General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ፡- ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

               #ማስታወቂያ

  ለኮሌጃችን የውስጥ ሰራተኞች እና  ለውጪ የተቋማችን አጋር  ማኅበረሰብ በሙሉ

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋማዊዩ የግል ኢንተርፕራይዝ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓል ያደለባቸውን  ምርጥ #በሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለመሸጥ እንሆ ይላል፡፡

ስለሆነም በተዘጋጀው ጥቂት የመሸጫ ቀናት ውስጥ ፈጥነው በመምጣት የመረጡትን ሰንጋ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት የሚችሉ መሆኑን ስንገልጽልዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ስለዚህ ለመግዛት ከፈለጉ ይምጡ ለበዓል ይሸምቱ ተብላችኋል።

#አድራሻ፡-   ቦታ - ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ
             ስልክ - 0991824160

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ረቡዕ:- ሚያዚያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

በከተማ ደረጃ በተደረገው የአሰልጣኞች ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሸነፈ!!

የኮሌጁ አሰልጣኞች በተቋም እና በክላስተር ደረጃ የተወዳደሩበት የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ በላቀ ውጤት አሸናፊ የነበረ ሲሆን በከተማ ደረጃ በተደረገውም ቀዳሚነቱን ይዞ አጠናቋል።

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።   

የኮሌጁ አሰልጣኞች የሰሩት ጥናትና ምርምር ርዕስ በስልጠና መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት  እንዲት ማሳደግ ይቻላል? የሚል ነበር፡፡

ባለፈው ዓመትም በአሰልጣኞች የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡ 

በሌላ በኩል በተያያዘ በሰልጣኞች መካከል ሲደረግ የነበረው የክህሎት ውድድር እንደ ከተማ በ4 ሙያዎች 1ኛ ደረጃ፣ በ2 ዘርፎች 2ኛ ደረጃን እና በ1 ሙያ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ 7 ሜዲያሊዎችን ማግኘት ተችሏል።
 
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ሐሙስ:- ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

  የትንሣኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ኮሌጁ ለተለያዩ አካላት ስጦታ አበረከተ!!      

በኮሌጁ ስጦታ ከተበረከተላቸው መካከል የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ የነበረቺውና ከ8 ወር በፊት ህይወቷ ያለፈው የአሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ቤተሰቦች ይገኙበታል። ለእነዚህ ቤተሰቦች ከተቋሙ ሰራተኞች 137ሺ ብር በማሰባሰብ የብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። በዓይነት ተገዝተው ከተሰጡት ውስጥ የተለያዩ አስቤዛዎችን እንዲሁም የሻማ ማምረቻ እና የችብስ መጥበሻ ማሽኖች ይገኙበታል።

ሌላው መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክኒያት በማድረግ ኮሌጁ ከ260ሺ ብር /ከሩብ ሚሊዮን ብር/ በላይ ወጪ የጠየቀ የማዕድ ማጋራትን ያደረገው ደግሞ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች እና ኮሌጁ በየወሩ ድጋፍ እያደረገ ለሚያሳድጋቸው 16 ልጆች ነው።
 
የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ጫና ላይ ላሉ የስራ ባልደረቦች የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሌላ ዜና የኮሌጁ አጋር ሆኖ 4 ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በመስራት የተቋሙ ገፅታ እንዲቀየርና የውስጥ ገቢው እንዲያድግ ያደረገው ፉት ፒች ኃላ/የተ/የግ/ ማኅበር ለኮሌጁ የጥበቃ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ይሁናችሁ ብሎ 50ሺ ብር ሰጥቷቸዋል፡፡

         "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ረቡዕ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የሶስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ሰልጣኞች በኮሌጁ የሚሰጠውን ስልጠና አጠናቀቁ!!

ቀድመው የጀመሩት የሶስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ሰልጣኝ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመረቁ።

ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጁ የተሰጣቸው ለ12 ቀናት ሲሆን ያጠናቀቁትም ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሁለት ወረዳዎች የተውጣጡት መሆናቸው ተገልጿል።

ጥቂት ቀናትን ዘግይተው ከጉለሌ ክፍለ ከተማ የመጡት ደግሞ በቀጣይ የሚያጠናቅቁ መሆኑ ተነግሯል።

ሰልጣኞች በቆይታቸው የጊዜ አጠቃቀም፣ የተግባቦት ችሎታ፣ የስራ ላይ ደህንነት፣ ወዘተ ያሉትን የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

የህይወት ክህሎት ስልጠና ያጠናቀቁ ወጣቶች በተለያዩ ተቋማት ለስድስት ወራት የሚቆይ የስራ ላይ ልምምድ ቆይታ እንደሚኖራቸውም ታውቋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ነገ አርብ ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ከ12:30 እስከ 1:00 የኮሌጁ አዲስ ዶክመንተሪ በአዲስ ቲቪ ስለሚቀርብ ይከታተላሉ ዘንድ ተጋብዘዋል።
መልካም ቆይታ!