ከላይ በአዋጅ ቁጥር 591/2000 መሰረት እንዳየነው የሀገሪቱ መገበያ ብር ነው፡፡ ይሄንን ህጋዊ ገንዘብ በቂ ምክንያት ሳይኖረው አልቀበልም ማለት ወንጀል እንደሆነ ስለ ደንብ መተላለፍ በደነገገው የወንጀል ህግ አንቀጽ 778 ደንግጎ ይገኛል፡፡ ቅጣቱም በመቀጮ ወይም በማረፊያ ቤት እስራት ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአንቀጽ 779 መሰረት በሀሰት የተዘጋጀ ወይም ወደ ሀሰት የተለወጠ ገንዘብ በእጁ የገባ ሰው ገንዘቡ የመጣበትን ሁኔታ ካወቀ ይሄንኑ ወይም የሀሰት ገንዘቡ በእጁ የሚገኝ መሆኑን ለሚመለከተው የመንግስት አካል ሳይዘገይ ካላስታስታወቀ እና ገንዘቡን ካላስረከበ በመቀጮ ወይም ማረፊያ ቤት እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡
በጥቅሉ ህጋዊ ገንዘቦችን የማዘጋጀት፣ ማሳተም እና ወደ ገበያው ማስገባት እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን ከገበያው ማስወጣት እና ማስወገድ የብሄራዊ ባንክ ስልጣን እና ሀላፊነት ሲሆን በእነዚሁ ህጋዊ ገንዘቦች ገጽታ፣ በገንዘቦች ላይ የሚጻፈውን ነገር፣ የኖቶቹ ስፋት፣ ቅርጽ እና መደባቸው እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ጉዳዮች መወሰን የብሄራዊ ባንክ ሀላፊነት ብቻ ነው፡፡ ይህ ታውቆ ተጠቃሚዎች እና ሰፊው ማህበረሰብ ብሄራዊ ባንኩ ባወጣው እና በየጊዜው በሚሰጣቸው መመሪያዎች መሰረት የብር ኖቶቹን በአግባቡ መያዝና መጠቀም እንዲሁም ከገንዘብ ኖቶች ጋር በተያያዘ ከሚፈፀሙ ወንጀሎች መቆጠብ ይጠበቅበታል፡፡
መረጃው፡- ከፍትሕ ሚኒስቴር የተገኘ ነው!
Federal Justice and Law Institute
ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ
#አለሕግ #Alehig
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍7
የመደራጀት መብት
መደራጀት በዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች ማእቀፍ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት ህግጋት ዉስጥ የተፈቀደ መብት ነዉ፡፡ ሰዎች በማህበር በመሆን የግልና የጋራ መብታቸውን ለማስከበር እና የጋራ ግዴታቸውን ለመወጣት፣ የጋራ ጥቅም ለማግኘት ወይም ጥቅሞቻቸውን ለማረጋገጥ፣ የሀገር ሰላምና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ሊደራጁ ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጂ የመደራጀት መብት በልዩ ሁኔታ በጠባቡ ሊገደብ የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ በዚህ ፅሑፍ የመደራጀት መብት በዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶች እና በሀገራችን ያለውን የህግ ጥበቃ እንመለከታለን፡፡
የመደራጀት መብት የህግ ማዕቀፍ
ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት እንዳለው በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31 ተመላክቷል፡፡ ሀገራችን አፅድቃ የህጓ አካል ያደረገቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) በአንቀፅ 20 እንዲሁም የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR) በአንቀፅ 22 ማንኛዉም ሰው የመደራጀት ነጻነት እንዳለው ደንግገዋል፡፡ በተጨማሪም አለም አቀፍ ሰብዓዊ መብቶች መግለጫ (UDHR) ማንኛዉም ሰው ያለፈቃዱ የማህበር ወይም የድርጅት አባል ያለመሆን መብት ጭምር ያለዉ መሆኑን ደንግጓል፡፡
በዚህም መነሻነት በሀገራችን የመደራጀት መብትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ህግጋት በሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ለአብነት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 መሰረት ሠራተኞችና አሠሪዎች እንደ አግባቡ የሠራተኞች ወይም የአሠሪዎች ማኅበር ለማቋቋምና ለመደራጀት፣ የማህበር አባል ለመሆንና በማህበርም ለመሳተፍ መብት አላቸው፡፡ ይህ መብት ሰራተኞች በማህበራት በመደራጀት ከአሰሪዎች እና ጥቅማቸውን ከሚነኩ ሌሎች ድርጅቶች ጋር ደሞዝን፣ በሥራ እድገትን፣ የእረፍት ጊዜን እና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ ለመደራደር እና መብታቸውን ለማስከበር የሚያግዛቸው ነው፡፡
በተጨማሪም ዜጎች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በሙያ ማህበራት፣ በበጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ በብዙሀን ማህበራት፣ በድርጅቶች ህብረቶች እና መሰል ለትርፍ ባልቋቋሙ ድርጅቶች መደራጀት ይችላሉ፡፡ በሌላ በኩል ተደራጅተው በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ የሚፈልጉ ደግሞ በምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ሥርአት አዋጅ 1162/2011 መሰረት መደራጀት ይችላሉ፡፡
የመደራጀት መብት በህግ ክልከላ የሚደረግበት አግባብ
የመደራጀት መብት በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሰነዶች እንዲሁም በሀገራችን ህገ መንግስት የተደነገገ መብት ሲሆን ሳይሻራረፍ እንዲከበር የህግ ጥበቃ ተደርጎለታል፡፡ ይህ መብት ለሀገር ደህንነት፣ ለህዝብ ሰላምና ጸጥታ፣ ለህዝብ ጤና እና ሞራል እንዲሁም የሌሎችን መብትና ነፃነት ለመጠበቅ ሲባል በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ በሆኑ በህግ በተደነገጉ ገደቦች ብቻ በጠባቡ ሊገደብ የሚችል ሲሆን ከዚህ ውጪ ምንም አይነት ገደብ ሊጣልበት እንደማይገባ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR) በበግልፅ አመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 31 መሰረት አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ህገወጥ ተግባራት ለመፈፀም መደራጀት የተከለከለ ስለመሆኑ ይደነግጋል፡፡
የመደረጀት መብት ዓለም ዐቀፋዊ ጥበቃ እንዲሁም በሀገራችን የህግ ጥበቃ የተደረገለት መብት በመሆኑ በህግ በልዩ ሁኔታ በግልፅ ከተደነገጉ ገደቦች ውጪ ሊገደብ አይችልም፡፡ በመሆኑም ዜጎች ይህን መብትና ግዴታቸውን አውቀው በመጠቀም ከራሳቸው አልፈው ለማህበረሰባቸው እና ለሀገር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ይጠበቃል፡፡
Source_ Federal ministry of justice

👍8❤1👏1
ስለ ይርጋ ሕጉ ምን ይላል?
****
በጊዜው ካልተጠቀምንበት መብትም የመጠቀሚያ ጊዜው ያልፍበታል። መድኃኒት፣ ምግቦች እና ሌሎች የተለያዩ ምርቶች የተመረቱበት ጊዜ እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው የሚያበቃበት ጊዜ በማሸጊያቸው ላይ ይጻፋል።
ምርቶቹ ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ ይወገዳሉ እንጂ ጥቅም ላይ አይውሉም። ምክንያቱም በጊዜያቸው ጥቅም ላይ ካልዋሉ ለጤና ጎጂ እና የሚፈለገውን አገልግሎት የማይሰጡ ስለሚሆኑ ነው።
በፍርድ ወይም በዳኝነት ወይም በአስተዳደር ውሳኔ መብትን የመጠየቂያ የጊዜ ገደቦችም በፍትሐ ብሔር ሕግ (በፍ/ብ/ሕግ)፣ በፍትሐ ብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ (በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ)፣ በአሠሪ እና ሠራተኛ ሕግ፣ በወንጀል ሕግ እና በሌሎችም ሕጎች ላይ ተደንግገዋል።
በዚህ ጽሑፍ መብትን ለማስከበር በፍትሐ ብሔር ጉዳዮች አልያም ከውል ወይም ከሕግ የሚመነጩ የንብረት እና የገንዘብ መብትን ለማስከበር ዳኝነት የመጠየቂያ ወይም ሌሎች ሕጋዊ ውጤት ያላቸው ድርጊቶችን የማከናወኛ የጊዜ ገደቦችን እና በጊዜ ገደቡ አለመጠቀም የሚያስከትላቸውን ውጤቶች እናያለን።
በእውነተኛ የፍርድ ቤት ሙግቶች ላይ በመጨረሻው የዳኝነት አካል የተሰጡ ይርጋን የሚመለከቱ አስገዳጅ የሰበር ውሳኔዎችን እና ይርጋን የሚደነግጉትን ሕጎችም እንቃኛለን።
1. የሟች እህታቸውን ውርስ ጊዜ ያሳጣቸው ወራሾች
ሟች ወ/ሮ ያልጋ ከአቶ ተገኝ ጋር ተጋብተው ሲኖሩ በ1982 ዓ.ም ይሞታሉ። ከባላቸው ጋር በጋብቻ ያፈሩት የጋራ ሀብት እንዳለ የሚያውቁት እህት ወንድሞቻቸው በጋራ የሟች እህታችን ወራሽ ነንና የሟችን ያካፍሉን ሲሉ አቶ ተገኝ ላይ ክስ ያቀርባሉ። መቼ? ነሐሴ 7 ቀን 1995 ዓ.ም። አቶ ተገኝም ወራሾች ሟች ከሞተች ከ13 ዓመት በኋላ ክሱን በማቅረባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1000(2) እና 1845 በሕጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ክሱን ስላላቀረቡ የውርስ ድርሻ የመጠየቅ መብታቸው በይርጋ ታግዷል ሲሉ መቃወሚያ ያቀርባሉ።
የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም ክሱ በይርጋ አይታገድም ብሎ የወራሾችን ድርሻ እንዲያካፍሉ አቶ ተገኝ ላይ ፈረደባቸው። ለፌ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡት ይግባኝም ስላልተሳካ የይርጋ መቃወሚያዬ ውድቅ በመደረጉ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲሉ ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ ያቀርባሉ።
ሰበር ሰሚ ችሎትም ክሱ የቀረበው ሟች ከሞቱ ከ13 ዓመት በኋላ መሆኑን ጠቅሶ የፍትሐ ብሔር ሕግ በወራሾች መካከል የሚነሣ የውርስ ይገባኛል ክርክር በ10 ዓመት ውስጥ መቅረብ እንዳለበት ገለጸ።
የሟች ወራሾች ክስ ያቀረቡት ግን በሟች ወራሽ ላይ ሳይሆን የጋብቻ የጋራ ንብረት ተጋሪ ላይ በመሆኑ ይህን የሚመለከት የክስ ማቅረቢያ ጊዜ ገደብ የለም። በልዩ ሕግ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ በሌለ ጊዜ ውልን የሚመለከተው የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 የይርጋ ገደብ ተፈፃሚ ይሆናል። በመሆኑም ክሱ ሟች ከሞቱ ከ13 ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች በይርጋ አይታገድም ብለው የሰጡት ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲል በሰ.መ.ቁ 25664 ላይ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሰጥቷል።
2. ከውል የሚመነጭ መብትን የመጠየቂያው ጊዜ
የአሁኑ የመንግሥት ቤቶች ኮርፖሬሽን የቀድሞው ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት በ1977 ዓ.ም ቤት ያከራየኋቸው ደንበኛ ቤቱን ካለ አከራዩ ፍቃድ ወደ ንግድ ድርጅት ቀይረው እየተጠቀሙበት ስላሉ ውሉ ይሰረዝና ቤቱን ያስረክቡኝ ሲል ክስ ያቀርባል።
የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም አከራይ ቤቱ ወደ ንግድ ቤት መቀየሩን ያወቀው በ1979 ዓ.ም ሲሆን በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ ክስ ስላላቀረበ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ታግዷል ሲል ክሱን ውድቅ አደረገው። አከራይ ይግባኝ ቢያቀርብም ስላልተሳካ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲል ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰበር አቤቱታ አቀረበ።
ሰበር ሰሚ ችሎትም በሰ.መ.ቁ 28686 በሰጠው ውሳኔ "ውል ባለመፈጸሙ ምክንያት እንዲፈጸም በመጠየቅ ወይም በውል አለመፈጸም ምክንያት የጉዳት ኪሣራ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ ወይም እንዲሰረዝ በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ በ10 ዓመት የጊዜገደብ ካልቀረበ በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1845 ላይ የተመለከተ ሲሆን የይርጋው ጊዜ መቆጠር የሚጀምረውም ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሠራበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ በቁጥር 1845 ላይ ተመልክቷል" ሲል ለውሳኔው መሠረት የሆነውን ሕግ አብራርቷል።
በመቀጠልም "በተያዘው ጉዳይ አከራይ በተከራይ ላይ ክስ የመሠረተው ለመኖሪያ ቤት የተከራየውን ቤት ወደ ንግድ ቤትነት የቀየረ ስለሆነና ይህም ውሉን መጣስ ስለሆነ ውሉ በፍርዱ ተሰርዞ ቤቱን እንድረከብ ይወስንልኝ በማለት እንደመሆኑ መጠን የውል መጣስ ተግባሩ በዚህ ቀን ተጀምሮ በዚህ ቀን ቆሟል ለማለት ከውሉ ባህሪይ አኳያ የማይቻል ከመሆኑም በላይ አሁንም እየቀጠለ ያለ ተግባር በመሆኑ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 መሠረት በማናቸውም ጊዜ ግዴታውን ለመጠየቅ ተገቢ ስለሚሆን ተከራይ የመኖሪያ ቤቱን ወደ ንግድ ቤት ከቀየሩበት ጊዜ ጀምሮ 10 ዓመት በመቁጠር ‘የስር ፍ/ቤት ክሱን በይርጋ ተገድቧል ማለቱ’ እና ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህን ውሳኔ በማፅናቱ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ሲል የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።
ለማሳያነት ያነሳናቸው የፍ/ብ/ሕ የይርጋ ጉዳዮች ናቸው። የአሠሪ እና ሠራተኛ ሕጉ ላይ ከቅጥር ውል ጋር እና ከሥራ ስንብት ጋር የተያያዙ መብቶችን ለመጠየቅ ገደቡ የስድስት ወር እንዲሁም አሠሪ ሠራተኛው ላይ ለሚወስደው የቅጣት እርምጃ ጥፋቱን መፈፀሙን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ እንዲሆን ተደንግግጓል።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ላይ ከክስ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ጋር የተገናኙ የይርጋ ገደቦችም አሉ። እንዲሁም ይርጋን መቆጠር ሊያቋርጡ የሚችሉ ተግባራትም አግባብ ባላቸው ሕጎች ላይ ተደንግገዋል።
በመሆኑም ክስ ቀርቦብን ምላሽ ስንሰጥም ሆነ መብታችንን ለመጠየቅ ክስ ስናቀርብ በሕጉ የተቀመጠው መብትን የመጠቀሚያ የጊዜ ገደብ አለማለፉን፣ ካለፈም ይርጋን ሊያቋርጥ የሚችል ሁኔታ መከሰቱን ጉዳዩን የሚመለከቱ ሕጎችን በማጣቀስ ማጣራት አለብን። ምክንያቱም መብትን ለመጠየቅም የተቀመጠ ጊዜ አለው።
EBC
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈

👍28❤1
ጫኝ እና አውራጆች ከባለንብረቱ ፍላጎት ውጪ የማንኛውንም ሰው ዕቃ ማውረድም ይሁን ማጓጓዝ አይችሉም፦
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ
በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም የጋራ መኖርያ ቤቶች፣ ሪልስቴቶች እና የማኅበር ቤቶች በብዛት በሚገኙባቸው የተለያዩ አካባቢዎች የተደራጁ ጫኝ እና አውራጆች ነዋሪዎችን ለእንግልት እና ምሬት ሲዳርጉ መቆየታቸው ተደጋግሞ ሲነገር ይሰማል።
ከባለቤቱ ፍላጎት ውጪ ማንኛውንም ዕቃ "እኛ ነን የምናወርደው" ማለት፣ ከፍ ያለ ዋጋ መጠየቅ እና መሰል ጉዳዮች የከተማዋ ነዋሪዎች ደጋግመው የሚያነሧቸው ችግሮች ናቸው።
ይሄንን ችግር ለማስቀረትም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አገልግሎት አሰጣጡን በሕግ እና ሥርዓት ለመከታተል እና ለመቆጣጠር ጫኝ እና አውራጅ ማኅበራትን መልሶ ከማደራጀት ባሻገር መመሪያ አውጥቶ ወደተግባር መግባቱ ይታወሳል።
ቢሮው በጫኝ እና አውራጅ ማኅበራት መመሪያ፣ በወንጀል መከላከል እና በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ከጫኝ እና አውራጆች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።
ጫኝ እና አውራጆች ከባለንብረቱ ፍላጎት ውጪ የማንኛውንም ሰው ዕቃ ማውረድም ይሁን ማጓጓዝ እንደማይችሉ እና ለእያንዳንዱ ዕቃ የዋጋ ተመን ስለመቀመጡ በውይይቱ ላይ ተነሥቷል።
ጫኝ እና አውራጆች ሕግ እና ሥርዓትን ብቻ ተከትለው ማገልገል እንዳለባቸውም ተመልክቷል።
አገልግሎታቸውን በሕግ እና ሥርዓት ብቻ ከማድረግ ባሻገር የአካባቢያቸውን ሰለም እና ፀጥታ በማስጠበቅ እንዲሁም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ከተማቸውን ማገልገል እንዳለባቸውም መጠየቁን አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።
በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች 5 ሺህ 375 ነዋሪዎች በጫኝ እና አውራጅ ሥራ ተሰማርተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸው ተጠቁሟል።
አስተዳደር ቢሮ
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍12❤1
በመስተንግዶ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ያልተገባ አለባበስ እንዳይለብሱ የሚከለክል ረቂቅ ደንብ ወጣ
*******
በሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች የአለባበስ ሥነ-ሥርዓት ሊኖራቸው እንደሚገባ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።
ቢሮው በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት የሚሠሩ ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ፣ የጌጣ ጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ደንብ የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ ረቂቅ ደንብ አውጥቷል።
አዲሱ ረቂቅ ደንብ በሆቴል እና መሰል አገልግሎቶች ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ባለሙያዎችን አለባበስ፣ የፀጉር አያያዝ፣ በሚታዩ የሰውነት አካላት ላይ የሚደረጉ ጌጣ ጌጦች አጠቃቀምን እና የሚጠቀሟቸው ሽቶዎች መጠንን የተመለከቱ ድንጋጌዎችን ይዟል።
ኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ይህንኑ ደንብ በተመለከተ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ የቱሪስት አገልግሎቶች እና ብቃት ማረጋገጥ ደረጃ ምደባ ዳይሬክተሮት ዳይሬክተር ከሆኑት ወ/ሮ ገነት ይመር ጋር ቆይታ አድርጓል።
ወ/ሮ ገነት በጉዳዩ ላይ በሰጡት ሐሳብ፣ የማኅበረሰቡ አካል እንደመሆናችን በዕለት ተዕለት እቅስቃሴያችን ውስጥ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ያለውን የሠራተኞች ያልተገባ አለባበስ አስተውለናል፤ ጉዳዩ ከምልከታችን በተጨማሪ የማኅበረሰቡ ቅሬታ ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም በመስተንግዶ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች የተራቆተ እና ሰውነታቸውን ከልክ በላይ የሚያሳይ ልብስ መልበስ እንደየማይችሉ ደንቡ ላይ መቀመጡን ገልጸዋል።
የሚታይ የሰውነት አካል ላይ ያለ ንቅሳት በአግባቡ መሸፈን እንዳለበት እና ሊታይ እንደማይገባውም በደንቡ መቀመጡን ገልጸዋል።

👍19❤1
በሌላ በኩል ሽታው ከበድ ያለ ሽቶ መቀባት፣ ‘ሂዩማን ሄር’ ማድረግ፣ ከሸሚዝ በላይ የሚደረግ የአንገት ጌጥ እንዲሁም በጆሮ ላይ የተደረደሩ ጌጦች ማድረግ የማይቻል ሲሆን፤ ወንዶች በፍፁም የጆሮ ጌጥ ማድረግ እንደማይችሉ በረቂቅ ደንቡ ተደንግጓል።
ይህ ረቂቅ ደንብ የመስተንግዶ ሥራ ላይ ብቻ እንደማያተኩር እና ለሁሉም የሥራ ዘርፍ የሚሆን የአለባበስ ሥርዓትን ያካተተ መሆኑን አንሥተዋል።
ለአብነትም በላውንደሪ ቤቶች የማያንሸራትቱ መጫሚያዎች፣ በምግብ ማብሰያ ቦታዎች ከሚፈናጠሩ እና ከሚያቃጥሉ ነገሮች ሊከላከሉ የሚችሉ አልባሳት እና ሌሎችም ከተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጋር የሚጣጣሙ እና ለሠራተኛው ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ የሚያስገድድ ረቂቅ ደንብ መሆኑን አክለዋል።
ይህ ረቂቅ ደንብ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ቅድሚያ ለሠራተኛ ደኅንነት ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተገልጋይ ለባለድርጅቶቹ እና ለሠራተኞቹ ክብር እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ያላቸው ባህል፣ ሥርዓት እና እሴት እንዳይሸረሸር የሚያደርግ መሆኑም ልብ ሊባል ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በአፎሚያ ክበበው
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
ይህ ረቂቅ ደንብ የመስተንግዶ ሥራ ላይ ብቻ እንደማያተኩር እና ለሁሉም የሥራ ዘርፍ የሚሆን የአለባበስ ሥርዓትን ያካተተ መሆኑን አንሥተዋል።
ለአብነትም በላውንደሪ ቤቶች የማያንሸራትቱ መጫሚያዎች፣ በምግብ ማብሰያ ቦታዎች ከሚፈናጠሩ እና ከሚያቃጥሉ ነገሮች ሊከላከሉ የሚችሉ አልባሳት እና ሌሎችም ከተለያዩ የሥራ ዘርፎች ጋር የሚጣጣሙ እና ለሠራተኛው ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ የሚያስገድድ ረቂቅ ደንብ መሆኑን አክለዋል።
ይህ ረቂቅ ደንብ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር ቅድሚያ ለሠራተኛ ደኅንነት ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ በተጨማሪም ማንኛውም ተገልጋይ ለባለድርጅቶቹ እና ለሠራተኞቹ ክብር እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮጵያውያን ያላቸው ባህል፣ ሥርዓት እና እሴት እንዳይሸረሸር የሚያደርግ መሆኑም ልብ ሊባል ይገባዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በአፎሚያ ክበበው
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍25❤8
ካሉበት ሆነው በኦላይን www.eservices.gov.et ላይ ተመዝግበው በፍትሕ ሚኒስቴር የሚሰጡ የጥብቅና ፈቃድ፣ የይቅርታና የቅሬታ ማቅረቢያ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ፡፡
ፍትሕ ሚኒስቴር
ፍትሕ ሚኒስቴር
👍15
ቅንጡ መኪና ለመንዳት ህልናዬ አይፈቅድም ..
ገመዳ_ በውጭ ሀገር እንደምናውቀው አትሌቶች
ቅንጡ Super Car የሚባሉትን መኪናዎች ነው
የሚያሽከረክሩት ቀነኒሳስ?
ቀነኒሳ- እውነት ለመናገር በሀገራችን አለኝ ብለህ ዘመናዊና ቅንጡ መኪና ይዘህ ለመውጣት ህሊናህ አይፈቅድም:: ምክኒያቱም ከቤትህ ወጥተህ እስክትመለስ በየመንገዱ ተቸግሮ ማደሪያና የሚበላው አጥቶ የሚለምንህ አለ። በዚህ ሁሉ ውስጥ አንተ አለኝ ብለህ በዚህ ህዝብ ላይ ልታይ ልታይ ማለት ምን ያደርጋል? አንድ አባባል አለ 'ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው' ።
በየመንገዱ የምታየው ሁሉ እናት አባትህ እህት ወንድምህ ነው:: ታዲያ ማን ላይ ነው ይህን የምታደርገው? ስለዚህ እኔ የማሽከረክረው መኪና በጣምም የወረደ ባይሆንም መካከለኛ ነው።"
በ Gammaddaa Show
እውነትም ቀነኒ ኬኛ!
Firehiwot Tamiru
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
"ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው"
ትሁቱ ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
ገመዳ_ በውጭ ሀገር እንደምናውቀው አትሌቶች
ቅንጡ Super Car የሚባሉትን መኪናዎች ነው
የሚያሽከረክሩት ቀነኒሳስ?
ቀነኒሳ- እውነት ለመናገር በሀገራችን አለኝ ብለህ ዘመናዊና ቅንጡ መኪና ይዘህ ለመውጣት ህሊናህ አይፈቅድም:: ምክኒያቱም ከቤትህ ወጥተህ እስክትመለስ በየመንገዱ ተቸግሮ ማደሪያና የሚበላው አጥቶ የሚለምንህ አለ። በዚህ ሁሉ ውስጥ አንተ አለኝ ብለህ በዚህ ህዝብ ላይ ልታይ ልታይ ማለት ምን ያደርጋል? አንድ አባባል አለ 'ድሀ በበዛባት አገር ሀብታምም ደሀ ነው' ።
በየመንገዱ የምታየው ሁሉ እናት አባትህ እህት ወንድምህ ነው:: ታዲያ ማን ላይ ነው ይህን የምታደርገው? ስለዚህ እኔ የማሽከረክረው መኪና በጣምም የወረደ ባይሆንም መካከለኛ ነው።"
በ Gammaddaa Show
እውነትም ቀነኒ ኬኛ!
Firehiwot Tamiru
Alternative legal enlightenment (ALE)አለ Provided by Legal Experts.
አማራጭ የሕግ እውቀት፣
ነፃ የሕግ ምክርና ድጋፍ ሰጪ ሕግ ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የሕግ ማብራርያ ያገኛሉ 🔴
#አለሕግ #Alehig
👉Telegram Channel 👈
https://t.me/lawsocieties
👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/
👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
❤15👍6😢3🔥2
ተማሪዎች ይህ የማካካሻ ክላስ እንዳያመልጣችሁ ⏸‼️
https://youtu.be/oSytbJuBjvw?si=iO619OATINejggFO

👍2

👍16❤2🔥1
Forwarded from ሕግ ቤት
የመቀሌ ኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ማህበር አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ እየተካሄደ ነው።
ውጤቱን የምናሳውቅ ይሆናል።
https://t.me/EthiopianLawStudentsUnion
👍4❤1
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ የጥብቅና ፍቃድ ተፈታኞች ውጤት ፤
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጥብቅና ፈቃድ ለመውሰድ ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ፈተና የተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት የፈተና ውጤቱ ከታች አባሪ በተደረገው ሰንጠረዥ መሰረት ይፋ የተደረገ ሲሆን፡-
1. የፈተና ማለፊያ ውጤቱ 50 እና ከዚያ በላይ እንዲሆን ስለተወሰነ የተባለውን ነጥብ ያመጣችሁ ተፈታኞች ባንቢስ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 (የጥብቅና ፈቃድ አስተዳደርና ነጻ የህግ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት) በመቅረብ ለፈቃድ ገምጋሚ ኮሚቴ መስፈርቶቹን አሟልታችሁ ፈቃዳችሁን ለመውሰድ እንድታመለክቱ፣
2. በፈተና ውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላችሁ አመልካቾች ፈተናው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የፈተና ኮዱን ብቻ በመግለጽ ቅሬታችሁን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በሚገኘው የጥብቅና ፈቃድ አስተዳደርና ነጻ የህግ ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በመገኘት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::
የጥብቅና ሙያ መግቢያ ፈተና ኮሚቴ
መረጃውን #share #like በማድረግ እንድታጋሩልን እንጠይቃለን::
መረጃዎች በፍጥነት እንዲደርሷችሁ ገፃችንን በሚከተለው መስፈንጠሪያ ይቀላቀሉ::
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር
ታህሳስ 09 ቀን 2016ዓ.ም
አዲስ አበባ ፤