ሰኞ፡- ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
የኮሌጁ አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ!!
የኮሌጁ ዲኖችና ሠራተኞች በተገኙበት በኮሌጁ ቅፅረ ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የችግኝ መርሃ ግብር ላይ የተለያየ ዝርያ ያላቸው በርካታ ችግኞች ተተክለዋል።
በዚህም መርሃ ግብር የጥላ ዛፍ፣ የአካባቢ ውበት ማስዋቢያ አበባዎች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ዕፅዋቶች ይገኙበታል።
የ7ኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካል በሆነው በዛሬው ዕለት ከ1500 በላይ ችግኞች በኮሌጁ የተተከሉ ሲሆን የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ''በመትከል ማንሰራራት'' በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ መሆኑ ይታወቃል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

❤5👍5
ረቡዕ፡- ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ከባለድርሻ አካላት ጋር የእቅድ ውይይት ተካሄደ!!
የኮሌጁ ቴክኖሎጂ ልማት እና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር የእቅድ ውይይት አደረገ።
ከ2 ክፍላተ ከተሞች ማለትም ከአዲስ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተማዎች እና ከወረዳዎች ከመጡ ባለድርሻዎች ጋር በዘርፉ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በዕለቱ የዕቅዱን ሰነድ ለተሳታፊዎች በገለፃ ያቀረቡት የዘርፉ ምክትል ዲን አቶ ደሜ መርሻ ናቸው።
እቅዱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን አጠናክሮ በመስራት የኢንተርፕራይዞች የኢኮኖሚ ዕድገት ከፍታን ማረጋገጥና የቴክኖሎጂ ፈጠራና ቅጂ አቅምን በማሳደግ በሀገሪቱ ዕድገት ላይ የድርሻን አበርክቶ ለመወጣት ነው።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም ተግባራትን ተናቦና ተቀናጅቶ በመስራት የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

❤10🙏3😢1
አርብ:- ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ለተመራቂ ሰልጣኞች የልል ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው!!
ለኮሌጁ እጩ ምሩቃን ሰልጣኞች 10 ቀናትን የሚፈጅ የልል ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
በመጀመሪያ ዙር ከ450 በላይ ተመራቂ ሰልጣኞች ስልጠናውን እየተከታተሉ ሲሆን የስልጠናው መሰረታዊ ዓላማ ተመራቂዎች ወደ ስራ ኢንዱስትሪው ሲቀላቀሉ የሚያስፈልጋቸውን ልል ክህሎት ለማስጨበጥ እንደሆነ ተገልጿል።
ለምሩቃኑ እየተሰጠ የሚገኘው ክህሎት የስራ ላይ ተግባቦት፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ የሲቪ አዘገጃጀት፣ ወዘተ ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ የልል ክህሎት ስልጠናዎች መሆኑን የገለፀው በስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ የኢንዱስትሪ ትስስርና ስራ ፈጠራ የስራ ክፍል ነው።
የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ቀጣይ ሳምንት የሚጠናቀቅ ሲሆን 2ኛውና የመጨረሻው ደግሞ ከዚያ በኋላ የሚቀጥል መሆኑን የስራ ክፍሉ ጠቁሞናል።
ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት ባለፈው ዓመት የኬፕለር ስልጠናን የወሰዱ የኮሌጁ አሰልጣኞች ናቸው ተብሏል።

❤13👍2👎1
ሰኞ:- ነሐሴ19 ቀን 2017 ዓ∙ም
ፋዊ የስልጠና ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ሰልጣኞች የላፕቶፕ ስጦታ አበረከተ!!
የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም /FAWE/ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የስልጠና ድጋፍ ለሚያደርግላቸው የኮሌጃችን ሰልጣኞች የላፕቶፕ ስጦታ አበረከተ።
ፋዌ ኢትዮጵያ ቻፕተር እና ፋዌ አፍሪካ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የሃርድ ስኪል ስልጠና ለሚከታተሉ ሰልጣኞች የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲትሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡
እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የተተገበርባቸው ጀነራል ዊንጌት እና አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሲሆኑ በሁለቱ ተቋማት እየሰለጠኑ ለሚገኙ ሰልጣኞች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ለስልጠና አጋዥ የሆነውን የላፕቶፕ ስጦታ አድርጓል።
በዛሬው ዕለት የላፕቶፕ ስጦታ የተበረከተላቸው 48 ሰልጣኞች ሲሆኑ 27ቱ በጀነራል ዊንጌት እየሰለጠኑ የሚገኙ ናቸው።
ፕሮግራሙ 80 ከመቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ5 እስከ 10 ፐርሰንት ለአካል ጉዳተኛ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ዕድል እንደሚሰጥ ይታውቋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

❤8