ወንጀል ሲፈፅም ጤነኛ የነበረው ግለሰብ ወንጀሉን ከፈፀመ በኋላ እንደ እብድ አድርጎታል፡፡
ዕብደቱ ግን ”አውቆ አበድ" ይሉትን አይነት ነበር፡፡
ሽንት እና ሰገራውን በላዩ ላይ ይፀዳዳል፡፡
የአዕምሮ ህመምተኛ መስሎ ከህግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ያልቆፈረው ጉድጓድ፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም።
*** https://t.me/lawsocieties
ጌቱ ከበደ እና ጌቱ ነጋሽ በሚል የተለያዩ ስሞች የሚጠቀመው ይኸው ግለሰብ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ሉባር ሆቴል ተብሎ ቢጠራው አካባቢ ከለሊቱ 10፡ 40 ሰዓት ገደማ በአንድ የመኖሪያ ቤት ውስጥ ገብቶ 19 ሺህ ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ አልባሳትን ሰርቆ ሲወጣ በአካባቢው ነዋሪዎች እጅ ከፍንጅ ሲያዝ ነበር ዕብደቱ የጀመረው፡፡
ወዲውኑ ራሱን የሳተ መስሎ መሬት ላይ ተጠቅልሎ ተኛ፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ግን በተፈጠረው ድንገተኛ ነገር ተገርመውም ተደናግጠውም ፖሊስ ጠሩ፡፡
ፖሊስ በስፍራው ሲደርስም ወንጀል ፈፃሚው አይናገርም፤ አይጋገርም፡፡
ችግሩን በህክምና ለማወቅ ወደ ጤና ጣቢያ ተወሰደ፡፡ ጤና ጣቢያውም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሪፈር ፃፈ፡፡ ሆስፒታሉም ባደረገው ምርመራ ምንም ችግር የለበትም ብሎ ምላሽ ሰጠ፡፡ ወንጀል ፈፃሚው ግን የጤና ለውጥም ሆነ መሻሻል አላሳየም፡፡ በድጋሚ ወደ ተለያዩ የህክምና ተቋማት ለተጨማሪ ምርመራ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቀናት ተወሰደ፡፡ አሁንም ውጤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡
ፖሊስ ጥርጣሬ ገብቶታል፡፡
ከተጠያቂነት ለማምለጥ የፈጠረው ዘዴ መሆኑን በተለያዩ ሁኔታዎች አረጋግጧል፡፡
ግለሰቡ ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ 16 የተለያዩ ወንጀሎችን ስለመፈፀሙ፣ በተለያዩ 6 ስሞች የሚጠቀም ስለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ ምርመራ የተገኘው የጣት አሻራ ሪከርድ ማስረጃ የፖሊስን የጥርጣሬ ከፍታ ጨምሮታል፡፡ ምናልባት የአዕምሮ ችግር ይኖርበት ከሆነ በሚል እሳቤ ከአቃቤ ህግ ጋር በመነጋገር የወንጀሉን ጉዳይ እየተመለከተ የሚገኘው ፍርድ ቤት ለአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ጠየቁ፡፡
ሆስፒታሉም ምርመራ ለማድረግ በቀጠሮ አሰናበታቸው፡፡ ጌቱ ከበደ ወይም ጌቱ ነጋሽ ለ3 ወራት ያህል ፖሊስ ጣቢያ ሲቆይ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሰው ፖሊስ ተሸክሞት ነበር፡፡
ቀን ቀን መፀዳጃ ቤትም አይሄድም፡፡ ምሽት ላይ ደግሞ እዚያው ማረፊያ ክፍል ውስጥ ይፀዳዳል፡፡ ፖሊስ ደግሞ የቆሸሸውን እና የተበላሸውን ማረፊያ ክፍል ያፀዳል፡፡
አንዳንድ ወንጀል ፈፃሚዎች እንዲህ አይነት የማምለጫ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡
ወንጀል ከፈፀሙ በኋላ ሰገራቸውን እላያቸው ላይ በመፀዳዳት ማንም እንዳይጠጋቸው ያደርጋሉ፡፡
ይህ ዘዴ ደግሞ ለፖሊስ አዲስ አልነበረም፡፡ እናም ጌቱ ከበደ ወይም ጌቱ ነጋሽ በዚህ መንገድ ዕድሉን እየተጠቀመ በነፃ እንዲለቀቅ ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡
ፖሊስ ምግብ ሲያቀርብለት አይበላም፡፡ ነገር ግን ጭር ሲልለት የተሰጠውን ምግብ ይሰለቅጠዋል፡፡
ፖሊስ ሲያየው ይተኛል ፤ ፖሊስ ከአጠገቡ ሲርቅ ደግሞ ተነስቶ ይቀመጣል፡፡ እንዲህ ሲያደርግ ደግሞ የፖሊስ አባላት ተከታትለው በሞባይል ስልካቸው በድብቅ ቀርፀውታል፡፡
የ3 ወራቱ የፖሊስ ጣቢያ ቆይታው በዚህ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤት ቆይቶ ጉዳዩን እንዲከታተል ወሰነ፡፡ ፖሊስም ተጠርጣሪውን ለማረሚያ ቤት ወስዶ ሲያስረክብ ማረሚያ ቤቱም በሸክም የመጣ ተጠርጣሪ አንቀበልም ብሎ መለሳቸው፡፡
ይህንኑ ፍርድ ቤቱ እንዲያውቀው ከተደረገ በኋላ ተጠርጣሪውን እንዲቀበል ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ የጤንነቱን ሁኔታ የሚያረጋግጥ የህክምና ማስረጃ እስኪመጣ ድረስ በዚህ ሁኔታ ውሳኔ እየተጠባበቀ ማረሚያ ቤት ውስጥ ለ 1 ዓመት ያህል ከቆየ በኋላ ከአማኑኤል ሆስፒታል የህክምና ምርመራ ውጤት መጣ፡፡ ጌቱ ከበደ ወይም ጌቱ ነጋሽ ምንም አይነት የአዕምሮ ህመም የለበትም የሚል፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የህክምና ማስረጃውን ከተመለከተ በኋላ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ/ም በፈፀመው የስርቆት ወንጀል በ5 ዓመት እስራት እንዲቀጣ በቅርቡ በዋለው ችሎት ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ አውቆ አበድነቱ እውነትን አላሸነፈለትም፤ አሸናፊው የፖሊስ ትዕግስት ሆኗል፡፡
ፖሊስ በትዕግስቱም የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አድርጓል፡፡
የመረጃ ምንጭ፡
ኢንስፔክተር ዮሃንስ ሸንዶ
ዘጋቢ፡- ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

👍9
January 14, 2023
January 14, 2023
ይግባኝ የማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ከሆነ ይግባኝ ማስፈቀጃ አያስፈልግም........
የሰበር መዝገብ ቁጥርም 220962 (ያልታተመ)
ይግባኝ የማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ከሆነ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር. 1862 ግዴታው የሚፈጸምበት ቀን ከአንድ የበአል ቀን ጋር ከገጠመ በዓል ባልሆነበት በማግስቱ ባለው የሥራ ቀን እንደሚተላለፍ በተደነገገው አግባብ ይግባኝ ጠያቂው ጊዜ ሳያባክን በቀጣዩ የሥራ ቀን ይግባኙን አዘጋጅቶ ያቀረበ ከሆነ ይግባኙ ማስፈቀጃ ሳያስፈልገው ሊቀርብ ይገባል።
#DanielFikadu
https://t.me/lawsocieties
የሰበር መዝገብ ቁጥርም 220962 (ያልታተመ)
ይግባኝ የማቅረቢያው የመጨረሻ ቀን የመንግስት ስራ ዝግ በሆነበት ቀን ላይ ያረፈ ከሆነ በፍትሐብሔር ሕጉ ቁጥር. 1862 ግዴታው የሚፈጸምበት ቀን ከአንድ የበአል ቀን ጋር ከገጠመ በዓል ባልሆነበት በማግስቱ ባለው የሥራ ቀን እንደሚተላለፍ በተደነገገው አግባብ ይግባኝ ጠያቂው ጊዜ ሳያባክን በቀጣዩ የሥራ ቀን ይግባኙን አዘጋጅቶ ያቀረበ ከሆነ ይግባኙ ማስፈቀጃ ሳያስፈልገው ሊቀርብ ይገባል።
#DanielFikadu
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍6
January 14, 2023
የሰ/መ/ቁ.150408: ቅጽ/23
እንደ ጋብቻ ሁሉ ፍችን በውክልና ማከናወን የሚቻል ስለመሆኑ
ጋብቻ ለመፈጸም በልዩ ሁኔታ በውክልና እንደሚቻል ህጉ እየፈቀደ የፍቺ ጥያቄ ፍርድ ቤት የባልና ሚስትን ክርክር በሚያይበት ጊዜ እንደነገሩ ሁኔታ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘው ባልና ሚስቱን በአንድነት ወይም በተናጠል ሲያነጋግር ወይም ጉዳዩን ሲመረምርና ምስክር ሲሰማ በዝግ ችሎት ያስችላል የሚለውን የቤተሰብ ህጉን ድንጋጌ አንቀጽ 110/ በመጥቀስ ጋብቻና ፍች በውክልና ሊጠየቅ አይችልም በሚል የሚቀርብ ክርክር ተገቢነት የለዉም፡፡
ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ ተጋቢዎችን በአካል የሚያነጋግራቸው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንጂ የግድ ማነጋገር እንዳለበት የሚደነግግ ባለመሆኑ እና ጋብቻ በእንደራሴ መፈጸም በመርህ ደረጃ የማይቻል ቢሆንም ከተጋቢዎች አንደኛው ጋብቻውን ለመፈጸም ፈቃዱን በማያሻማ ሁኔታ በመግለጽ በግንባር ለመገኘት የማያስችለው ከባድ ምክንያት ሲያጋጥመው ጉዳዩ ለፍትህ ሚኒስትሩ ቀርቦ ሲረጋገጥ ጋብቻውን በእንደራሴ አማካኝነት መፈጸም እንደሚቻል በግልጽ በተሻሻለው የፌደራል ቤተሰብ ህግ አንቀጽ 12 ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም የተሰጠው የውክልና ማስረጃ ይዘት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.58 እና በፍ/ብ/ህ/ቁ.2199 ተወካዩ ፍቺን ጨምሮ በማናቸውም ጉዳዮች ወክሎ ለመከራከርም ሆነ ሌላ የህግ ባለሙያ ለመወከል እንደሚችል በውክልና ሰነዱ ላይ በግልጽ የተመለከተ ከሆነ ፍች በዉክልና አይጠየቅም ተብሎ ሊከለከል አይገባም፡፡

👍2
January 15, 2023
Job Vacancy:
Lawyer
Deadline: Jan 20, 2023
https://www.ethiojobs.net/display-job/450432/Lawyer.html?searchId=1673433942.8762&page=1

የአሰሪና ሰራተኛ ይርጋን በሚመለከት
የስራ ውል ማቋረጥ ያልታተመ የሰበር ውሳኔ፣
የሰበር መዝገብ ቁጥር 221210.
አንድ አሰሪ ስራውን እንዳይሰራ ቢታገድና ፍቃዱ ባይታደስለትም ለሰራተኞቹ የስንበት ደብዳቤ ሰጥቶ የስራ ውሉን እሰካላቋረጠ ድረስ ሰራተኞቹ
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011. አንቀጽ 163(4) መሰረት የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛውም ሆነ በአሠሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውሉ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የታገዳል በሚለው ድንጋጌ መሰረት የይርጋ መከራከሪያን ማንሳት አይችልም።
ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ ዳንኤል ፍቃዱ
የስራ ውል ማቋረጥ ያልታተመ የሰበር ውሳኔ፣
የሰበር መዝገብ ቁጥር 221210.
አንድ አሰሪ ስራውን እንዳይሰራ ቢታገድና ፍቃዱ ባይታደስለትም ለሰራተኞቹ የስንበት ደብዳቤ ሰጥቶ የስራ ውሉን እሰካላቋረጠ ድረስ ሰራተኞቹ
በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011. አንቀጽ 163(4) መሰረት የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በሠራተኛውም ሆነ በአሠሪው የሚቀርብ ማንኛውም የክፍያ ጥያቄ የሥራ ውሉ በተቋረጠ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ የታገዳል በሚለው ድንጋጌ መሰረት የይርጋ መከራከሪያን ማንሳት አይችልም።
ጠበቃና የህግ አማካሪ፣ ዳንኤል ፍቃዱ
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍7❤2
January 15, 2023
January 15, 2023
Forwarded from Lawyer and Consultant
Peace.pdf
505.7 KB
January 15, 2023
አለሕግAleHig ️
ሙስናን መታገል በፋሽን ወይስ በፓሺ❓❓ 👇👇👇የቀጠለ..👆👆👆 የልቦና ውቅር ለውጥ‼️ አሁን እየታየ ያለው ነባራዊ አይን ያወጣ የሙስና ምክንያት እና የሚያመጣው ተፅዕኖ 👈 ዛሬ እሁድ ምሽት 2:30 ቀጥታ ስርጭት ይቀላቀላሉ 👆👆👆👆👆👆👆
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
January 15, 2023
#የቀብድ ግብይት አዋጪ ነው! በዋጋ ንረት ወቅት ያለወለድ አበዳሪ አካል ተጎጂ ነው።
ለወዳጃችሁ የዛሬ ዓመት ያበደራችሁትን ገንዘብ ዘንድሮ ሲከፍል ያንኑ ነው። በማህበራዊ ምክንያት የገንዘቡ የመግዛት አቅም ስለተዳከመ ወዳጅ ወለድ አስቦ አይሰጥም! አበዳሪ ለማካካሻ ወለድ አይጠይቅም።
በተመሳሳይ ቀብድ ቀድሞ ተቀባይ በማህበራዊ ተፅዕኖ የዋጋ ለውጥ ላለመፍጠር ይገደዳል። በተቃራኒው ቀብድ ቀድሞ በመክፈል የተፃፈም ሆነ ያልተፃፈ ስምምነት ውስጥ የወደቀ ሸማች ነባር ዋጋ ለመክፈል እድል ያገኛል።
#ለምሳሌ፦ ዛሬ 3ሺ ብር ለተባላችሁት እቃ ከወር በኋላ 3ሺ ብር ይዛችሁ ብትመጡ 4ሺ ብር ቢገባ ዋስትና የላችሁም! ነገር ግን በማህበራዊ ዋስትና ዘዴ ባንዱ #ቀብድ ከወር በፊት 1ሺ ብር ከፍላችሁ ቢሆን ከወር በኋላ 4ሺ ብር ዋጋ ላይ ላትወድቁ ትችላላችሁ።
ሻጮች የእጅ በእጅ ክፍያ እና የቀብድ ክፍያ መካከል ረጅም የጊዜ ልዩነት እና የዋጋ ልዩነት ላይፈጥሩ ይችላሉ የሚለው ታሳቢ ተደርጎ #እድሉ_ያላችሁ ሰዎች ለመሸመት ለወሰናችሁት ቁስ ፈጣን ውሳኔ ከሌላችሁ የዋጋ ንረት ተገማች ስላልሆነ በቀብድ መገበያየት መጥፎ አይደለም።
የዋጋ ንረት የመቀነስ ባህሪ ባለው ገበያ ላይ የቀብድ ተጠቃሚ ሻጭ ነው። በቀብድ 4ሺ ብር ያሰረው ዋጋ በገበያ ተመን 3ሺ ብር ቢወርድ ዋጋ ለመቀነስ ላይገደድ ይችላል።
የዋጋ ንረት እና የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከሙ ካልቀረ ለመሸመት ያሰቡትን በፍጥነት መሸመት ወይም እድሉ ካለ በቀብድ የጊዜ የዋጋ ለውጥን መቀነስ ይቻላል።
በቅርቡ አንዲት ልጅ ፈርኒቸር ቤት ትከራከራለች። "የዛሬ ወር ጫማ መደርደሪያ 2,800ብር እንዲሰራልሽ 500ብር ቀብድ ስጪ ሲለኝ ስላልወሰንኩ ዛሬ ላይ ያንኑ ምርት 4,000ብር ገብቷል አለኝ" ትላለች ሻጭ "ያንቺ ጥፋት ነው! ያኔ ወስነሽ ቢሆን በቅናሹ ይሰራልሽ ነበር! አሁንም ካልወሰንሽ በቀጣይ የሚደርስበትን የግብዓት ዋጋ አላውቅም" ይላል። Via #WaseAlpha

👍8👎1🔥1
January 16, 2023
*የፍትህ አካላት ስንል
ማን ማንን ያካትታል.....⁉️
👇👇👇👇👇👇👇
1.
2.
3.
4.
5.
....❓
ማን ማንን ያካትታል.....⁉️
👇👇👇👇👇👇👇
1.
2.
3.
4.
5.
....❓
👍3
January 16, 2023
ሰው ብዙ የተፈጥሮ ህጎችን ጥሷል ወይም ተላልፏል ‼️⚖️
ነገር ግን አንድ የተፈጥሮ ህግን መሻር (መተላለፍ) ቢፈልግም አልቻለም ወደፊትም አይችልም‼️
ይህ ህግ ምንድን ነው⁉️
ነገር ግን አንድ የተፈጥሮ ህግን መሻር (መተላለፍ) ቢፈልግም አልቻለም ወደፊትም አይችልም‼️
ይህ ህግ ምንድን ነው⁉️
January 16, 2023
January 16, 2023
January 17, 2023
January 17, 2023
#Update
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ሹመት ያጸደቀው፤ በሶስት ድምፅ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ

👍9👎1
January 17, 2023
#Update
ወይዘሮ አበባ እምቢአለ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።
ምክር ቤቱ የወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ወ/ሮ አበባ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኛነት ፣ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግነት፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል።
አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።
#tikvahethiopia

👍11
January 17, 2023
January 17, 2023
January 17, 2023
January 18, 2023
Forwarded from ሕግ ቤት
የህግ የተማሪዎችን ህብረት እንደገና ለማነቃቃት እና አዲስ ስራ አስፈፃሚ አባላቶችን ለመምረጥ እንቅስቃሴ ጀምረናል።
በየዩኒቨርሲቲው ያላችሁ የህግ ማህበራት መረጃችሁን ላኩልን፣
https://t.me/EthiopianLawStudentsUnion
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 ከየት ዩኒቨርሲቲ ነው
👉የማህበሩ ፕሬዚደንት ስም
👉 አባላት ዝርዝር
👉 መመስረቻ እና መተዳደሪያ
👉 ስልክ
የኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ህብረት
ከዚህ በታች ባለው ኢሜል ላኩልን
👇👇👇👇👇👇👇
lawschoolstudentsunion@gmail.com
አማራጭ
በአለ ህግ ቴሌግራም ግሩፕ ላይ በፕሮግራም መወያየት እንችላለን።

👍6👏3
January 18, 2023
#ህጉ ምን ይላል?
ድፍንፍን ለማድረግ የተሞከረው ሹም ሽረት #ከህግ አንፃር፣
ስለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት “ መልቀቂያ እና ሹመት ” ህገ መንግስቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በፌደራል መንግስት ጠቅላይ ሚኒሰቴር አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ
አላማ- በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚሾሙ ዳኞች ግልጽ፣ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ አሰራር የሚሾሙበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በብቃት፣ በሙሉ ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት የሚያከናውኑበትን አሰራር ማረጋገጥ፤
"የፌደራል ዳኞች" ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙ ዳኞች ሲሆኑ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ይጨምራል ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ የዳኞች የሥራ ስንብት/ መልቀቅን በተመለከተ
ከዳኝነት ሥራ ለመልቀቅ ጥያቄ ሲያቀርብ የሁለት ወር / እንጊሊዝኛው 3 ወር ይላል / ቅድሚያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤
በተጨማሪም
የፌደራል ጠቅላይ ፕሬዚዳንት ወይም ምክትል ፕሬዚዳንት ስለቀረበበት ከስራ የሚሰናበቱት ጉዳይ በጉባዔው ታይቶ ውሳኔ ሲያገኝ እና ጥያቄው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ለህዝብ ተወካዮች ቀርቦ ምክርቤቱ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቀው ነው ፡፡
የፌደራል ጠቅል ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምከትል የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባሎች እንደመሆናቸው ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ አንቀጽ 19 ላይ ዝርዘር ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል
የጉባዔው አባሎች ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮(፩ ) ሀ፣ ለ፣ሐ፣መ፤ ሠ እና ሰ ከተመለከቱት በስተቀር ማንኛዋም የጉባኤ አባል፤
ሀ) ከደንብ መተላለፍ ውጭ በሆነ ወንጀል ተከሶ ሲፈረድበት፣
ለ)በጤና ችግር ምክንያት ስራውን በአግባቡ ማከናወን ሲሳነው፤
ሐ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤት አባልነት ሲመረጥ ወይም በሹመት፤ ወይም በዝውውር በፌደራል ወይም በክልል መንግስት ሥራ አስፈጻሚ ቦታ ሲመደብ፤
መ) ይህን አዋጅ ወይም የጉባዔውን የውስጥ የአሰራር ሥነ ሥርዓት ባለማክበሩ ጉዳዩ ለጉባኤው ቀርቦ ለአባልነት ተገቢ አለመሆኑ ከጉባኤው ጠቅላላ አባላት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ሲወሰን፤
ሠ) በሌላ ማናቸውም ምክንያት በጉባኤው ላለዉ ከፍተኛ ኃላፊነት አባል ሆኖ ለመቀጠል የማይችል ሲሆን እና በጉባኤዉ ሲወሰን፤ ከጉባዔው አባልነት ይሰናበታል ፡፡
፪/ ማንኛውም የጉባኤው አባል ከጉባኤው ጽሕፈት ቤቱ በኩል ከአንድ ወር አስቀድሞ ለጉባዔው በጽሁፍ ማቅረብ አለበት፡፡
ተሿሚዎችን በተመለከተ
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም - የሚያበቁ ተጨማሪ ሁኔታዎች
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም ከዚህ በላይ በአንቀጽ ፳፪ ከተደነገገው በተጨማሪ የሚከተሉት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
፩/ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ወይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ያገለገለ እና በሥራዉ ዘመን መልካም ሥነ-ምግባርን ፣ታታሪነትን ፣ ብቃትን እና ቅንነትን ያሳየ፤ ይህም በዳኞች ምልመላ ኮሚቴ ከተረጋገጠ፤ ወይም
፪/ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው ቢኖርም በዳኝነት ሙያ ከተጠቀሰው የአገልግሎት ጊዜ ሁለት ሶስተኛውን ያገለገለ በዳኝነት ሥራዉ ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ልትቀርብ ይችላል፡፡
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ እና ፪ የተደነገገው ቢኖርም በማንኛውም የህግ ሙያ ቢያንስ ፳ ዓመት ያገለገለ በሥራው ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
ህገመንግስቱ እና የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ሰንበትና ሹመቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለመት መንገድ መሆን እንዳለበት በግልጽ ቢደነግጉም ፣ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላትም የምክር ቤት አባላት አዲስ የተሸሙት ግለሰቦች ማንነት በተገቢው ሁኔታ ለመገምገም ቀድሞ ስለግለሰቦቹ አለመነገሩን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በምን ምክንያት እንደለቀቁ አለመብራራቱ ጥያቄ አንስተው የነበር ቢሆንም መልቀቂያውና ሹመቱ መጽደቁ አልቀረም፡፡
#Daniel_Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ
(ጠበቃና የህግ አማካሪ)/
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Law_Societies

👍15❤3🔥1👏1💅1
January 18, 2023
ልዩነታችን ውበታችን ነው። ብናውቅም ባናውቅም የተለያየ እምነት እና ባህል ላከበረው ሀብት ነው።
እንኳን አደረሳችሁ። መልካም ጥምቀት። #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
እንኳን አደረሳችሁ። መልካም ጥምቀት። #አለ_ህግ #Ale_Hig
https://t.me/lawsocieties
👍13❤1
January 19, 2023
በጃንሜዳ በከተራና በጥምቀት በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 13 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ
👉 ከተለያዩ ግለሰቦች የተሰረቁ 20 ሞባይል ስልኮችም በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፣
**
(ኢ ፕ ድ)
የአዲስ አበባ ፖሊስ ስርቆትና ሌሎች ደረቅ ወንጀሎች ቢፈፀሙ እንኳ ፈጣን ምላሽ እና አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በጃንሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚቋቋም መግለፁ ይታወሳል።
ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥር 10 በጃንሜዳ በተከበረው የከተራ በዓል ዕለት የስርቆት ወንጀት የፈፀሙ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች ላይ 3 ሞባይል ስልክ በኤግዚቢትነት ተይዟል።
በተመሳሳይ ጥር 11 በበዓሉ ዕለት ፀበል ለመረጨት የነበረውን ግፊያ እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከተያዙት ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በቁጥር በርከት ያለውን ሰልክ መስረቃቸውን የጠቀሰው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አንደኛው 9 ስልኮችን በኪሱ፣ አንደኛው ደግሞ 8 ሞባይል ስልኮችን በሆዱ ደብቀው የተገኙ ናቸው ተብሏል።
ሞባይል ስልክ የተሰረቀባቸው ግለሰቦች በጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያው ቀርበው በማመልከታቸው ከተያዙት ስልኮች መካከል የተወሰኑት ባለቤቶቻቸው የተገኙ ሲሆን ሌሎቹን አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርቦ መጠየቅና ማረጋገጥ እንደሚቻል ተገልጿል።
በአጠቃላይ 13 ተጠርጣሪዎች እና 20 ሞባይል ስልክ የተያዘ ሲሆን በዓሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እና ወንጀል የሚፈፅሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ህብረተሰቡ እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር ቆመው እያሳዩት ላለው ተባባሪነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

👍4
January 19, 2023
January 19, 2023
ወራሽነቱን በፍርድ ቤት አሳውጆ የቤት ስመ ንብረት ካዞረ ሰው ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል ፊት ቀርቦ የሽያጭ ውል በመፈፀም ቤት የገዛ ግለሰብ የቅን ልቦና ገዥ በመሆኑ በሌሎች ወራሾች ውሉ እንዲፈርስ የሚጠየቅበት አግባብ የለም።
የፌ/ጠ/ፍ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተያያዘ የቅን ልቦና ገዥነትን አስመልክቶ የሰጠው የህግ ትርጉም- ያልታተመ*
https://t.me/lawsocieties
የፌ/ጠ/ፍ ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ጋር በተያያዘ የቅን ልቦና ገዥነትን አስመልክቶ የሰጠው የህግ ትርጉም- ያልታተመ*
https://t.me/lawsocieties
Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/
👍8🔥1😁1
January 19, 2023
January 19, 2023
January 20, 2023
222680.pdf
869 KB
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ላይ የሚገኘው parol evidence rule በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ በሚታመንበት ጊዜ ተፈጻሚነት የለውም።
የውሉ ይዘት ለምሳሌ የገንዘቡ መጠን፡ በውሉ ላይ ያለው ቀን ወዘተ በሌላ ውጫዊ ማስረጃ ሊስተባበል ይችላል።
በውል አዋዋይ ፊት ተረጋግጦ ያልተመዘገበ የቤት ሽያጭ ውል መኖሩ ታምኖ የውሉ ይዘት ፊርማን ጨምሮ በአከራከረ ጊዜ በምን አይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ይገባል? የሚለው ጥያቄ በተመለከተ የሰበር ችሎት የሚከተለውን የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የቤት ሽያጭ ውል በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ውል አዋዋይ ፊት መደረግ አለበት በሚል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1723/1 ስር የተደነገገበት አንዱ አላማ ውሉ በጽሁፍ በሰፈረው አግባብ በእርግጥ የተደረገ ስለመሆኑ እና ይዘቱም እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡በመሆኑም በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡

👍8
January 20, 2023