አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" 16.3 ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ! " - ICS

" ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ከ16.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስበናል። ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራም ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል " - ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት (የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር) #EPA

@tikvahethiopia
አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም  ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፒያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን  በቀን  አሽከሪከዎች ከ40 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት  ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ  በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች  ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣  ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና   ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና  አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአደራ የቲክቶክ አካውንታችሁን እንድናስተዳድር፣ የምትፈልጉትን ቪዲዮ ብቻ በመልቀቅ በአደራ እንዲቆይ የምትፈልጉ ልታዋሩን ትችላላችሁ።
#Share
በጃፓን ሀገር አንድ ለየት ያለ ሕግ አለ እሱም ሜታቦ ሕግ በመባል ይታወቃል፡፡
💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥
ይህ ሕግ ወፍራም መሆንን የሚከለክል ሲሆን በዚህ ሕግ መሰረት አንድ ዕድሜው ከ40 እስከ 74 የሆነ ወንድ ጃፓናዊ የወገቡ መጠን ዙሪያ ከ90 ሴንቲ ሜትር መብለጥ እንደሌለበት የተደነገገ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ለሴቶች ደግሞ ከ 85 ሴንቲ ሜትር በላይ እንዳይሆን ያስገድዳል፡፡

በዚህ መሠረት አንድ ጃፓናዊ የወገብ መጠኑ በሕግ ከተቀመጠው በላይ ከፍ ካለ የውፍረት መቀነሻ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርግ ወይም እንድታደርግ በሕግ የሚገደዱ ሲሆን በየዓመቱም የጃፓናውያን የወገባቸውን ልክ ማሳወቅ ግዴታ አለባቸው ሀገሪቱ ይህንን ሕግ ያረቀቀችው የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ ስትል እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

(Success Tax professional)
እርስዎ የሚያውቁት አስገራሚ ሕግ ካለ ቢያጋሩን!
Via Comedian Eshetu Melese

🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱
https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱Website: alehig.com

Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram: ✉️ @MikiasMelak

Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት

We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከማይንቀሳቀስ ንብረት ጋር በተያያዘ የመንደር ውል ህጋዊ የሚሆንባቸው 5/አምስት/ ሁኔታዎች 👉(Abraham Yohanes)

የማንይቀሳቀስ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በ ፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ካልተደረገ ተቀባይነት የለውም። ነገር ግን ከተወሰኑ የሰበር ችሎት ውሳኔዎች በመነሳት የመንደር ውል ህጋዊ ተብለው የሚቆጠሩበት ሁኔታዎች አሉ። እነዚህ 5 ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው።

❶ኛ የሽያጭ ውል መኖሩ ከታመነ ወይም ካልተካደ

ገዢ ውል እንዲፈፀምለት ክስ አቅርቦ ከሳሽ መከላከያ መልሱ ላይ በመካከላቸው ውል መኖሩን ካመነ ወይም ካልካደና በሌሎች ነጥቦች ላይ መልስ ከሰጠ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት አልተደረገም ብሎ ውድቅ ሊያደርገው አይችልም።

❷ኛ በማህበር በመደራጀት የተሰራ ቤት በሽያጭ ማስተላለፍ (ሰ/መ/ቁጥር 36294 ቅፅ 8)

በማህበር በመደራጀት እየተሰራ ያለ ቤት ቤቱ ተጠናቆ ካርታ እስኪወጣለት ድረስ የማህበሩ አባል የሆነ ሰው ይህን ቤት ቢያስተላልፍ ቤት የመስራት መብቱን ወይም እጣውን እንዳስተላለፈ እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረትን እንዳስተላለፈ አይቆጠርም። የማህበሩ አባል በስሙ ካርታና የባለቤትነት ማስረጃ እስካልተሰጠው ድረስ ቤቱ ወይም እየተሰራ ያለው ቤት በማህበሩ አጠቃላይ ይዞታ ስር የሚገኝ በመሆኑ የማህበሩ አባል ለ 3ኛ ወገን ሊያስተላልፍ የሚችለው እጣውን ወይም ጥቅሙን እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት አይደለም። እንዲህ አይነት ውሎች የግድ ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ሊረጋገጡ አይገባም።

❸ኛ ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (ሰ/መ/ቁጥር 32222 ቅፅ 7)

ብዙን ግዜ እንዲህ አይነት ውል ከ Real Estate ቤቶች ግንባታ ጋር የተያያ ነው። ምንም እንኳን ውላቸው ላይ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ቢሉም ዉሉ በሚደረግበት ግዜ ቤቱ ያልነበረ በመሆኑ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት ከአንዱ ወደ ሌላው ተላልፏል ሊባል አይችልም። ያልነበረን ቤት ሰርቶ ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል የግንባታ ውል እንጂ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ሊባል የሚችል ባለመሆኑ ውሉ በፍርድ ቤት ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት መረጋገጥ አይኖርበትም።

❹ኛ አዋዋይ ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች ለተወሰነ ግዜ ሳይፈፀምበት የቆየ የመንደር ውል (የሰ/መ/ቁጥር 36740 ቅጽ 8)

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ በሰጠው ውሳኔ መሠረት በግራ ቀኙ መሀከል የተደረገው የመንደር ውል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ ነገር ግን አስተዳደራዊ ወይም የፕሮቶኮል ጉዳዮች የተሟሉት የተወሰነ ግዜ ከቆየ በኋላ ቢሆንም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰው አካል ፊት ያልተደረገ ነው በሚል ውድቅ ሊደረግ አይገባም የሚል ነው።

ችሎቱ በዚህ መዝገብ ላይ እንዳለው ቤቱን የሚመለከቱ እዳና እገዳ ለማጣራትና ክፍያ ለመፈፀም የውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት በውል ላይ ማህተም ሣያሣርፍበትና የፕሮቶኮል ቁጥር ሰጥቶ ሣያረጋግጥበት የተወሰነ ጊዜ ያለፈ ቢሆንም እነዚህ አስተዳደራዊ ጉዳዮች እስኪከናወኑ ድረስ በውል ላይ ማህተም ሣያርፍበት መቆየቱ ወይም የፕሮቶኮል ቁጥር ሣይሰጠው መዘግየቱ ውል እንዳልተደረገ የሚያስቆጥረው ነው ለማለት አያስችልም፡፡

❺ኛ የሊዝ መብትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል (የሰ/መ/ቁጥር 191095 & 225796)

በሊዝ የተገኘ ይዞታ ላይ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ወይም ተጀምሮ በግማሽ ከመጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብት ዘመኑ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በቦተው የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ ይቻላል። ነገር ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ ግማሽ ግንባታ ከተከናወነ በኋላ ከሆነ በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ ከተሰራው ህንፃ ጭምር በመሆኑ የሊዝ መብት ማስተላለፍ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንደ ማስተላለፍ ይቆጠራል። ስለዚህ ሁለት ነገር መታየት ይኖርበታል። የመጀመሪያው አንድ ሰው መሬት በሊዝ ወስዶ ምንም አይነት ግንባታ ካልፈፀመበት ወይም ግንባታ ጀምሮ በግማሽ ከማጠናቀቁ በፊት የሊዝ መብቱን በመንደር ውል ማስተላለፍ ይችላል። ሁለተኛው የግንባታው ደረጃ ግማሽና ከዛ በላይ የደረሰ ከሆነ ግን የሚተላለፈው በቦታው ላይ የመጠቀም መብት ብቻ ሳይሆን በቦታው ላይ የተገነባውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ጭምር በመሆኑ ውሉ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ መረጋገጥ ይኖርበታል።
https://t.me/Law_issue
15 ሺህ 574 የጋብቻ ምዝገባ💎
3 ሺህ 769 ፍቺ ምዝገባ💎💎
ተከናውኗል 💎
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መራቆት ነውር ባልሆነባት ሀገር ሂጃብን መከልከል ያሳፍራል!💬⚠️⚠️⚠️

መከልከል የነበረበት መጥፎ ድርጊት ስንት ነበር?🔽⁉️🚫▶️🔖
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በማስታወቂያ አዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 17 ንዑስ አንቀፅ 4 መሰረት በአንድ ሰዓት የስርጭት ጊዜ ውስጥ የአንድን ምርት ወይም አገልግሎት ተመሳሳይ የንግድ ማስታወቂያ ከሁለት ጊዜ በላይ ማሰራጨት አይቻልም፡፡

*በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡