አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የፐርፐዝ ብላክ አክስዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ 12 የማኅበሩ አመራሮች በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰሱ


የፐርፐዝ ብላክ አክስዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት ፍስሀ እሸቱ (ዶ/ር) ጨምሮ 12 የማኅበሩ አመራሮች በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ተከሰሱ፡፡

ከተከሳሾቹ መካካል ፍስሀን እሸቱ (ዶ/ር) ጨምሮ ምክትላቸው ኤርሚያስ ብርሃኑ (ዶ/ር)፣ ወይዘሮ ኤፍራታ (ሶፊያ/)፣ ነጋሽ ደስታ፣ ተፈራ ኃይሉ፣ ሚሊዮን ስዩም፣ ናኦሊ ዳዲ፣ ብርሀኑ ወልዴ እና ዋስይሁን ዋጋው የተባሉት አመራረሮች ይገኙበታል፡፡

ባልተጨበጠ መንገድ መሀል ሜክሲኮ ላይ በ1.5 ሚሊዮን ብር የቤት ባለቤት እናደርጋለን የሚለውን ማስታወቂያ አነበበ የተባለው ታደለ ሠይፉ እንዲሁም ትንሣኤ ተስፋዬ፣ ራሱ ፐርፐዝ ብላክ እና ኖቶር ዲዛይን የተሰኙ ድርጅቶች በክስ መዝገቡ ተካትተዋል፡፡

በፍትህ ሚኒስቴር የሙሰና ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት የክስ መዝገብ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ፐርፐዝ ብላክ የተሰኘው አክሲዮን ማኅበር አንድ ብሎ ሲቋቋም የግብርና ሥራዎች እና አግሮ ፕሮሰሲንግ አክሲዮን ሽያጭ ለማከናወን ነበር፡፡

በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ እያለ ከ 2013-2015 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት 280 ሚሊዮን ብር ገደማ ከስሮ ባልተገባ መንገድ ጎዶሎውን ሞልቶ ለመጠቀም ተከሳሾቹ የተከሰሱበትን ወንጀል መፈጸማቸውን በክስ መዝገቡ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በዚህም መሀል ሜክሲኮ ሰንጋተራ በአስራ አምስት ቀን ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ብር ለሚከፍሉ ቤት እናስረክባለን በማለት አማላይ ማስታወቂያ በመገናኛ ብዙሀን በማሰራጨት ከ1 ሺህ 245 ግለሰቦች ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ አታልለው ወስደዋል በሚል ዐቃቤ ሕግ በከባድ አታላይነት የሙስና ወንጀል ከስሷቸዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ በአጠቃላይ ሰባት የሙስና ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ የሙስና ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ተነብቦላቸዋል፡፡

ችሎቱ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመቀበልና ያልተገኙትን ፖሊስ እንዲያርባቸው ለጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።
በጥላሁን ካሳ
#EBC

Stay Connected with #AleHig!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://linktr.ee/alehig

Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

official website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
👍16
1👍1
ስትወሰልት ያገኛት ሚስቱን ያጋለጠው ባል የስድስት ወራት እስር ተፈረደበት

ባልየው ሚስቱን እጅ ከፍንጅ ከያዘ በኋላ ከውሽማዋ ጋር በመደራደር ገንዘብ ተቀብሏል ተብሏል

በሚስቱ ክስ የተመሰረተበት ባልም የተላለፈበትን የስድስት ወራት እስር ይግባኝ ቢልም እስከ መጨረሻው ያለው ፍርድ ቤት ውኔውን አጽንቷል

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/48h4mKT
👍11🌚62👎2👏1
ሐሰተኛ የባንክ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍተው የሚያጭበረብሩት ሌቦች

አጭበርባሪዎቹ ለ10 ቀናት ህጋዊ ተቋም መስለው ቅርንጫፍ ከፍተው ሰዎችን ሲያታልሉ ነበር ተብሏል

ፖሊስ አጭበርባሪዎቹን እያደነ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ ስለመያዛቸው አልተገለጸም

ተጨማሪ ያንብቡ https://bit.ly/3NuYCni


Stay Connected with #AleHig!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://linktr.ee/alehig

Telegram
https://t.me/AleHig

Telegram_Group
https://t.me/AleHig_Group

Facebook Page
https://www.facebook.com/AlehigOfficial/

LinkedIn
https://www.linkedin.com/company/alehig/

YouTube
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

TikTok
https://www.tiktok.com/@alehigofficial

Instagram https://www.instagram.com/alehigofficial

Twitter /X
https://x.com/AlehigOfficial?t=yFRauAZ7v70Je2MEPIGGsQ&s=09

Website
https://www.alehig.com

#LegalAwareness #AleHig #LegalUpdates #AccessToJustice
👍10😁63😱3
Forwarded from ስለፍትሕ (Licensed Lawyer Mikias Melak 🔊 ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ)
"ባለቤትሽ ጋር ለምን አልመለስም አልሽ በማለት በባለቤቷ ህዝብ ፊት እንድትገረፍ የተወሰነባት የልጆች እናት"

ጉዳዩ እንዲህ ነው። ወ/ሮ ኩሹ ቦናያ ምስራቅ ቦረና ዞን ዋጪሌ ወረዳ ቃቀሎ ቀበሌ ነዋሪ ናት። ወ/ሮ ኩሹ ከአቶ ገልገሎ ዋሪዮ ጋር ትዳር ከመሰረቱ 12 አመታት አስቆጥሯል ሶስት ልጆም ወልዷል።

ፋስት መረጃ ከቤተሰብ የደረሰው መረጃ ወ/ሮ ኩሹ ሶስተኛ ልጃቸውን ነፍስጡር ሆነው ባለቤታቸው የሀገር መከላከያ ተቀላቅለው ለግዳጅ 4 አመት ሌላ ቦታ ቆይቷል።

አራት አመታትን ሶስት ልጆችን ብቻቸውን ያሳደጉት ወ/ሮ ኩሹ ከአራት አመታት በኋላ ባለቤታቸው ከመከላከያ ተሸኝቶ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ጉዳዩን ለፋስት መረጃ ያስረዱት የቤተሰብ አባል አቶ ገለግሎ ሲመለሱ የተለያዩ ሱሶችን ስለለመዱ ትዳሩ እንደቀድሞ ሰላማዊ ሊሆን አልቻለም ጭቅጭቅ እና ግጭት ተከሰተ ይላሉ።

ወ/ሮ ኩሹ ትዳራቸው እንዳይፈርስ በተደጋጋሚ በሽማግሌ ብታስመክርም ባለቤቷ ሊስተካከል ስላልቻለ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ወደ ቤተሰቦቿ ትሄዳለች።

ይህን ጊዜ ባል ሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ ወደ ቤቷ እንድትመለስ ያስጠይቃል፣ ወ/ሮ ኩሹ የእኔ ጉዳት አልታየም በፍፁም አልመስም በማለት የሽማግሌዎቹን ጥያቄ ውድቅ ታደርጋለች።

ሽማግሌዎቹም የምንልሽን ስሜ ቶሎ ወደ ቤትሽ ተመለሺ ካልሆነ ቅጣት እንጥልብሻለን በማለት ሲያጠነቅቋት እንደቆዩ ተበዳይ ትናገራለች።

በእምቢታ የፀናችው ወ/ሮ ኩሹ በሽማግሌዎቹ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎባት በገመድ ከግንድ ጋር ታስራ በልጆቿ እና በህዝብ ፊት በባለቤቷ እንድትገረፍ ተደረገ።


ስትገረፍ የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ህዝቡ ቁጣውን መግለፅ ጀመረ። (ቪዲዮ በቴሌግራም ገፃችን ላይ ይገኛል)።

ይህን ውሳኔ አስተላልፏል የተባሉት ሽማግሌዎች ጃርሶ ቦሩ፣ ገልገሎ ጃተኒ፣ ዲዳ ዋሌ፣ ዲዳ ጃተኒ፣ አለካ ጃርሶ፣ ባርጪ ኢያ፣ ዲባ ጎሊቻ የተባሉ ሲሆኑ ፋስት መረጃ በደረሰው መረጃ እነዚህ ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች 5 ቀን ታስረው በዋስትና መለቀቃቸውን ሰምተናል።
https://t.me/AboutJustices
👍19💔42🤔2
የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር 'በክልሉ እየተፈጸመ የሚገኘው የዳኞች እስር' እንዲቆም  ጠየቀ፤ 8 ዳኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

በአማራ ክልል ውስጥ "ዳኞችን ያለአግባብ ማሰር እና ማዋከብ የተለመደ እና ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ ደግሞ ተባብሶ የቀጠለና ሞትንም እስከማስከተል የደረሰ ሆኗል" ሲል የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር አስታውቋል።

ማህበሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ባለፈው አንድ አመት ብቻ በክልሉ ውስጥበሚገኙት ሁሉም ዞኖች ከ35 በላይ ዳኞች ያለአግባብ ታስረው የተፈቱ መሆኑን ማረጋገጡን ገልጿል። በአሁኑ ወቅትም 8 ዳኞች በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዳኞቹ በዋናነት እየታሰሩ የሚገኙት ከስራቸው ጋር በተገናኘ ነው ያለው ማህበሩ በወንጀል የሚፈለጉ እንኳን ቢሆን በሕግ አግባብ ምርመራ አጣርቶ መያዝ ሲገባ ከሚያስችሉበት ችሎት ጭምር በአደባባይ በሚያገለግሉት ህዝብ ፊት እየተያዙ የሚታሰሩበት ሁኔታ እጅግ አደገኛና የተቋሙንም ነጻነት ጨርሶ እያጠፋ ይገኛል ሲል ከሷል።

አከሎም ይህ ሁኔታ ዳኞች ስራቸውን በነፃነት እንዳይሰሩ እንቅፋት የሆነ እና ክብራቸውንም የሚነካ በመሆኑ ሁሉም ዳኛ ለሙያው ያለው ፍቅር እንዲቀንስና የስራ ሞራልን እየጎዳ ያለ ተግባር ነው ብሏል።

እስካሁን ባለው ሂደትም የማህበሩ አመራሮች በተለያየ እርከን ከሚገኙ የፍ/ቤት አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ችግሩ በንግግር እንዲፈታ ጥረት ሲያደርጉ የቆዩ ቢሆንም ችግሩ አሁንም ተባብሶ ቀጥሏል ተብሏል። በመሆኑም ማህበሩ የክልሉ መንግስት የሚመለከታችሁ አካላት በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙትን ዳኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እንዲያደርግ ጠይቋል። በቀጣይም በዳኞች ላይ የሚፈጸም ያልተገባ እስር እንዲቆም እና ይህን ተግበር በሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቅርቧል::
@Ethiopialegalinfo
👍39😭61
በሕግ ፊት እውቅና ያላቸው የጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች


ሀ.
በክብር መዝገብ ሹም ፊት የሚፈጸም ጋብቻ


ለ.
በሃይማኖት ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ

ሐ.
በባህል ሥርዓት መሠረት የሚፈጸም ጋብቻ ናቸው። #የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ከአንቀጽ 2 እስከ 4
ሁሉም ዓይነትየጋብቻ አፈጻጸም ሥርዓቶች በሕግ ፊትእኩል እውቅና እና ውጤት አላቸው።



ተጋብተው 6 ወር ያልሞላቸው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት አይቀፈድላቸውም።

#የተሻሻለው የቤተስሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 2

ማንኛውም ተጋቢዎች ፍቺ በሚጠይቁበት ወቅት በአቤቱታቸውም ሆነ በቃል የፍቺያቸውን ምክንያት እንዲገልጹ አይገደዱም።

#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 3

በተጋቢዎች መካከል ያለ ጋብቻ ሊፈርስ የሚችለው
ሀ. ከተጋቢዎቹ አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ ወይም
ለ. ጋብቻ ለመፈጸም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በሕግ መሠረት ጋብቻው እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም
ሐ. የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ብቻ ነው። ከዚህ ውጪ በመንደር የሚደረጉ የመፋታት ስምምነቶች ተቀባይነት የላቸውም።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75


በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ጋብቻ ያለ መሆኑን ለማስረዳት የጋብቻ ምስክር ወረቀት በማቅረብ ማስረዳት ይቻላል።

የጋብቻ ምስክር ወረቀቱ በሌለ ጊዜ ጋብቻ ለመፈጸሙ የትዳር ሁኔታ መኖሩን በማረጋገጥ ማስረዳት ይቻላል።
#የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 94 እና 95
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
በማንኛውም ፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ
👍294
ደመወዝ‼️

ከዚህ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የደሞዝ ስኬል

የተሻሻለው የመንግስት ደሞዝ ጭማሪ ስኬል ይፋ ሆኗል።
የጥቅምት ወር የመግስት ሰራተኞች ደመወዝ በተጠቀሰው ስኬል መሰረት ይተገበራል።
👍19👎11😁64
ችሎት ከዕረፍት መልስ የሚጠብቅህ እንዲህ ከሆነ ምን መደረግ አለበት?
👍276😁2
የጥብቅና_ፈቃድ_መግቢያ_ፈተና_ከአለሕግ.pdf
1015.8 KB
Share የጥብቅና ፈቃድ መግቢያ ፈተና ከአለሕግ.pdf
https://t.me/AleHig
👍81
Forwarded from ሕግ ቤት
የዳኝነት_ገንዘብ_አከፋፈል_መመሪያ_ቁ_177_1945.pdf
328 KB
ከሳሽ የሆነ ወገን ያቀረበው ክስ በፍ/ስ/ስ/ስ/ህ/ቁ-229&231 መሠረት ክሱ ውድቅ ከተደረገበት በደንቡ መሠረት ለዳኝነት የከፈለው የሚመለስለት ሆኖ(ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ-232(1)ለ እንዲሁም በራሱ ተነሳሽነት ክሱን ሲያቋረጥ ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ አንቀፅ-11 መሠረት ገንዘቡ ይመለስለታል።
https://t.me/Lawsocieties
👍1
TOR traning ( AFD ) Oromia region (Gelan Guda Subcity).pdf
227.3 KB
AHRE is seeking a qualified trainer to deliver training on labor rights and basic human rights for employees in the Oromia region (Gelan Guda Sub City). Please find the details of the call in the PDF below.
https://t.me/AleHig
👍5