Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል:- ትምህርት ሚኒስቴር::

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-፣ታህሳስ 14/2013

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል:- ትምህርት ሚኒስቴር::

የትምህርት ሚኒስቴርና የአገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ዝግጅት በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ፒ ኤች ዲ)
450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታህሳስ መጨረሻ ድረስ ከውጭ እንደሚገቡ እና 12 ሺህ ላፕቶፖች ደግሞ ለፈታኞች ለማከፋፈል ዝግጁ መሆናችውን ተናግረዋል።

በትምህርት ቤቶች ላይ ተተክለው ከሚኒስቴሩና የፈተናዎች ኤጀንሲ ሰርቨሮች ጋር የሚገናኙ 1 ሺህ 500 ቪሳት ቴክኖሎጂ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መሳሪያዎቹን የሚተክሉ 250 ባለሙያዎች ስልጠና ወስደው ወደ ሥራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በኦንላይን የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና እስከ ጥር መጨረሻ ድረስ ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

#ምንጭ፣ ትምህርት ሚኒስቴር
#የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል::
አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ታህሳስ 25/2013

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል::

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን የገለጹት ኃላፊው፣ በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

#OBN