አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
#Wagagen Bank#7 - Position

▪️1 -Archive library
▪️2 -Attorney I❤️
▪️3 -Trade service officer I
▪️4 -District Hr business partner I
▪️5 -Sr Foreign banking & Remmittance Officer
▪️6 - Sr trade service officer
▪️7 - Manager, foreclosure & debt Litigation
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3vVJy8Y

▪️Deadline - May 07/2022
#Bank of Abyssinia#

▪️1 - Legal Credit.Attorney
▪️2 - Legal Credit.Senior Attorney
▪️3 - Grade I Branch Operation Manager
▪️Find More Details Here
👇👇👇👇👇
https://bit.ly/3F7Ibbl

▪️Deadline - May 05/2022
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው።።።።።።።።።።።።።።።።
#አለ_ህግ #Ale_Hig
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Cost Sharing Directive .pdf
85.8 KB
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት ክፍያ አሰባሰብ አፈፃፀም መመሪያ
@Lawsocieties
የአሰሪና ሰራተኛ ውል.docx
20.6 KB
የቤተሰብ ውክልና #አለ_ህግ #Ale_Hig

የቤተሰብ ውክልና ፡- መሰረቱ የፍትሃብሔር ህግ አንቀጽ 2203 እና /ወይም 2205 ድንጋጌዎች ሆኖ በፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ህግ አንቀጽ 58 መሰረት ለቅርብ ዘመድ ማለትም ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት፣አያት፣ እናት ለሆኑ ሰዎች የሚሰጥ የውክልና ዓይነት ነው፡፡

ውስን ውክልና

ውስን ውክልና፡- ተወካይ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ንብረቱን በስም እና ዝርዝር መረጃውን በመጥቀስ የውክልና ስልጣን የሚሰጥበት ነው ፡፡
ሙሉ ውክልና

ሙሉ ውክልና፡- ተወካይ አጠቃላይ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቱን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ መስጠት ሳያስፈልገው በጥቅሉ ውክልና የሚሰጥበት ነው፡፡
#አለ_ህግ @Lawsocieties
አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf
3.4 MB
Share 'አዲሱ-የንግድ-ሕግ 55932.pdf'
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️
ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው።
#አለ_ህግ #Ale_Hig
አለሕግAleHig ️
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️ ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው። #አለ_ህግ #Ale_Hig
በህግ አምላክ ❗️
ቃሉ ከብዙ ዓመታት በፊት ጀምሮ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገራት ላይ መሰረት ያለው ነው።መነሻውም ሰወች ሕጉን ብቻ ሳይሆን ሕግ ያወጣውን አካል ምላሽ እንዲመለከቱና ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚያሳስብ ነው።ሰወች ህገ ወጥ ድርጊት ሲፈፅሙ ለድርጊታቸው ህገወጥነት ምላሽ የሚሰጥ አካል እንዳለ በዚሁ ቃል ያስታውሳሉ።እንዲያውም አንዳንዴ ሕጉን ያወጡ ንጉሶች ስም እየተጠራ በእነሱ አምላክ ስም ድርጊት ፈፃሚው ድርጊቱን እንዲያቆም ይጠየቅ እንደነበር ይነገራል። ይሄንን የሰማ ህገ ወጥ አካል ድርጊቱን የሚያቆመው ከድርጊቱ በሁዋላ የሚመጣበትን ምላሽ በቃሉ ውስጥ ስለሚመለከት ነው።
ሌላኛው ደግሞ ሕግን የሚሰጥ ፈጣሪ እንደሆነ ሰወች ያምናሉ።ይሄም እምነታቸው ሕግን እንዲከተሉ ምክንያት ይሆናቸዋል።በዚህ እይታ ደግሞ በሕግ አምላክ የሚለው ቃል ሰወች ፈጣሪን ፈርተው ከድርጊታቸው እጃቸውን እንዲመልሱ ምክንያት ይሆናቸዋል።በአጠቃላይ የቃሉ አንድምታ ይሄንን ይመስላል።
One Love:
#አለ_ህግ #Ale_Hig
አለሕግAleHig ️
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️ ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው። #አለ_ህግ #Ale_Hig
በህግ አምላክ ማለት አንድም ህግ ይህን እንድታደርግ አይፈቅድልህም ብታደርግም ትቀጣበታለህና በህግም ትገዘበታለህና ህግን ስለፈጠረው አምላክ ብለህ ተወኝ ለማለት የምንጠቀምበት ሲሆን
ዋናውና ቁልፉ ነገር ግን ማንም ሰው ከህግ በታች መሆኑን የሚያሳይና ህግን ማክበር እንዳለበት የሚያሳይ ነው
Erkyihun:
#አለ_ህግ #Ale_Hig
አለሕግAleHig ️
በህግ አምላክ ምን ማለት ነው❗️ ቀድሞ በጥሩ ማብራሪያ የመለሰ ሽልማት አለው። #አለ_ህግ #Ale_Hig
👉በህግ አምላክ ማለት:-
አገሬው ስለ ሕግ ሃያልነት ሲናገር "በሕግ አምላክ ሲባል እንኳን ሰው ወራጅ ውሃ ይቆማል" ይል ነበር፡፡ ሕግ ተፈጥሮንም እስከማቆም ሃይል እንዳለው አድርጎ ለመግለፅ ምን ዓይነት በሕግ የፀና እምነት ቢኖር ነበር ያስብላል፡፡ በሕግና ፍትሕ ላይ እምነት ያለው ሕዝብ ያለማንም አስገዳጅነት ለሕግ ተገዢ ነው፡፡ ክስተቶችንም ተከትሎ ለሕግ ያለውንም እምነት በተለያዬ መንገድ ይገልፃል፡፡ ግጭቶችን በጉልበት ከመፍታት በሕግ መፍታት ተመራጭ እንደሆነም ያምናል፡፡ በጉልበቱ አዳሪ ሲገጥመው ሰይፍን በሰይፍ ከመመለስ በሕግ አምላክ ቢል ይመርጣል፡፡ ከማትረባ ጉልበት በሕግ አምላክ ይሻላል የሚለውም ለዚህ ይመስላል፡፡ ስለዚህ የሕግ መከበር ሕበረተሰቡ ስለሕግና ፍትሕ ባለው አመለካከት ይወሰናል ማለት ነው፡፡ ሕግ በሕበረተሰቡ ውስጥ በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ እንዲያመጣ ከተፈለገ እያንዳንዱ ሰው ስለሕግ ያለው አመለካከት አብሮ መመለወጥና ማደግ ይኖርበታል፡፡ ሕበረተሰቡ ለሕግና ፍትሕ ያለው አመለካከት ሁለት ነገሮችን ይገልፅልናል፡፡ በአንድ  በኩል ሕብረተሰቡ ስለሕግ ያለውን እምነት ሲገልፅልን በሌላ በኩል ደግሞ የሕግ መከበር ያለበትን ደረጃ ያሳየናል፡፡

👉ዘመናዊ የፍትሕ ሥርዓት ሳይዋቀር በፊት አገሬው ስለሕግ የበላይነት የፀና እምነት ነበረው ማለት እንችላለን፡፡ አስገዳጅ ነገር ሳይኖር በአገር ደንብ ብቻ መንገድ ላይ ባላጋራውን ሲያገኘው በሕግ አምላክ ብሎ ተላላፊው መንገደኛ ጉዳዩን እንዲመለከትለት ያደርግ ነበር፡፡ ተላላፊው መንገደኛም ዳኝነቱን ተቀብሎ የግራ ቀኙን ጉዳይ ሰምቶ ይፈርዳል፡፡ ውሳኔው ከተስማማቸው ይፈጽማሉ ካልተስማቸው በአካባቢው ወዳለው ጭቃ ሹም ተያይዞ መሄድ ነው፡፡ ይህን ተላላፊ መንገደኛ ዳኛ የሕግ ሙሁር አበራ ጀንበሬ የመንገድ ዳሩ ፍርድ ቤት(የመንገድ ዳር ዳኛ) በማለት ሲገልፁት ከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት ደግሞ "ዳኛ የውሃ ወራጅ ዳኛ" በማለት ይገልፀዋል፡፡ ስያሜው ምንም ይሁን ተላላፊውን መንገደኛ ዳኛ፣ ባላጋራዎችን ተከራካሪ አድርጎ ሲያቆማቸው የነበረው ያገር ደንብና ልማድ፣ፈቃደኝነትና ለሕግና ፍትሕ የፀና እምነት መኖር  እንጅ ሌላ አስገዳጅ ሃይል አልነበረም፡፡

👉በአጠቃላይ በህግ አምላክ ማለት ለህግ ተገዢ ሁን ወይም ለህግ ብለክ ድርጊትህን አቁም ወይም ተዉ እንደማለት ነዉ፡፡
Am the one☝️:
#አለ_ህግ #Ale_Hig
Just to say thank you for your participation❗️🙏
አዲሱ_የሒሳብ_መዝገብ_አያያዝ_መመሪያ.pdf
1.1 MB
#እንድታውቁት #አለ_ህግ #Ale_Hig

የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት የቅሬታ ምንጭ ሆኖ የቆየው

" የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 152/2011 " ን በአዲስ መመሪያ እንዲተካ ማድረጉን አሳውቋል።

መመሪያውን ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት የታክስ አስተዳደሩን ቀልጣፋ ለማድረግ እና ግልጽነት የጎደላቸውን አሰራሮች ግልጽ ለማድረግ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ።

አዲሱ መመሪያ ቁጥር 176/2014 በሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 152/2011 ላይ የነበረውን አሰራር ያሻሽላል ተብሏል።

አዲሱ ወይም የተሻሻለው የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ቁጥር 176/2014 ከላይ በPDF ተያይዟል።

tikvah ethiopia

#አለ_ህግ #Ale_Hig
የፌዴራል ጠበቆች ምዝገባ - መራዘሙን ስለማሳወቅ
#አለ_ህግ #Ale_Hig
የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማኅበር በአባልነት ላቀፋቸው ጠበቆች አስፈላጊውን አገልግሎት በመስጠት ኃላፊነት እና ግዴታውን ለመወጣት ይችል ዘንድ እስከ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ

1. በድህረ-ገጽ በኦንላይን በዚህ አድራሻ http://t.ly/RzWs ወይም
2. በፍትሕ ሚኒስቴር ዋና መ/ቤት ወይም በአራዳ ምድብ ችሎት በሚገኘው የማኀበሩ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት
እንድትመዘገቡ መጠየቁ ይታወሳል።

በዚህ መሠረት በርካታ ጠበቆች በኦንላይን እና በአካል በመገኘት ምዝገባቸውን አከናውነዋል።

ምዝገባው እንዲከናወን የታሰበበት ጊዜ የበዓል ቀናት የተበራከቱበት መሆኑን በመገንዘብ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ለመመዝገብ ያልቻሉ ጠበቆች ምዝገባውን እንዲያከናውኑ ተጨማሪ ቀን መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ማኅበሩ አምኗል።

በዚህ መሠረት ያልተመዘገባችሁ የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች በሙሉ የምዝገባ ጊዜው

ከሰኞ ከግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ማኅበሩ ያሳስባል።

በኦንላይን ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ http://t.ly/RzWs

በአካል ተገኝተው ለመመዝገብ፦
1. የጥብቅና ደብተርዎን መያዝዎን አይዘንጉ፤
2. የጥብቅና ደብተርዎን የፊት ገጽ እና ፈቃድዎ የታደሰበትን የሚያሳየውን ክፍል ኮፒ አድርገው መያዝዎን አይዘንጉ
3. ለማኅበሩ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ መያዝዎን አይዘንጉ፤
4. የግብር መለያ ቁጥር መያዝዎን አይርሱ፤

የኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማኅበር
#አለ_ህግ #Ale_Hig