Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#Breaking News

****ለክቡራን ደንበኞቻችን******
ዛሬ ቀን 15/03/2013ዓ.ም ከቀኑ 6:45 ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቋረጡ ይታወቃል። ሆኖም ችግራ ከዋና ማሠራጫ ጣቢያ በመሆኑ ችግሩ እስከሚፈታ በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።
#የአፋር #ክልል #ኤሌክትሪክ #አገልግሎት

#Source: Afar Region Electric Utility
#የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ኡንዴ የህዳሴው ግድብ 2ኛው ዙር ሙሌት አስመልክቶ የእንኳን ደስ ያላቹህ መልእክት

እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል።

መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አሻራ የሆነው የህዳሴ ግድባችን 2ኛው ዙር ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ በአፋር ህዘብና መንግስት ስም የደስታ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።

የህዳሴ ግድባችን ህዝባችንና መንግስታችን ከጫፍ እስከ ጫፍ በተባባረ ክንድ እየገነባነው የሚገኝ አገራችንንም ሆነ መላው አፍሪካንም የሚያኮራ ታላቅ ፕሮጀክት ነው።

ለዚህ ፕሮጀክት ስኬት ዋነኛ መንስኤው ስለ ህዳሴው ግድብ ህዝብና መንግስት በጋራ በመሰለፍ ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸው፣ ይህንኑም ተመሳሳይ ድልም ከውጭም ሆነ ከውስጥ ሰላማችንን ለማደፍረስ፣ ኢትዮጵያችንን ለማፈራረስ የሚቋምጡ ሀይሎችን አደብ ለማስገዛት በህብረት ጥረታችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል።

ሁሌም ስኬታችን የሚያማቸው የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ እንዲሁ በቀላል የምትፈርስ አለመሆኗን በደንብ ሊረዱ ይገባል። በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው የአፋር ህዝብም ለግድቡ ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለግድቡ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ የተሰማን ደስታ ላቅ ያልሆነ ነው።

ኢትዮጵያችን ያለኛ ኢትዮጵያውያን ማንም የላትና ሁላችንም አንድ ሆነን ልማታችን በማፋጠን፣ አደናቃፊ ሀይሎችን ስርአት በማስያዝ ወደምንፈልገው የብልፅግና ጉዞ እንሻገር በማለት በመጨረሻም በ2ኛው ዙር የግድቡ ሙሌት መሳካት ደስ ብሎናል እንኳ ደስ ያላቹህ።


#ምንጭ: አ/ብ/ክ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤ
#የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፐረዝዳንት ክቡር አወል አርባ የሰጠው መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች::

ሰመራ-ሃምለ 17፤ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የህውሀት ጁንታ በአፋር በኩል የቆየ የግዛት የማስፋፋት ከንቱ ሲራን የአፋር ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ በጠንካራ ክንዶች ግብአተ መሬታቸውን እንዲፈጽም የክልሉ ርእስ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ጥሪ አቀረቡ ፡፡

የህውሀት ጁንታ ቡድን በአፋር በኩል የቆየ ከንቱ የግዛት ማስፋፋት ህልሙን ለማሳካት የሚያደርገውን መቀዥቀዥ የክልሉ ህዝብ በተደራጀ እና በተቀናጀ በአስተማማኝነት ደረጃ አንድነቱን ጠብቆ በጠንካራ ክንዶች ግብአተ መሬታቸውን እንዲፈጽም መዘጋጀት እንዳለበት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በሰጡት ወቅታዊ መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የአፋር ህዝብ በኢትዩጵያ አንድነት ፣ በሉአላዊነቱ እና በድንበር ጠባቂነቱ የማይደራደር ፣ ታማኝ ሀገር ወዳድ ፣ ጀግናና አቃፊ ህዝብ መሆኑ ወደኋላ ያለው የትናት ታሪኩ ህይዋ ምስክር ነው፡፡ ዛሬም የሚታይ የሚዳሰስው የቀንተቀን ተግባሩ ይሂው ነው በማለት ነገም በአስተማማኝ ሁኔታ ወዶ እና ፈቅዶ የሚፈጽመው የህይወቱ እና የማንነቱ አንድ አካል የሆነ ጀግና ህዝብ ነው ብለዋል ፡፡

ይህን ታሪኩን የዘነጉት የሚመስሉ የህውሀት ጁንታ ቡድን ለ27 አመት ያደርሱት የግፍ እና የጭቆና ተግባራቸውን ከሊላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በአንድነት በመሆን አሽቅንጥሮ ጥሎ ህዝቡ ምርጫውን በፍትሀዊነት እና በሰላም ወስኖ የኢትዮጵያን አንድነት በማረጋገጥ እና የብሄር ብሂረሰቦችን ማንነት እና ፍላጎት በማክበር አዲስ የለውጥ መንገድ ላይ እንገኛለን ፡፡

ይህ ያልጣመው አሽባሪው የህውሀት ጁንታ እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ ትፍረስ በሚል አስነዋሪ እና አሳፋሪ ተግባሩን አንግቦ አገር ለማፈራረስ እና ግዛቱን ለማስፋት ከንቱ እና የማይሳካለትን ተግባሩን ሙከራ ለማድረግ እንዳበደ ውሻ በመቀዥቀዥ ላይ ይገኛል ሲሉ ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ፡፡

ይህን አስነዋሪ እና አሳፋሪ የክህደት ተግባሩን በአፋር ንጽሀን አርብቶ አደር ህዝብ ህጻናት፣ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ አይነስውሮች ላይ በፈጸመው ጥቃት ሞት እና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ፣ ሴትችን የመድፈር እና ትምህርት ቤቶችን ተቋማትን በማቃጠልም ሀገርን የማፈራርስ እና በአፋር በኩል የቆየ የማይሳካለትን ከንቱ የግዛት ማስፋፋት የቅዥት ህልሙን ለማሳካት ሙከራ እያደረገ ይገኛል ፡፡

በመሆኑም ይህን ከንቱ እና አሳፋሪ ሙከራውን ጀግናው እና በሀገሩ የማይደራደረው የክልሉ ወጣት እና ህዝብ በየደረጃው ያለው ከመንግስት እና ከጀግናው የክልሉ ልዩ ሀይላችን እና ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ጎን በመሰለፍ ወራሪውን ጁንታ አስተማማኝ እና የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ በአንድነት እና በቁርጠኝነት በመቆም በጠንካራ ክንዳችን ወራሪውን ድባቅ በመምታት ህልውናችንን እና ሉአላዊነታችንን ለማስከበር በጋራ እንነሳ ሲሉ ጥሪያቸውን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል ፡፡
#የአፋር ክልል ሴቶች አሸባሪውን የህወሓት ቡድን በመቃወም ሰልፉ አካሄዱ
********************************
የአፋር ክልል ሴቶች የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ሴራ በመቃወም በሰመራ ከተማ ሰላማዊ ሰልፉ እያካሄዱ ነው፡፡

ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ሴቶች የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ሴራ ከመከላከያና ልዩ ሀይሎች ጎን በመሰለፍ ለማክሸፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለጻቸው ተጠቅሷል።

የቡድኑ ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ድባቅ ይመታል ሲሉም ገልጸዋል።

በአሸባሪው ፊት-አውራሪነት በንጹሃን ህጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የአለም ህዝብ ሊያወግዘው ይገባልም ብለዋል።

"ትውልዱ የአባቶቻችንን አደራ አያጥፍም፣ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፣ የጁንታው ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በልጆቿ የተባበረ ክንድ ድባቅ ይመታል" የሚሉ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የክልሉ ሴቶች በአሸባሪው ህወሓት ላይ መንግስት በጀመረው የህልውና ዘመቻ እስ ከህይወት መስዋዕትነት በመከፈል ታሪካዊ አደራቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ሰልፈኞቹ በአሁኑ ወቅት በሰመራ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን የጥፋት ድርጊት የሚያወግዙና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፉ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ይገኛል ።

#EBC
#የአፋር ክልላዊ መንግስት መሰከረም 20/2014 ዓ.ም የአዲሱን መንግስት እንደሚመሰርት የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ መግለጫ ሰጡ።

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መሰከረም 20/2014 ዓ.ም የአዲሱን መንግስት እንደሚመሰርት የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አሚና ሴኮ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል ።

በ6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት ተወዳድረው ድምፅ ያገኙ አባላት የ6ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ጉባኤያቸውን ሀሙስ መሰከረም 20 በሚያደረጎት ጉባኤ ነባሩን የምክር ቤት አባል በመሸኝት አዲስ በተመረጡት የምክር ቤት አባል በመተካት አዲስ መንግሰት ይቋቋማል ሲሉ አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አሚና ሴኮ ገልፀዋል።

አዲሱ ምክር ምክር ቤት ዘመኑን ሊመጥኑ የሚችሉ የተማሩ አባላት በከፍተኛ ደረጃ የተቀላቀሉበት እና ብቃት ያላቸው ሴቶች ም ከነበረው ምክር ቤት ከፍተኛ ነው በማለት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አሚና ሴኮ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም አፈ-ጉባኤዋ የምክር ቤት አባላት ቀደም ብለው መስከረም 19/2014 ዓ.ም እንዲገቡ መልእክት ተላልፋል ።
#ጁንታው ሲቪሊያንን ታርጌት ያደረገ የከባድ መሳሪያ ድብደባ በጭፍራ እያደረገ ነው!

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ጭፍራ ወረዳ በኩል ነፁሀን ሲቪሎችን ቀጥታ ኢላማ ባደረገ መልኩ፣ ከተማውን የማውደም እና የዘር ማጥፋትን ያለመ ጥቃት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ እየፈፀመ ይገኛል።

ከተማን በከባድ መሳሪያ ማውደም ከባድ ወንጀል ነው። ጁንታው የተያያዘው ንፁሀንን ማሸበርና በመድፍ የታገዘ ድብደባ በጭፍራ ወረዳ እያካሄደ ነው።

ወራሪው ጁንታ በጋሊኮማ ያደረሰው የዘር ማጥፋት ወንጀል አልበቃ ብሎት ከሰሞኑ ደግሞ በአፋር በተለያዩ አካባቢዎች በበራህሌ፣ በመጋሌ፣ በኡዋ እና በጭፍራ በኩል ከርቀት ከባድ መሳሪያ ንፁሀንን ሲቪሎችን ኢላማ ያደረገ ተኩስ ከፍቷል።

ንፁሀንን መግደል እና ዘር ማጥፋት ዘመቻን ስራዬ ብሎ የተያያዘው ጁንታው በአፋር በፈንቲ ረሱ በኩል እና በኪልበቲ ረሱ ዞኖች በኩል ካሁን በፊት ያደረገውን ወረራ የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሺያ እና ህዝባዊ ሰራዊት በሚገባ በመመከት ወደ መጣበት በመመለስ የደረሰበትን ኪሳራ ለመሸፈን በሚመሰል መልኩ ከሰሞኑ ከርቀት ከባድ መሳሪያዎችን ንፁሀንን ኢላማ ባደረገ መልኩ መተኮስ ይዟል።

ጁንታው በፈንቲ ረሱ ወረራ ባደረገ ጊዜ የተፈናቀሉ ሴቶች፣ ህፃናትና አዛውንቶች እና ህፃናት የተጠለሉበት ጊዚያዊ ማረፊያዎችን ትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን ኢላማ ባደረገ መልኩ ነው ዘመቻውን በአፋር ንፁሀን ላይ የከፈተው አሸባሪው የህወሀት ጁንታ።

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ታሪክ የማይሽር ጠባሳን በጋሊኮማ ንፁሀንን በመጨፍጨፍ ጥሎ ያለፈ ሲሆን አሁንም ዳግም ያንን ክፉ ታሪክ ለመድገም በሚመሰል መልኩ በከባድ መሳሪያ ድብደባ ጀምሯል።

በአፋር ንፁሀን ደም ላይ "ታላቋን ትግራይ" ለመመስረት አልሞ የተነሳው አሸባሪው ህወሀት በአፋር ባደረገው ወረራ በርካታ ንፁሀን አርብቶ አደሮችን ጨፍጭፏል፣ ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል። በርካታ ህዝባዊ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ ወዘተ እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማት መስጂዶችና መድረሳዎችንም ጭምር አውድሟል። በዚህም የአፋር ህዝብ ላይ ትልቅ ኪሳራን አድርሷል።

ይሁንና የአፋር ህዝብ ባደረገው ብርቱ ተጋድሎ አሸባሪው ህወሀትን ወደመጣበት እንዲመለስ አድርጓል። አሁንም በድጋሚ አፋርን ለመውረር ከመጣ የአፋር ህዝብ ለጁንታው የሚገባውን ሰጥቶ ወደመጣበት በድጋሚ የሚመልሰው ይሆናል።

እዚህ ላይ ምንም መረሳት የሌለበት ጉዳይ ምንም የማያውቁ ህፃናት እና አዛውንቶችን፣ ንፁሀን ሴቶችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት የፈሪነት ምልክት እንጂ ጀግንነት አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።

አሸባሪው ወራሪው ህወሀት ህፃናት እና ሴቶችን እንዲሁም አዛውንቶችን ኢላማ ከማድረግ ባሻገር፣ የአፋር አርብቶ አደር የኢኮኖሚ መሰረት የሆነውን እንስሳውን ግመል፣ ከብት እና ፍየል ጭምር በከባድ መሳሪያ በመደብደብ ህዝባችን ላይ የሚደርሰው ጉዳት እጥፍ ድርብ እንዲሆን በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመጨረሻም የአፋር ህዝብ ካሁን ቀደም እንዳደረገው ሁሉ አሸባሪው ህወሀት በገባበት የአፋር ክልል በኩል ሁሉ መቀበሪያው እንደሚሆን ፣ ህዝባችንም ወረራን ለመመከት የቀድሞ ታሪኩን አሁንም የሚደግም ይሆናል።

#የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት
#የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ላይ ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

ሰመራ-ታህሳስ 23/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ላይ ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች በሚል ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

የውይይት መድረኩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አዋል አርባ እና የአፋር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር ኢሴ አዳም በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ በደህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ያሉትን ጉዳዮች ለአመራሩ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አዋል አርባ በህብረ ብሔራዊ ዘመቻ ከተመዘገቡ ድሎች መካከል ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለማዳን በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የፈጠሩት አገራዊ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በድህረ ጦርነቱ ተግባሮችም ተጠናክሮ እንድቀጥሉ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳ ያላቸውን የውስጥና የውጭ ኃይሎችን ወረራ እየመከትን የተጀመሩ የብልጽግና ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችሉ ዘላቂ ሠላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

አክለውም ተገደን በገባንበት ጦርነት የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ትኩረት መሰጠት እንደአለበት ገልጿል።

የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም እኩል ትኩረት ያገኛሉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የጋራ አቋም፣ ወጥ እሳቤ እና ተቀራራቢ አፈፃፀም አሁን ካለው አመራር የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የአፋር ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሴ አዳም በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ዓላማ የክልሉን አመራር ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት እና ማብቃት ነው ብለዋል፡፡

ጦርነቱ በህልውና ላይ የመጣ በመሆኑ ህልውናችንን ለመመከት የፈጠርነውን አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና አቅም አድርገን መጠቀም አለብን ሲሉም ገልጸዋል።

አመራሩ በተለይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተፈጠረውን ትብብርና አንድነት በቀጣይነት ለልማት መጠቀም እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡

አንድነትን ማጠናከር እና በድል ማግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ ለይቶ መፍታት ከውይይት መድረኩ የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ዛሬ ሶስተኛ ቀን በያዘው በዚሁ መድረክ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የዞንና የወረዳ አስተባባሪ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን በዝርዝር ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቱ በዞን ፣ በወረዳ ፣ በከተሞች ፣ በቀበሌ እና እሰከ ህዝብ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።
#እንደተለመደው የአፋር ህዝብ በእርግጠኝነት ያሸንፋል ምክንያቱም የአፋር ህዝብ በገሃድ የቆመ እና ንፁህ መሬቱን እና ሰላም ወዳድ ህዝቡን ለመጠበቅ እየሞተ ነው።

#ኢትዮጵያ#ታሸንፋለች።
#የአፋር#ህዝብ#ያሸንፋሉ

As usual the Afar people will definitely win because the Afar people is on the manifest right and is dying in defense of his pure land and peace-loving people.

#Ethiopia#will#win
#Afar#people#will#win

ጥር 16, 2014
#የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ።

ሰመራ-መጋቢት 12፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ.)

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ።

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 6ተኛው የክልል ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ጀምሯል።

በተጀመረው ጉባኤውም የመንግስት ምስረታ ቃለ ጉባኤ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ፀድቋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የ2014 ዓ.ም የ6ወር እቅድ የአፈፃፀም ሪፖርት ማቅረብ ጀምረዋል ምክር ቤቱም በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

ምክር ቤቱ በሌሎች ቀሪ አጀንዳዎች ጉባኤውን ማካሄዱን ይቀጥላል ።
#የአፋር እና የአማራ ህዝቦችን ጠንካራ ግንኙነት ለማስቀጠልና በጋራ ለመልማት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል መንግስታት አስታወቁ።

ሰመራ- ሰኔ 02/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የአፋር እና የአማራ ህዝቦችን ጠንካራ ግንኙነት ለማስቀጠልና በጋራ ለመልማት እንደሚሰሩ የሁለቱ ክልል መንግስታት አስታወቁ።

በአፋር እና በአማራ ህዝቦች መካከል ያለውን የቆየ እና የዳበረ ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ሁለቱም ሕዝቦች በጋራ በልማት በሚያድጉበት ጉዳይ ላይ የአፋር እና የአማራ ክልል መንግስታት ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱም የሁለቱ ክልሎች ፕሬዝዳንቶችን አቶ አወል አርባ እና ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች የተገኙ ሲሆን በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ፣ በተለይም በጸጥታ፣ በኢኮኖሚ እና እርስ በርስ ግንኙነትን ማጠናከር ዙሪያ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ውይይቱ ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም የተነሱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችም በተግባር መሬት እንዲወርዱ ሁሉም ባለድርሻ አካል በሃለፊነት ስሜት መስራት እንዳለበት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

#Afargcao
#የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ኡንዴ ለብሄራዊ ቡድናችን ያስተላለፉት የደስታ መልዕክት

መላው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ባስመዘገበው ድል እንኳን ደስ ያላቹህ ደስ ያለን!

ትላንት ምሽት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታውን በአሸናፊነት አጠናቋል።
ቡድኑ እያሳየ ያለው መነቃቃት አጅግ ደስ የሚያሰኝ ነውና እንኳን ደስ ያላቹህ እንኳን ደስ ያለን።

በአፍሪካ ዋንጫው መድረክ ሀገራችን ኢትዮጵያ የነበራት ከፍተኛ ቦታ ታሪክ ሆኖ እንዳይቀር ዳግም በውድ ልጆቿ ለመመለስ እየሄዱ ያለው ሂደት እጅግ የሚያስደስት እና ሊበረታታ የሚገባው ጅማሮ ነው።

የመጨረሻውን ድል ለመቀዳጀትና አብሮ ለመደሰት በሂደት ያሉ ድሎችን አብሮ መስራት፣ ጠንካራ ጎኖች እንዲጠንክሩ ፣ መሻሻል ያለባቸው ደግሞ እየተሻሻሉ እንዲሄዱ ከጎን መሰለፍ ግድ ስለሚል ሁሉም ኢትዮጵያ ከወዲሁ ከብሔራዊ ቡድናችን ጎን በመሆን የሚጠበቅብንን ድጋፍ ልናደርግ ይገባል።

በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ድሎችና ስኬቶች በስፖርቱ ዘርፍም እንዲደገም ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፣ በድጋሚ ድል ለብሄራዊ ቡድናችን እንመኛለን፣ እንኳን ደስ ያላቹህ እንኳን ደስ ያለን።

አቶ አወል አርባ ኡንዴ

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር