አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.89K photos
25 videos
1.87K files
3.59K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ከተሻሻለው የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጠር የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

ከፖሊስ በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የጉዳት አይነት የሚገልጽ የፅሁፍ ማስረጃ ሳይቀበሉ ጥገና የሚያከናውኑ ጋራዦች / የጋራዥ ባለቤቶች / በወንጀል ህግ የሚጠየቁት እንዳለ ሆኑ የ20 ሺህ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ያላደረገ የተሽከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ ያሽከረከረ ማንኛውም ሰው 5,000 ብር ይቀጣል።

  የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሳይኖረው ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም ሰው 7000 ብር ይቀጣል።

ከባለቤትነት ወይም በይዞታው የተያዘውን ተሽከርካሪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለሌላው ሰው አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም የተሸከርካሪ ባለንብረት 3,000 ብር ይቀጣል።

🚨የትራፊክ ግጭት ወይም ጉዳት አድርሶ በቦታው ላይ ያልቆመ ወይም ባደረሰው የትራፊክ ጉዳት የተጎዳውን እና ሕክምና የሚያስፈልገውን ሰው ወደ ህክምና በመውሰድ እንዲታከም ያላደረገ 👉 በወንጀል ህጉ መሰረት ይጠየቃል።

ወጣት አሽከርካሪዎች፣ ጀማሪ አሽከርካሪዎች ፣ ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ፣ የንግድ ተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች እና አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች የአልኮል መጠን በትንፋሽ በየትኛውም መጠን ከተገኘ 2,000 ብር ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ታግዶበት ሳለ ያሽከረከረ 3,000 ብር ቅጣት ይጣልበታል።

አልኮል መጠን በትንፋሽ ውስጥ ፦
🍻 0.24 እስከ 0.6 ሚሊግራም/ሊትር 1,500 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.61 እስከ 0.8 ሚሊግራም /ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 0.81 እስከ 1.0 ሚሊግራም/ሊትር 2,000 ብር ያስቀጣል።
🍻 1.0 ሚሊግራም/ሊትር በላይ የተገኘበት 3,000 ብር ይቀጣል።

በተሽከርካሪ ላይ ተገቢ ያልሆነ አካል የጨመረ ወይም ከተፈቀደለት ወንበር ውጭ ተጨማሪ ወንበር ወይም መቀመጫ የጨመረ የተሽከርካሪ ባለንብረት 400 ብር ይቀጣል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ሞተር እየሰራና በተሽከርካሪው ውስጥ መንገደኞች እያሉ ነዳጅ መሙላት 1,500 ብር ያስቅጣል።

ቴሌቪዥን ወይም ሌሎች ምስሎችን ተሽከርካሪ ውስጥ እየተመለከተ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የደህንነት ቀበቶ ሳያስር ወይም ተሳፋሪዎች የደህንነት ቀበቶ ማሰራቸውን ሳያረጋግጥ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተንቀሳቃሽ ስልክ በእጁ ይዞ እያነጋገረ፣ ወይም መልዕክት እየጻፈ እየላከ ወይም እያነበበ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ጫት ቅሞ ወይም እየቃመ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

የተሽከርካሪ የፊት ወይም የኃላ ሰሌዳ ሳይኖረው ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ለአውቶብስ ብቻ ተብሎ በተለየ መንገድ ላይ ያሽከረከረ 1,500 ብር ይቀጣል።

ቀይ መብራት የጣሰ 1,500 ብር ይቀጣል።

የትራፊክ ተቆጣጣሪ ትዕዛዝ ያልፈጸመ፣ ወይም የተሳሳተ መረጃ የሰጠ ወይም እንዲቆም ሲታዘዝ በእንቢተኝነት ሳይቆም የሄደ 1,000 ብር ይቀጣል።

የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ኖሮት ሳይዝ ያሽከረከረ ወይም የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዱን ሳያሳድስ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከተፈቀደው ፍጥናት በታች ያሽከረከረ ወይም የቀኙን ጠርዝ ሳይዝ በዝግታ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

ከመጠን በላይ ድምጽ እያሰማ ወይም የጆሮ ማዳመጫ እያዳመጠ ያሽከረከረ 1,000 ብር ይቀጣል።

መንገድ ላይ ያለን ውሃ በተሽከርካሪው አማካኝነት እግረኛ ላይ እንዲረጭ ያደረገ 1,000 ብር ይቀጣል።

(ተጨማሪ የጥፋት ዝርዝር እና ቅጣቶቹን ከላይ ያንብቡ)
#tikvahethiopia
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 12
ምክር ቤቱ በሙስና የተጠረጠሩ ሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞችን አሰናበተ🚫🚫▶️🔴🚨
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው የሁለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የስንብት ውሳኔን አጽድቋል፡፡

የስንብት ውሳኔውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እጸ-ገነት መንግስቱ አቅርበዋል፡፡

ዳኛ አዱኛ ነጋሳ እና ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የተጣለባቸውን ሕዝባዊ ኃላፊነት ባለመወጣት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት መፈጸማቸውን ወ/ሮ እጸ-ገነት አብራርተዋል፡፡

የተሰጣቸውን ሹመት አላግባብ በመጠቀም፣ ዳኛ አዱኛ ነጋሳ ገንዘብ እና ቼክ በመቀበል ፤ ዳኛ አክሊሉ ዘሪሁን የአስር ሚሊዮን ብር ቼክ በመቀበል ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት መፈጸማቸውን ሰብሳቢዋ ጠቅሰዋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ ቋሚ ኮሚቴው ከፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጋር በጥልቀት እንደመከረበት ወ/ሮ እጸ-ገነት ተናግረው ፣ ውሳኔውን ምክር ቤቱ እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፡፡

ውሳኔውን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት አስተያየቶችን የሰነዘሩ ሲሆን፣ “ቅጣቱ አስተማሪ አይደለም፤ አስተማሪ የሕግ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል ፤ ወደ መረጠን ሕዝብ ስንሄድ አገልግሎት እና ፍትህ የምናገኘው በገንዘብ ነው ስለሚሉን ውሳኔው ተገቢ ነው” ብለዋል፡፡

በአንጻሩ፣ “ቋሚ ኮሚቴው ዳኞቹ ከመሰናበታቸው አስቀድሞ የፌዴራሉን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማዳመጥ ይገባዋል፤ የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤን ውሳኔ እንደ ምስክር ተጠቅሞ ዳኞችን ከስራ ማሰናበት የዳኞቹን መብት ይጋፋል” የሚሉ አስተያየቶች ቀርበዋል፡፡

በተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ከቀረበ በኋላ ውሳኔው ውሳኔው ውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 5/2017 ሆኖ በሁለት ድምጸ-ተኣቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡(ፓርላማ)
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 14
አከራካሪ የነበረው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ📊
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 15ኛ መደበኛ ጉባዔው የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል፡፡
💠
🛎💎
በጉባኤው ላይ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)፣ እንደ ሀገር በሪፎርሙ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል ገቢ መሰብሰብ አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ኢኮኖሚው ከሚመነጨው ሀብት ገቢ ለመሰብሰብ ረቂቅ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ታክስ የሚሰበሰብበት መሰረት መስፋት ስላለበት ረቂቅ አዋጁ ታክስ ለመሰብሰብ ወሳኝ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ  የቋሚ ኮቴውን  ሪፖርትና የውሳኔ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸውም፣ ረቂቅ አዋጁ ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ገቢ በመሰብሰብ ለመሰረተ-ልማቶች እና ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለማዋል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አቶ ደሳለኝ አብራርተዋል፡፡

አዋጁ በሌሎች አፍሪካ ሀገራት ስራ ላይ ከዋለ ከ 30 ዓመታት በላይ እንደሆነው ያወሱት አቶ ደሳለኝ፤ ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ሆኖ ወደ ስራ ሲገባ የሚፈለገውን ገቢ በመሰብሰብ የመሰረተ-ልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ረቂቅ አዋጁን  አስመልክቶ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት ሪፖርቱን እና የውሳኔ ሃሳቡን በመቃዎም አስተያየት እና ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የህዝቡን የኑሮ ደረጃ እና  የገቢ ምንጭን  ያላገናዘበ፣ ለታክስ ከፋዩ ተደራራቢ ጫና የሚፈጥር፣ ቋሚ ኮሚቴው ለታክስ ከፋዩ ሳይሆን ለታክስ አስከፋዩ ውግንና ያሳየበትን የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቡን ጠይቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በበኩላቸው፣ ረቂቅ አዋጁ በሕዝቡ ላይ የተጋነነ ጫና እንደማይፈጥር እና ከታክስ የሚገኘው ገቢም ተመልሶ ህዝቡን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ነው ያብራሩት፡፡

በመጨረሻም፣ ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1365/2017 አድርጎ በአራት ተቃውሞ፣ በአስር ድምጸ-ተዓቅቦ እና በአብላጭ ድምጽ አጽድቆታል።
ምክር ቤቱ ( ዜና ፓርላማ ) ጥር 06፣ 2017 ዓ.ም.፤
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 14
" 16.3 ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ! " - ICS

" ባለፋት ስድስት ወራት 10 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅደን ከ16.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስበናል። ከ721 ሺህ 623 በላይ ፓስፖርቶችን የማተም ስራም ተሰርቷል። ከታተመው 98 በመቶው ለተገልጋዮች ተሰጥቷል " - ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት (የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር) #EPA

@tikvahethiopia
January 15
በኢትዮጵያ በተደረጉ ጥናቶች ለታካሚዎች ከሚታዘዙ 100 መድኃኒቶች ውስጥ 48ቱ ከበሽታው ጋር ተያያዥነት የሌላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️

"እስከ መውለጃ ሰዓቴ ድረስ ልጄ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ተነግሮኝ ነበር"

የሕክምና ስህተት ተጎጂ እናት


ሦስተኛ ልጄን ስወልድ ባጋጠመኝ የሕክምና ስህተት እኔ እና ቤተሰቦቼ የሥነ-ልቦና ጫና ደርሶብናል ስትል በሕክምና ስህተት ልጇ የተጎዳችባት እናት ወ/ሮ ሶስና ይርጋ ትናገራለች፡፡

ጤናማ የሆነ የእርግዝና ጊዜ አሳልፋ እንደነበር የምትገልፀው ወ/ሮ ሶስና፤ ልትወልድ 72 ሰዓት ሲቀር በልጇ አንገት ላይ እትብት መጠምጠሙን እና የከፋ ጉዳት እንደማያደርስ ከሕክምና ባለሙያዎች እንደተነገራት ታስረዳለች፡፡

"ከወሊድ በኋላም ነገሮች ልክ መሆናቸው ስለተነገረን ወደ ቤት አመራን" የምትለው ወላጅ እናት፣ ከቀናት በኋላ ግን  ልጇ ላይ ለየት ያሉ ባህሪዎችን ማስተዋል መጀመሯን ትገልጻለች፡፡

ይህንንም ተከትሎ  ወደ ጤና ተቋም ያመራችው እናት፣ በመውለጃዋ ወቅት ልጇ አንገት ላይ ተጠምጥሞ የነበረው እትብት የልጇ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ማድረሱን ከሕክምና ባለሞያዎች እንደተነገራት በመግለጽ የገጠማትን የሕክምና ስህተት ታስረዳለች፡፡

ችግሩ በጊዜው ስላልተነገረኝ እና ልጄ አስፈላጊው የሕክምና እገዛ በወቅቱ ስላልተደረገላት በአዕምሮዋ ላይ በደረሰው ችግር ምክንያት መንቀሳቀስ እና እኩዮቿ የሚያደርጉትን መፈጸም እንዳትችል ሆናለች ስትል ነው ወ/ሮ ሶስና የምትገልጸው።

ልጇን በማሳደግ ሂደት ውስጥ እያሳለፈች ስላለው ከባድ ጊዜ እና የሥነ-ልቦና ጫና በመግለጽ፤ የሕክምና ስህተት በሚፈፅሙ የጤና ባለሙያዎች ላይ አስተማሪ እና ጠንካራ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቃለች፡፡

የኢቲቪ አዲስ ቀን ፕሮግራም በ‘የሀገር ጉዳይ’ መሰናዶው የሕክምና ስህተትን እና ተጠያቂነቱን ተመልክቶታል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ የሆኑት አቶ ጳውሎስ ተሰማ፤ የሕክምና ስህተት በእውቀት ማነስ ወይም በቸልተኝነት ሊፈጠር እንደሚችል ይገልጻሉ፡፡

በኢትዮጵያ ስህተቱን የሚፈፅሙ ባለሙያዎችን ተጠያቂ ለማድረግ የተፈጸመውን ስህተቱን የሚያረጋግጡ ገለልተኛ ተቋማት አለመኖራቸውን ያነሳሉ፡፡

ይህም ጥፋተኞችን ተጠያቂ በማድረግ አስተማሪ እና የማያዳግም እርምጃ እንዳይወሰድ እክል መሆኑን ነው የገለፁት፡፡

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የሕክምና ስህተት በቴክኖሎጂ እና  የዘመነ የአሰራር ሥርዓትን ባልተገበሩ ሀገራት ላይ ትልቅ ችግር መሆኑን ያነሳሉ።

የሕክምና ባለሙያዎች ለሞያ መርሃቸው የሚገዙ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው ሊሆኑ ይገባል የሚሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ባለሙያዎች ብቃታቸውን ከጊዜው ጋር ማሳደግ እንደሚገባቸው ይገልጻሉ።

ከሕክምና ስህተት ተጠያቂነት ጋር ተያይዞ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ከፌደራል ባሻገር በክልሎችም ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አስቀምጠዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሕክምና ስህተት ጋር በተያያዘ የጀመረውን ከአገልግሎት ማገድ እስከ ሕጋዊ እርምጃ ያሉ ውሳኔዎችን ከፍትሕ አካላት ጋር በመተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተደረጉ ጥናቶች ለታካሚዎች ከሚታዘዙ 100 መድኃኒቶች ውስጥ 48ቱ ከበሽታው ጋር ተያያዥነት የሌላቸው እንደሆኑ ተመላክቷል፡፡

በአማካኝ በ1 ሺህ ቀናት ውስጥ 433 የሚሆኑ የሕክምና ስህተቶች እንደሚከሰቱ ተገልጿል፡፡

በሀገሪቱ ከሚደረጉ የቀዶ ጥገናዎች መካከል 22 በመቶ የሚሆኑት የሕክምና ስህተት እንደሚገጥማቸውም ነው የተመላከተው፡፡

ለዚህም ዋና ምክንያቶች የሕክምና ባለሙያዎች እና የታካሚ ቁጥር ያለመመጣጠን የሚፈጥረው ጫና፣ የሕክምና ግብዓቶች ያለመሟላት፣ የሕክምና የአሰራር ሥርዓቶችን ያለመጠበቅ፣ ለሕክምና ባለሙያዎች ወቅታዊ የሆነ ስልጠና ያለመስጠት እና የባለሙያዎች ቸልተኝነት እና መሰል ተግባራት መሆናቸው በዝርዝር ይቀመጣል፡፡

በአፎሚያ ክበበው
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 15
አሽከርካሪዎች በቀን እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ እንደሚከፍሉ በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ

ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአዲስ አበባ ኮሪደሮች ላይ የሚጠየቀው የመኪና ማቆሚያ ዋጋ የሕብረተሰቡን አቅም  ያላገናዘበ እንደሆነ ጥናት ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጥናት በፒያሳ ፣ በቦሌ ፣ በአራት ኪሎ ያሉ አራት የኮሪደር መንገዶችን ላይ ባሉ የመኪና ማቆሚያዎች ላይ ትኩረት የተደረገ ሲሆን  በቀን  አሽከሪከዎች ከ40 እስከ 140 ብር ድረስ ለመኪና ማቆሚያ ወጪ እንደሚያደርጉ ተመላክቷል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ በቀን ለመኪና ማቆሚያ የማያወጡት ብር አቅማቸውን ያላገናዘበ እንደሆነ ተናግረዋል።

አንድ ወር የፈጀው ጥናት በእነዚህ ኮሪደር መንገዶች የእግረኛም ሆነ የመኪና ፍሰቱ ቀልጣፋ መሆኑን ከ400 የጥናቱ ተሳታፊዎች 65 በመቶ የሚሆኑት የገለጹ ቢሆንም የመንገድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና የመኪና መጨናነቅን ቀንሷል ብሎ ቢያመላክትም ከንግድ ሱቆችና ከመኖሪያ ቤቶች መፍረስ እግረኛንም ሆነ የመኪናን ቁጥር ከመቀነሳቸው ጋር ያያያዘው ነገር የለም ተብሏል፡፡

ጥናቱን ያጠኑት ሻካ አናላይቲክስ ከ አለም አቀፍ የቢዝነስ ልማት  ጋር በመተባበር ሲሆን የቢዝነስ ልማቱ  በኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ አሰፋ " ጥናቱ ያተኮረባቸው ኮሪደሮች  ከፒያሳ አራት ኪሎ ፣ ከአራት ኪሎ እንግሊዝ ኤንባሲ ፣  ከአራት ኪሎ ቦሌ ድልድይና   ከሜክሲኮ ሳርቤት እንደሆነና  አጠቃላይ ጥናቱ አንድ ወር ፈጅቷል" ማለታቸው ተገልጿል፡፡
January 17
January 17
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር ሕገ ወጥ ነው በሚል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወሰነ

ℹ️
‼️‼️‼️‼️✔️✔️🔼🔼🔼
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱን አስታዉሶ ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ዛሬ ጥር 9ቀን  2017 ዓ.ም.ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ 3ቀን 2015 ዓ.ም የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ወስኖልኛል ሲል በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል::💎
🔴Attorney and Legal Consultant
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ

We are delighted to connect with you! You can easily reach us through the following platforms to stay informed and access our legal services:

Website & Social Media
Linktree:📱📱📱📱📱📱📱📱  

              https://linktr.ee/alehig

📱Facebook:
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

📱Telegram Channel:⭐️
https://t.me/AleHig

🌐 📱📱📱📱Website: alehig.com


Direct Contact🔈⬇️✉️

📱WhatsApp: ✉️ +251920666595
📱Telegram:  ✉️ @MikiasMelak


Our Commitment
alehig.com
📊አለሕግ🔽
🔠🔠🔠    🔠🔠🔠
Alternative Legal Enlightenment & Services
🔼⭐️
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት


We provide expert legal advice, support, and resources on various laws, proclamations, regulations, and directives to empower and guide you.

Feel free to reach out anytime‼️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
January 17
January 17
በአደራ የቲክቶክ አካውንታችሁን እንድናስተዳድር፣ የምትፈልጉትን ቪዲዮ ብቻ በመልቀቅ በአደራ እንዲቆይ የምትፈልጉ ልታዋሩን ትችላላችሁ።
#Share
January 19