ET Securities
708 subscribers
644 photos
7 videos
34 files
338 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

www.Etsecurities.com

YouTube.com/@etstocks

Fb.me/etstocks
Download Telegram
#News | ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።
#ካፒታል
ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።
በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
#Ethiotelecom
#Ethiotelecom

መንግሥት ከኢትዮ ቴሌኮም ኩባንያ የ10 በመቶ ድርሻ ሽያጭ ከ25 እስከ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ እንደሚጠብቅ ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። አንድ ሰው ከኩባንያው ሊገዛ የሚችለው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የአክስዮን መጠንም እንደተወሰነ ዋዜማ ተረድታለች። ከኩባንያው ድርሻ ለመግዛት የተፈቀደላቸው፣ ኢትዮጵያዊያንና በውጭ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ብቻ እንደኾኑ ምንጮች ገልጸዋል። ኩባንያው በቴሌብር አማካኝነት ነገ የ10 በመቶ ድርሻውን መሸጥ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
#Ethiotelecom
#Telebirr

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጊዜው የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ! ለጊዜው የተነሳው ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ እንደሆነ ተነግሯል።

መንግስት የኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል። የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው።

መረጃው ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ነው!
@Etstocks