አለሕግAleHig ️
16.2K subscribers
2.84K photos
25 videos
1.86K files
3.56K links
ከጠበቃና የሕግ አማካሪ
አማራጭ የሕግ እውቀትና አገልግሎት
Alternative legal enlightenment & Service
Website: alehig.com
https://linktr.ee/alehig
WhatsApp👉 #+251920666595
Telegram👉 @MikiasMelak
የሕግ ምክርና ድጋፍ፣ የተለያዩ ህጎች፤ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ #የሕግ_መረጃ
Download Telegram
ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በንግድ ሕጉ
...........#ከላይ #የቀጠለ........

2. የባለ አንድ አባል ኃለፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር አስፈላጊነት
በአገራችን የንግድ ሕግ መሠረት የንግድ ማህበር ወይም ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የአባላት ቁጥር ቢያንስ ሁለት መሆን ይኖርበታል ፡፡ ነገር ግን ይህ መስፈርት የንግድ ማኅበራት ከሚቋቋሙበት ዓላማ፤ አሁን አገሪቱ ከምትከተለው ነጻ የገበያ ሥርዓትና በወቅቱ ተቀባይት እያገኘ ከመጣው ዓለም አቀፍ የንግድ አሠራር ልምድ ጋር በሚከተሉት ምክንያቶች የሚጣጣም አይደለም፡፡ የመጀመሪያው ባለሀብቶች በንግድ ማኅበር ተደራጅተው እንዲሠሩ የተደረገበት ዋናው ዓላማ ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ በሚለው ብሂል የንግድ ሥራው የሚያስፈልገውን አዋጭ የንግድ ሐሳብና ካፒታል በጋራ አመንጭተው ወደ ንግድ ሥራ ቢገቡ ውጤታማ ይሆናሉ በሚል እሳቤ ነው፡፡ የንግድ ሕጉ በወጣበት በ1952 ዓ.ም በሀገሪቱ ያሉ ባለሀብቶች ያላቸው የካፒታል መጠን ብቻቸውን ማህበር ለመመስረት የሚያስችላቸው አይደለም የሚል አስተሳሰብ ስለነበረና በተጨባጭም በወቅቱ የነበረው የካሽ ገንዘብ እንቅስቃሴ አነስተኛ ስለነበረ ህጉ ይህ ታሳቢ አድርጎ እንደወጣ መረዳት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ይህ አስተሳብ ሕጉ በወጣበት ዘመን ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በቂ የንግድ ሐሳብና ካፒታል ያላቸው ባለሀብቶች ከፍላጎታቸው ውጭ ከሌሎች ጋር የግድ እንዲጣመሩ ማስገደዱ ባለሀብቶች በነጻነት በመረጡት የንግድ መስክ ተሠማርተው ራሳቸውንም ሆነ አገራቸውን እንዳይጠቅሙ እንቅፋት ይፈጥራል፡፡

አሁን በተግባር እየታየ እንዳለው የሕጉን አነስተኛ የአባላት ቁጥር ግዴታ ለማሟላት እና ሌላ ሰው በሚያቋቁመው የንግድ ኩባንያ ውስጥ ላለማስገባት ሲሉ ምንም የንግድ ሐሳብም ሆነ የገንዘብ አስተዋጽኦ ያላደረጉ የቤተሰብ አባላትንና ሌሎች የቅርብ ሰዎቻቸውን አባል አያደረጉ ማህበር ይመሰርታሉ፡፡ ይህም በአንድ በኩል ምንም አስተዋጽኦ የሌላቸውን ሰዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በሁለትና ከዚያ በላይ በሆኑ ሰዎች የተመሠረቱ ኃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ኩባንያዎች አባላት ቁጥር በተለያየ ምክንያት ለምሳሌ ያህል በባለትዳሮች፣ በቤተ ዘመዳሞችና በጓኛሞች ወዘተ መካከል አለመግባባት ሲፈጠር አንዱ አባል ከማኅበሩ የሚወጣበት ሁኔታ ሲከሰት ኩባንያው ውጤታማ ቢሆንም በህጉ በአንድ አባል መቀጠል ስለማይቻል እንዲፈርስ ይደረጋል ፡፡ ግለሰብ ባለሀብቶች ከፍላጎታቸው ውጭ ከሌሎች ሰዎች ጋር የንግድ ማኅበር እንዲያቋቁሙ መገደዳቸው የሚያስከትለው ሌላው ችግር የንግድ ማኅበር ከሌላ ሰው ጋር ላለማቋቋም ሲሉ ወደ ግል ንግድ እንዲያተኩሩ አድርጓል፡፡ ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው በአገራችን ከኩባንያዎች ቁጥር ይልቅ የግለሰብ ንግድ ከፍተኛውን ቁጥርና የገበያ ድርሻ ይዞ ይገኛል ፡፡ ይህ አሠራር የተለያዩ ችግሮችን ማስከተሉ ይነገራል፡፡ አንደኛ ለንግድ ሥራ የሚመድቡትን ሀብት ከግል ንብረታቸው ነጥለው በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማስተዳደር የሚኖራቸውን ዕድል የሚዘጋ ነው፡፡ ሁለተኛው በኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ አቋቁመው ከኩባንያው በላይ የሚመጣ ዕዳን ወደ ግል ሀብታቸው እንዳይተላለፍ የሚገድበውን ዕድል ያሳጣል፣ በዚህም የተነሣ በዕዳ እንዳይጠየቁ ንብረታቸውን የሚያሸሹበት ሁኔታ ስለሚፈጥር ሕገ ወጥነትንን ያበረታታል፡፡

ሌላው ችግር በግላቸው ኩባንያ መሥርተው ከጊዜ በኋላ የኩባንያውን ዕድገትና ውጤት እያዩ ሌሎች ግለሰቦችን በመሳብ ተጨማሪ ካፒታል እንዳያሰባስቡና የንግዱን ሥራ ለማስፋፋት ጥረት እንዳያደርጉ እንቅፋት ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህም በአገራችን የንግድ ኩባንያዎች እንዳይስፋፉ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከመንግሥት ቁጥጥር አኳያም ሲታይ ከኃላፊነታቸው የተወሰኑ የግል ኩባንያዎች በተለየ ሁኔታ የግለሰብ ንግድ የተደራጀ አመራርና የኦዲት እንዲሁም ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ ስላልተጣለባቸው አሠራራቸው ሕግን የተከተለ ለመሆኑ መንግሥት ለማረጋገጥ የሚያስችልበት ሁኔታ በጣም የጠበበ ነው፡፡

አንድ ሰው ብቻውን ኩባንያ እንዲያቋቋም መፍቀዱ የተለያዩ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ በአንድ ሰው ብቻ ኩባንያ እንዲያቋቋም መፈቀዱ ወደፊት የሚቋቋሙትን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት ተቋቁመው በተለያዩ ምንያቶች የአባላቱ ቁጥር ወደ አንድ ዝቅ በማለቱ ብቻ በሕጉ አንቀጽ 511 መሠረት እንዲፈርሱ የሚደረጉትን ከመፍረስ ይታደጋቸዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ባለሀብቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለማቋቋም የሕጉን ግዴታ ለማሟላት ሲሉ ብቻ ከማይፈልጉት ባለሀብት ጋር የሚጣመሩበትን ዕድል ይቀንሳል፡፡ ሦስተኛ ባላሀብቶች ከግለሰብ ንግድ ይልቅ ኩባንያ እንዲያቋቁሙ ስለሚያደርግ የኩባንያዎች ዕድገት በአገሪቱ እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል፡፡ አራተኛ ባለሀቶች ኩባያዎችን ሲያቋቁሙ መንግሥት ተገቢውን ቁጥጥር ለማድረግ አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

በመሆኑም እነዚህን ጉዳዮች ታሳቢ በማድረግ አዲሱ የንግድ ሕግ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደ አንድ የንግድ ማህር አይነት እውቅና የሰጠበት ሁኔታ አለ፡፡
3. የማህበሩ ምንነት እና የተጠያቂነት ስርዓት

ባለ አንድ አባል ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማለት አንድ ሰው በግሉ በሚሰጠው መግለጫ መሠረት የተቋቋመ የንግድ ማኅበር ነው ሲሆን ማኅበሩ ከአባሉ የተለየና የተነጠለ የራሱ የሕግ ሰውነት ያለው ነው ፡፡ ይህ ማለት አንድ ሰው ብቻ የሚመሰርተው የንግድ ማሀበር ሲሆን ይህ ማህበር ኃላፊነቱ ከተወሰነ የግል ማኅበር (private limited company) ጋር እጅግ ተመሳሳይ ነው። ከተጠያቂነትም አንቀፅር አባሉ ወይም መስራቹ የራሱን መዋጮ ሙሉ በሙሉ እስከ ከፈለ ድረስ ማኅበሩ ላይ ለሚፈለገው ዕዳ በግሉ ተጠያቂ አይሆንም ፡፡ የማህበሩ ባህርይ ኃላፊነቱ የተወሰነ በመሆኑ ማለትም የሚመጣ ተጠያቂነት በማህበሩ ሀብት ላይ ብቻ የተገደ በመሆኑ አባሉ ኃላፊነቱን ከተወጣ ማለትም መዋጮውን ሙሉ በሙሉ እና በወቅቱ እሰከከፈለ ድረስ ኃላፊነት የለበትም ማለት ነው፡፡

ከላይ እንደተመለከትነው ይህ ማህበር በአንድ ሰው የሚመሰረት በመሆኑ የምስረታ እና የአስተዳደር ስርዓቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው፡፡ ስለዚህ በመርህ ደረጃ አባሉ መዋጮውን በወቅቱ ከከፈል ለሚመጣው ተጠያቂነት በግሉ ኃላፊነት የለበትም ቢባልም፣ ተጠያቂ የሚሆንባቸው ሁኔታዎች ግን አሉ፡አባሉ ማኅበሩን፣ ወይም የማኅበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ጉዳት ላይ የሚጥል ህገ-ወጥ ድርጊት ሆን ብሎ ከፈፀመ፤ የባለ አንድ አባል ማኅበር ንብረትን ከራሱ ንብረት ጋር ከቀላቀለ፤ የባለ አንድ አባል ማኅበርን እና የራሱን ማንነት ካልነጣጠለ፤ ስለ ማኅበሩ የፋይናንስ አቋም የማኅበሩን ገንዘብ ጠያቂዎች ሊያሳስት የሚችል መረጃ ሆን ብሎ ካወጣ፤ ያለ ተመጣጣኝ ክፍያ የማኅበሩን ሀብት ለራሱ ወይም ለሶስተኛ ወገኞች የግል ጥቅም ካዋለ፤ በሕግ ሊከፈል ከሚችለው በላይ የትርፍ ክፍያ ከፈጸመ፤ ወይም ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ከፈጸመ ማንኛውም ባለ አንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አባል ወይም ማኅበሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቁጥጥር ያለው ሌላ ሰው ከማኅበሩ ጋር በአንድነት እና በተናጠል ተጠያቂ እንደሚሆን ህጉ በግልፅ ደንግጓል ፡፡
ተገልጋዮች የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል (የመኖሪያ ቤት፣ የሊዝ መብት፣) አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ተቋማችን ሲመጡ የሚከተሉትን ቅድመሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• የባለቤትነት ካርታ (ጀርባ ማህተም ያረፈበት) ካርታው ዲጂታል ከሆነ የጀርባ ማህተም አያስፈልግም)፡፡
• የሻጭ እና የገዥ በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
• ሻጭ/ገዥ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ የመሸጥ ስልጣንን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ሰነድ(ውክልና)፤
• የሻጭ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• የንግድ ድርጅት ቤት ሲሆን የዋና ንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
• የገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ፤
• ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባዔ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው፣ የስጦታ ተቀባዩ እና የሁለት ምስክሮች ጊዜው ያላለፈበት ወይም በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ፤
#የኮንዶሚኒየም ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-

• የኮንዶሚኒየሙ ባለቤት ቤቱን ከተረከበው አምስት አመት ስለመሙላቱ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ
• የተዋዋዬች እና የሁለት ምስክሮች በዘመኑ የታደሰ መታወቂያ
በማህበር የተሰራ ቤት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• የባለቤትነት ካርታ ጀርባው ስለትክክለኛነቱ በማህተም የተረጋገጠ፤ ከክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ዕዳ ዕገዳ እንደሌለበት የማረጋገጫ ደብዳቤ፤
• የሻጭ ወይም የስጦታ አድራጊው የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት (ውክልና)፤
• የተዋዋዬች እና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ፤
የሊዝ መብት ሲሆን፤ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የሽያጭ ወይም የስጦታ ዝርዝር እንዳለ ሆኖ በተጨማሪ፡-
• ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የሊዝ ውል፤
• የሚተላለፈው የሊዝ መብት የንግድ ድርጅት ከሆነ ከገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ፤
• የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ ያስፈልጋል፡፡

#ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ አገልግሎቶችን ለማከናወን እያንዳንዱ አገልግሎት በተናጠል 45 ደቂቃ የሚወስድ ነው፡፡

መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ በማድረግ ራሰዎንና ሌሎችን ከሙስና እና እንግልት ይታደጉ፡፡

የቴሌግራም አድራሻችንን ይቀላቀሉ፡፡https://t.me/GudayAsfetsami