ET Securities
650 subscribers
575 photos
7 videos
27 files
289 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአምስት ባንክ ላልሆኑ የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች (Forex Bureau) የስራ ፈቃድ ሰጠ!

የውጪ ምንዛሬ ቢሮዎቹ…

ዶላር #መግዛት የሚችሉት (ብር ሰጥተው ዶላር የሚቀበሉት)….

ከማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት እስከ 10ሺ ዶላር!

የጉምሩክ ዲክላራሲዮን (ከውጪ በካሽ ይዘው የገቡትን ዶላር የተመዘገበበትን ማረጋገጫ ከሚያቀርቡ) የቻሉትን ያህል ዶላር መግዛት ይችላሉ!

ዶላር #መሸጥ የሚችሉት (ብር ተቀብለው ዶላር የሚሰጡት)

ወደውጪ ለመሄድ አስፈላጊውን የጉዞ ሰነድ ለሚያቀርቡ የግል ተጓዦች (ለምሳሌ ቪዛ) እስከ 5ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

ለንግድ ስራ ተጓዦች (አስመጪ ሊሆን ይችላል) እስከ 10ሺ ዶላር ሊሸጡ ይችላሉ!

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
ዶ/ር እመቤት መለሰ  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ

በቅርቡ የንብ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመው የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

የገንዘብ ሚኒስቴር መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም  በፃፈው  ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው፤ ዶ/ር እመቤት መለሰ  ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ  ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ዶ/ር እመቤት፣ የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ከመሆናቸውም በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስትራቴጂ ፕላኒንግና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡

የፖሊሲ ባንኩን ላለፉት 4 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ዮሐንስ አያለዉ  በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ካስታወቁ በኋላ፣ የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ በቅርቡ መሾማቸው ይታወሳል።

Source~ Addisadmas
@etstocks
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ትልልቆቹ 50 ባንኮች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

ታዋቂው 'African Business' መፅሄት ባወጣው እና መሠረት ሚድያ በተመለከተው በዚህ ዝርዝር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአምናው ሁለት ደረጃ በማሻሻል 28ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ 44ኛ ሆኗል።

ከግል የኢትዮጵያ ባንኮች አዋሽ ባንክ 68ኛ፣ ዳሸን ባንክ 87ኛ እንዲሁም አቢሲኒያ ባንክ 89ኛ ሆነዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ይህ የኢትዮጵያ ባንኮች በአፍሪካ ያላቸው ደረጃ ከሰሞኑ ይፋ የሆነው የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን እና ተያያዞ የመጣውን የብር መዳከምን ታሳቢ ያላደረገ ሲሆን ይህ ለውጥ ታሳቢ ተደርጎ ቢሆም ኖሮ የባንኮቻችን ደረጃ በእጅጉ ዝቅ እንደሚል የዘርፉ ባለሙያዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በተለይ የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ለውጥ ብር እጅጉን ስለተዳከመ ያላቸው የካፒታል መጠን በእጅጉ እንደሚያሽቆለቁል እና እስከ 100 ያለውን ደረጃ እንደማያገኙ አስተያየት እየተሰጠ ነው።

በሌላ በኩል ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመንግስት የ700 ሚልዮን ዶላር የካፒታል ድጋፍ ስላገኘ ቦታውም ብዙም ላይለቅ እንደሚችል ተገምቷል።

Source: meseretmedia
@Etstocks
ኢትዮጵያ ትልቅ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ካላቸው 5 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ተካተተች

#Ethiopia  | በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ኢትዮጵያ ትልቅ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP)  ካላቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል መካተቷ ተገለጸ።

በዓመቱ ከፍተኛ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ካስመዘገቡ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ  ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ ፣ግብጽ እና አልጀሪያ ይገኙበታል።

በዚህ መሠረት  የአምስቱ  ሀገራት አመታዊ  ጥቅል ምርት  ሲሰላ ወደ 1 ነጥብ 4 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሏል።

ይህ ማለት እንደ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት(IMF) መረጃ የአምስቱ ሀገራት አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) ተደምሮ ከቀሪዎቹ የአፍሪካ ሀገራት አመታዊ ጥቅል ምርት ጋር እኩል ይሆናል ነው የተባለው።

Condoaddis.com/category/etstocks
Ride Increases Prices, Adds TOT

Joining the wave of entities adjusting their rates, Ride has announced an increase in its flag-down and duration fees, along with the introduction of a Turnover Tax (TOT).

Read More

Source: shegamedia
@Etstocks
📊 Ethiopian Private Banks Financial Results 2022-23 FY

🏦 An overview of how Ethiopia’s private banks performed this past fiscal year. Key metrics like profits, deposits, and loan ratios all in one place.

Compiled by: Aksion.et
#common_Stock
#መደበኛ_አክሲዮን

መደበኛ አክሲዮን የድርጅት ባለቤትነትን የሚወክል ሲሆን የአንድ ኩባንያ መደበኛ አክሲዮን ስንገዛ በዚያ ኩባንያ ውስጥ ባለድርሻ እንሆናለን ማለት ነው።

የመደበኛ አክሲዮን መገለጫዎች


ባለቤትነት፡ የመደበኛ አክሲዮኖች የባለቤት ማረጋገጫ ሲሆኑ፣ ምንም ያህል ጥቂት አክሲዮኖች ቢንይዝ እንኳን የዚያ ኩባንያ አካል ነን።

የመምረጥ መብት፡- የመደበኛ ባለአክሲዮኖች በኩባንያው ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ የመምረጥ መብት አላቸው። የመምረጥ መብት ብዙውን ጊዜ ከያዝነው የአክሲዮን ብዛት ጋር ተመጣጣኝ ነው። ይህ ማለት የቦርድ አባላትን መምረጥ ወይም ዋና ለውጦችን ማጽደቅ ባሉ አስፈላጊ የኩባንያ ውሳኔዎች ላይ አስተያየት መስጠት እንችላለን ማለት ነው።

የሼር ክፍያ፡- የመደበኛ ባለአክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ሊያገኙ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ኩባንያዎች የትርፍ ክፍፍል ( Dividend ) የመክፈል ግዴታ የለባቸውም እና በምትኩ በንግድ ሥራው ውስጥ ለማፍሰስ ሊመርጡ ይችላሉ።

ስጋትና አዋጪነት፡ ድርጅቱ ሲያተርፍ ከትርፉ ተካፋይ ሲሆኑ ከከሰረም ደግሞ የኪሳራው ተካፋይ እንሆናለን።

Source: stockmarketet
@Etstocks
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል።

በዚህ መሰረት፦
- ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
- ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
- ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር 
- የአውሮፕላን ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።

መረጃው ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ነው የተገኘው።

Source: Tikvah Ethiopia

LinkedIn |𝕏|
Facebook |YouTube Website
Ethiopia's financial future is taking an exciting turn as senior officials of the Ministry of Finance race against time to establish a regulatory framework injecting vitality into the budding capital market. The plan is to incorporate enticing incentives into an income tax law that has gone unchanged for over two decades. The officials' momentum stems from a comprehensive policy proposal by Brook Taye (PhD), former director general of the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA).

Read More

Source: addisfortune
@Etstocks
Source~ Banks Ethiopia
@Etstocks
የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት የገቢ ታክስ ህጎችን ማሻሻልን ጨምሮ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለመደገፍ የሚያስችል የቁጥጥር ማዕቀፍ ላይ እየሰሩ ነው።

- ዶ/ር ብሩክ ታዬ የቀድሞ የኢትዮጲያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ የገበያውን ዕድገት ለማነቃቃት በኮርፖሬት የታክስ መዋቅር ላይ ለውጦች እንዲደረጉ መክረዋል።

- የገበያ ተሳትፎን ለማበረታታት ከካፒታል ትርፍ፣ ከቦንድ ወለድ እና ሼር ፕሪሚየም ተቆራጭ የሚደረጉ ታክሶች እንዲነሱ ክለሳ መደረግ እንዳለበት ተገልጿል።

- የገንዘብ ሚኒስቴር የግብር ሕጎችን እያሻሻለ ቢሆንም እስካሁን የፊስካል ተጽእኖዎችን ሙሉ በሙሉ አልተረዳም።

- አሁን ያሉት የታክስ ህጎች የካፒታል ገበያን እድገት እንቅፋት እንደሆኑ የካፒታል ገበያ ባለስልጣናት እና አማካሪዎች ተናግረዋል። ባንኮች ለገበያ ዕድገት ወሳኝ ቢሆኑም ሙሉ በሙሉ በካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሰማራት ጥርጣሬ አላቸው።

- ESX 1.51 ቢሊዮን ብር ካፒታል ቢሰበስብም ብዙ ኩባንያዎች እንዲዘረዝሩ ግን የታክስ ማበረታቻዎችን ይፈልጋል።

- ባለሙያዎች ድርብ ታክስን ( Double Taxation ) ለማስወገድ፣ የረጅም ጊዜ ቁጠባዎችን ለማበረታታት እና የኢንቨስትመንት ብዝሃነትን ለማሻሻል የታክስ ማሻሻያዎች መኖር እንዳለባቸው ይገልጣሉ።

- ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በመንግስት የተያዙ ድርጅቶች በESX ላይ ለመዘርዘር ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው።

- ደጋፊ የታክስ ከባቢ አለመኖሩ የካፒታል ገበያውን የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ሊገድበው ይችላል ተብሏል።

Source: Addis Fortune

website |LinkedIn |𝕏| Facebook | Telegram |YouTube
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የዛሬ 30 ዓመት በቀዳሚነት ወደ ገበያ በመግባት የሚጠቀሱት አዋሽ ባንክና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከግል የፋይናንስ ተቋማት ገበያውን በመምራት እየተጓዙ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ሁለቱ እህትማማች የፋይናንስ ተቋማት የተመሠረቱበትን 30ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቁት፣ በኢንዱስትሪው በየዘርፋቸው በገበያው ውስጥ በመሪነት ደረጃ የሚያስቀምጣቸውን አፈጻጸም ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማቱን የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የሁለቱም ተቋማት ሥራ አስፈጻሚዎች ትናንት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ በገበያ ውስጥ የያዙት ድርሻ እየሰፋ መምጣቱንም ጠቁመዋል፡፡

የ30 ዓመታት ጉዞ በተመለከተ የአዋሽ ባንክ ሥራ አስፈጻሚው አቶ ፀሐይ ሽፈራው አክለው እንደገለጹትም፣ ‹‹ቀድመው ወደ ባንክና ኢንሹራንስ ክፍለ ኢኮኖሚው በመግባት የመጀመሪያዎቹ የሆኑት እህት ኩባንያዎቹ፣ በዘርፉ ላለፉት 30 ዓመታት አገልግሎታቸውን ከወቅቱ ጋር እያዘመኑ በመሄድ ከፍተኛ ተከታታይነት ያለው ዕድገት አስመዝግበዋል፤›› ብለዋል፡፡

የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጂባት ዓለምነህም፣ ኩባንያቸው ከግል መድን ሰጪዎች መካከል በጄኔራል ኢንሹራንስ ዘርፍ ተከታታይ ዓመታት የመሪነት ደረጃውን አስጠብቆ በመጓዝ ሲሆን፣ በሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ደግሞ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ግንባር ቀደም ሆኖ የአንደኛነትን ደረጃውን ይዞ መቀጠሉንም አመላክተዋል፡፡

እህት ኩባንያዎቹ በተከታታይ ስኬትን በማስመዝገብ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የባንክና የኢንሹራንስ የአገልግሎት አሰጣጥ ተግባራዊ በማድረግ ገቢያቸውን በማሳደግና በትርፋማነት በመጓዝ ለአገራዊ ኢኮኖሚው የራሳቸውን አበርክቶ እየሰጡ መሆኑንም ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
ዳዮት ታዮ
📌Ethio Telecom to kick off Ethopian stock trading with 10% flotation next week

Source~ Reuters
@etstocks
መንግስት ነዳጅ ላይ ሊያደርግ ባሰበው ፊፎርም ምክንያት የዛሬ አመት አንድ ሊትር ነዳጅ ከ117 ብር በላይ እንደሚሆን ታውቋል

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከቀናት በፊት የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻን በማድረግ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋን በየሶስት ወሩ እንደሚጨምር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ መግለጫ ላይ ይፋ የተደረገው መረጃ "የተሟላ ማስተካከያ" እስከሚደረግ ድረስ ይህ በየሶስት ወሩ የሚደረገው ጭማሪ እንደሚቀጥል ነው።

ከዚህ መግለጫ ጋር አብሮ የተለቀቀ አንድ ሰነድ እንደሚያሳየው የአለም የነዳጅ ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል ቢሆን የዛሬ አመት የነዳጅ ዋጋ 117 ብር ይገባል።
.
.
.
Read More

Source ~ MeseretMedia
@Etstocks
#News | ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።
#ካፒታል
ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።
በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
#Ethiotelecom
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2 ወር  282 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መስጠቱን አስታወቀ!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሐምሌ 22, 2016 እስከ መስከረም 30, 2017 ድረስ ለዋና ዋና ዘርፎች  282,459,436 ዶላር ለበርካታ ደንበኞች መደልደሉ ተገልጿል።

የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ የተሠጣቸው፡-

- መድሃኒቶች እና የህክምና አቅርቦቶች፡ 208.3 ሚሊዮን ዶላር

- ማሽነሪዎች፡ 42.8 ሚሊዮን ዶላር

- ጥሬ ዕቃዎች እና የፍጆታ ዕቃዎች፡ 18.2 ሚሊዮን ዶላር

- የአገልግሎት ክፍያ እና ልዩ ልዩ፡ 13.2 ሚሊዮን ዶላር

ሆኖም ደንበኞቹ የተጠቀሙት 28 በመቶ ብቻ መሆኑን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ  አስተዳደር ማሻሻያውን ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ምንጩን ለማሣደግ ተወዳዳሪ የምንዛሬ ተመን በመስጠት እየሠራሁ ነው ብሏል።

ምንጭ ~ ቅዳሜገበያ @Etstocks