ET Securities
651 subscribers
573 photos
7 videos
26 files
288 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
#News የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የልዩ የዉጭ ምንዛሪ ጨረታን በአማካይ ዋጋ በዶላር 107.9 ብር መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የተካሄደውን የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ አድርጓል።

27 ባንኮች ተሳትፎዉበታል በተባለዉ በዚህ ልዩ ጨረታ አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች አማካይ ዋጋ በአንድ ዶላር 107.9 ብር እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል። ይህም ነገ ከነሐሴ 2፤2016 ዓ.ም. ጀምሮ በዉጪ ምንዛሪ ተመን ላይ ተግባራዊ ይደረጋሉ ።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ ዉጤቱን ተከትሎ እንደተናገሩት "ተግባራዊ የተደረገዉን በባንክ ምንዛሪ ዋጋ እና በትይዩ የገበያ ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት እና እንዲሁም የምንዛሪ ተመን መረጋጋት ትርጉም ያለው እድገት ሆኖ በማየታችን ደስተኞች" ነን ብለዋል።

የዉጪ ምንዛሪ ግብይት አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ባንክ ሥርዓት እንዲሸጋገር የሚያደርግ ሲሆን በዚህም የውጭ ምንዛሪ የሚያመጡትን ላኪዎች እንዲሁም ብዙ ኩባንያዎችን እና የውጭ ምንዛሪ ለሚፈልጉ ሥራ ፈጣሪዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመልክቷል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ልዩ የዉጪ ምንዛሪ ጨረታዉን ከዛሬ ጀምሮ ሊያካሄድ መሆኑን መግለፁ የሚታወስ ሲሆን ቢዘህም ፍላጎቱ ያላቸዉ ባንኮች በጨረታው መሳተፍ እንደሚችሉ አስታዉቆ ነበር።


#News The National Bank of Ethiopia has announced a special foreign currency auction with an average price of 107.9 Birr per dollar.

National Bank of Ethiopia today, August 1, 2016.  He announced the results of the special foreign exchange auction.

According to the National Bank, the average price of the winning bidders in this special auction is 107.9 Birr per dollar.  This is from tomorrow, August 2, 2016.  They will be applied on the foreign exchange rate.

Following the results, National Bank Governor Mamo Mehretu said, "We are happy to see the difference between the bank exchange rate and the parallel market rate, as well as the stability of the exchange rate, as a meaningful development."

He observed that most of the foreign exchange trading activity is transferred to the banking system, thus contributing to the exporters who bring foreign currency as well as many companies and entrepreneurs who need foreign currency.

It should be remembered that the National Bank of Ethiopia announced that it will hold a special foreign exchange auction from today, and it announced that interested banks can participate in the auction.

www.condoaddis.com/240807-1
#News አማራ ባንክ ከታክስ በፊት ከ 377 ሚሊየን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን የገለፀ ሲሆን ተቀማጭ ገንዘብ ከ 25 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ሲል አስታዉቋል ።

ባንኩ በተጠናቀቀው የ2023/24 በጀት ዓመት የተሻለ ከታክስ በፊት ብር 377.2 ሚሊየን ትርፍ ያስመዘገበ መሆኑን እና ብር ተቀማጭ ገንዘብ ከ 25.1 ቢሊየን ብር ላይ መድረሱን ገሌጿል።

ከ1.8 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት የሚነገርለት ባንኩ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች አጠቃላይ ብር 20.3 ቢሊየን ብድር መስጠቱን ገለጿል።

አማራ ባንክ የበጀት ዓመቱን አፈፃፀም በተመከለተ በሰጠዉ መግለጫ ከ 571 ሺ በላይ የሞባይል ባንክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም ከ50 ሺ በላይ የካርድ ተገልጋዮችን ማፍራት የቻለ ሲሆን በርካታ የኤቲኤም እና የፖስ ማሽኖችን በተለያዩ ቦታዎች በማኖር በዲጂታል ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ችያለሁ ብሏል ።

ካፒታል
#News | ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ።
#ካፒታል
ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።
በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
#Ethiotelecom