#ህጉ ምን ይላል?
ድፍንፍን ለማድረግ የተሞከረው ሹም ሽረት #ከህግ አንፃር፣
ስለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት “ መልቀቂያ እና ሹመት ” ህገ መንግስቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በፌደራል መንግስት ጠቅላይ ሚኒሰቴር አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሾማሉ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ
አላማ- በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሚሾሙ ዳኞች ግልጽ፣ ገለልተኛና ተአማኒ በሆነ አሰራር የሚሾሙበትን ሥርዓት በመዘርጋት ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በብቃት፣ በሙሉ ነጻነት፣ ገለልተኝነትና ተጠያቂነት የሚያከናውኑበትን አሰራር ማረጋገጥ፤
"የፌደራል ዳኞች" ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሾሙ ዳኞች ሲሆኑ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንቶችን ይጨምራል ።
የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ የዳኞች የሥራ ስንብት/ መልቀቅን በተመለከተ
ከዳኝነት ሥራ ለመልቀቅ ጥያቄ ሲያቀርብ የሁለት ወር / እንጊሊዝኛው 3 ወር ይላል / ቅድሚያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፤
በተጨማሪም
የፌደራል ጠቅላይ ፕሬዚዳንት ወይም ምክትል ፕሬዚዳንት ስለቀረበበት ከስራ የሚሰናበቱት ጉዳይ በጉባዔው ታይቶ ውሳኔ ሲያገኝ እና ጥያቄው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት ለህዝብ ተወካዮች ቀርቦ ምክርቤቱ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ ሲያጸድቀው ነው ፡፡
የፌደራል ጠቅል ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምከትል የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባሎች እንደመሆናቸው ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ አንቀጽ 19 ላይ ዝርዘር ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል
የጉባዔው አባሎች ሥራቸውን ስለሚለቁበት ሁኔታ
፩/ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮(፩ ) ሀ፣ ለ፣ሐ፣መ፤ ሠ እና ሰ ከተመለከቱት በስተቀር ማንኛዋም የጉባኤ አባል፤
ሀ) ከደንብ መተላለፍ ውጭ በሆነ ወንጀል ተከሶ ሲፈረድበት፣
ለ)በጤና ችግር ምክንያት ስራውን በአግባቡ ማከናወን ሲሳነው፤
ሐ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤት አባልነት ሲመረጥ ወይም በሹመት፤ ወይም በዝውውር በፌደራል ወይም በክልል መንግስት ሥራ አስፈጻሚ ቦታ ሲመደብ፤
መ) ይህን አዋጅ ወይም የጉባዔውን የውስጥ የአሰራር ሥነ ሥርዓት ባለማክበሩ ጉዳዩ ለጉባኤው ቀርቦ ለአባልነት ተገቢ አለመሆኑ ከጉባኤው ጠቅላላ አባላት በሁለት ሶስተኛ ድምጽ ሲወሰን፤
ሠ) በሌላ ማናቸውም ምክንያት በጉባኤው ላለዉ ከፍተኛ ኃላፊነት አባል ሆኖ ለመቀጠል የማይችል ሲሆን እና በጉባኤዉ ሲወሰን፤ ከጉባዔው አባልነት ይሰናበታል ፡፡
፪/ ማንኛውም የጉባኤው አባል ከጉባኤው ጽሕፈት ቤቱ በኩል ከአንድ ወር አስቀድሞ ለጉባዔው በጽሁፍ ማቅረብ አለበት፡፡
ተሿሚዎችን በተመለከተ
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም - የሚያበቁ ተጨማሪ ሁኔታዎች
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለመሾም ከዚህ በላይ በአንቀጽ ፳፪ ከተደነገገው በተጨማሪ የሚከተሉት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
፩/ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ወይም በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኝነት ቢያንስ አስር ዓመት ያገለገለ እና በሥራዉ ዘመን መልካም ሥነ-ምግባርን ፣ታታሪነትን ፣ ብቃትን እና ቅንነትን ያሳየ፤ ይህም በዳኞች ምልመላ ኮሚቴ ከተረጋገጠ፤ ወይም
፪/ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፩ የተደነገገው ቢኖርም በዳኝነት ሙያ ከተጠቀሰው የአገልግሎት ጊዜ ሁለት ሶስተኛውን ያገለገለ በዳኝነት ሥራዉ ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ልትቀርብ ይችላል፡፡
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ እና ፪ የተደነገገው ቢኖርም በማንኛውም የህግ ሙያ ቢያንስ ፳ ዓመት ያገለገለ በሥራው ላይ በቆየችበት ጊዜ መልካም ሥነ-ምግባሩ፣ ታታሪነቱ እና የላቀ ሞያዊ ብቃቱ የተመሰከረለት ሰው የጉባዔውን ሁለት ሦስተኛ የድምፅ ድጋፍ ካገኘ በልዩ ሁኔታ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ዕጩ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል።
ህገመንግስቱ እና የፌደራል ዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ከላይ በተዘረዘረው መልኩ ሰንበትና ሹመቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለመት መንገድ መሆን እንዳለበት በግልጽ ቢደነግጉም ፣ ከአንዳንድ የፓርላማ አባላትም የምክር ቤት አባላት አዲስ የተሸሙት ግለሰቦች ማንነት በተገቢው ሁኔታ ለመገምገም ቀድሞ ስለግለሰቦቹ አለመነገሩን እንዲሁም ከዚህ ቀደም የነበሩት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት በምን ምክንያት እንደለቀቁ አለመብራራቱ ጥያቄ አንስተው የነበር ቢሆንም መልቀቂያውና ሹመቱ መጽደቁ አልቀረም፡፡
#Daniel_Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ
(ጠበቃና የህግ አማካሪ)/
#አለ_ህግ #Ale_Hig #Law_Societies
https://t.me/lawsocieties

Telegram
ሕግ ቤት
ሕግ ቤት Access legal information
ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ያማክሩ
@HigBet #ሕግ_ቤት
lawsocieties@gmail.com
https://www.facebook.com/Ethiopianlegalinfo/

የኮ/መ/ቁ 282704/ፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ንግድ ችሎት ውሳኔ /
ቼክ በንግድ ህጋችን እንደ ንግድ ወረቀት ይቆጠራሉ ተብለው በን/ህ/ቁ 732/2/ ስር ከተዘረዘሩት የንግድ ወረቀቶች አንዱ ነው፡፡ ቼክ ከንግድ ወረቀቶች ውስጥ አንዱ ቢሆንም ከሌሎች የንግድ ወረቀቶች የሚለይባቸው ልዩ ባህሪያት ያሉት፣ ገንዘብን ተክቶ በስፋት አገልግሎት እየሠጠ ያለ፣ በንግድ ህጉ እንዲሁም በሌሎች ህጐቻችን ልዩ ጥበቃ የተሠጠው የንግድ ወረቀት ሲሆን ከነዚህ ልዩ ባህሪያት አንዱ ቼክ እንዲቀረበ የሚከፈልበት የንግድ ወረቀት መሆኑ ነው፡፡ ይህም በን/ህ/ቁ 854 ስር ተመልክቷል፡፡ የቼኩ አምጪ / Drawee / ቼኩን ለክፍያ ለከፋዩ ባንክ /Payee/ አቅርቦ ቼኩ ሳይከፈልበት ከተመለሰ የቼኩ አውጪ /Drawer/ ስለ ቼኩ አከፋፈል ዋስ በመሆኑ እና ገንዘቡን የመክፈል ሀላፊነት ያለበት በመሆኑ በቼኩ ላይ የተፃፈውን ገንዘብ የቼኩ አውጪ እንዲከፍለው መጠየቅ ይችላል፡፡ ይህም በን/ህ/ቁ 840 ፣ 868 ፣ 881 /1/ ስር ተመልክቷል፡፡ የቼኩ አውጪም በን/ህ/ቁ 840 መሠረት ገንዘቡን የመክፈል ሀላፊነት አለበት፡፡
የቼኩ አውጪ ከዚህ ኃላፊነት ሊድን የሚችለው ማለትም በቼኩ ላይ የተፃፈውን ገንዘብ ለቼኩ አምጪ የመክፈል ኃላፊነት የማይኖርበት፣ ቼክን መሠረት አድርጐ ለቀረበ ክስ በቼኩ አምጪ ላይ ሊቀርቡ ይችላሉ ተብለው በህጉ ተለይተው እና ተወስነው በን/ህ/ቁ 717 ስር የተቀመጡትን መከላከያ ምክንያቶች ያቀረበ፣ ይህን መከላከያ ምክንያቱንም ያስረዳ ሲሆን ነው፡፡ ይህ መከላከያም በን/ሕ/ቁጥር 717/1//3/፣ 849፣ 850 ስር የተቀመጠውን አይነት ከቼኩ አምጪ ጋር ያለውን የግል ግንኙነት መሠረት ያደረገ /Personal Relation Ship Defence/ ወይም በን/ሕ/ቁጥር 717/1/2/ ስር የተመለከቱት አይነት ከቼኩ አወጣጥ፣ ፎርም፣ የተፃፋ ቃላትና ፊርማ መሠረት ያደረጉ ቼኩን የሚመለከቱ መከላከያዎች /Real Defence/ ያቀረበ እና ይህንም መከለከያውን ያስረዳ ሲሆን ነው፡፡
#Daniel fikadu ዳንኤል ፍቃዱ /ጠበቃና የህግ አማካሪ/

239841 - Stamped.pdf
932.4 KB
የስራ ላይ ጉዳት ካለ በግልጽ ዳኝነት ካልተጠየቀበት ካሳ ሊወሰን አይገባም የሰ/መ/ቁጥር 239841
#Daniel Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)/

የመንግስት ( የቀበሌ/የኪራይ) ቤቶችን በተመለከተ የፌደሬሽን ምክር ቤት የሰበር ውሳኔን በመሻር ውሳኔ አስተላለፈ።
***
#Daniel Fikadu Law Office
ከዚህ ቀደም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስንት ሰሚ ችሎት በሠ/መ/ቁ. 189707 እና በሠ/መ/ቁ. 228002 ጠቅለል ሲደረግ
ቤትን ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት አያጎናጽፍም ሠ/መ/ቁጥር 228002 አንድን ቤት ለረጅም ግዜ መያዝ ብቻውን የባለቤትነት መብት የማያጎናጽፍ በመሆኑ እንዲሁም ቤቱ የቀበሌ / የመንግስት / ቤት መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌሉበትሁኔታ በተቋሙ የመረጃ ስርአት ቅጽ 008 በቀበሌ ቤትነት መመዝገቡ ብቻ ቤቱ በመንግስትየተወረሰ የቀበሌ /የመንግስት ቤት ነው ሊያስብለው አይችልም። በአዋጅ ቁጥር 47/67 ተወርሶ ለረጅም ግዜ በመንግስት እጅ የነበረ ቤትን በሚመለከት በስህተት አላግባብ ያለህጋዊ ምክንያት ተሰጥቷል የተባለው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመከነና በመንግሰት ባለቤትነት የሚታወቅ ስለመሆኑ በተገለጸበት በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት መንግስት የወረሰው መሆኑን የሚያሳይ ቅጽ 003 እና ቅጽ 004 በሌለበት ቤቱን የመንግስት ንብረት አያሰኘውም።
የሚል ውሳኔ ወስኖ የነበረ ሲሆን ይህንን ውሳኔ የኢፌድሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው 6ተኛ የፓርላማ ዘመን 3ተኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤው በህገ መንግስት አጣሪው በቀረበለት መሰረት በመ/ቁጥር 108/15 የሠ/መ/ቁ .189707 ህገመንግስታዊነት አጣርቶ ውሳኔውን ሽሮታል።
ስለሆነም የመንግስት ቤትን ለረጅም ጊዜ ከአዋጅ 47/67 በኋላ ይዞ ያስተዳድር የነበረ ሁለቱ ቅፃች ቅፅ 003 እና 004 ባይኖሩትም ባለይዞታነቱ ይቀጥላል።

1_26_full_published_cassation_Stamped_Copy_Copy_Stamped.pdf
101 MB
ALL published Cassation Decisions in one
ALL PUBLISHED CASSATION DECISIONS IN ONE
ሁሉም የታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በአንድ ከቅጽ 1 -26
#Daniel Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)/
ALL PUBLISHED CASSATION DECISIONS IN ONE
ሁሉም የታተሙ የሰበር ውሳኔዎች በአንድ ከቅጽ 1 -26
#Daniel Fikadu /ዳንኤል ፍቃዱ (ጠበቃና የህግ አማካሪ)/
ከሳሽ ስለሚያሲይዘው የወጪና ኪሳራ ዋስትና ሰ/መ/ቁ. 218235
በፍርድ ቤት ክስ ያቀረበ ከሳሽ በክሱ ተረቺ ቢሆን ለተከሳሽ ወጪና ኪሳራ ለመክፈል ፈቃደኛ ላይሆን ይችላል በሚል ዋስትና እንዲያስይዝ ሊጠየቅ አይገባም።
የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 200(1) ለመክፈል አቅም ማጣትን አስመልክቶ የተደነገገ በመሆኑ ለመክፈል አቅሙ ካለ ፍ/ቤቱ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ፍርዱን የሚያስፈፅም በመሆኑ ለመክፈል ፈቃደኛ አለመሆን ከመነሻውም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 200(1) ዋስትና ለማስጠራት በቂ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰድ አይሆንም።
#daniel fikadu