አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.86K photos
25 videos
1.86K files
3.58K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
አዲሱ_የቤት_ሽያጭ_ዋጋ_ተመን_አሰራር_እና_ታክስ_አገልግሎት_ክፍያ_ማንዋል_ቁጥር_01_2016_watermark.pdf
1017.2 KB
በአዲስ አበባ ከተማ #ለአፓርትመንት_ቤቶች እና #ለጋራ_መኖሪያ_ቤቶች ወይም ኮንዶሚኒየም ቤቶች አማካኝ የሽያጭ ዋጋ ተመን በ34 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።
በተሻሻለው  የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን መሰረት ከኮንደሚንየም እና አፓርትመንት ውጪ ለሆኑ ግንባታዎች፦
➡️ የግንባታ ነጠላ ዋጋ በጭቃ የተሰራ ቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 15,000 ብር፣
➡️ በብሎኬት የተሰራ የቪላ ቤት (G+0) ነጠላ ዋጋ በካሬ 20,000 ብር፣
➡️ የህንጻ ወለላቸው ከG+1 እስከ G+5 25,000 ብር እና፣
➡️ G+6 እና በላይ የሆኑ ቤት ወይም ህንጻ ነጠላ ዋጋ በካሬ 30,000 ተደርጓል፡፡

የቦታው መገኛ ዋጋ ('location value') ለከተማው የቦታ ደረጃ የጸደቀው ወቅታዊ አማካይ የሊዝ ጨረታ ዋጋ እንዲሆን መደረጉም ተገልጿል

የቤት ስም ንብረት ዝውውር ክፍያ ማለትም አሹራ 4 በመቶ እና የቴምብር ቀረጥ 2 በመቶ ከጠቅላላ የቤቱ ሽያጭ ዋጋ ተሰልቶ ከ ከመጋቢት17 ቀን 2016 ጀምሮ እንዲከፈልም ቢሮ አዟል።

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር  ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የቤት ሽያጭ ዋጋ ተመን #መሻሩንም ቢሮ ጠቅሷል።

በፍርድ ቤት እና በባንክ ሃራጅ ሽያጭ የስም ንብረት ዝውውር የሚጠየቅባቸው ይዞታዎችን በተመለከተ ይዞታ አገልግሎትና መብት ፈጠራ ደንብ ላይ በተቀመጠው አግባብ ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል።
ይህ ማሻሻያ መምሪያ ከመውጣቱ በፊት የስም ንብረት ዝውውር አገልግሎት ጠይቀው በሂደት ላይ ሆኖ ክፍያ የፈጸሙ ተጋልጋዮች በቀድሞ አሰራር በከፈሉት ክፍያ መሰረት ይስተናገዳሉ ተብሏል።

ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች የትመና ስራ የሚሰራላቸው ግንባታው በደረሰበት ወይም አሁን ላይ ባለበት ግንባታ ደረጃ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ያሳወቃል።
https://linktr.ee/alehig
👍30🔥2🥰21
Forwarded from ስለፍትሕ (Talk To Lawyer)
ፐርፐዝብላክ ፍትሐብሔር ክስ ተመስርቶበታል
👇👇👇👇👇
ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲግ አክሲዮን ማህበር በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ልደታ ፍትሐብሔር ምድብ ችሎት በከፊል የሚጠናቀቅ ወደፊት የሚገነባ አፓርታማ ሽያጭ ውል የገቡ ግለሰቦች ተሰባስበው ክስ እንደመሰረቱበት ታወቀ፡፡


ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የቦታው ስመ ሀብት ቢጂአይ-ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ሜክሲኮ የሚገኘው የቢጂአይ-ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ በግዥ አግኝቸዋለሁ ባለው ቦታና ሕንፃ ላይ ከሚገነባቸው የጋራ ህንፃዎች (አፓርታማዎች) ውስጥ የመኖሪያ ቤት ገንብቶ ለግለሰቦች በሽያጭ ለማስረከብ ባደረገው ጥሪ በጣም ብዙ ግለሰቦች በትልልቅ ሚዲያዎች ሳይቀር የተደረገውን መግለጫ እና ጥሪውን እና የድርጅቱን አመራሮች ያሉትን አምነው የግዢ ውል የፈፀሙ ግለሰቦች ተሰባስበው በጋራ ፐርፐዝብላክ ኢቲኤች ትሬዲግ አክሲዮን ማህበር ላይ በሚሊዮኖች ለማስከፈል በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐብሔር ችሎት ክስ ከፍተዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ከፐርፐዝ ብላክ ለዚህ የጋራ ህንፃ አፓርታማ ቤት ይገነባበታል የተባለው ቦታ በቀብድ ውል የተከፈለ 1 ቢሊዮን ብር ታግዶ እንደነበር እና በመካከላቸው አለመስማማት ተፈጥሮ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃብሔር ምድብ ችሎት በፍርድ ቤት መር አስማሚ በኩል በስምምነት ውል ማቋረጣቸው ይታወቃል፡፡                                                                                             እንዲሁም የድርጅቱ አመራሮች በከፍተኛ የማታለል እና የማጭበርበር እንዲሁም የሙስና ወንጀሎች ተከሰው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ለፍትሕ እንቁም 💯
@AboutJustices
https://t.me/AboutJustices
👍261🔥1😱1
Forwarded from አለሕግAleHig ️
ሚዲያዎች ሙያዊ በሆነ ጉዳይ ላይ ዘገባ ሲሰሩ መጠንቀቅ አለባቸው                
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        
በሀገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሠረት ሊጣሉ የሚችሉት የቅጣት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው::

➨መቀጮ (ከ10 ብር - 10,000 ብር)
➨ቀላል እስራት (ከ 10 ቀን - 3 አመት)
➨ፅኑ እስራት (ከ 1አመት - 25 አመት) ➨የእድሜ ልክ እስራት እና
➨የሞት ፍርድ ናቸው
በወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 108 መሠረት የፅኑ እስራት ቅጣት ከ 1 አመት እስከ 25 አመት ብቻ ሲሆን ፣ ነገር ግን በህግ በልዩ ሁኔታ ተገልፆ ሲገኝ የእድሜ ልክ እስራት ሊወሰን ይችላል።
አንቀፅ 184 ንዑስ አንቀፅ (1) (ለ) ስር በግልፅ እንደሰፈረው ነፃነትን የሚያሳጡ ተደራራቢ ወንጀሎች ባጋጠሙ ግዜ ለያንዳዳቸው ወንጀሎች ቅጣታቸው ተወስኖ ሁሉም ቅጣቶች የሚደመሩ ቢሆኑም በጠቅላላው ክፍል ከተቀመጠው ከፍተኛ ቅጣት መብለጥ ግን አይችልም።
ይህ ማለት ተደራራቢ ወንጀሎቹ በቀላል እስራት የሚስቀጡ ከሆነ  ቅጣታቸው  ተደምሮ ከ 3 አመት ሊበልጥ አይችልም፣ እንዲሁም በፅኑ እስራት የሚያስቀጡ ከሆነ ከተቀመጠው ጣሪያ 25 አመት በላይ መብለጥ አይችልም።
  ከዚህ አንፃር የተወሰነውን ውሳኔ ስንመለከት ፍርድ ቤቱ መሠረታዊ የህግ ስህተት ፈፅሟል። ምክንያቱም በሀገራችን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሠረት ሊወሰን የሚችለው ከፍተኛ የፅኑ እስራት ቅጣት 25 አመት ብቻ ሆኖ ሳለ ወንጀለኛውን በ 70 አመት እንዲቀጣ መወሰኑ የህግ መሠረት የሌለው ነው።
ህጉ ካስቀመጠው የ25 አመት ፅኑ እስራት ውጪ በህጉ በግልፅ ተደንግጎ ሲገኝ ብቻ 'የሞት ፍርድ' ወይም 'የእድሜ ልክ እስራት' ሊወሰን ይችላል።
በተሻገር ደምስ
ሕግን አለማወቅ ይቅርታን ሊያስገኝ አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ  2035(2)
ለመሰረታዊ የሕግ እውቀት በቴሌግራም
ቤተሰብ ይሁኑ👇👇👇👇
https://t.me/AleHig
አማራጭ የሕግ እውቀት አለ
Alternative legal enlightenment/ALE
Legal Information🔵
📞+251920666595
👉Telegram👈
https://t.me/AleHig

👉YouTube 👈
https://www.youtube.com/@Ale_Hig

👉Website 👈
http://alehig.com
👍161
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE https://t.me/AleHig
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com
👍5
የሕጻናት ቀለብ አወሳሰን መርሆች
🥰1
የሕጻናት ቀለብ አወሳሰን መርሆች


1. በዋነኝነት የሕጻናት ጥቅም እና ደህንነት ቀዳሚ ማድረግ አለበት፡፡

2. ሕጻናት ወላጆቻቸውን የማወቅ እና ከወላጆቻቸው እንክብካቤ የማግኘት መብት ላይ መመስረት አለበት፡፡

3. ወላጆች አቅማቸው በፈቀደ መጠን ልጆቻቸውን የማሳደግና የመንከባከብ ህጋዊ ኃላፊነት ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት:: ወላጆች ኢኮኖሚያዊ ኃላፊነታቸውን እንደየገቢያቸው መጠን ሊጋሩ እንደሚገባ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት፡፡

4. በሕጻናት ቀለብ አወሳሰን ሂደት ወላጆች ለመኖር የሚያስፈልጓቸውን መሰረታዊ የሆኑ ምግብ፣ መጠለያ እና አልባሳት ታሳቢ ማድረግ አስፈላጊ ቢሆንም በየትኛውም ሁኔታ ግን ለሕጻናት ቀለብ የመስጠት ግዴታን የሚገድብ መሆን የለበትም፡

5. የሕጻናትን መሠረታዊ ፍላጎቶችና ልዩ ወጪዎች ታሳቢ ማድረግ ያለበት ሲሆን ከወላጆቹ አንዱ የተሻለ ገቢ ያለው ከሆነ ሕጻኑ የዚህ ገቢ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፡፡

6. በማስረጃ የተረጋገጠ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር ስራ ባለመስራት ወይም ገቢ ባለማግኘት ቀሪ የሚሆን አይደለም፡፡

7. የሕጻናቱን እድሜ፣ ብዛት፣ የጤና ሁኔታ፣ ልዩ ፍላጎት፣ የሁለቱም ወላጆቹን የገቢ እና ወጪ መጠን እና ተቀባይነት ያላቸው ወይም ህጋዊ ተቀናሾች ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡

8. ቀለብ የመስጠት ግዴታ ያለበት ወላጅ በመምሪያው መሰረት ከሚወሰነው የቀለብ መጠን በተጨማሪ ለመክፈል ፍቃደኛ ከሆነ ወይም ይከፍል ከነበረ ይህንኑ ከግምት ማስገባት አለበት፡፡

9. በሕጻኑ ወላጆች የጋብቻ ሁኔታ የሚወሰን ባለመሆኑ የቀለብ ጥያቄ በቀረበ ጊዜ መወሰን አለበት፡፡

10. ፆታዊ መድሎ የሌለበት መሆን አለበት፡፡

11. በወላጆች መሠረታዊ የኑሮ ሁኔታ ላይ የተጋነነ ችግር ማስከተል የለበትም፡፡ በተለይም የመምሪያው አፈፃፀም ወላጆች ሌላ ቤተሰብ እንዳይመሰርቱ፤ ወይም ስራ ሰርተው ገቢ እንዳያገኙ የሚገፋፋቸው መሆን የለበትም፡

12. ወላጆች በልጆቻቸው አስተዳደግ እና እንክብካቤ ላይ በጋራ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ በተቻለ መጠን ወላጆች የሞግዚትነት ኃላፊነትታቸውን በጋራ እንዲወጡ የሚያስችል ሊሆን ይገባል፡፡

13.
የዋጋ ግሽበት ወይም የኑሮ ውድነትን ወይም የሕጻኑ ፍላጎት መጨመርን ወይም የቀለብ ሰጪን የመክፈል አቅም መለወጥን መሠረት አድርጎ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል፡፡

#አለሕግ #AleHig @AleHig
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE https://t.me/AleHig
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com
👍54😁1
ስግብግብነት አለ ስንል በተገባር ነው!
ትንሿ ውሀ /ግማሽ ሊትር ውሀ 50 ብር የሚሸጥ ነጋዴ ስግብግብ ካልሆ ምን ይባላል?

ትዝብ ብቻ በቂ አይመስልም እንዲህ አይነት ነጋዴን ማውገዝ ያስፈልጋል‼️ #AleHig_አለሕግ #አለሕግ #AleHig @AleHig
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ አማራጭ የሕግ እውቀት
Alternative legal enlightenment/ALE https://t.me/AleHig
WhatsApp👉 #+251920666595
https://linktr.ee/alehig
Telegram👉 @MikiasMelak የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ መሰረታዊ የሕግ እውቀት alehig.com
😢8👍7🙈3🥱2