አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.83K photos
25 videos
1.86K files
3.55K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
🔈 #የኢትዮጵያውያንድምጽ

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጋዊ መኖሪያ ማግኘት ያልቻሉበት ምክንያት ምንድነው ?

የጅቡቲ መንግስት ሰነድ አልባ ስደተኞች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በፈቃዳቸው ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ካወጀ ሰነባብቷል፡፡ የተሰጠው ቀነገደብ በመጠናቀቁም መጠነ ሰፊ አፈሳ እንደሚጀምር አውጇል፡፡

በዚያች ሀገር የሚኖሩ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በበኩላቸው፣ ሀብት ንብረታችንን ሸጠን የምንወጣበት ጊዜ ይስጠን እያሉ ይማፀናሉ፡፡ ለዚህም ቀነገደቡ እንዲራመዝላቸው ይፈልጋሉ፡፡

ለመሆኑ እነዚህ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን (ቁጥራቸው በትንሹ ከ200 ሺህ በላይ ይገመታል) ለምን እስካሁን ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ መያዝ አልቻሉም፡፡

ይህን ጥያቄ ያነሳንላቸው ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሶስት ስደተኞች፣ ሕጋዊ ለመሆን ስላለው ሁኔታ የሚከተለውን ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡ 
  
ሕጋዊ ለመሆን ያለው ችግር ምንድነው ?

" ሁሉም ሰው ህጋዊ መሆን ይፈልጋል፡፡ ችግሩ የገንዘቡ መብዛት ነው፡፡ ሒደቱም ረጅም የድለላ ሰንሰለትን የሚያልፍ እና በእጅጉ ረዥም፣ አድካሚና ውስብስብ ነው፡፡ የአንድ ሰው የአመት ገቢ እንኳ አይበቃም፡፡

ህጋዊ ለመሆን ለጅቡቲ መንግስት የሚከፈለው ገንዘብ አንድ አመት ሙሉ ሰርቶ ማጠራቀም አይቻልም፡፡ የዚህ ሀገር ህጋዊ መሆኛ አሰራር ለድሀና ለስደተኛ የሚመጥን አይደለም፡፡ እንኳን ግለሰብ ቀርቶ፣ ድርጅቶችም አይችሉትም፡፡

የንግድ ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው ህጋዊ የስራ ፈቃድ ለማውጣት፣ እስከ 200 ሺህ ፍራንክ (160 ሺህ ብር ገደማ) ይጠየቃሉ፤ ለአንድ ሰራተኛ፡፡ ለግለሰብ ደግሞ እስከ 70 ሺህ ፍራንክ ይደርሳል በህጋዊው መንገድ፡፡ ግን አብዛኛውን ጊዜ ህጋዊው አካሔድ ስለማይገኝ በደላሎች በኩል እስከ 120 ሺህ ፍራንክ ትጠየቃለህ፡፡ አሁን በቅርቡ 120 ሺህ ፍራንክ ከፍለው ያወጡ ሰዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም ከ150 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ያስወጣሀል፡፡ ይህን ያህል ከፍለህ የምታገኘው የመኖሪያ ፈቃድ፣ ተሰጠህ ሳይሆን ገዛህ ነው ሊባል የሚችለው፡፡ አንዴ ከፍለህ የሚያበቃ ነገር ደግሞ አይደለም፡፡ በየአመቱ ከ 20 ሺህ እስከ 30 ሺህ ፍራንክ እየከፈልክ ታሳድሳለህ ፈቃድህን፡፡

እንደ ሌሎች ሀገራት ብዙ አመት ከቆየህ በኋላ ህጋዊ ነዋሪ አትሆንም፡፡ ሁሌም ጊዜያዊ ነዋሪ እየተባልክ በየአመቱ ፈቃድህን እያደስክ ትኖራለህ፡፡ የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ አይሰጡህም፡፡ ይህ ችግር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ስደተኛ፣ ሰነድ አልባ ሆኖ በስጋት ውስጥ እንዲኖር አስገድዶታል፡፡

ህጋዊ ሰነድ ለማግኘት ደግሞ ፓስፖርትህ ላይ ቪዛ መመታት አለበት ይሉሀል፡፡ ይህን ቪዛ ለማስመታት ከጅቡቲ ትወጣና እንደገና መግባት አለብህ፣ ቪዛ ለማግኘት የግድ ከጅቡቲ መውጣት አለብህ በየአመቱ፡፡ ተመልሰህ ስትገባ ኤርፖርት ቪዛ ይሰጠሀል፡፡ አዲስ አበባ እና ድሬዳዋም ይመታልሀል፡፡ ግን ቅድመ ሁኔታው በጣም ብዙ ነው፣ አሰልቺም ጭምር፡፡ በዚህ መልኩ፣ ህጋዊ የመሆኛው ሒደት ውድና አድካሚ ነው፡፡ ምንም አይነት ግልፅ የሆነ ህጋዊ አሰራር የላቸውም፡፡     

ይህን የምታደርገው ደግሞ ፓስፖርት ካለህ ነው፡፡ ፓስፖርት ይዘን ነው፣ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የምትጠይቀው፡፡ የእኛ ኤምባሲ ፓስፖርት ለመስጠት 200 ዶላር ይጠይቃል፡፡ በጅቡቲ ፍራንክ ሳይሆን፣ በዶላር ክፈል ነው የምትባለው፡፡ ይህ ራሱ በጣም ብዙ ነው፡፡

ከአንድ አመት በፊት የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለመውሰድ ክፍያው ዝቅተኛ ነበር፡፡ 100 ዶላር፣ 150 ዶላር የነበረበት ወቅት ነበር፡፡ አሁን በጣም ነው የጨመረው፡፡ አዲስ ፓስፖርት ተቀይሯል ተብሎ ነው የጨመረው፡፡ አንድ የጥበቃ ሰራተኛና አንዲት የቤት ሰራተኛ የሆኑ ስደተኞች የአንድ ወር ሙሉ ደመወዛቸው ለፓስፖርት ማውጫ አይበቃቸውም፡፡ ሙሉ ደመወዝ ለዚህ ብቻ ልታውለው አትችልም፡፡ መብላት መጠጣት መልበስ የሚባሉ ነገሮች አሉ፡፡ 200 ዶላር ለመቆጠብ ጊዜ ይፈጃል፡፡ ሰዉ ደግሞ የተወሰነ አመት ሰርቶ፣ ገንዘብ አጠራቅሞ ወደ ሀገሩ መመለስ ነው እንጂ፣ ያገኛትን ገንዘብ ለመኖሪያ ፈቃድና ለፓስፖርት መጨረስ አይፈልግም፡፡

ስለዚህ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ያለው የፓስፖርት ክፍያ ቢቀንስ ጥሩ ነበር፡፡ እንደው 100 ዶላር እንኳን ቢያደርግልን፡፡ በሁሉም አቅጣጫ፣ ህጋዊ ሰነድ ማግኘት የምትችልበት ሁኔታ ነው መፈጠር ያለበት፡፡ ኤምባሲያችን ይህ ጉዳይ እንዲቀረፍ መስራት አለበት፡፡

የጅቡቲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃዱ ቀለል ባለ መንገድ እንዲገኝ ማድረግ አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ለዚህ ጫና ማድረግና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት በደላሎች እየተበዘበዘ ያለውን ህዝብ ችግር ከግምት አስገብቶ መስራት አለበት፡፡ ሁሉም ሰው ህጋዊ መሆን ይፈልጋል፡፡ ስርዓቱ ለዚህ መመቸት አለበት ነው የምንለው፡፡ "

ስደተኞቹ ህጋዊ ሰነድ ለመያዝ ይገጥሙናል ስላሉዋቸው ችግሮች እንዲሁም የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት እስከ 200 ዶላር መክፈል አግባብ አይደለም በማለት ላቀረቡት ቅሬታ፣ በጅቡቲ ካለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ማብራሪያ ካገኘን እናቀርባለን፡፡  ሆኖም የፓስፖርት የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ በህገደንብ የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 520/2016 ላይ እንደተገለፀው፣ በውጭ ሀገራት በኤምባሲ በኩል የሚሰጥ ባለ 32 ገፅ መደበኛ ፓስፖርት የአገልግሎት ክፍያው 200 ዶላር መሆኑን ተመልክተናል፡፡ በኦንላይንና በእድሳት ደግሞ 250 ዶላር እንደሚያስከፍል ይጠቅሳል ደንቡ፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM