Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ::

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ህዳር 22/2013

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ::

ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህውሓት ከፍተኛ አመራርና በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት የነበራቸው እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል።

#OBN
#ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች በጁንታው ኃይል ታግተው የነበሩ 1240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ዋግኸምራ ዞን ሠቆጣ ከተማ ገብተዋል።

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ህዳር 23/2013

ከሰሜን ዕዝ ከተለያዩ ብርጌዶችና ክፍለ ጦሮች በጁንታው ኃይል ታግተው የነበሩ 1240 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ዋግኸምራ ዞን ሠቆጣ ከተማ ገብተዋል።

የሠራዊት አባላቱ ከህዳር 20፣2013 ዓ.ም ከ 8 ሰዓት ጀምሮ እስከ እስከ ትላንት ማታ 12 ሰዓት ድረስ ነው ወደ ሰቆጣ የገቡት።

የመከላከያ ሰራዊት አባላቱ ሰቆጣ ለመግባት በርካታ ውጣ ውረድ ማለፋቸውንም ገልጸዋል።

በተለይም የተከዜን ኮሪደር ተከትለው በቀን እና ሌሊት የእግር ጉዞ እንዲሁም ወንዝና ጫካ እያቆራረጡ ሰቆጣ መግባታቸውን የሠራዊቱ አባላት መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የአካባቢው አስተዳደር ለሰራዊቱ የምግብ እና የህክምና አቅርቦት ማመቻቸቱም ተመልክቷል።

#OBN
#የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል::
አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ታህሳስ 25/2013

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል::

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን የገለጹት ኃላፊው፣ በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

#OBN