB
ደንብ ቁጥር 178/2016 በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ
179:20176የሰው_ኃይል_ስምሪት_በልዩ_ሁኔታ_ለማመጣጠን.pdf
1.3 MB
179/2016 የሰው ኃይል ስምሪት በልዩ ሁኔታ ለማመጣጠን
180:2017-2025-02-03-67a10ad7ae7f6.pdf
992.3 KB
180/2017 የወንዞች ዳርቻ ልማት እና ብክለት መከላከል ደንብ
181_2017_ፕላን_ዝግጅት፣_አፈፃፀም፣_ክትትልና_ቁጥጥር_ደንብ_ማሻሻያ_ደንብ.pdf
668.2 KB
181/2017 ፕላን ዝግጅት፣አፈፃፀም፣ክትትልና ቁጥጥር ደንብ ማሻሻያ ደንብ
182_2017_የመንግስት_አገልግሎቶችን_በውል_በሶስተኛ_ወገን_ለማሠራት_የወጣ_ደንብ.pdf
852.8 KB
182/2017 የመንግስት አገልግሎቶችን በውል በሶስተኛ ወገን ለማሠራት የወጣ ደንብ
183_2017_የብስክሌት_መጋራት_አገልግሎት_እና_የብስክሌት_መስመር_አጠቃቀም_ደንብ.pdf
835.8 KB
183/2017 የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብ
184_2017_መደበኛ_ያልሆነ_የጎዳና_ላይ_ንግድን_ሥርዓት_ለማስያዝ_የወጣ_ደንብ.pdf
1.5 MB
184/2017 መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ
185:2017_በምሽት_የንግድ_እና_የትራንስፖርት_አገልግሎት_እንዲሰጥ_ለማድረግ_የወጣ_ደንብ.pdf
1.4 MB
185/2017 በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ.pdf
186:2017_የተርሚናል_አገልግሎት_አሰራርና_ቁጥጥር_ደንብ.pdf
1.6 MB
186/2017 የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ.pdf
#ፋይዳ

" ከግንቦት 18/2017 ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ግዴታ ነው " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፦
- የትምህርት መረጃ ድጋሜ ለመውሰድ፣ ለማጣራትና ለማረጋገጥ
- Official Transcript ለማስላክ
- ስም ላይ የፊደላት ግድፈትን ለማስተካከል
- True Copy ለማግኘት እና የድጋፍ ደብዳቤ ለማጸፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተገልጋይ ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የግዴታ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ አገልግሎቱ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ላይ የትምህርት መረጃ አገልግሎት ዘወትር በሥራ ቀናት እየሰጠን እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተገልጋዮች https://services.eaes.et ላይ ባሉበት ሆነው በማመልከት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

በተጨማሪም " በኢትዮ ፖስታ ወይም በተወካይ በኩል አገልግሎቱን ባሉበት ሆነው ማግኘት  ይችላሉ " ብሏል።

@tikvahethiopia
ድምፃዊ አስጌ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በወጣበት መግለጫ ድምፃዊዉም መግለጫ አውጥቷል

አስጉ:- የሀገር ካስማ ምስክር ነው!!..

በመጀመሪያ ደረጃ  ፣ ጽሑፌ ላይ "ሁሉም ሴቶች" የሚል የለም። ምንም አማርኛ አራተኛ ቋንቋዬ ቢሆንም "ሴቶች" ስል ከአንድ በላይ ፣ መሆናቸውን እንጂ "ሁሉም" ማለት እንዳይደለ ፣ ጠንቅቄ አውቃለሁ።

ሲቀጥል ፣ አታብድም እንጂ ፣ አታፈቅርም ፣ የሚል ፅሑፍም በየትኛውም የፊት ገጽ(ማህበራዊ ሚዲያ) ላይ አላጋራሁም።

እንዲያውም ፣ ለሴቶች ድምጽ ፣ መሆኔን ነው የማውቀው ፣  ዓለም ያልመሰከረላቸውን ፣ ጥንካሬ ነው የመሰከርኩላቸው።

ወንድ ልጅ ፣ ሴት ልጅ ፣ ጥላው ስለሄደች(ስለተከዳ) ብቻ ፣ ሰማይ የተዘጋበት ፣ ሊመስለው ይችላል ፣ አቅሉን ሊስት ፣ ሊያብድ እና ፣ ጨርቁን ጥሎ ፣ ጎዳና ሊወጣ ይችላል። ለዚህም ፣ እስከዛሬ ትመጣለች እያለ ፣ በተስፋ የሚጠብቀውን ፣ መንገድ ላይ ቆሞ ፣ መንገድ የጠፋውን ፣ እሷን ፍለጋ ራሱን ያጣውን ፣ ወንድማችንን ማየት በቂ ነው።

ሴቶች ጋር ግን ፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ፣ ዕምብዛም አይታይም። ይሄ ደግሞ ፣ ጥንካሬያቸውን እና ልዩ ፍጡር መሆናቸውን ፣ ነው የሚያሳየው። ከዚህ ተነስቼ ነው ፣ ሴት ልጅ ፣ በፍቅር አታብድም የምለው። ለምን አያብዱም ትለናለህ ፣ እናብዳለን ብላችሁ ፣ የምታብዱ ሴቶች ፣ እደግመዋለው አታብዱም ፤ እንድታብዱም አልፈልግም ፤ እኔ የልጄ(ሴት) አባት ፣ የእናቴ(ሴት) ልጅ ነኝ። ማበድም ደግሞ ፣ የፍቅርም የጀግንነትም ፣ መገለጫም አይደለም'ና ፣ የወሰድኩባችሁ ክሬዲት ካለም ፣ በይፋ መልሼአለሁ🙌 ፣ ይቅርታዬንም እነሆ።🙏🏽
 
ለሚመለከተው ግን ፣ አንድ ነገር ፣ ማለት ፈልጋለሁ፤

ተደፍረው የተገደሉ ፣ ሕፃናትን ፣ ዶሴ አቧራ ፣ ሳናራግፍ ፤💔🙌
📍📚አክሱም ላይ ፣ በሂጃብ ምክንያት ፣ ከትምህርት ገበታ ፣ ስለታገዱ ሴቶች ፣ ዝምታችንን ሳንሰብር ፤

📌በትግራይ ጦርነት ጊዜ ፣ ከ15 እስከ 49 ዓመት ዕድሜ ክልል ፣ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ፣ 10% የሚሆኑት ሲደፈሩ ፣ ያልነበርን ፣
(ለቀነኒ አዱኛ ወዳጆች እና ቤተሰብ መጽናናትን እመኛለሁ)💔🙌

"አታብዱም" ተባልን ተብሎ ፣ መግለጫ ማውጣት ፣ ከየት ተማርን ፣ እንዴት ቻልንበት ፣ ሞራሉንስ ከየት አገኘን ማለት እወዳለሁ።

ግና ግን ፣ ለሴት ልጅ ያለኝን ፣ ፍቅር'ና ክብር ፣ በልጄ : በእናቴ እና ፣ ዙሪያዬ ባሉ ፣ እንዲሁም ፣ በቅርበት ፣  በሚያውቁኝ ሴቶች ፣ ማየት ፣ ማረጋገጥ ፣ ይቻላል ፤ "የሀገር ካስማ" (ለሴቶች እኩልነት የተሰራ ሙዚቃ) ምስክሬ ነው።

በመጨረሻም ፣ በነፃ ሀሳባችን ፣ በአማርኛችን ፣ በመልካችን እና በመጣንበት አቅጣጫ ፣ ለማሸማቀቅ የሚደረገውን ፣ የትኛውንም ተግባር'ና እንቅስቃሴ እቃወማለሁ🙌 ፣ አመሰግናለሁ!!

አሁን ኑና እሰሩኝ::

ሴት በፍቅር አታብድም!!

Via አስጉ.✍️✍️✍️
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ማግኘት ያልቻሉበት ምክንያት ምንድነው ?

የጅቡቲ መንግስት ሰነድ አልባ ስደተኞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በፈቃዳቸው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካወጀ ሰነባብቷል፡፡ የተሰጠው ቀነገደብ በመጠናቀቁም መጠነ ሰፊ አፈሳ እንደሚጀምር አውጇል፡፡

በዚያች ሀገር የሚኖሩ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በበኩላቸው፣ ሀብት ንብረታችንን ሸጠን የምንወጣበት ጊዜ ይስጠን እያሉ ይማፀናሉ፡፡ ለዚህም ቀነገደቡ እንዲራመዝላቸው ይፈልጋሉ፡፡

ለመሆኑ እነዚህ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን (ቁጥራቸው በትንሹ ከ200 ሺህ በላይ ይገመታል) ለምን እስካሁን ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ መያዝ አልቻሉም፡፡

ይህን ጥያቄ ያነሳንላቸው ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሶስት ስደተኞች፣ ሕጋዊ ለመሆን ስላለው ሁኔታ የሚከተለውን ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡ 
  
ሕጋዊ ለመሆን ያለው ችግር ምንድነው ?

" ሁሉም ሰው ህጋዊ መሆን ይፈልጋል፡፡ ችግሩ የገንዘቡ መብዛት ነው፡፡ ሒደቱም ረጅም የድለላ ሰንሰለትን የሚያልፍ እና በእጅጉ ረዥም፣ አድካሚና ውስብስብ ነው፡፡ የአንድ ሰው የአመት ገቢ እንኳ አይበቃም፡፡

ህጋዊ ለመሆን ለጅቡቲ መንግስት የሚከፈለው ገንዘብ አንድ አመት ሙሉ ሰርቶ ማጠራቀም አይቻልም፡፡ የዚህ ሀገር ህጋዊ መሆኛ አሰራር ለድሀና ለስደተኛ የሚመጥን አይደለም፡፡ እንኳን ግለሰብ ቀርቶ፣ ድርጅቶችም አይችሉትም፡፡

የንግድ ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው ህጋዊ የስራ ፈቃድ ለማውጣት፣ እስከ 200 ሺህ ፍራንክ (160 ሺህ ብር ገደማ) ይጠየቃሉ፤ ለአንድ ሰራተኛ፡፡ ለግለሰብ ደግሞ እስከ 70 ሺህ ፍራንክ ይደርሳል በህጋዊው መንገድ፡፡ ግን አብዛኛውን ጊዜ ህጋዊው አካሔድ ስለማይገኝ በደላሎች በኩል እስከ 120 ሺህ ፍራንክ ትጠየቃለህ፡፡ አሁን በቅርቡ 120 ሺህ ፍራንክ ከፍለው ያወጡ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም ከ150 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ያስወጣሀል፡፡ ይህን ያህል ከፍለህ የምታገኘው የመኖሪያ ፈቃድ፣ ተሰጠህ ሳይሆን ገዛህ ነው ሊባል የሚችለው፡፡ አንዴ ከፍለህ የሚያበቃ ነገር ደግሞ አይደለም፡፡ በየአመቱ ከ 20 ሺህ እስከ 30 ሺህ ፍራንክ እየከፈልክ ታሳድሳለህ ፈቃድህን፡፡

እንደ ሌሎች ሀገራት ብዙ አመት ከቆየህ በኋላ ህጋዊ ነዋሪ አትሆንም፡፡ ሁሌም ጊዜያዊ ነዋሪ እየተባልክ በየአመቱ ፈቃድህን እያደስክ ትኖራለህ፡፡ የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ አይሰጡህም፡፡ ይህ ችግር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ፣ ሰነድ አልባ ሆኖ በስጋት ውስጥ እንዲኖር አስገድዶታል፡፡

ህጋዊ ሰነድ ለማግኘት ደግሞ ፓስፖርትህ ላይ ቪዛ መመታት አለበት ይሉሀል፡፡ ይህን ቪዛ ለማስመታት ከጅቡቲ ትወጣና እንደገና መግባት አለብህ፣ ቪዛ ለማግኘት የግድ ከጅቡቲ መውጣት አለብህ በየአመቱ፡፡ ተመልሰህ ስትገባ ኤርፖርት ቪዛ ይሰጠሀል፡፡ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋም ይመታልሀል፡፡ ግን ቅድመ ሁኔታው በጣም ብዙ ነው፣ አሰልቺም ጭምር፡፡ በዚህ መልኩ፣ ህጋዊ የመሆኛው ሒደት ውድና አድካሚ ነው፡፡ ምንም አይነት ግልፅ የሆነ ህጋዊ አሰራር የላቸውም፡፡     

ይህን የምታደርገው ደግሞ ፓስፖርት ካለህ ነው፡፡ ፓስፖርት ይዘን ነው፣ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የምትጠይቀው፡፡ የእኛ ኤምባሲ ፓስፖርት ለመስጠት 200 ዶላር ይጠይቃል፡፡ በጅቡቲ ፍራንክ ሳይሆን፣ በዶላር ክፈል ነው የምትባለው፡፡ ይህ ራሱ በጣም ብዙ ነው፡፡

ከአንድ አመት በፊት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመውሰድ ክፍያው ዝቅተኛ ነበር፡፡ 100 ዶላር፣ 150 ዶላር የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን በጣም ነው የጨመረው፡፡ አዲስ ፓስፖርት ተቀይሯል ተብሎ ነው የጨመረው፡፡ አንድ የጥበቃ ሰራተኛና አንዲት የቤት ሰራተኛ የሆኑ ስደተኞች የአንድ ወር ሙሉ ደመወዛቸው ለፓስፖርት ማውጫ አይበቃቸውም፡፡ ሙሉ ደመወዝ ለዚህ ብቻ ልታውለው አትችልም፡፡ መብላት መጠጣት መልበስ የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ 200 ዶላር ለመቆጠብ ጊዜ ይፈጃል፡፡ ሰዉ ደግሞ የተወሰነ አመት ሰርቶ፣ ገንዘብ አጠራቅሞ ወደ ሀገሩ መመለስ ነው እንጂ፣ ያገኛትን ገንዘብ ለመኖሪያ ፈቃድና ለፓስፖርት መጨረስ አይፈልግም፡፡

ስለዚህ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ያለው የፓስፖርት ክፍያ ቢቀንስ ጥሩ ነበር፡፡ እንደው 100 ዶላር እንኳን ቢያደርግልን፡፡ በሁሉም አቅጣጫ፣ ህጋዊ ሰነድ ማግኘት የምትችልበት ሁኔታ ነው መፈጠር ያለበት፡፡ ኤምባሲያችን ይህ ጉዳይ እንዲቀረፍ መስራት አለበት፡፡

የጅቡቲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃዱ ቀለል ባለ መንገድ እንዲገኝ ማድረግ አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ለዚህ ጫና ማድረግና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በደላሎች እየተበዘበዘ ያለውን ህዝብ ችግር ከግምት አስገብቶ መስራት አለበት፡፡ ሁሉም ሰው ህጋዊ መሆን ይፈልጋል፡፡ ስርዓቱ ለዚህ መመቸት አለበት ነው የምንለው፡፡ "

ስደተኞቹ ህጋዊ ሰነድ ለመያዝ ይገጥሙናል ስላሉዋቸው ችግሮች እንዲሁም የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት እስከ 200 ዶላር መክፈል አግባብ አይደለም በማለት ላቀረቡት ቅሬታ፣ በጅቡቲ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማብራሪያ ካገኘን እናቀርባለን፡፡  ሆኖም የፓስፖርት የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ በህገደንብ የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 520/2016 ላይ እንደተገለፀው፣ በውጭ ሀገራት በኤምባሲ በኩል የሚሰጥ ባለ 32 ገፅ መደበኛ ፓስፖርት የአገልግሎት ክፍያው 200 ዶላር መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በኦንላይንና በእድሳት ደግሞ 250 ዶላር እንደሚያስከፍል ይጠቅሳል ደንቡ፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" የተሽከርካሪ ታርጋ አይፈታም ክልክል ነው ፤ ደንቡም ላይ ተቀምጧል " - የመንገድ ደኅንነት እና መድን ፈንድ

➡️ " ተሳፋሪን ለማውረድ ክልክል የነበሩ ቦታዎች እየተፈቀዱ ነው ተጨማሪ ቦታዎችም እየታዩ ቅሬታ የሚነሳባቸው ቦታዎች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው ! "

ከነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ የዋለው " የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 557/2016 " ተግባራዊ ከሆነ ስምንት ወራት ተሻግሯል።

ነባሩ ደንብን በመተካት ተሻሽሎ የወጣው ደንብ የጥፋት እርከንን በሦስት በመክፈል የትራፊክ ቅጣቱንም ከ500 ብር እስከ 1,500 ብር ከፍ አድርጓል።

ደንቡ የከተማ የፍጥነት ወሰንን በ 50 ኪሜ በሰዓት ከመወሰኑ በተጨማሪ ፣ የራዳር መቆጣጠሪያ የሚያውኩ መሳሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስን ይከለክላል።

በተጨማሪም አደጋ አድርሰው በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ አሽከርካሪዎች የአደጋውን ምክንያት ለመመርመር ህይወታቸው ካለፈ በኋላም የደም ናሙና እንዲወሰድ የሚፈቅዱ አዳዲስ ጉዳዮችን አካቷል።

ደንቡ ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ " የቅጣት ገንዘቡ የተጋነነ ነው " የሚሉ ቅሬታዎችን ጨምሮ " ያለ አግባብ እየተቀጣን ነው " የሚሉ ቅሬታዎች በአሽከርካሪዎች ዘንድ ይሰማል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደንቡ ተግባራዊ ከሆነ ጀምሮ ውጤታማነቱ ተገምግሟል ወይ ? ስለሚነሱት ቅሬታዎችን ምን ምላሽ አላቹ ? ሲል የሚመለከተውን አካል ጠይቋል።

የመንገድ ደኅንነት እና መድን ፈንድ ህግ ትግበራ ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ ብርክቲ ባህሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" ደንቡ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ክልሎች እንዲደርሳቸው ተደርጓል ከደረሳቸውም በኋላ የማስተዋወቅ እና ምን ምን ተሻሻለ የሚለውን ነገር የማሳወቅ ስራ ሰርተናል።

ጀምረዋል አልጀመሩም የሚለውን አንድ ዙር ተገምግሟል አብዛኛው ክልል ጀምሯል ማለት ይቻላል አጀማመራቸው እኩል ባይሆንም።

' ቅጣቱ ተጋኗል ' የሚል ቅሬታ በሚመለከት ከዚህ በፊት የነበረው ቅጣት አስተማሪ አልነበረም በጣም አነስተኛ ነበር።

ዋናው አላማችን አደጋን መቀነስ ነው ቅጣቶቹ የተቀመጡት ከአደጋ አንጻር ነው።

ቢያንስ ግንዛቤ እየኖረው ነው ' ቅጣቱ ይሄን ያህል ነው ' የማለት የመጠንቀቅ ነገር አለ ለውጥ አለ።

ደረጃ አንድ፣ ሁለት ፣ ሦስት እና ልዩ ጥፋት እርከን ተብሎ ነው የተቀመጠው።

አሽከርካሪዎች ደጋግመው ሊያጠፏቸው ይችላሉ የተባሉትን ጥፋቶች ከመጠናቸውም አንጻር ታይቶ በአንደኛ ደረጃ የጥፋት እርከን ነው የተቀመጡት።

ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ከበድ ያለ አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ ተብለው የተለዩ ጥፋቶች ናቸው ቅጣታቸውም 1,500 ብር ነው።

' ተጋኗል ' የሚል ካለ የማያጠፋን አይመለከትውም ቅጣት የሚመለከተው አጥፊውን ብቻ ነው።

ስፒድ ሊሚተር የሚገጠምላቸው አሽከርካሪዎች አሉ ይህንን ሲፒድ ሊሚተር በትክክል እንዳያሳይ የሚያበላሽ አለ እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂዎችን የሚያሰናክሉ ካሉ የገጠሙት ነገር ይወረሳል ፣በወንጀልም ይጠየቃሉ ቅጣትም አለው።

ይህን አይነቱን ጥፋት የሚያጠፉ አሽከርካሪዎች እንዳሉ ከዚህ ቀደም በተሰሩ ጥናቶች በመታወቁ በደንቡ ላይ እንዲካተቱ ሆኗል።

ከዚህ ቀደም በነበረው ድንብ ላይ ጠጥቶ ወይም አደንዛዥ እጽ ተጠቅሞ አደጋ ያደረሰ እና ህይወቱ ያለፈ አሽከርካሪ ላይ ጠጥቶ ይሁን አይሁን ለማረጋገጥ የሚቻልበት መንገድ አያስቀምጥም ነበር።

በአሁኑ ደንብ አሽከርካሪው በህይወት ባይኖርም የደም ናሙና እንዲወሰድ ይፈቅዳል አተገባበሩ ላይ መመሪያ እየተዘጋጀ ነው።

ተሳፋሪን ለማውረድ ክልክል የነበሩ ቦታዎች እየተፈቀዱ ነው ተጨማሪ ቦታዎችም እየታዩ ቅሬታ የሚነሳባቸው ቦታዎች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገርን ነው።

ህጉ ገና መውጣቱ ነው ረዥም ጊዜው አይደለም መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ምን ላይ ነው ያለው ? የሚለውን ከሁሉም ክፍል የተወጣጣ ቡድን በስራ ላይ ነው።

ከዚህ ቀደም አሽከርካሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት ስለሚያጠፉ የትራፊክ ፖሊሶች ታርጋ ይፈቱ ነበር መንጃ ፈቃድም ይወስዱ ነበር።

አሁን ላይ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ይህንን የሚያስቀር መተግበሪያ አበልጽጓል።

ከዚህ በኋላ ሰሌዳ መፍታትም ሆነ መንጃ ፈቃድ መውሰድ ሳያስፈልግ አሽከርካሪን የሚቀጣበት አሰራር ነው።

ከዚህ በኋላ ታርጋ አይፈታም ክልክል ነው ደንቡም ላይ ተቀምጧል።

ሲስተሙ ይፋ ተደርጓል ወደ ተግባር እየገቡበት ነው ተሞክሮው ተወስዶ ወደ ክልሎችም የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል።

በህጉ መሰረት እንደማይፈቀድ ሁሉም ግንዛቤ እስከሚኖረው ድረስ ጊዜ ይጠይቃል ነገር ግን ታርጋ መፍታት አይፈቀድም " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም " የተሽከርካሪን ሰሌዳን መፍታት ክልክል ነው " የሚለው ህግ በተጨባጭ ለምን ተግባራዊ አልሆነም ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አቶ ክበበው ሚደቅሳ አቀርቦላቸው ነበር።

አቶ ክበበው " ሰሌዳ ቁጥሩ የሚፈታበት አጋጣሚ ይኖራል፣ እሱም የሚሆነው የቅጣት እግድ የደረሱ ከሆነ፣  መንጃ ፍቃዳቸው ላይ ያለው ስልክ ቁጥራቸው የማይሰራ ወይም የክፍለ ሀገር ከሆነ ይፈታል፣ ምክንያቱም አስገዳጅ ምክንያቶች ስለሆኑ በሂደት ግን የሁሉም ሰው አንዳይፈታ እናደርጋለን " ሲሉ መልሰው ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
143_2011_143_2011ለውጦችን_ስለማሳውቅ.pdf
1.2 MB
ውድ ግብር ከፋዮቻችን የታክስ እንቅስቃሴ ለውጥ ላይ ከሆነ በመመሪያ 143 /2011 መሰረት ለውጥ የተካሄደባቸውን እንቅስቃሴዎች ያሳውቁ
ማንኛውም ድርጅት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የመተዳደሪያ ደንብ፣ የሽርክና ማህበር ስምምነት ወይም ሌላ የመመስረቻ ወይም የምዝገባ ሰነድ ቅጂ ለባለሥልጣኑ መቅረብ አለበት፡፡ እነዚህ ሰነዶች ላይ ማንኛውም ለውጥ ሲደረግ ድርጅቱ ለውጡ በተደረገ በ30 ቀናት ውስጥ ለውጡን በጽሑፍ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ አለበት፡፡
ሀ. በንግድ ድርጅቱ ስያሜ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ለ. በድርጅቱ ስም የተመዘገበ፡-
i. ቋሚ የንግድ ሥራ፣ የቢሮ እና የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ፣
ii. በማምረቻ ቦታ ወይም ታክስ ከፋዩ በሚጠቀምበት መጋዘን ላይ የተደረገ የአድራሻ ለውጥ፤
iii. በፖስታ ወይም በመደበኛ እና በተንቀሳቃሽ ሰልክ፣ ፋክስ ወይም ኢ-ሜል አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ሐ. በዋነኛ የሥራ እንቅስቃሴው ወይም በቅርንጫፍ ወይም በንግድ ሥራው ዘርፍ ወይም መስክ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
መ. በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ ወይም የመመስረቻ ጽሑፍ ወይም የሽርክና ስምምነት ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ሠ. በአክሲዮን ባለድርሻ አባላት ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ረ. በድርጅቱ ወይም በታክስ እንደራሴው የባንክ ሂሳብ ወይም የባንክ ቅርንጫፍ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ሰ.በታክስ እንደራሴው እና ከሚኒስቴሩ ጋር ግንኙነት በሚያደርግበት የኤሌክትሮኒክስ አድራሻ ላይ የተደረገ ለውጥ፤
ሸ. በተመዘገበና በተከፈለ ካፒታል ላይ የተደረገ ለውጥ፤……………..
ሙሉን ለማግኘት ከላይ የተቀመጠውን መመሪያ ያንብቡ
እናመሰግናለን !!