አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
February 21
February 22
የጋራ ንብረት ምንነትና አስተዳደር
የጋራ ንብረትን በተመለከተ የጋራ ንብረት የሚባለው ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ በግብይት የሚያገኟቸው ንብረቶች፣ ባልና ሚስት በግል ጥረታቸው የሚገኝ ገቢ፣ ከግል እና ከጋራ ንብረታቸው የሚገኟቸው ገቢዎች ሁሉ ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በስጦታ ወይም በኑዛዜ በጋራ የተሰጧቸው ንብረቶች የጋራ ንብረቶች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር በአንደኛው ተጋቢ ስም የተመዘገበ ሀብትም ቢሆን እንኳን የተጋቢዎች የጋራ ሀብት እንደሆነ የህግ ግምት የሚወሰድበት መሆኑ ነው፡፡
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
February 23
18 ሺሕ 576 እግረኞች ተቀጡ! ልብ በሉ እግረኞች?
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ስድስት ወራት 18 ሺህ 576 የትራፊክ ደንብ የተላለፉ እግረኞች መቀጣታቸውን የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።

ከእነዚህ ውስጥ 7 ሺ 497 እግረኞች በገንዘብ ሲቀጡ 11 ሺ 79 ያህል ደንብ የተላለፉ እግረኞች ደግሞ በማህበራዊ አገልግሎት መቀጣታቸው ተሰምቷል።

ከቅጣት የተሰበሰበ ከ450 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ መደረጉም ተገልጿል።

በከተማዋ በተመረጡ እና የእግረኛ መሰረተ ልማት በተሟሉባቸው 22 ቦታዎች የትራፊክ ቁጥጥር መደረጉን የትራፊክ ቁጥጥር እና ትራፊክ አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አያሌው ኢቲሳ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ተግባራዊ የተደረገው የቅጣት አሰራር አሁን ላይ በእግረኞች ላይ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ከመቀነስ አንጻር ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል።

በከተማዋ ከሚደርሰው የትራፊክ አደጋ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው በእግረኞች ላይ የሚደርስ መሆኑን በጥናት መረጋገጡን አክለዋል።
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
February 25
112_2008_አንቀጽ_21_ንዑስ_አንቀጽ_3_ማሻሻያ.pdf
1.2 MB
ከጉምሩክ አሠራር ጋር በሚያጋጥሙ ጥፋቶች ላይ የሚወሰዱ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ወጥነት ባለው ሁኔታ በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲስተናገዱ መመሪያ ቁጥር 112/2008 ተደንግጓል ፡፡ ስለሆነም እነዚህን ጥፋቶች ላለመስረት ቅደመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደተጠበቀ ሆኖ ተከስተው ከተገኙ ደግሞ በመመሪያው መሰረት መስተናገድ ይገባል፡፡ በመመሪያውም በአዋጅ ቁጥር 859/2006 (እንደተሸሻለ 1160/2011) እንደተጠበቀ ሆኖ አስተዳደራዊ ቅጣት የሚያስከትሉ ጥፋቶች እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተዘርዝረዋል፡-
በወጪ እና ገቢ ዕቃዎች ላይ የተጣለ ገደብን አለማክበር
ቀረጥና ታክስ እንዳይከፈል ወይም አሳንሶ እንዲከፈል ማድረግ
ያለ ጉምሩክ ዕውቅና እሽጎችን መፍታትና ምልክቶችን ማንሳት
ናሙናዎችን አለመመለስ
ያጓጓዥ ግዴታዎችን ያለማክበር
የጉምሩክ መጋዘን ግዴታዎችን ያለማክበር
የጉምሩክ ትራንዚት ሥነ ሥርዓት አለማክበር
ከቀረጥ ነጻ የገባ ዕቃ ያለ አግባብ መገልገል
በጊዜአዊነት ወደ ሀገር የገባን ዕቃ ያለ አግባብ መገልገል
ሌሎች ጥፋቶች
February 25
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
February 26
180017-2025-02-03-67a10ad7ae7f6.pdf
992.3 KB
February 27
February 28
ደንብ_ቁጥር_178_2016_በሆቴልና_መሰል_አገልግሎት_ሰጪ_ተቋማት_ባለሙያዎች_የደንብ_ልብስ_አለባበስ.pdf
1 MB
February 28
ማስጠንቀቂያ :- 1ሚሊየን ብር ሊቀጡ ይችላሉ

አለማወቅ ከቅጣት አያድንም

👉 በባህሪው አደገኛ የሆነ ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ በወንዝ ዳርቻ ያሰወገደ ድርጅት አንድ ሚሊዮን ብር ይቀጣል፣

👉 ደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ወንዝ ላይ የጣለ ግለሰብ 500 ሺህ ብር ይቀጣል

👉 ፍቃድ የወሰዱም ሆነ ሳይወስዱ ፍሳሽን ቀጥታ በወንዞች ዳርቻ ሲያስወግዱ ቢገኙ 100 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣

👉 በወንዝ ዳርቻና አካባቢ መጸዳዳት ሁለት ሺህ፤

👉 የፈሳሽ ማጣሪያ ሳይኖር በወንዝ ዳርቻና አካባቢ ተሽከርካሪ ማጠብ 400ሺህ ብር፤

👉 እንስሳትን ማሰማራት፣ ማስገባት ከተፈቀደው ውጪ ተሽከርካሪ ማሽከርከር 30 ሺህ ብር

👉 ለመዝናኛ፣ ለመናፈሻና ለፖርክ ከተፈቀደ ውጪ ግንባታ መገንባት 200 ሺህ ብር፤

👉 ከአምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማንኛውም ያልታከመ ቆሻሻ መልቀቅ 300 ሺህ ብር ያስቀጣል፣

👉 ኬሚካል ነክ ቆሻሻዎችን የማከሚያ ዘዴ ሳይጠቀም የለቀቀ ግለሰብ 50 ሺህ፤ ድርጅት 300 ሺህ ብር ይቀጣሉ፣

👉 ማንኛውም በካይ ቆሻሻ ከተፈቀደ የፈሳሽ ማጠራቀሚያ ውጪ ያፈሰስ ግለስብ 50 ሺህ ድረጅት 400 ሺህ ብር፤

👉 የአትክልትና ፍራፍሬ ተረፈ ምርቶችን በወንዝ ዳርቻ ማስወገድ ግለሰብ 20 ሺህ፣ ድርጅት 100 ሺህ፤

👉 ዘይት፣ ጨዋማ ፈሳሽ፣የሞተር ዘይት፣ ነዳጅ ሳሙና ነክ ነገሮችን በወንዝ ዳርቻ ያስወገደ 400 ሺህ ብር ይቀጣል፣

👉 ማንኛውም ያልተጣራ ቆሻሻ ወደ ወንዝ መልቀቅ ግለሰብ 150 ሺህ ድርጀት 300 ሺህ ይቀጣል፣

👉 ፍቃድ ሳይሰጠው ያልታከመ ቆሻሻን ወደ ወንዝ ያስወገደ ግለሰብ 15 ሺህ ብር ድርጅት 40 ሺህ ብር ይቀጣል፣
የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ📱
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website 📱 alehig.com
https://linktr.ee/alehig
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
March 1
March 3
#Alehig #አለሕግ AleHig is currently in Nairobi, Kenya💎. Our local phone has not been working for a week, but you can reach us via WhatsApp +251920666595.
#africa #attorney #lawyerlife
East Africa Law Society
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
March 4
March 6