አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.85K photos
25 videos
1.86K files
3.57K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
የቤት ኪራይ ውል - አንኳር ነጥቦች
_____

የውሉ ሥርዓት፡-
የቤት ኪራይ ውል ተዋዋይ ወገኖች፣ ማለትም አከራይ እና ተከራይ፣ በመረጡት ሥርዓት (በጽሑፍ ወይም በቃል) ሊደረግ ይችላል፡፡ ሕግ በጽሑፍም ሆነ በቃል ለሚደረጉ የቤት ኪራይ ውሎች እኩል ጥበቃ ይሰጣል፡፡

የኪራዩ መጠን እና የሚከፈልበት ጊዜ፡-
አከራይና ተከራይ በቤት ኪራይ ውል በስምምነት ከሚወስኗቸው ጉዳዮች መካከል የኪራዩ የዋጋ ልክ እና ኪራዩ የሚከፈልበት ጊዜ ይጠቀሳሉ፡፡ አከራይና ተከራይ በኪራይ ውሉ የኪራዩን የዋጋ መጠን እና ኪራዩ የሚከፈልበትን ጊዜ ካልወሰኑ፤ በፍትሐብሔር ሕጋችን የተቀመጡ ድንጋጌዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡ የፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀጽ 2950(2) አከራይና ተከራይ በውላቸው ውስጥ የኪራዩን የዋጋ መጠን ካላስቀመጡ ወይም በሚያጠራጠር ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ባለሥልጣናት በወሰኑት ታሪፍ መሠረት ወይም የተወሰነ ታሪፍ የሌለ እንደሆነ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል የኪራዩ የዋጋ መጠን እንደሚወሰን ይደነግጋል፡፡ በተመሳሳይ፣ አከራይና ተከራይ ኪራዩ የሚከፈልበትን ጊዜ በውላቸው ካልተወሰኑ ወይም ካልተስማሙ ተፈጻሚ የሚሆነው ደንብ በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀጽ 2951 ሠፍሯል፡፡ በዚሁ መሠረትም የቤት ኪራይ ውሉ ለአንድ ዓመት ወይም ለተወሰኑ ብዙ ዓመታት ተደርጎ እንደሆነ ኪራዩ በየሦስት ወር መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡ ሆኖም የቤት ኪራይ ውሉ በጣም አጭር ለሆነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ በየወሩ መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡

የተከራዩትን ቤት ስለማደስ፡-
በቤት ኪራይ ውል ሊወሰን ወይም ስምምነት ሊደረግበት የሚችለው ሌላኛው ጉዳይ የቤቱ እድሳት ነው፡፡ በፍትሐብሔር ሕጉ አንቀጽ 1954 መሠረት ማደስ የቤቱን መዝጊያዎችን ወይም መስኮቶችን፣ የቤቱን ወለሎችን ወይም ንጣፎችን፣ የውሃ መስመሮችንና የፍሳሽ ማስወገጃዎችን ማደስ እና ቤቱን የማፅዳት እና በደንብ የመያዝ ተግባሮችን ያጠቃልላል፡፡ ተከራይ ለማደስ የተዋዋለውን የተከራየውን ቤት በራሱ ኪሳራ (ወጭ) ለማደስ እንደሚገደድ በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀፅ 1953 ተደንግጓል፡፡ ሆኖም ግን ቤቱ በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር የተበላሸ ሲሆን ተከራዩ ቤቱን የማደስ ስራ መፈፀም አይጠበቅበትም፡፡ ይሁን እንጂ በቤት ኪራይ ውሉ ውስጥ በማርጀት ወይም ካቅም በላይ በሆነ ነገር የተበላሹትንም ጭምር አድሳለው በማለት ተከራዩ የተስማማ ከሆነ እንዲያድስ ይገደዳል፡፡

የተከራዩትን ስለ ማከራየት (የኪራይ ኪራይ)፡-
ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ ለማከራየት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ተከራዩ የተከራየውን ቤት ሊያከራይ የሚችለው አከራዩ ለዚህ የኪራይ ኪራይ ተቃውሞ ከሌለው ብቻ ነው፡፡

የቤት ኪራይ ክፍያን በጊዜው አለመክፈል፡-
ተከራይ የቤት ኪራይ ክፍያውን በጊዜው ያልከፈለ እንደሆነ የሚያስከትለው ውጤት በፍትሐብሔር ሕጋችን አንቀፅ 2952 ሰፍሯል፡፡ የቤት ኪራይ ውሉ ለአንድ ዓመት ወይም ከአንድ ዓመት ለበለጠ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ አከራዩ የሠላሳ ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፤ የቤት ኪራይ ውሉ ለአጭር ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ ደግሞ አከራዩ የአስራ አምስት ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተከራዩ ኪራዩን ያልከፈለ እንደሆነ አከራዩ ውሉን የሚያቆርጥ መሆኑን ለተከራዩ ያሳውቃል፡፡ በዚህ በተሰጠው የማስጠንቀቂያ ጊዜ ውስጥ ተከራዩ ያልከፈለ እንደ ሆነ አከራይ ውሉን ለማቋረጥ ይችላል፡፡

የቤት ኪራይ ውል የሚፈርስባቸው ምክንያቶች፡-
በአከራይና ተከራይ መካከል የተደረገ የቤት ኪራይ ውል በልዩ ልዩ ምክንያቶች ሊፈርስ ወይም ሊቋረጥ ይችላል፡፡ የቤት ኪራይ ውሉ ለተወሰነ ጊዜ ተደርጎ የውሉ ጊዜ ሲያበቃ፤ ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት ውላቸውን ለማቋረጥ ሲስማሙ፤ ተከራይ ኪራዩን በጊዜው ባለመክፈሉ አከራዩ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥቶት በዚህ ጊዜ ውስጥም ያልከፈለ እንደሆነ፤ አከራይ ቤቱን ፈልጎት ለተከራይ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ወይም ተከራዩ ቤቱን መልቀቅ ፈልጎ ለአከራዩ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት የቤት ኪራይ ውል ሊቋረጥ ይችላል፡
Vacancy at Commercial Bank of Ethiopia[For Fresh Graduate]

👇Position: Legal Trainee
https://t.me/lawsocieties
Experience: 0 years / Fresh Graduates /
Qualification: LLB Degree
Place of Work : All Districts

📌Deadline: March 31, 2022

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ
👉Read Detail:-https://bit.ly/38Fw1Ht
contract 6.docx
21.9 KB
Share 'contract 6.docx'
የመኪና ሽያጭ ውል ስምምነት
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ
contract 9.docx
20.8 KB
Share 'contract 9.docx'
የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል
#አለ_ህግ
https://t.me/lawsocieties
#አለ_ህግ ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com

https://t.me/lawsocieties
#Share
#አለ_ህግ
#አለ_ስራ
ተገልጋዮች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል (የመኖሪያ ቤት፣ የሊዝ መብት፣) አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ተቋማችን ሲመጡ የሚከተሉትን ቅድመሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
• የባለቤትነት ካርታ (ጀርባ ማህተም ያረፈበት) ካርታው ዲጂታል ከሆነ የጀርባ ማህተም አያስፈልግም)፡፡
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው ስም የተመዘገበ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ (ለምሳሌ ካርታ..)፤
• የሻጭ እና የገዥ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ሻጭ/ገዥ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ፤
• የሻጭ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• የንግድ ድርጅት ቤት ሲሆን የዋና ንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
• የገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባዔ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው፣ የስጦታ ተቀባዩ እና የሁለት ምስክሮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
#የኮንዶሚኒየም ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• የኮንዶሚኒየሙ ባለቤት ቤቱን ከተረከበው አምስት አመት ስለመሙላቱ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ
• የተዋዋዬች እና የሁለት ምስክሮች በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ
በማህበር የተሰራ ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• የባለቤትነት ካርታ ጀርባው ስለትክክለኛነቱ በማህተም የተረጋገጠ፤ ከክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ዕዳ ዕገዳ እንደሌለበት የማረጋገጫ ደብዳቤ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር
https://t.me/GudayAsfetsami
ተገልጋዮች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል (የመኖሪያ ቤት፣ የሊዝ መብት፣) አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ተቋማችን ሲመጡ የሚከተሉትን ቅድመሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• የባለቤትነት ካርታ (ጀርባ ማህተም ያረፈበት) ካርታው ዲጂታል ከሆነ የጀርባ ማህተም አያስፈልግም)፡፡
• የሻጭ እና የገዥ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ሻጭ/ገዥ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ(ውክልና)፤
• የሻጭ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• የንግድ ድርጅት ቤት ሲሆን የዋና ንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
• የገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባዔ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው፣ የስጦታ ተቀባዩ እና የሁለት ምስክሮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
#የኮንዶሚኒየም ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-

• የኮንዶሚኒየሙ ባለቤት ቤቱን ከተረከበው አምስት አመት ስለመሙላቱ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ
• የተዋዋዬች እና የሁለት ምስክሮች በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ
በማህበር የተሰራ ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• የባለቤትነት ካርታ ጀርባው ስለትክክለኛነቱ በማህተም የተረጋገጠ፤ ከክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ዕዳ ዕገዳ እንደሌለበት የማረጋገጫ ደብዳቤ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• የተዋዋዬች እና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ፤
የሊዝ መብት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የሊዝ ውል፤
• የሚተላለፈው የሊዝ መብት የንግድ ድርጅት ከሆነ ከገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ፤
• የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ ያስፈልጋል፡፡

#ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ አገልግሎቶችን ለማከናወን እያንዳንዱ አገልግሎት በተናጠል 45 ደቂቃ የሚወስድ ነው፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ራሰዎንና ሌሎችን ከሙስና እና እንግልት ይታደጉ፡፡

የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ፡፡https://t.me/GudayAsfetsami
የፌዴራል_ፍርድ_ቤት_መር_አስማሚነት_መመሪያ_ቁጥር_12_2014.PDF
4.5 MB
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥ 1234/2013 አንቀጽ 45(8) እና 48(4) በተሰጠው ስልጣን መሰረት የፌዴራል ፍርድ ቤት መር አስማሚነት መመሪያ ቁጥር 12/2012 አወጥቷል፡፡ የመመሪያውን ዲጂታል (ፒዲኤፍ) ቅጂ እነሆ ብለናል፡፡
https://t.me/lawsocieties
#Share
#አለ_ህግ
Awash Insurance Company ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
👩 position:- 1: Junior Recovery Case Officer[For Fresh Graduate]
2: Office Administrator/Secretary
3: Attorney I
4: Manager, Budget Collection, Disbursement and Investment
https://bit.ly/36sQnpv
📚 ትምህርት ዓይነት እና ደረጃ፡- MA in Financial Management or Accounting, LLB Degree in Law, iploma/Level IV in Secretarial Science and Office Management or similar field of study
🇪🇹 የስራ ቦታ:- Kilinto
🧭የምዝገባ ጊዜ /Deadline/: እስከ መጋቢት 19 /2014 ዓ.ም

https://t.me/lawsocieties
#Share
#አለ_ህግ
#አለ_ስራ
ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ይህንን ጥረት ከግብ ለማድረስ ተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት እና ማሟላት ስላለባቸው መስፍርቶች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

ለዚህም ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጠቃሚ መረጃዎችን በዚሁ ገጽ ላይ የምናስተላልፍ ይሆናል ፡፡
ክቡራን ተገልጋዮቻችን መረጃዎችን ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ዜጎችን ከእንግልትና ከሙስና እንዲታደጉ በማክበር እንጠይቃለን፡፡

#ጠቃሚ መረጃዎች፡

•ማናቸውም ሰነዶች ለአገልግሎት ሲቀርቡ በዕለቱ መቅረብ አለባቸው፡፡

•በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ ከጣቢያ የአጃቢውን ፖሊስና የግለሰቡን ስም የሚገልፅ ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• በፍርድ የተከለከለ ሰውን ንብረት በተመለከተ ፍርድ ቤት ልዩ ትዕዛዝ ካልተሰጠ በስተቀር ለሌላ ማስተላለፍ አይችልም፡፡

•መስማት የተሳናቸውና በምልክት ቋንቋ የሚግባቡ ሰዎች ወደ ተቋማችን ለአገልግሎት ሲቀርቡ መስማት ከተሳናቸው ማህበር አስተርጓሚ ሰው በደብዳቤ ተመድቦላቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

•የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች ጉዳቱ ንብረታቸውን ለማስተዳደር የማያስችላቸው እንደሆነ በፍርድ ቤት ሞግዚት እንዲሾምላቸው ጠይቀው በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ቀርበው ውል መዋዋል የማይችሉ እንደሆነ በሞግዚታቸው አማካኝነት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

•የአስተርጓሚነት ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ የውጭ ዜጐች ከኤምባሲወይም ቆንስላ ቢሮ የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አልፎ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/lawsocieties
የኢትዮጵያ የኩባንያ ሕግ (3ኛው የተሻሻለ እትም) በቅርብ ቀን ታትሞ ይወጣል፡፡ ስለ 2ኛው እትም የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችን በመስጠት ላበረታታችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬን እያቀርብኩ ስለ 3ኛው እትም ጥቂት መረጃ ልስጣችሁ፡፡

የገጽ ብዛት፡478
የመጽሐፉ መጠን፡ B5 (width 17.6 cm Height 25 cm)
ISBN 978-99944-3-573-1
አከፋፋይ፡ አንከቡት መጻሕፍት

ይህ 3ኛ እትም ከአዲሱ የንግድ ሕግ አንጻር ከእንደገና የተከለሰ ሲሆን አምስት አዳዲስ ምዕራፎችም ተካተውበታል፡፡ እነዚህም፡-

ስለ ባለ አንድ አባል ኩባንያ
ስለ ካፒታል/አክሲዮን ገበያ አሰራር
ስለ ተቧደኑ ኩባንያዎች
ስለ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነት
በኩባንያዎች ውስጥ ስለሚደረጉ መሠረታዊ ለውጦች (ለምሳሌ የካፒታል ለውጥ፣ ውህደት፣ የማህበር ዓይነት መለወጥ፣…)

ስለ መጽሐፉ ከመግቢያው ላይ ተቀንጮቦ የተወሰደ ጥቂት ማብራሪያ ይሄውላችሁ፡-

ይህ መጽሐፍ የሚያጠነጥነው ኩባንያ እንዴት እንደሚቋቋም፣ እንዴት እንደሚተዳደርና እንደሚፈርስ ነው፡፡ መጽሐፉ ከአዲሱ የንግድ ሕግ፣ ከተለያዩ አዋጆች፣ የፍርድ ውሳኔዎችና የሌሎች አገራት ተሞክሮዎች በመነሳት የኢትዮጵያን የኩባንያ ሕግ ይተነትናል፡፡
የኢትዮጵያ የኩባንያ ሕግ (3ኛው የተሻሻለ እትም) በቅርብ ቀን ታትሞ ይወጣል፡፡ ስለ 2ኛው እትም የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችን በመስጠት ላበረታታችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬን እያቀርብኩ ስለ 3ኛው እትም ጥቂት መረጃ ልስጣችሁ፡፡

የገጽ ብዛት፡478
የመጽሐፉ መጠን፡ B5 (width 17.6 cm Height 25 cm)
ISBN 978-99944-3-573-1
አከፋፋይ፡ አንከቡት መጻሕፍት

ይህ 3ኛ እትም ከአዲሱ የንግድ ሕግ አንጻር ከእንደገና የተከለሰ ሲሆን አምስት አዳዲስ ምዕራፎችም ተካተውበታል፡፡ እነዚህም፡-

ስለ ባለ አንድ አባል ኩባንያ
ስለ ካፒታል/አክሲዮን ገበያ አሰራር
ስለ ተቧደኑ ኩባንያዎች
ስለ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነት
በኩባንያዎች ውስጥ ስለሚደረጉ መሠረታዊ ለውጦች (ለምሳሌ የካፒታል ለውጥ፣ ውህደት፣ የማህበር ዓይነት መለወጥ፣…)

ስለ መጽሐፉ ከመግቢያው ላይ ተቀንጮቦ የተወሰደ ጥቂት ማብራሪያ ይሄውላችሁ፡-

ይህ መጽሐፍ የሚያጠነጥነው ኩባንያ እንዴት እንደሚቋቋም፣ እንዴት እንደሚተዳደርና እንደሚፈርስ ነው፡፡ መጽሐፉ ከአዲሱ የንግድ ሕግ፣ ከተለያዩ አዋጆች፣ የፍርድ ውሳኔዎችና የሌሎች አገራት ተሞክሮዎች በመነሳት የኢትዮጵያን የኩባንያ ሕግ ይተነትናል፡፡ የኩባንያ ሕግ ዋና ትኩረት ሰዎች ኃላፊነት የተወሰነበትን አደረጃጀት (ኩባንያን) ተጠቅመው በጋራ የንግድ ስራን ሲሰሩ የሚፈጠሩ ችግሮችን መፍታት ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች በዋናነት ሦስት ናቸው፡፡ አንደኛው የኩባንያው አስተዳዳሪዎች ባለአክሲዮኖችን እንዳይበድሉ መከላከል ነው፤ ሁለተኛው አብላጫ ድርሻ ያላቸው አነስተኛ ድርሻ ያላቸውን እንዳይበድ መከላከል ነው፡፡ ሦስተኛው ጉዳይ ሰዎች የኩባንያ አደረጃጀትን በመጠቀም በሦስተኛ ወገኖች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ መከላከል ነው፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ርዕሰ-ጉዳዮች (ከክፍል ሁለት እስከ ክፍል አራት ያሉት) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እነዚህን ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ሕግ እንዴት እንደሚመልስ የሚተነትኑ ናቸው፡፡
መጽሀፉ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበ ነዉ፡፡ ክፍል አንድ ስለ ንግድ ማህበራት በጠቅላላው የሚዳሰስበት ሲሆን በውስጡ ሁለት ምዕራፎችን ይዟል፡፡ እነዚህም ስለ ኩባንያዎች የንግድ ምዝገባ እና ፈቃድ የሚናገረው ምዕራፍ አንድ፣ እና ስለ ንግድ ማህበራት ዓይነቶች እና ባህሪዎቻቸው የተተነተነበት ምዕራፍ ሁለት ናቸው፡፡ በምዕራፍ አንድ የሚነሱት ሀሳቦች በጥቅሉ ሁሉንም ነጋዴዎች የሚመለከቱ በመሆናቸው ለግል ንግድም (sole proprietorship) ተፈጻሚ የሆኑ ሕጎች የተዳሰሱበት ነው፡፡ ለዚህኛው ምዕራፍ ምንጭ የሆኑ ሕጎች የአዲሱ ንግድ ሕግ አንደኛ መጽሐፍ እና የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ፣ አዋጁን ለማስፈጻም የወጡ ደንቦችና መመሪያዎች ናቸው፡፡ ምዕራፍ ሁለት ሁሉንም ዓይነት የንግድ ማህበራት የሚመለከቱ የንግድ ሕጉ ሁለተኛው መጽሐፍ ጠቅላላ ድንጋጌዎች የተዳሰሱበት ክፍል ነው፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ እንደሚያመለክተው ትኩረቱ ኩባንያዎች ላይ ስለሆነ የሽርክና ማህበራት በዚህ ምዕራፍ ብቻ ነው የተዳሰሱት፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የሽርክና ማህበር ዓይነት ራሱን በቻለ ንዑስ ርዕስ ስር ቀርቧል፡፡
ክፍል ሁለት ስለ አክሲዮን ማህበር የቀረበበት ክፍል ሲሆን በውስጡ ብዙ ምዕራፎችን ይዟል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ስምንት ምዕራፎች አሉ፡፡ እነዚህም ከምዕራፍ ሦስት እሰከ አስር ያሉት ሲሆኑ ስለአክሲዮን ማህበር አመሰራረት፣ ስለ አክሲዮን ማህበር ካፒታልና አጠባበቁ እንዲሁም ስለ አክሲዮን፣ ስለ ኩባንያዎች መልካም አስተዳደር፣ ስለ ዳይሬክተሮች ቦርድ፣ ስለ ኩባንያ ኦዲተር፣ ስለ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ስለ አነስተኛ ባለአክሲዮኖች ጥበቃ፣ ስለ ኩባንያዎች መግለጫ እና ስለ ካፒታል/አክሲዮን ገበያ የሚዳስሱ ክፍሎች ናቸው፡፡የመጨረሻው ስለ ካፒታል ገበያ የሚዳሰስበት ክፍል አዲሱ የካፒታል ገበያ አዋጅ ወደ ስራ ሲገባ በአብዛኛው ተፈጻሚነቱ የአክሲዮን ማህበራት ላይ ስለሚሆን በዚህ ረገድ ከአክሲዮን ማህበራት ሕግ ጋር ያለውን ዝምድና እና ተፈጻሚነት ለማብራራት ታስቦ የገባ ምዕራፍ ነው፡፡
ክፍል ሦስት በኢትዮጵያ ውስጥ በብዛት እየተሰራባቸው ስላሉት ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት የተዳሰሰበት ክፍል ነው፡፡ ክፍሉ ከምዕራፍ አስራ አንድ እሰከ ምዕራፍ አስራ አራት ያሉትን አራት ምዕራፎች ይይዛል፡፡ ምዕራፍ አስራ አንድ ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አመሠራረት ይዳስሳል፡፡ ምዕራፍ አስራ ሁለት ስለ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ካፒታል እና አክሲዮን ይቀርብበታል፡፡ እንዲሁም ምዕራፍ አስራ ሦስት ስለ ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ማህበር አካላት፣ ስልጣንና ኃላፊነት የተዳሰሰባቸው ክፍሎች ናቸው፡፡ በዚህ ክፍል የመጨረሻው ምዕራፍ ስለ ባለአንድ አባል ኃለፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የሚዳሰስበት ነው፡፡ ይህ በአዲሱ የንግድ ሕግ ከተከዋወቁት የኩባንያ ዓይነቶች አንደኛው ነው፡፡ ባለአንድ አባል ኩባንያ የኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ልውጥ (variant) ስለሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ ይቀርባል፡፡
ክፍል አራት ሌሎች ልዩ ልዩ ርዕሰ-ጉዳዮች የሚደሰሱበት ክፍል ነው፡፡ ይህም ከምዕራፍ አስራ አምስት እስከ ምዕራፍ አስራ ስምንት ያሉትን አራት ርዕሶች የሚሸፍን ሲሆን በሌሎች ክፍሎች ውስጥ ሊቀርቡ የማይችሉ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ ርዕሶች የተዳሰሱበት ክፍል ነው፡፡ ምዕራፍ አስራ አምስት ስለ መሠረታዊ ለውጦች የቀረበበት ሲሆን ኩባንያዎች ከምስረታ ጀምሮ እስከ መፍረስ ድረስ በሚኖራቸው ዕድሜ የሚያልፉባቸው መሠረታዊ ለውጦች የሚቀርብበት ነው፡፡ የመሠረታዊ ለውጥ ዓይነቶች፣ አደራረጋቸው እና በለውጥ የማይስማሙ አባላት መብት በዚህ ምዕራፍ ይቀርባል፡፡ ምዕራፍ አስራ ስድስት ስለ ኩባንያዎች መቧደን ሲሆን የቡድን ዓይነቶች፣ የእናት ኩባንያዎች እና የተቀጥላዎች ግንኙነት፣ የተቀጥላ ኩባንያ አነስተኛ ባለአክሲዮኖችና የባለገንዘቦች መብቶችን የተመለከቱና ተያያዥ ሀሳቦች ይቀርቡበታል፡፡ ይህ በአዲሱ የንግድ ሕግ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ርዕስ ነው፡፡
ምዕራፍ አስራ ሰባት ስለ ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነት ነው፡፡ ይህም ኩባንያዎች በማህበረሰብ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት እንደመሆናቸው ያለባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት ትክክለኛ አረዳድና አተገባበር የሚቃኝ ምዕራፍ ነው፡፡ የመጨረሻው ምዕራፍ አስራ ስምንት ስለ ኩባንያዎች መፍረስና ሂሳብ መጣራት የሚቀርብበት ይሆናል፡፡ ይህ ምዕራፍ የአክሲዮን ማህበርን እና ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበርን የመፍረስ፣ የሂሳብ ማጣራት እና የመዝጋት ሂደት እና ሕጋዊ ውጤት የሚተነትን ክፍል ነው፡፡
#Share #Ale_Law
#አለ_ህግ #Ale_Law
Forwarded from አለሕግAleHig ️ (Lawyer Mike 🔊የህግ ባለሙያ)
#አለ_ህግ ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጆች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ክሶች፣ የውል ፎርሞች፤ መፅሐፍቶች 🔴ሁሉም ሕጎች በአንድ🔴 All in one, for All.
አለ_ህግ፣ መሰረታዊ የህግ መረጃ እውቀት፤ ሀብት እና ሀይል ነው። contact us: @LawsocietiesBot or email us: lawsocieties@gmail.com

https://t.me/lawsocieties
#Share
#አለ_ህግ
#አለ_ስራ
Lawyers for Human Rights (LHR) is pleased to announce the signing of a Memorandum of Understanding (MoU) with Abbay Media. Both parties have agreed to strengthened and collaborate on their own respective roles in bringing social change that is favourable to Human rights and the protection of Human Rights in general.

The joint effort will reinforce the contribution of civil societies and media engagement in the human rights space; resulting in much better cooperation and interaction for better protection and promotion of human rights values.

#Ethiopia #HumanRight #HumanRightLawyers #LawyersforHumanRights #LHR #media #abbay