#በአፋር ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አወገዙ
አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ጥቅምት 28, 2013
በአፋር ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕወሓት ቡድን በመከላከያ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አወገዙ
በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሕወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት አጥብቀው እንደሚያወግዙ ገለጹ።
ፓርቲዎቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሠመራ ከተማ ዛሬ ባካሄዱት የምክክር መድረክ፣ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እየወሰደ ያለው እርምጃ ሁሉም ዜጋ ሊደግፈው ይገባል በማለት ተናግረዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የአፋር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ኢሴ አደን “የሕወሓት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመው የእብሪት ጥቃት ዛሬም እንደ ትናንቱ ሁሉን በበላይነት ለመምራት ያለውን ፍላጎት በሕዝብ ላይ ለመጫን የተደረገ ሙከራ ነው” ብለዋል።
ድርጊቱ የሀገርን ህልውና እና የሕዝብን ሰላም አደጋ ላይ ለመጣል የተቃጣ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ምንጭ: ብልጽግና ፓርት, አፋር ቅርንጫፍ

#የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም ከሽፏል- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት::
ሰመራ-አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት፣ህዳር 20 ፣ 2013
የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም ከሽፏል- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት::
የህወሃት ጁንታ አስቦት የነበረው ሀገር የማፍረስ ህልም መክሸፉን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገለጸ።
የህወሓት ጁንታ ለመቆጣጠር እስካሁን በተመዘገበው ድልም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
ከሌሎች የመረጃና ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የጁንታውን ድብቅ ሴራ በማጋለጥ ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረትም ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሰራ መሆኑን በመግለጫው አመልክቷል።
በስግብግቡ የጁንታ ላይ የተገኘው አኩሪ ድል የመላው የአገራችን ህዝቦች በተለይም ደግሞ የትግራይ ህዝብ አኩሪ የትግል ውጤት በመሆኑ ተቋሙ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
የህወሓት ስግብግብ ጁንታ በፖለቲካው አውድ የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ ትግራይ ክልል በመመሸግ ህገወጥ ተግባራትን ሲፈፅም ቆይቷልም ብሏል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በመግለጫው።
ጁንታው የሰሜን ዕዝ የሰራዊቱ አባላትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት በመፈጸም እንዲሁም በአማራ ክልል ህዝቦች ላይ ግልፅ ጦርነት በማወጅ የአገርን ብሄራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጻረር ከፍተኛ ክህደት መፈፀሙንም በመግለጫው አመልክቷል።
ቡድኑ ጦርነቱን የጀመረው በግልፅ፣ በተደራጀ እና በከዳተኛ አባሎቹ ጭምር ተገቢ ጥናት ፈፅሞ የሰራዊቱን ቁልፍ ትጥቆች፣ ስንቆች፣ የማዘዣ ጣቢያዎችና የዕዝ ሰንሰለቶች ለመቆጣጠርና ለመበጣጠስም በማለም መሆኑን ጠቅሷል።
ይሁን እንጂ ህልሙ ሙሉ በሙሉ ባሰበው ልክ አልተሳካለትም፣ ከሽፏል፣ ያሳካው ነገር ቢኖር ትውልድ ይቅር የማይለው አሳፋሪ እና አስነዋሪ ታሪክ ማስመዝገብ ነው ብሏል።
የስግብግብ ጁንታ ህልም እንዳይሳካ በራሱ የግንኙነት ኔትወርክ ውስጥ ሰርጎ በመግባት፣ ተባባሪ አካላትና አባላትን፣ የወገንን ኃይል እንዲሁም ሰላም ወዳዱን የትግራይ ህዝብ በመጠቀም መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን ለተመዘገበው ድል ድጋፍ ማድረጉንም አመልክቷል።
የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከሌሎች የመረጃና የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የጁንታው ድብቅ ሴራ እንዳይሳካ ማክሸፉንም ገልጿል።
#ምንጭ: OBN

#የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል:- ትምህርት ሚኒስቴር::
አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-፣ታህሳስ 14/2013
የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል:- ትምህርት ሚኒስቴር::
የትምህርት ሚኒስቴርና የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ)
450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ እና 12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ መሆናችውን ተናግረዋል።
በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል።
#ምንጭ፣ ትምህርት ሚኒስቴር

#የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ኡንዴ የህዳሴው ግድብ 2ኛው ዙር ሙሌት አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላቹህ መልእክት
እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል።
መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሻራ የሆነው የህዳሴ ግድባችን 2ኛው ዙር ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ በአፋር ህዘብና መንግስት ስም የደስታ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
የህዳሴ ግድባችን ህዝባችንና መንግስታችን ከጫፍ እስከ ጫፍ በተባባረ ክንድ እየገነባነው የሚገኝ አገራችንንም ሆነ መላው አፍሪካንም የሚያኮራ ታላቅ ፕሮጀክት ነው።
ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ዋነኛ መንስኤው ስለ ህዳሴው ግድብ ህዝብና መንግስት በጋራ በመሰለፍ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸው፣ ይህንኑም ተመሳሳይ ድልም ከውጭም ሆነ ከውስጥ ሰላማችንን ለማደፍረስ፣ ኢትዮጵያችንን ለማፈራረስ የሚቋምጡ ሀይሎችን አደብ ለማስገዛት በህብረት ጥረታችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።
ሁሌም ስኬታችን የሚያማቸው የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ እንዲሁ በቀላል የምትፈርስ አለመሆኗን በደንብ ሊረዱ ይገባል። በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የአፋር ህዝብም ለግድቡ ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ የተሰማን ደስታ ላቅ ያልሆነ ነው።
ኢትዮጵያችን ያለኛ ኢትዮጵያውያን ማንም የላትና ሁላችንም አንድ ሆነን ልማታችን በማፋጠን፣ አደናቃፊ ሀይሎችን ስርአት በማስያዝ ወደምንፈልገው የብልፅግና ጉዞ እንሻገር በማለት በመጨረሻም በ2ኛው ዙር የግድቡ ሙሌት መሳካት ደስ ብሎናል እንኳ ደስ ያላቹህ።
#ምንጭ: አ/ብ/ክ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤ

#ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና አዋሽ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፣፣
ሰመራ-ግንቦት 09/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና አዋሽ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፣፣
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለምምህራን ለቤት ግንባታ፣ ለመኪና እና ለቤት እቃዎች ግዥ የሚሆን ብድር ለማመቻቸት የሚያስችል ስምምነት ግንቦት 10/2014 ከአዋሽ ባንክ ጋር ተፈራርሟል፡፡
የጋራ ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን የቤት እና የተሽከርካሪ ባለቤት የሚያደርግ ብድር የሚያመቻች እና ዩኒቨርሲቲው ለሚሰራቸው ሰፋፊ የገቢ ማመጫ ስራዎች የሚያግዝ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ስምምነቱ ለረጅም ጊዜ የመምህራን ጥያቄ የነበረውን የመኖሪያ ቤት እና የተሸከርካሪ ፍላጎት ለመፍታት የታለመ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም መምህራን ትኩረታቸውን በምርምር እና በማስተማር ላይ እንዳደርጉ ለማሽቻል ዩኒቨርሲቲው ካቀዳቸው ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር እቅዶች አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም ለአስተዳደር ሰራተኞች ቤት መስሪያ የሚሆን ቦታ ለማግኘት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ የደሴ ሪጅናል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ እሸቱ በበኩላቸው ባንኩ ስምንት ከሚሆኑ ተመመሳሳይ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እንደዚሁ አይነት ስራ እየሰራ ስለሆነ ለሠመራ ዩኒቨርሲቲም ከነበረው በተሻለ ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡
ስራውን ሲያስተባበሩ የነበሩት አቶ ዳውድ አህመድ በበኩላቸው ይህ ስምምነት ለሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን መልካም አጋጣሚ ነው ብለዋል፡፡ ስራውን ለመስራት በተደረገላቸው ግብዣ በርካታ ባንኮች ቢቀርቡም አዋሽ ባንክ በወለድ አልባም በወለድም ያቀረበው አማራጭ የተሻለ ስለነበር አሸናፊ ሆኖ ለስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡ ይህ ስምምነት ዩኒቨርሲቲው እና ባንኩ ዋናውን ፊርማ ከተፈራረሙ ብኋላ በፍጥነት ወደተግባር ይገባል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕራይዝ ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ አብዱለጢፍ በበኩላቸው የዛሬው ፊርማ ዩኒቨርሲቲው ላቀደው ዘርፈብዙ የገቢ ማመንጫ ስራዎች አጋዥ ሃይል የሚሆን እና ሁለቱንም የሚጠቅም ስምምነት ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም የመኖሪያ ቤት እና ተሸከርካሪ ለመምህራኑ መሰረታዊ ፍላጎት በመሆኑ እድሉን መጠቀም አለበት ሲሉ አደራ ብለዋል፡፡
#ምንጭ: በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙት ዳይሬክቶሬት