General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ:- መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በክላስተር ደረጃ የአሰልጣኞች ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተካሄደ!!

በክላስተር ደረጃ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር  የሰሩ  አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።

በዚህ ውድድር 3  የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ያሉ ኮሌጆች ከየተቋማቸው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ያገኙ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።  እንደ ክላስተር ከ3ቱ አሸናፊው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ ለሚደረገው ውድድር የሚቀርብ ሲሆን በዚህ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች የተሰራው ቀዳሚውን አጠናቋል፡፡ 

መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት  እንዲት ማሳደግ ይቻላል? በሚለው ወቅታዊ  ርዕስ ላይ የተሰራው የኮሌጁ የጥናት ሰነድ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ባለፈው ዓመት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡ 

   "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ሐሙስ፡ - ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ

የወደቁትን አንሱ የነደያን በጎ አድራጎት ማህበር ጧሪና ቀባሪ የሌላቸውን አዛውንቶች፣ የአዕምሮ ህሙማን እና አሳዳጊ የሌላቸው ልጆችን እየሰበሰበ ከሚንከባከቡ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡

ይህንን ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ደግሞ ከማህበረሰሰቡ፣ ከድርጅቶችና ከተለያዩ ለጋሽ አካላት በማሰባሰብ ነው፡፡

ስለሆነም ወድ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ማህበሩ እገዛ የሚሆን ሁለችንም በምንችለው አበርክቷችንን እናድርግ እያለን ይኸውም ተሰብስበው የሚሰጡ ስጦታዎች በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ /በአልባሳት/ ነው፡፡

ስለሆነም አገልግሎት የሚሰጡና በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ አካላት ሊሆኑ የሚችሉ አልባሳትን እና በጥሬ ገንዘብ የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ እየገለጽን የበጎነት ስጦታችሁን በኮሌጁ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮና በቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ ማድረስ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

ሌላም መንገድ አለ የኮሌጁ ሰራተኞች ለሆናችሁ ደግሞ ከሚያዚያ 6 ቀን እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ያለውን የምሳ ድጎማ ኩፖን ለድጋፉ ይዋልልኝ ካላችሁ ካፌ ሄዳችሁ ማሳወቅ ትችላላችሁ፡፡

ድጋፋችንን ለሚሹ አካላት በምንችለው ስናበረክት በውስጣችን የሚታተመው የበጎነት ደስታና የመንፈስ እርካታ እጅግ የላቀ ነው፡፡

የኮሌጁ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ
ቅዳሜ፡- ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡

በዚህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበራ ብሩን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው የስራ ኃላፊዎች ፣ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት፣ የተለያዩ ኮሌጆች ዲኖች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖች፣ ማናጅመንት አባላትና የዲፓርትመንት ተጠሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ በኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው እና ዶ/ር አበራ ብሩ አማካኝነት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ተቋማዊ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፓርት በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ጀማል ሐሰን አማካኝነት ቀርቧል፡፡  

አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራው ሂደት ምን ይመስላል የሚለውን ደግሞ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የኮንትራክት አዲሚኒስትሬሽን ኤክስፐርት በሆኑት ኢ/ር ዘውዴ ሽፈራ አማካኝነት ገለፃ ተደርጓል።

በሌላ በኩል ተቋሙ የዉስጥ ገቢውን ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ የተቋቋመው ኃላ/የተ/የግል ድርጅት ለቀጣይ ያሉት ተስፋዎች፣ ያመጣው ፋይዳና ያሉበት ክፍተቶችን የሚያሳይ ጥናታዊ ቀርቧል።

በመጨረሻም በቀረቡት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ጥናታዊ  ጽሑፍ ሰነዶች መሠረት ከተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቶ እና ገንቢ አሰተያየት ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
 
     ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ማክሰኞ፡- ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም  

ለኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች በፕሮጀክት ቤዝድ አሰጣጥ ስልጠና ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ተሰጠ!!
 
ከሁሉም ኮሌጆቸ ለተወጣጡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች በፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና አሰጣጥ ዙሪያ ትናንት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ የጋራ ግንዛቤ ተሰጠ።

በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 15ቱ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ላይ ያሉ አሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸውን እንዲያሻሽሉና ፕሮጀክትን መሰረት ያደረገ እውቀት እንዲያገኙ ታሳቢ በማድረግ ለተዘጋጀው ስልጠና ግንዛቤ እንዲኖራቸው በትናንትው ዕለት ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በዚህ ገለፃ  ላይ ከሁሉም ኮሌጆች 583 አሰልጣኞች ተገኝተዋል።

ኮሌጁ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናን ሲጀምር የኮነስትራክሽን ዘርፍ ማሰልጠኛ ት/ቤት የነበረ መሆኑና በቀጣይም የአካባቢን ጸጋ መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት በያዘው ዕቅድ ኮንስትራክሽንን ቀዳሚ ምርጫ ያደረገ መሆኑ ለተዘጋጀው ስልጠና ተመራጭ አድርጎታል።

ስልጠናው ለ26 ቀናት የሚሰጠ ሲሆን መሰረታዊ ዓላማው የዘርፉ አሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸውን በመሙላት የሙያ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡና የሚሰጡትን ስልጠና ፕሮጀክትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ ታቅዶ ነው ተብሏል።

         "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"