አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
<<ሊገባን ይገባል አሁን እየተፋፈርን ስለሆነ ነው እንጂ ማንም ኑሮን እየተቋቋመው (Afford) እያደረገ አይደለም፡፡ከሁለትና ሦስት ዓመት በፊት 10 እና 15 ሺህ ደመወዝ የሚያገኙት ሠራተኞች ጥሩ ነበሩ፡፡አሁን ግን 30 ሺህ እና 40 ሺህ ብር ደመወዝ የሚያገኙት ጥሩ ደረጃ ላይ ናቸው አልልም፡፡ የቤት ኪራይ:የትምህርት ቤት ክፍያው:የኑሮ ውድነት ሰማይ ወጥቷል::>>

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ
ለሪፖርተር ጋዜጣ ከሰጠው ቃለምልልስ የተወሰደ
የስራ_ማስታወቂያ_ዕጩ_ዳኛ_እና_ዐቃቤ_ሕግ.pdf
753 KB
ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፍትሕ ባለሙያዎች ማሠልጠኛና የሕግ ምርምር ኢንስቲትዩት በክልሉ ሥር በሚገኙ ወረዳዎች ዳኛ ወይም ዐቃቤ-ሕግ ሆኖ ለመሥራት ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ያወጣው ማስታወቂያ

ብዛት፡- 300
የመመዝገቢያ ጊዜ፡- ከታኅሳስ 30 እስከ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም
Losing a top performer will cost far more than retaining them.
Pay people what they're worth.
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ውሸት ለማናገር ቀላል ነች፣💎
እውነት ግን ለሚናገሩት ሆነ ለሚሰሙት ከባድ ነው
💎📸💎
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Asset Recovery draft proc. Amharic from COM to HPR.pdf
1.1 MB
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንብረት ማስመለስ አዋጅ

በወንጀልና በሙስና የተፈራ ንብረት የማስመለስ  አዋጅ ጸደቀ
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው14ኛ መደበኛ ስብሰባው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

አዋጁ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈራን ንብረት ማስመለስ የሚያስችሉና የሕግ-ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ድንጋጌዎችን የያዘ ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በረቂቅ አዋጁ የተደረጉ ማስተካከያዎችና የተጨመሩ አንቀጾችን አስመልክተው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በአዋጁ ላይ በአስረጅ፣ በህዝብና የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት ግብዓት እንደሰበሰበ ገልጸዋል።

የንብረት ማስመለስ አዋጅ የመንግስትና የህዝብ ንብረትን ለማስመለስ የነበረውን የሕግ ክፍተት የሚሞላ እንደሆነ አስረድተዋል።

አዋጁ ዜጎች በላባቸውና በወዛቸው ንብረት እንዲያፈሩ የሚያበረታታ፣ በወንጀል ንብረት የሚያፈሩትን ተጠያቂ የሚያደርግ፣ የአገርን ዕድገት የሚያሳልጥ እንደሆነ አስተያየት የሰጡ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል።

ግለሰቦች በወንጀልና በሙስና ያፈሩትን ንብረት የሚያስመልስ በመሆኑ በተፈጻሚነቱ ላይ ጥንቃቄ ማድረግና አስፈጻሚ አካላትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ እና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት እንዳይጋፋ መታየት አለባቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል።     

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዕጸገነት መንግስቱ በአዋጁ ሃብት የማፍራትና የማውረስ ሕገ-መንግስታዊ መብትን የሚቃረን ድንጋጌ አለመካተቱንም አብራርተዋል።

የጸረ-ሙስና ትግል እንዲጠናከር የሚያደርግ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘና የተመዘበረ የአገር ሃብትን ለማስመለስ የሚያስችልና ሕገ-ወጥነትን የሚያስቆም አዋጅ እንደሆነም ጨምረዋል።

ምክር ቤቱ በአዋጁ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ ዝርዝር ውይይት በማድረግ በ ሶሰት ተቃውሞ እና በአራት  ድምጸ  ታቅቦ  በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
https://www.alehig.com/federal-democratic-republic-of-ethiopia-property-recovery-proclamation-approved/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM