አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ይህንን ጥረት ከግብ ለማድረስ ተገልጋዮች ስለሚፈልጉት አገልግሎት እና ማሟላት ስላለባቸው መስፍርቶች በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

ለዚህም ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ጠቃሚ መረጃዎችን በዚሁ ገጽ ላይ የምናስተላልፍ ይሆናል ፡፡
ክቡራን ተገልጋዮቻችን መረጃዎችን ለሌሎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ዜጎችን ከእንግልትና ከሙስና እንዲታደጉ በማክበር እንጠይቃለን፡፡

#ጠቃሚ መረጃዎች፡

•ማናቸውም ሰነዶች ለአገልግሎት ሲቀርቡ በዕለቱ መቅረብ አለባቸው፡፡

•በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ ከጣቢያ የአጃቢውን ፖሊስና የግለሰቡን ስም የሚገልፅ ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• በፍርድ የተከለከለ ሰውን ንብረት በተመለከተ ፍርድ ቤት ልዩ ትዕዛዝ ካልተሰጠ በስተቀር ለሌላ ማስተላለፍ አይችልም፡፡

•መስማት የተሳናቸውና በምልክት ቋንቋ የሚግባቡ ሰዎች ወደ ተቋማችን ለአገልግሎት ሲቀርቡ መስማት ከተሳናቸው ማህበር አስተርጓሚ ሰው በደብዳቤ ተመድቦላቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

•የአካል ጉዳት ያለባቸው ግለሰቦች ጉዳቱ ንብረታቸውን ለማስተዳደር የማያስችላቸው እንደሆነ በፍርድ ቤት ሞግዚት እንዲሾምላቸው ጠይቀው በደረሰባቸው የአካል ጉዳት ምክንያት ቀርበው ውል መዋዋል የማይችሉ እንደሆነ በሞግዚታቸው አማካኝነት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

•የአስተርጓሚነት ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ የውጭ ዜጐች ከኤምባሲወይም ቆንስላ ቢሮ የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አልፎ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/lawsocieties
#ጠቃሚ መረጃ

የውክልና ስልጣን መሻር እና መተዉ:-
1.1 . ስልጣን ስለመሻር
በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 2226(1)ስለ ሿሚው ውክልናን መሻር በሰፈረው ድንጋጌ ሿሚው የጊዜ እና የሁኔታ ገደብ ሳይደረግበት በራሱ ግንዛቤ አስፈላጊ መስሎ በታየው ወይም ባሰበው ጊዜ ሁሉ ለእንደራሴው የሰጠውን የውክልና ስልጣን ማንሳት እና በመካከላቸው የነበረውን ግንኙነት ማቋረጥ ይችላል፡፡

ይህን ለማድረግ በፍትሐብሄር ህግ ስለ ውሎች በጠቅላላው በሚል ርዕስ ስር ከተደነገገው በተለየ መልኩ ሿሚው ውክልናውን የሚሽር ስለመሆኑ የቅድሚያ ማስጠንቀቀያ ለእንደራሴው እንዲሰጥ አይገደድም፡፡

በመሆኑም የውክልና ሥልጣን ለመሻር በፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 2226(1) በተቀመጠዉ መሠረት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ዝርዝር እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል።

• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መሻሪያ ሰነድ፤

• የውክልና ሻሪው ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን መኖር ፤

• የሻሪ ወይም የሻሪዎች መታወቂያ፤

• ቀደም ሲል የተረጋገጠና የተመዘገበ የውክልና ሥልጣን ሰነድ፤

• ውክልናዉን ለመሻር የቀረበው የንግድ ማህበር ከሆነ ፈራሚው የሚሻረውን ውክልና የሰጠው ሥራ አስኪያጅ ካልሆነ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ የተሾመበት ቃለጉባኤ።

1.2. የውክልና ስልጣን ስለመተው

ወካዩ የውክልና ግንኙነቱን ማቋረጥ በፈለገ በየትኛውም ጊዜ ሁሉ ስልጣኑን የመሻር መብት እንዳለው ሁሉ እንደራሴውም ስልጣኑን ላለመጠቀም ወይም ለመተው በፈለገ ጊዜ ሁሉ ስልጣኑን ሊተው እና ሊያቆም ይችላል፡፡

ይሁንና ከወካዩ ስልጣን በተለየ መልኩ ተወካዩ ስራውን ለማቆም በወሰነ ጊዜ አስቀድሞ ወካዩን የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡ህጉ ይህንን ግዴታ ያደረገበት ምክንያት እንደራሴው ስራውን በሚያቆም ጊዜ ንብረቱ ወይም ስራው ከጠባቂ ማጣት የተነሳ ለብልሽት፣ለብክነት ወይም ለጥፋት እንዳይዳረግ በማሰብ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት የውክልና ሥልጣን ለመተው (በፍ/ህግ ቁጥር 2229(1)መሠረት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ዝርዝር፤

• በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣንን መተው ሰነድ፣

• ውክልናውን የሚተወው ሰው ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን መኖር ፣

• ውክልናውን የሚተወው ሰው/ዎች መታወቂያ፣

• ቀደም ሲል የተረጋገጠና የተመዘገበ የውክልና ሥልጣን ሰነድ፣ አስፈላጊ ነው፡፡

ከህግ ጥ/ማ/ማ/የስራ ክፍል፤
https://t.me/lawsocieties